ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
በዝቋላ ክብሮም
<unknown>
#መዝሙር #በዝቋላ_ደብር_ጸናህ

በዘማሪ #ክብሮም_ግደይ

እንኳን ለብጹዕ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ።

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#መዝሙር #በዝቋላ_ደብር_ጸናህ

በዘማሪ #ክብሮም_ግደይ

በዝቋላ ደብር ጸናህ
በምድረ ከብድ ታይቷል ዝናህ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አባታችን
ዛሬም ጸልይ ለሀገራችን(2)

የአንበሳው ደቦል ነብሩም ተርቦ
በፍቅር ይኖራል የእግሩን ትቢያ ጠግቦ
የዋሻዎች ሞገስ የገዳማት ሀብት
የባህታውያን መምህር አጽናን በሃይማኖት

ገዳም ንሂስ ተግባረ ቅዱስ
ሀብተ ፈውስ ነህ ስምህን ላወድስ
አኗኗርህ ግሩም ምድራዊ መልአክ
ለምነህ አስምረን ምህረትን ከአምላክ

የምድረ ከብድ ፀሐይ የጸሎት አርበኛ
ከቤትህ እንዳንርቅ ለምንልን ለኛ
ሰይጣን ላሳታቸው ከቤትህ ለራቁ
ከእስራት ፍታቸው ክብርህን እንዲያደንቁ

የስምኦን በረከት የአቅሌስያ ፍሬ
የዝቋላው ኮከብ የዋሻው ገበሬ
ሰይጣን እንዳይጥለን ዳግመኛ ከእሳት
ገብረ መንፈስ ቅዱስ አጽናን በሃይማኖት

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit