ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
.....የቀጠለ
❝...#ጌታ_ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።❞
ያዕቆብ 4: 15
ክፍል 2

ሰላም ወዳጆች ? ትላንት በክፍል 1 ቆያታችን እያገባደድን እየመጣን ስላለው ዓመት አጭር የግምገማ እና ለምን አላሳካነውም ለሚሉ ጥያቄዎች መልስ መስጠት ጀምረን ነበር ።

ምክንያተኝነትን እና ምክንያትን ለዓላማ እንዲሁ ለ መንፈሳዊ እድገት መቀጨጭ ዋና አስተዋጽዖ እንዳለው በግርድፉ ተመልክተን ነበር ።
ዛሬም በዚህ በክፍል ሁለት አንድ አንድ ነገር እንነገራለን ።

ዓመቱን እንዴት እንዳሳለፍን ለራሳችን ስንጠይቅ ብዙ ነገሮች በአእምሯችን እንደተመላለሱ ለመገመት ሊቅነትን አይጠይቅም ። ዋናው ነገር ግን እርሱ አይደለም ።
መልሶቹ ውጫዊው አጋደለ ወይስ ውስጣዊው???
ወደ ሌላ ወይስ ወደራሳችን ?
ወደ ሰፊው ዓለም ወይስ ወደ ራሳችን ዓለም ?

መልሱ ወደ ወጪ ካመዘነ አሁንም ደግመን የምንጠይቅበት ሰዐት ነው ። ምክንያቱም መልሱን አላገኘነውም ! አለቀ።

ብዙ ጊዜ የችግራችን (መንፈሳዊ ይሁን ዓለማዊ) መንስኤ ውጫዊ እንደሆነ ካሰብን ውጫዊ መፍትሔ ስንፈልግለት እንደ ባዘንን ሳንንድን ሌላ የተሰጠንን ጊዜ እናባክናለን ። ቅዱሱ መጽሃፍ ❝...የመዳን ቀን አሁን ነው።❞ 2ኛ ቆሮ 6: 2 ሲል አሁን የመለወጫ የመወሰኛ ጊዜ ነው እያለን እንደሆነ ልብ ይሏል።

ቅዱስ ጳውሎስ እንደተናገረው
❝ነገር ግን በዚያ በሚመኩበት እንደ እኛ ሆነው ሊገኙ፥ #ምክንያትን ከሚፈልጉቱ #ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ።❞
—2ኛ ቆሮ 11: 12
ምክንያተኝነትን እያስወገድን ራሳችንን መመልከት ያስፈልጋል። ሌላው ብዙ ስንጠይቅ መራቀቅን ለጊዜው እያስቀመጥን ቢሆን ደግሞ መልካም ያደርገዋል ።
ሁለት የፍልስፉና መጽሀፍ ያነበበ ወዳጄ" ሰላም ነው?" ስለው የመለስልኝ መልስ ፈገግ ቢያሰኘኝ ነው ይህን ማለቴ !
ጓደኛዬ :- ውስጣዊ ነው ውጫዊ ???

በገድለ አቡነ ተክለሃይማኖት ያለች ልትራቀቅ ወድዳ ፍዳ ያመጣች አንዲት መነኩሲት ሰው ላስታውሳት። አባታችን ጸሀይ ዘኢትዮጲያ አቡነ ተክለሃይማኖት በደብረሊባኖስ በነበሩበት ወቅት አራዊት እየመጡ የልጆቻቸውን አዝመራ እየበሉ አስቸገሯቸው ። ልጆቹም ሄደው " አባታችን! እንስሳት አራዊት አትክልታችንን እየበሉ አስቸገሩን " አሏቸው።
ቅዱስ አባታችንም "ልጆቼ ተውአቸው ። እኛ ወደ ጫካ መጣንባቸው እንጂ እነርሱ አልመጡብንም" ሲሉ መለሱላቸው ።

እንዲህ ሆነው ሳለ ከዕለታት በአንድ ቀን አንዲት አረጋዊት መናኝ ስተመገብ አንድ ዝንጀሮ መጥቶ በጥፊ ጠርቅሞ ቀምቷት በላ ። አባታችንም ይህንን አይተው :- " የተሰጡትን ትቶ ሌላ ያልተሰጡትን መሻት የያዙትን ያሳጣል። እኔ በዱር የተዘራውን ትበሉ ዘንድ ብፈቅድ ከሰው እጅ እየቀማችሁ መብላት ጀመራችሁ?" ብለው "ወንጌልን በምሰክለት በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አፋችሁን የታሰረ ይሁን! " በቃለ ማእሰር ዘጓቸው ። ከዚያን ቀን ጀምሮ መብላት ተሳናቸው ።

በስተመጨረሻም ሩጫቸውን ጨርሰው ሊያርፉ ሲሉ ልጆቻቸው ጠርተው ሲሰናበቱ መረቋቸው። በዚህ ጊዜ ያች ሴት ልትራቀቅ ወድዳ " አባቴ በጸሎቶ ያሰሩትም ይፍቱ " ብላ ጠየቀች። እርሳቸውም " የታሰረውም ይፈቱ " ሲሉ ዝንጀሮውም አብሮ ተፈታ ። በዚህም ከቀደመው የበዛውን አጠፉ።
ስናጠቃልለው በነገርም ያለ ነገርም # አትራቀቅ ...!

እንቀጥላለን ።