ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
930 photos
24 videos
271 files
193 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
❝...#ጌታ_ቢፈቅድ ብንኖርም ይህን ወይም ያንን እናደርጋለን ማለት ይገባችኋል።❞
ያዕቆብ 4: 15
ክፍል 1

ሰላም ወዳጆች...
እንዴት ነው ?
ዓመቱ እንዴት እየተጠናቀቀ ነው?

እግዚአብሔር ፈቅዶ 2014 ዓ.ም ዘመነ ማርቆስን ለማገባደድ በጣት የሚቆጠሩ ቀናት ቀርተውናል ። እስቲ ዘወር ብለን ያለፈውን ጊዜያቶች እንዴት እንዳሳለፍን እንመርምር። መመርመር በጥያቄ ይጀምራል እና ይህንን ልጠይቅ... !

ስንቱን አተረፍንበት.... ?
ስንቱን ከሰርንበት.... ? ለምን ?
ስንቱንን በሚጠቅመን ነገር አሳለፍንበት ...?
ስንቱን በማይጠቅም ነገር አሳለፍንበት.... ? ለምን?
ምን ያህሉን ጊዜ አዲስ ዕውቀት ለመጨመር ተጋንበት ?
ስንት መጽሃፍትን አነበብን ? ስንቱን ኖርነው ?
በዚህ ዓመት ልንፈጽመው #ካቀድነቸው ነገሮች ውስጥ ምን ያህሉን አሳካናቸው ? ምን ያህሉን አላሳካነውም? ለምን ?
ከሁሉም ከሁሉም ግን ወሳኙ ጥያቄ ምን ያህሉን ጊዜ ለእግዚአብሔር ሰጠነው ? ምንያህሉን ጊዜ ከእግዚብሔር ጋር ተገናኘንበት ? የሚለው ነው ?

በእርግጥ ይህንን ጥያቄ ሙሉ ለሙሉ ለመመለስ ጊዜ ቢያስፈልገውም እንዲው የግምገማ ጊዜ ቢኖረን ከሚል ወንድማዊ ፍቅር ጠየኩኝ ። በእርግጠኝነት መናገር የምችለው ግን ለሁሉም ላላሳካነቸው ነገሮች ያሳምንም አያሳምንም ? ይብዛም ይነስም አዕምሮአችን ምክንያት ይሰጠናል ።

#ንግባኬ_ሀበ_ጥንተ_ነገር እንዲል ሊቁ ወደ ቀደመ ነገሬ ስመለስ ከላይ ላሉት ጥያቄዎች ለምን ሙሉ ለሙሉ ማሳካት አልቻልኩም ብለን ስንጠይቅ መልሱ ወደ አንድ ነገር ያመራናል ።
የጊዜ አጠቃቀም እና ምክንያታዊነት!

ስለ ጊዜ አጠቃቀም በሌላ ርዕስ ብመለስበት ስለሚሻል ስለ ምክንያታዊነት ይህንን ልበል! ቅዱስ መጽሀፍ እንደሚያስተምረው ለየትኛውም ስንፉናችን ምክንያት ሊያድነን አይችልም።

❝እኔ መጥቼ ባልነገርኋቸውስ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው #ምክንያት የላቸውም።❞ ዮሐንስ 15: 22
ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲያስተም ስላደረገው ተዓምር እስራኤላውያን እንዳይሰናከሉ አንድም ለሰው ልጅ ተዐምራቱ ላይ እንዳንሰናከል ምክንያትን ለማስወገድ አንድን ተዐምር በአራት ወንጌላውያን ሲያስመሰከር ሲያጽፍ እንገኘዋለን። ይህም ተዐምር...
• ቅዱስ ማቴዎስ... ቦታው የተመቸ (ሳር እና ለምለም) እንደነበር ይገልጣል። ለምን ይህንን መግለጥ አስፈለገው ቢሉ አይሁዳውያን ቦታው አልተመችንም ስለዚህም አልበላንም እንዳይሉ!
ማቴዎስ 14 :19
ሕዝቡም #በሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ፥ አምስቱንም እንጀራና ሁለቱን ዓሣ ይዞ ወደ ሰማይ አሻቅቦ አየና ባረከ፥ እንጀራውንም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጠ፥ ደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ።

• ቅዱስ ማርቆስ ደግሞ ቦታው ምድረ በዳ (ከከተማ ወጣ ያለ ስፍራ) እንደነበር ይገልጻል ። ለምን ይህንን ገለጠ ቢሉ ከከተማ ገዝተው አበረከትን ይላሉ እንዳይሉ!
ማርቆስ 8 ፡ 4
ደቀ መዛሙርቱም፦ በዚህ #በምድረ_በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል? ብለው መለሱለት።
• ቅዱስ ሉቃስ ወቅቱን ይገልጽልናል። መሽቶ እንደነበር ። ተዐምሩን ለምን በቀን አላደረገም ቢሉ በጠዋት ቢያደርገው በልተን መጥተናል ባሉት ነበር በምሳ ቢያደርገው የጠዋቱ አለ ባሉት ነበር ። ስለዚህ አብረው ውለው ማታ አድርጎ ምክንያት አሳጣን።
ሉቃስ 9: 12
❝ቀኑም ይመሽ ጀመር፤ አሥራ ሁለቱም ቀርበው፦ በዚህ በምድረ በዳ ነንና በዙሪያችን ወዳሉ መንደሮችና ገጠሮች ሄደው እንዲያድሩና ምግብ እንዲያገኙ ሕዝቡን አሰናብት አሉት።❞
• ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ አካባቢውን በመግለጽ ይጀምራል። ምክንያት ቢሉ አይሁድ የማንጻት ለማዳ ነበራቸው እና! ሳይታጠቡ አይበሉም ነበር እና !
ዮሐንስ 6: 1
❝ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው።❞
ይህ የሚያስተምረን ለየትኛውም ድክመታችን ምክንያት እንደሌለን ነው።

ከምክንያተኝነት በመቀጠል ትልቁ ችግር ከእቅዳችን እግዚአብሔርን ማስወጣት ነው ። ምንም ነገር ስንጀምር ፈቃደ እግዚአብሔርን ካላስቀደምን ጦርነት ሳይጀምር እንደተሸነፈ ወታደር ነን !

ሊቁ እንደተናገረው። " እግዚአብሔር የሌለበት ዕቅድ እና መስመር የሳተ መንገደኛ አንድ ነው " ሁለቱም መድረሻቸው አያታወቅም እና!

እንቀጥላለን... !

መ/ር ዲ/ን እስጢፋኖስ ደ.
26/12/2014