#መድኃኔ_ዓለም
እንኳን አደረሳችሁ!
"እርሱ በእውነት ክርስቶስ የዓለም መድኃኒት እንደሆነ እናውቃለን" (ዮሐ 4÷42)
ኢየሱስ ማለት መድኃኒት ማለት ነው መድኃኒትነቱ በጥቂት ሰዎች ብቻ የተገደበ፤እንደነ ኢያሱ በእስራኤል ዘሥጋ ማዳን ብቻ የተገለጠ ሳይሆን፤በሥጋ፣ በመንፈስና በነፍስ ማዳን ላይ የተመሠረተ ለሰው ልጆች ሁሉ የተሰጠ፤ ያውም ከአዳም ጀምሮ እስከ ዓለም መጨረሻ ድረስ ለሚነሳው ትውልድ ሁሉ የሆነ ማዳን ነው፡፡
ስለዚህም መድኃኒትነቱ ውሱን እንዳልሆነ ለማጠየቅ ˝ኢየሱስ˝ የሚለው በምልኣት ሲገለጥ ˝የዓለም-መድኃኒት˝ ብለን እንጠራዋለን፡፡
ዓለም ማለት ዘመድ፤ ዘመደ ፍጥረት ፤ሰማይ ከነግሡ ምድር ከነልብሱ፤ሰማይ ከነደመናው ምድር ከነጉተናው ማለት ሲሆን ሁሉን የጠቀለለ ስም ነው፡፡
በሊቃውንቱ ሃያ ዓለማት እና ሃያ አየራት እንዳሉ ይገለጣል፤ሃያ ዓለማት የሚባሉትም ዘጠኝ ዓለመ እሳት፤አምስት ዓለመ ምድር፤አራት ዓለመ ማይ እና ሁለት ዓለመ ነፋስ ናቸው፤(9+5+4+2=20)፤አየራቱም በዚህ ልክ ናቸው ይላሉ (ቅዳሴ.ማር አንድምታ)፡፡
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲሰቀል ዓለሙን ሁሉ ለማዳን ነው ሲባል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን በአዳም ምክንያት ተረግሞ የነበረውን ዓለም ለሰው ልጆች በግዛት መልክ ተስጥቶ የነበረውን ሁሉ ዓለም ለመባረክ መሆኑንም ማወቅ ያስፈልጋል፤ለአዳም "ከሰማይ በታች ከምድር በላይ ያለውን ሁሉ ብላ ጠጣ ግዛ ንዳ" (ዘፍ 1÷29-31) ተብሎ መሰጠቱ ይታወቃል፤ይህም በረከት ነው፡፡
አዳም ያልታዘዘውን ዕፀ በለስ በልቶ ሲረገም ደግሞ የእርሱ የሆነው ሁሉ አብሮ ተረግሟል፤
♦ለዚህም "ካንተ የተነሣ ምድር የተረገመች ትሁን" (ዘፍ 3÷17) የሚለው ቃል ማረጋገጫችን ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስም፡-
♦"ምድርም አለቀሰች ረገፈችም ፤ዓለም ደከመች ረገፈችም፤የምድርም ሕዝብ ታላላቆች ደከሙ" በማለት በኢየሩሳሌም ምርኮ አንፃር የነበረውን የዓለምን ስቃይ አመልክቶናል (ኢሳ 24÷4)፡፡
ነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤልም፡-
♦"ወሶበ ዐለወ አቡነ አዳም ኮነ ፍናዊሁ ለዓለም መብእሰ ወጐጻጒጸ" "አዳም ትእዛዙን ባፈረሰ ጊዜ የዚህ ዓለም ጎዳናው ጒድጓድ ሆነ፤ጠባብ ያነሰ የከፋ መከራው የበዛ፤ ፃር ጋር የተመላ ሆነ" (ዕዝ.ሱቱ 5÷2)፡፡
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም፡-
♦ "ስለዚህ ምክንያት ኃጢአት በአንድ ሰው ወደ ዓለም ገባ" (ሮሜ 5÷12)፡፡
ጌታችንም ለሐዋርያት ሲያስተምር፡-
♦"ርእዮ ለዓለም በማእሰረ ኃጢአት እንዘ ይትኀጐል፤ፈቂዶ ይፈውስ ትዝምደ ሰብእ…." "ዓለም በኃጢአት ማሰሪያ ተይዞ ሲጎዳ አይቶ የሰውን ባህርይ የሰውን ነገድ ይፈውስ ዘንድ …" ብሏል (ትምሕርተ ኅቡአት)፡፡
ስለዚህ ለአዳም የተሰጠ ዓለም በአዳም ምክንያት የተረገመ ሆኖ ነበር፤ ዓለማችን በአዳም ምክንያት መከራንና ሞትን ተቀብላ አስተናገደች፤ይህ መርገም ለዓለም አንዲወገድላት ሌላ ሁለተኛ አዳም ያስፈልግ ነበር፤ እሱም "የዓለም መድኃኒት" መሆን አለበት፤ሁለተኛው አዳም ክርስቶስ ወደዚህ ዓለም መጣ፤ ዓለምን በደሙ ፈሳሽነት አጠባት፤ በሰው ውስጥ የሚገኙትን አራቱን ባህርያት አደሳቸው፤ ተረግማ የነበረችው ምድር በጌታ ደም ታጥባ ፋሲካን አደረገች ("ወምድርኒ ትገብር ፋሲካ ተኀፂባ በደመ ክርስቶስ" እንዲል ቅ.ያሬድ)፤ ክርስቶስ መርገማችንን ቀበረልን፤ ልጅነታችንን መለሰልን!!!
ዛሬ በዚህ ደም ታጥበን ነጽተን መንግሥቱን እንጠባበቃለን
ፍቅሩንና መከራውን እያሰብን
ቁስሉንና ሞቱን እያስታወስን እንማፀናለን
ለዓለም ቤዛነት መስቀል ላይ የተፈተተው ጌታ ዛሬም እንደማይተወን እናምናለን
ስለዚህም እንዲህ እያልን እንለምነዋለን፦
መድኃኔ ዓለም ሆይ!
• 6,666 ጊዜ ስለተገረፈው ጀርባህ
• ስለተቸነከሩት እጆችህና እግሮችህ
• ስለተወጋው ጎንህ
• ስለ ቅዱስ ሥጋህና ስለ ክቡር ደምህ
• በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ስለወለደችህ ስለ እናትህ ስለ ማርያም ብለህ
ይቅር በለን!!!
አሜን!!!