ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#በመጀመሪያ ስለጠየቁ እናመሰግናለን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ወደ መልሱ ስናመራ
#ቃሉ ዘጸ 7÷3 እና ዘጸ 14÷4 ላይ በተዳጋጋሚ የተነገረ ኃይለ ቃል ነው ።
በመጀመሪያ ይህ ልማደ ቅዱሳን መጻሕፍ ነው ቅዱሳን መጻሕፍት በልማዳቸው ምሥጢርን እንጂ ዘይቤን አይጠነቅቁም::ምን ለማለት ነው በምሥጢር ሊተላለፍ ለተፈለገው ነገር ይጨነቃሉ ወይም ምሥጢር እንዳይፈልስ ይጠነቀቃሉ እንጂ የንግግር ወይም(የአጻጻፍ )ዘዬ ላይ ብዙ አይጨነቁም:: የንግግር ወይም የአጻጻፍ ዘይዬ ከባሕል ከቋንቋና ከልማድ ጋር ተያይዘው የመጡ ናቸው ቋንቋ ባሕልና ልማድ ደግሞ ብዙ ዐይነት ነው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በብዛት በዕብራውያን ልማድ የተጻፈ ነው ስለዚህ ዕብራዊ ባሕል ና ልማድ የሌለው ሰው በቀላሉ ሊረዳውና ሊገነዘበው ያዳግተዋል ማለት ነው ስለሆነም ሁሉም ዓለም በቀላሉ ይረዳውና ይገነዘበው ዘንድ ቢቻል ዕብራዊ የንግግር ወይም የአጻጻፍ ስልትን ቢያውቅ ይመረጣል ይህ ግን በልዮነት የተመላች ዓለምን በአንዴ ወደ አንድ የመጨፍለቅ ያክል ነውና አዳጋች ነው :: ሁሉም የራሴ የሚለው ባሕል ልማድና የንግግር ፣ የአጻጻፍ ዘይ አለውና ። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ባወቀ ቅዱሳን መጻሕፍት ለዘይቢያዊ የአነጋገርና የአጻጻፍ ዘዴ እምብዛም ሳይጨነቁ ምሥጢርናብቻ እንዳጠነቅቁ አድርጎ አጻፈው :: በዘይቤ ብዙ ዓይነት ባሕል በዙ ይነት ዘይቤ አለና በምሥጢር ግን ሁሉም በተመሳሳይ መንገድያ አረዳድ ይረዱታልና ይህ ሆነ :: በመሆኑም መጻሕፍ ቅዱሳዊ ኃይለ ቃላትን ከአነጋገርና ከአጻጻፍ ዘይቢያቸው አንጻር ብቻ ማየቱ ተገቢ አይደለም ማለት ነው :: ይህ በእንዲህ ሆኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን በንባብ የጠመመውን በትርጓሜ በትሥጓሜ የጠመመውን በምሥጢር አስማምታ ቃለ ወንጌልን ለልጆቿ ትመግባለች በዚህ አንጻር ወደ ሀሳቡ አንግባ

በመሠረቱ እግዚአብሔር የፈርዖን ዐይነት ልብ ያላቸውን ጠማማ ሰዎች ልባቸውን ቃና ለማድረግ የሚተጋ ቀናዬ አምላክ ነው እንጂ ጠማሞች ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ አምላክ አይደለም:: ነገር ግን ሰው ከእግዚአብሔር በተቸረው ነጻ ፍቃዱ ልቡን ሊያደነድን ወይም ድንጋይ ሊያደርግ ይችላል :: ታድያ እግዚአብሔር በዚህ ጊዜ በጊዜም ያለጊዜም በምክንያትም ያለ ምክንያትም በመምህራንም ያለ መምህራንም ይመለስ ዘንድ በልዮ ልዮ አጠራሩ ይጠራዋል ግን ፍላጎቱን ተጋፍቶ የግድ ቅን ሁን ብሎ አያስገድደውም ፍትሐዊ አምላክ ነውና :: እሺ በጄ ብሎ ቢመለስ መልካም ነው በመመለሱ ቅን በመሆኑ ሊያገኝ የሚችለውን ዋጋ በጊዜው ይከፍለዋል እሺ በጄ ብሎ ባይመለስ ግን እንደ ጥመቱ መጠጥ የጥመቱን ዋጋ በጊዜው አወራርዶ ያስረክበዋል


" በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ። እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።

#ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። 2ሳሙ 22÷26-28

ስለዚህ ለሙሴና ለአሮን እንዲሁም በወቅቱ ቅን ለሆኑት ሕዝቦች(ለሕዝበ እሥራኤል) በቅንነት ፈረደላቸው በአንጻሩ ጠማማ በሆኑት በፈርዖን እና በሰራዊቱ ደግሞ ፈረደባቸው ።

ስለዚህ ከቅኖች ጋር ቅን ሆኖ እንደሚገኝ በቅንነትም እንደሚፈርድላቸው ለጠማሞችም እንደ ጥመታቸው እንደሚፈርድባቸው ለመናገር የፈርዖንን ልብ አጸናለው አለ
እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ የለም (ምሉዕ በኩልሄ )በሁሉ ያለ ነው አኗኗሩ ግን ይለያያል ከክፋዎች ጋር በመአቱ ከቅኖች ጋር ደግሞ በምሕርቱ ይገኛል።

"ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።”መዝ 138(139)፥10

#እግዚአብሔር ከቅኖቹ ከነሙሴ ጋር በቅንነት አለ ከጣማሞቹ ከነ ፈርዖንም ጋር በጠማምነት አለ ።
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊትም አክሎ በሌለ ሥፍራ ላይ ይህንኑ ሀሳብ እንዲ ሲል ያጠነክርልናል

" ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።" መዝ 18÷ 25



ይህ ማለት ግን ክብር ምሥጋና ይግባውና እግዚአብሔር ጠማማ ነው ጠማማነት ይስማማዋል ማለት አይደለም እርሱ በባሕሪው ፍጹም ቅን አምላክ ነው:: ስለሆነም እግዚአብሔር ፈታሄ በርትዕ ኮናኔ በጽድቅ እየተባለ ይጠራል።



ስለዚህ #እግዚአብሔር _የፈርዖንን_ልብ_አጸናለው አለ ሲባል ይመለስ ዘንድ ሊቀ ነቢያት ሙሴንና ካህኑ አሮንን ወደ እርሱ ልኬ እግዚአብሔር ዕወቅ እሥራኤልንም ልቀቀ ብለው አሻፈረኝ ብሎ ልቡን እንዳደነደነ እንደ ደንዳንነቱ መጠን እመልስለታለው ሲል እንደ ጸና ብኝ እጸናበታለው ሲል የፈርዖንን ልብ አጸናለው ብሎ ተናገረ

አንድም ይህ የደነደነ አልመለስ ያለ ልብ ኃያልነቴን ብርታቴን ያይ ዘንድ ሕዝበ እሥራኤልም ቅን ፍርዴን አይተው በሃይማኖት እንዲጸኑ በምግባርም እንዲቀኑ የፈርዖን ዳተኛ ልብ ምን እዳመጣበት እስከሚያዮ ድረስ የፈርዖንን ልብ ትጸናለች ሲል ነው።


እንጂማ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰማዕት ወነቢይ የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ከበርሃ ጀምሮ ጠማማው ይቅና ተራራውም ዝቅ ይበል ካልተስተካከለ መንገድ የለምና እያለ የጠመመ ልብ ያላቸውን በስብከቱ እያቀና ሥርጓጉጡንም ልብ በትምህርቱ እየደለደለ እንደ ተራራ በክፉትና በትዕቢት የተወጠረ ልባቸውን በትዕትና ዝቅ እንዲያደርጉ ያስተማረለት እርሱ #እግዚአብሔር የደነደነ ሰው ልብን በፍቅር የሚሰብር እንጂ እንደ ክፉሁ መካሪ ወደ ጥፋት ስንሄድ እያየ የሚያበረታታንና የሚመክን ልባችንንም በክፉሁ እንዲጸና የሚያደርግ አምላክ አይደለም ከዛ ይልቅ የደነደነ የድንጋዮን ልብ የሚያወጣ በጥሩ ውኃ(በጥምቀቱ) ከአረጀንበት የኃጢያት ብስቁልና አውጥቶ በልጅነት ዳግም ንጽሕ ያደረገን ፍቅራዊ አባታችን ነው

#ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። #አዲስም_ልብ_እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ #የሥጋንም_ልብ እሰጣችኋለሁ።
#ሕዝ 36÷25_26

የሁላችን ልብ እንደ ፈርዖን የደነደነ ነውና ልባችን እንዲሁ አንዲቀር አያጽናብን የድንጋዮንም ልብ አውጥቶ የሥጋውን ልብ ይስጠን....አሜን🙏