ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Audio
#መዝሙር #ልመናዬን_ስማኝ

#በዘማሪ #ክብሮም_ግደይ

ልመናዬን ስማኝ ቃሌን አድምጠኝ/2/ 
እውነተኛ አምላክ ሰላምህን ስጠኝ/2/ 

ክርስቲያኖች ሁሉ ትእዛዙን አክብሩ 
ምስጋናን አቅርቡ ስገዱ ዘምሩ 
የጌታን አመጣጥ ለዓለም ንገሩ 
ደቀመዛሙርቱ ወንጌል አስተምሩ 
አዝ --- 
በመልካም የሚሄድ ጽድቅን የሚሰራ 
የፈጣሪውን ስም በከንቱ የማይጠራ 
ይጎበኛል በምድር ከሰማዩ ስፍራ 
በቀኝ ይቀመጣል ከቅዱሳን ጋራ 
አዝ --- 
ስለጠላቶቼ በጽድቅ ምራኝ 
በጦር ቃል ከበቡኝ ተሳለቁብኝ 
መሐሪ ይቅር ባይ መጠጊያ ሁነኝ 
አንተ በቸርነትህ ይቅርታ ስጠኝ 

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit