ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
ዐውደ ምሕረት
Photo
#የመቅደሱ_ፈተናዎች
ፈተና በዓለም ሲገጥም በመቅደሱ ጥላ ተጠልሎ ፣ቆይቶ ፣ደጅ ተጠንቶ የጊዜው ጊዜ
ይታለፋል ። ግን በቤተ መቅደሱ ስንፈተን ወዴት ሄደን ፈተናውን ማለፍ ይቻለን ይሆን!?።
ከባድ ነው !“ መዝ 39(40)፥1
#እመ_አምላክ_ቅድስት_ድንግል_ማርያምን የገጠማት ከባዱ ፈተና ይህው የመቅደሱ
ፈተና ነበር።
ክቡራን የሆኑ ወላጆቿ ቅድስት ሐናና ቅዱስ እያቄም እግዚአብሔር የዓይናችን ማረፊያ
የልባችን ተስፈ የምትሆን ልጅ ቢሰጠን ውኃ ቀድታ ጥጥ ፈትላ ታገልግለን አንልም በቤትህ
የምታገለግል አድርገን ላንተው እንሰጣለን እንጂ ሲሉ በተሳሉት ስእለት መሠረት
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ነሐሴ ሰባት ቀን ጸንሰው ግንቦት አንድ ቀን ወለዷት

ሦስት ዓመት ሲሆናትም ቅድስ ሐና በስእለታችን መሠረት ለእግዚአብሔር ልንሰጣት
ያስፈልገናል ይዘናት ወደ ቤተ መቅደስ እንሂድ አለች ቅዱስ እያቄምም የልጅ ፍቅርሽ
ይውጣልሽ ብዬ እንጂ ዝም ያልኩት ነገሩንስ ሳስበው ነበር ካንቺ ከመጣማ በይ ነኝ
ስእለታችንን እንፈጽም አለ። “ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ
ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፤ የተሳልኸውን ፈጽመው።” ተብሎ ተጽፎልና መክብብ 5፥4
# ወደ_ቤተ_መቅደስ ሲደርሱ የመጀመሪያው ፈተና መጣ በቤተ መቅደስ መኖሯስ ጥሩ ነገር
ነበር ግን የምግቧ ነገር እንዴት ይሆናል? የሚል ፈተና። ብዙቹ የቤተ መቅደሱ መተናዎች
ይህ እኮ ጥሩ ነበር ብለው የሚጀምሩ ሲሆኑ እመካከላቸው ግን የሚል አፍራሽ ቃል ወይም
ድርጊት የተቀላቀለበት ነው። ቄስ እገሌኮ ሲቀድሱ ድምጣቸው ውብ ነው ግን ሰዓት
ያስረዝማሉ ፤ ሰባኪ እንትና አቤት ትምህር አሰጣጡ ግን ትንታኔ ያበዛል ፤ ዘማሪማ እንደ
እሷ ያለ የትም አይገኝም ግን ወደ ዘፈን ትወስደዋለች ። ግን...ግን... ግን...
" #አሁን_ከሰማይ የወረድኩ የሕይወት እንጀራ እኔ ነኝ" የሚል የሕይወት እንጀራ ክርስቶስን
የምትወልድ ሆና ሳለ ቁራሽ እንጀራ አጡላትና በመቅደስ መኖሯ ጥሩ ነበር ግን ምን ትበላ
ይሆን ? ብለው ተቸገሩ ዮሐ 6÷56 የብትውና ሕይወት ከሰዎችና ከዓለም ምኞት
የሚገለሉበትና የሚርቁበት ሕይወት እንጂ ከፈተና የሚገለሉበት ሕይወት አይደለም ይልቁኑ
ፈተና በብቸኞች (ባዕታዊያን)ላይ ይበረታል። በዐታዊቷ እመቤታችንም ወደ በዓቷ ከመግባቷ
እስከ መውጧታ በአያሌው ተፈትናለች።
ዲያቢሎስ ተንኮለኛ ነው አስቀድሞ በመቅደስ የሕይወት ፍሬ መገኛ የሆነች ጸዋሪተ ፍሬ
ኤፍራታን እመቤታችንን ምግብ የሌለ አስመሰሎ በእጅጉ ፈተናት በኋላ ልጇ ወዳጇን ኢየሱስ
ክርስቶስን ደግሞ በመቅደሱ በገዳመ ቆሮንቶስ ተገናኝቶ ድንጋዮን ዳቦ አርግና እንብላ እያለ
በምግብ መትረፍረፍ ይፈትን ዘንድ አለውና " በዘርህና በዘሯ መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ
እንደተባለ" ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስ ይህን በመቅደሱ በገዳመ ቆሮንቶስ የገጠመውን የስስት
ፈተና በትእግሥት ድል የሚነሳው ነው እናቱ እናታችን እመቤታችን ቅድስት ድንግል
ማርያምም ይህን የመቅደስ ፈተና በቅዱስ ፋኑኤል እጅ በሚታይ በሰማያዊ መና
በተትረፈረፈ በረከት ድል የነሳችው ሆነች ።
#ሌላኛው_የመቅደስ ፈተና በቤተ መቅደሱ ጸንተን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሥራ
ሊሰራብን ባሰበ ጊዜ የሚገጥም የፈተና አይነት ነው 12 ዓመት በቤተ መቅደት ተቀምጣ
15ዓመት በሆናት ጊዜ መላእኩ ተልኩ መጥቶ ደስ ያለሽ ደስተኛይቱ ሆን ከሦስቱ አካላት
አንዱን አካል ከሦስቱ ቅዱስ አንዱን ቅዱስ ያለ ዘርዓ ብሕሲ (ያለ ወንድ ዘር) ትጸንሺዋለሽ
ትወልጅማለሽ ስሙንም አማኑኤል ትይዋሽ ብሎ አበሰራት ይህ ጊዜ አይሁድ ሴት ያለ ጋብቻ
ጸንሳ ከተገኘች በድንጋይ ተወግራ ትሙት የሚል ሕግ ነበራቸውና እንዳይወግሯት ጻድቁ
ዮሴፍ ይጠብቃት ዘንድ ተመረጠ አይሁድ ግን ቤተ መቅደሳችንን ታረክሳለች እንዴት ያለ
ወንድ ልትጸንስ ትችላለች አሉና ማየ ዘለፋ የተጸነሰ ጽንስ የሚያሶርድ መጠጥ ሰጧት
ጠጥታ የምትሞት መስሏቸው ቢያዮ ጨራሽ ፊቷ ከፀሐይ ሰባት እጅ አበራ በዚህ
ትተዋታል።
ከዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኃላ በስምተኛው ቀን ሌላኛው የመቅደሱ ፈተና መጣ
ይገርዙት ዘንድ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ የማዳኑን ነገር ሳያይ እንዳይሞት ተስፋ
የተሰጠው ስምዖንን በቤተ መቅደስ አገኙትና ባረካቸው እንዲም አለ " ጌታ ሆይ፥ አሁን
እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን
ማዳንህን አይተዋልና፤ ........እነሆ፥ የብዙዎች ልብ አሳብ ይገለጥ ዘንድ፥ ይህ በእስራኤል
ላሉት ለብዙዎቹ ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው ለሚቃወሙትም ምልክት ተሾሞአል፥
በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል አላት።” ሉቃስ 2፥29-35 የስእለትም ልጅ
አይደለች መከራዋ ብዙ ነውና ። እረፍት ያጣች እርሷ የብዙ ደካሞች እረፍታችን ሆነች
መከረኛዋ እርሷ የመከረኞች ተስፋችን ሆነች ። በበዐቷ የተፈተነች ብቸኞች እኛኝ ከፈጣሪና
ከአእላፍ ቅዱሳን መላእክት ጋር አዛመደችን።
#የእመቤታችን_የቅድስት_ድንግል_ማርያም እረድኤትና በረከት በሀገራችን በኢትዮጵያ
በሕቦቿም በሕዝበ ክርስቲያኖች ላይ ዘለለዓለሙ ጸንቶ ይኑር!አሜን!
ኃ/ማርያም አ.አ ኢትዮጵያ
ታህሳስ3/2013ዓ.ም