ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
Forwarded from ኣዝመራ / /ገብረመስቀል) ንዓይ ሂወተይ ክርስቶስ እዩ
እግዚአብሔርም፡የግብጽን፡ንጉሥ፡የፈርዖንን፡ልብ፡አጸና፥ርሱም፡የእስራኤልን፡ልጆች፡አሳደደ፤የእስራ ኤልም፡ልጆች፡ከፍ፡ባለች፡እጅ፡ወጡ

ስለመ እግዚአብሔር ይብዝላቹ
ዓወደ ምህረት መምህሮቸ ይሁ ብታብራሩልኝ እንድ እህታችን ሁለት ጊዜ እንደዛ ብላ ጠየቀትን በማሕበር የፍርኦን ልብ እግዚአብሔር ነው ውይ ያደነደነው ምን ለማለት ፍልጎ ነው ክይቅርታ
#በመጀመሪያ ስለጠየቁ እናመሰግናለን ቃለ ሕይወትን ያሰማልን ወደ መልሱ ስናመራ
#ቃሉ ዘጸ 7÷3 እና ዘጸ 14÷4 ላይ በተዳጋጋሚ የተነገረ ኃይለ ቃል ነው ።
በመጀመሪያ ይህ ልማደ ቅዱሳን መጻሕፍ ነው ቅዱሳን መጻሕፍት በልማዳቸው ምሥጢርን እንጂ ዘይቤን አይጠነቅቁም::ምን ለማለት ነው በምሥጢር ሊተላለፍ ለተፈለገው ነገር ይጨነቃሉ ወይም ምሥጢር እንዳይፈልስ ይጠነቀቃሉ እንጂ የንግግር ወይም(የአጻጻፍ )ዘዬ ላይ ብዙ አይጨነቁም:: የንግግር ወይም የአጻጻፍ ዘይዬ ከባሕል ከቋንቋና ከልማድ ጋር ተያይዘው የመጡ ናቸው ቋንቋ ባሕልና ልማድ ደግሞ ብዙ ዐይነት ነው መጽሐፍ ቅዱስ ደግሞ በብዛት በዕብራውያን ልማድ የተጻፈ ነው ስለዚህ ዕብራዊ ባሕል ና ልማድ የሌለው ሰው በቀላሉ ሊረዳውና ሊገነዘበው ያዳግተዋል ማለት ነው ስለሆነም ሁሉም ዓለም በቀላሉ ይረዳውና ይገነዘበው ዘንድ ቢቻል ዕብራዊ የንግግር ወይም የአጻጻፍ ስልትን ቢያውቅ ይመረጣል ይህ ግን በልዮነት የተመላች ዓለምን በአንዴ ወደ አንድ የመጨፍለቅ ያክል ነውና አዳጋች ነው :: ሁሉም የራሴ የሚለው ባሕል ልማድና የንግግር ፣ የአጻጻፍ ዘይ አለውና ። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ባወቀ ቅዱሳን መጻሕፍት ለዘይቢያዊ የአነጋገርና የአጻጻፍ ዘዴ እምብዛም ሳይጨነቁ ምሥጢርናብቻ እንዳጠነቅቁ አድርጎ አጻፈው :: በዘይቤ ብዙ ዓይነት ባሕል በዙ ይነት ዘይቤ አለና በምሥጢር ግን ሁሉም በተመሳሳይ መንገድያ አረዳድ ይረዱታልና ይህ ሆነ :: በመሆኑም መጻሕፍ ቅዱሳዊ ኃይለ ቃላትን ከአነጋገርና ከአጻጻፍ ዘይቢያቸው አንጻር ብቻ ማየቱ ተገቢ አይደለም ማለት ነው :: ይህ በእንዲህ ሆኖ ሳለ ቤተ ክርስቲያን በንባብ የጠመመውን በትርጓሜ በትሥጓሜ የጠመመውን በምሥጢር አስማምታ ቃለ ወንጌልን ለልጆቿ ትመግባለች በዚህ አንጻር ወደ ሀሳቡ አንግባ

በመሠረቱ እግዚአብሔር የፈርዖን ዐይነት ልብ ያላቸውን ጠማማ ሰዎች ልባቸውን ቃና ለማድረግ የሚተጋ ቀናዬ አምላክ ነው እንጂ ጠማሞች ሆነው እንዲቀጥሉ የሚያግዝ አምላክ አይደለም:: ነገር ግን ሰው ከእግዚአብሔር በተቸረው ነጻ ፍቃዱ ልቡን ሊያደነድን ወይም ድንጋይ ሊያደርግ ይችላል :: ታድያ እግዚአብሔር በዚህ ጊዜ በጊዜም ያለጊዜም በምክንያትም ያለ ምክንያትም በመምህራንም ያለ መምህራንም ይመለስ ዘንድ በልዮ ልዮ አጠራሩ ይጠራዋል ግን ፍላጎቱን ተጋፍቶ የግድ ቅን ሁን ብሎ አያስገድደውም ፍትሐዊ አምላክ ነውና :: እሺ በጄ ብሎ ቢመለስ መልካም ነው በመመለሱ ቅን በመሆኑ ሊያገኝ የሚችለውን ዋጋ በጊዜው ይከፍለዋል እሺ በጄ ብሎ ባይመለስ ግን እንደ ጥመቱ መጠጥ የጥመቱን ዋጋ በጊዜው አወራርዶ ያስረክበዋል


" በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ። እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ፥ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።

#ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ። አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፤ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ። 2ሳሙ 22÷26-28

ስለዚህ ለሙሴና ለአሮን እንዲሁም በወቅቱ ቅን ለሆኑት ሕዝቦች(ለሕዝበ እሥራኤል) በቅንነት ፈረደላቸው በአንጻሩ ጠማማ በሆኑት በፈርዖን እና በሰራዊቱ ደግሞ ፈረደባቸው ።

ስለዚህ ከቅኖች ጋር ቅን ሆኖ እንደሚገኝ በቅንነትም እንደሚፈርድላቸው ለጠማሞችም እንደ ጥመታቸው እንደሚፈርድባቸው ለመናገር የፈርዖንን ልብ አጸናለው አለ
እግዚአብሔር የሌለበት ቦታ የለም (ምሉዕ በኩልሄ )በሁሉ ያለ ነው አኗኗሩ ግን ይለያያል ከክፋዎች ጋር በመአቱ ከቅኖች ጋር ደግሞ በምሕርቱ ይገኛል።

"ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።”መዝ 138(139)፥10

#እግዚአብሔር ከቅኖቹ ከነሙሴ ጋር በቅንነት አለ ከጣማሞቹ ከነ ፈርዖንም ጋር በጠማምነት አለ ።
ልበ አምላክ ክቡር ዳዊትም አክሎ በሌለ ሥፍራ ላይ ይህንኑ ሀሳብ እንዲ ሲል ያጠነክርልናል

" ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።" መዝ 18÷ 25



ይህ ማለት ግን ክብር ምሥጋና ይግባውና እግዚአብሔር ጠማማ ነው ጠማማነት ይስማማዋል ማለት አይደለም እርሱ በባሕሪው ፍጹም ቅን አምላክ ነው:: ስለሆነም እግዚአብሔር ፈታሄ በርትዕ ኮናኔ በጽድቅ እየተባለ ይጠራል።



ስለዚህ #እግዚአብሔር _የፈርዖንን_ልብ_አጸናለው አለ ሲባል ይመለስ ዘንድ ሊቀ ነቢያት ሙሴንና ካህኑ አሮንን ወደ እርሱ ልኬ እግዚአብሔር ዕወቅ እሥራኤልንም ልቀቀ ብለው አሻፈረኝ ብሎ ልቡን እንዳደነደነ እንደ ደንዳንነቱ መጠን እመልስለታለው ሲል እንደ ጸና ብኝ እጸናበታለው ሲል የፈርዖንን ልብ አጸናለው ብሎ ተናገረ

አንድም ይህ የደነደነ አልመለስ ያለ ልብ ኃያልነቴን ብርታቴን ያይ ዘንድ ሕዝበ እሥራኤልም ቅን ፍርዴን አይተው በሃይማኖት እንዲጸኑ በምግባርም እንዲቀኑ የፈርዖን ዳተኛ ልብ ምን እዳመጣበት እስከሚያዮ ድረስ የፈርዖንን ልብ ትጸናለች ሲል ነው።


እንጂማ እግዚአብሔር አስቀድሞ ሰማዕት ወነቢይ የሆነው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ከበርሃ ጀምሮ ጠማማው ይቅና ተራራውም ዝቅ ይበል ካልተስተካከለ መንገድ የለምና እያለ የጠመመ ልብ ያላቸውን በስብከቱ እያቀና ሥርጓጉጡንም ልብ በትምህርቱ እየደለደለ እንደ ተራራ በክፉትና በትዕቢት የተወጠረ ልባቸውን በትዕትና ዝቅ እንዲያደርጉ ያስተማረለት እርሱ #እግዚአብሔር የደነደነ ሰው ልብን በፍቅር የሚሰብር እንጂ እንደ ክፉሁ መካሪ ወደ ጥፋት ስንሄድ እያየ የሚያበረታታንና የሚመክን ልባችንንም በክፉሁ እንዲጸና የሚያደርግ አምላክ አይደለም ከዛ ይልቅ የደነደነ የድንጋዮን ልብ የሚያወጣ በጥሩ ውኃ(በጥምቀቱ) ከአረጀንበት የኃጢያት ብስቁልና አውጥቶ በልጅነት ዳግም ንጽሕ ያደረገን ፍቅራዊ አባታችን ነው

#ጥሩ ውኃንም እረጭባችኋለሁ እናንተም ትጠራላችሁ፥ ከርኵሰታችሁም ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አጠራችኋለሁ። #አዲስም_ልብ_እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ #የሥጋንም_ልብ እሰጣችኋለሁ።
#ሕዝ 36÷25_26

የሁላችን ልብ እንደ ፈርዖን የደነደነ ነውና ልባችን እንዲሁ አንዲቀር አያጽናብን የድንጋዮንም ልብ አውጥቶ የሥጋውን ልብ ይስጠን....አሜን🙏
እነሆ ሐዲስ መላእክ
ተክለ ኤል
ተፈጥሮ ከመላእክት ወገን ያልሆነ ሰው ሆኖ ሳለ ነገር ግን በሃይማኖቱ ጽናት በምግባሩ ቅንሐት እና በተጋድሎዎ ብዛት ምድራዊ ሲሆን ሰማያዊ አዳማዊ ሲሆን መላእካዊ ለመሆን የበቃ ሐዲስ መላእክ ነው :: ተክለ ኤል

ቅዱሳን መላእክት በዘር የተገኙ አይደሉም ተክለ ኤል (ተክለ ሃይማኖት ) ግን ከሕግ ዘር የተገኘ ሰው የሆነ አዲስ መላእክ ነው ::

‹ተክል› ማለት ፍሬያማ ዕንጨት፣ ዛፍ፣ ቅመም፣ ቅጠላ ቅጠል፣፣ የሚሸተት፣ቢበሉት ጥጋብ ፣ቢያርፉበት ጥላ የሚሆን ገነታዊ ዕፅ፣ እንዲሁም ሕግ ሥርዓት ማለት ነው /ማቴ.፲፭፥፲፫/፡፡

"ኤል" ማለት ደግሞ እግዚአብሔር ማለት ነው :: ስመ መላእክት ስመ እግዚአብሔርን ያዘለ በመሆኑ የሁሉም ቅዱሳን መላእክ ስም "ኤል" የሚል መቀጽል አለው ለምሳሌ :-ሚካ-ኤል ፣ ገብር-ኤል ፣ ዑራ -ኤል፣ ወዘተ .... ስለዚህ ተክለ ኤል ስንልም የእግዚአብሔር ተክል ማለታችን ነው :: ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ባስልዮስ ዘ ቄሳሪያ እኔስ #እግዚአብሔር ባልኩ ጊዜ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለቴ ነው ብሎ እንደተናገረ እግዚአብሔር ስንል አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለታችንና ተክለ ኤል ማለት የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተክል ማለት ጭምር ነው::

ቦታው በሸዋ ክፍለ ሀገር ዛሬ ኢቲሳ በመባል በሚታወቀው ከከሰም ጅረት አካባቢ ባለ ቦታ በጥንቱ ፈጠጋር ቡልጋ በደብረ ጽላልሽ አውራጃ ዞረሬ በተባለው ሥፍራ ነው ። በዚሁ ሥፍራ (ዘርዐ ዮሐንስ) ፀጋ ዘአብ የሚባል የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህን የነበረ ጻድቅ ሰው ነበር "ጸጋ ዘአብ " ማለት የአብ ሥጦታ ማለት ነው ካህኑ ጸጋ ዘአብ በሃገሩ ደጋግ ከሆኑ ሰዎች ወገን ሣራ የምትባል ሴት አገባ ።

ሁለቱም ፈሪያ እግዚአብሔር ያደረባቸው በጎ ሥራን የሚሠሩ ሰዎች ነበሩ የፀጋ ዘአብ ሚስት ሣራ ሃይማኖት ከምግባር መልክና ደም ግባት ከሙያ ጋር አሟልቷ የሰጣት ሴት ነበረች ። አማቷ የፀጋ ዘአብ አባት " ወረደ ምሕረት " የሥራዋን ደግነት አይተው " እግዚኀረያ " ብለው ስም አወጡላት ጌታ የመረጣት ማለታቸው ነው።

በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ ወላጆቻቸውም ፍስሐ ፂዮን ።(የፂዮን ደስታዋ)ብለው ሰየሟቸው፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል። ይህን ጊዜ እናታቸው እግዚ ኀረያም በመገረም ሆና " ይህ ሥራ የአባት ነው ላንተ የሚገባህ ጡት መጥባት ነው" ብላ ጡቷን አጎረሰችሁ ፡፡

ቅዱሳን መላእክት ቀን ከሌት ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ያመሰግናሉ ኢሳ 6፥÷6 ይህም የህጻኑ ሁኔታ መላእካዊ ግብሩን ገና በህጻንነት የገለጠ ሁኔታ ነበር። ካህኑ ፀጋ ዘአብ የወቅቱን የቤተ ክርሰቲያን አገልግሎታቸውን ጨርሰው ወደ ቤታቸው ሲገቡ ሚስታቸው እግዚ ኀረያ በመገረም ሆና የሦስት ቀን ልጃቸው ፍስሐ ፂዮን እንዴት ባለ ምሥጋና ፈጣሪያቸውን እንዳመሰገነ ነገረቻቸው ጸጋ ዘአብም ህጻኑን ተቀብለው ታቅፈው እየሳሙ ልጄ ሺህ ዘመን ኑርልኝ እንዲ እያልክ በቤተ መቅደስ ስትቀድስ አይህ ዘንድ እመኛለው አሉ።
‹‹ተክለ ሃይማኖት›› ብሎ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ፍስሐ ፂዮን የሚለውን ስሙን በፈጣሪው ትዛዝ መሠረት ጠራቸው፡፡ በተወለዱ በ15 ዓመታቸው ዲቊናን፤ በ22 ዓመታቸው ደግሞ ቅስናን ከግብፃዊው ጳጳስ ከአባ ጌርሎስ ወይም (አባ ቄርሎስ) ዘንድ ተቀብለዋል፡፡

ሐዋርያዊ ተግባርንም በከተታ እና በፈጠጋር (በጽላልሽና በአካባቢዋ፣በዳሞት በምድረ ወላይታና አካባቢው ፣በአምሓራና በሸዋ በሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ፣ በኣድያማተ ትግራይ፣በገዳመ ዋሊ (ዋልድባ) ፣በገነተ ማርያም ላስታ በደብረ ዘመዶ ማርያም ገዳም በዚያው በላስታ፣ በኤርትራ ገዳማት ፣በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ገዳም ወዘተ በአገሪቱ ወንጌል ባልተዳረሰበት ቦታ ሁሉ እየተዘዋወሩ ኢትዮጵያ አንዲት የሐዋርያት ወንጌል ሰፍተዋታል ።
ጻድቁ አባታችን ሕይወታቸዉን ሙሉ ለእግዚአብሔር በመስጠት፣ እንደ በሬ ተጠምደው፣ እንደ ገበሬ ታጥቀው፣ ይህንን ዓለም ንቀው፣ በጾም በጸሎት ተወስነው በብሕትውና በመኖራቸው፤ እርሳቸው በአሚነ ሥላሴ ጸንተው ሌሎችንም እንዲጸኑና እንዲያምኑ በማድረጋቸው፤ እንደዚሁም እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ወንጌልን በመላው ኢትዮጵያ እየተዘዋወሩ በመስበክ በጌታችን በመድኀኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ድውያነ ሥጋን በተአምራት፣ ድውያነ ነፍስን በትምህርት የፈወሱ ሰባኬ ወንጌል በመኾናቸው ‹‹ተክለ ሃይማኖት›› ተብለው ይጠራሉ፡
በየ ደረሱበትም ከሥራው ጽናት ከተአምራቱ ብዛት የተነሳ አንተ ሰውነህን ወይስ መላእክ ነህ ንገረን ይሉት ነበር በዚህም በደብረ ዳሞት አቡነ አረጋዊ ገዳም 10 ዓመት ከቆዮ በኃላ ተሰናብቷቸው ሊሄድ ተነሳ ሁሉም ከፍቅሩ ጽናት የተነሳ አለቀሱለት አበምኔቱም ይህን ሰው ኃጢያቴ አባሮታልና ወየውልኝ ብሎ መነኮሳቱን ሰብስቦ ሊሸኙት ተነሱ ከገዳሞም ያለ እረጅም ገመድ(ጠፈር)መውረድም ሆነ መውጣት አይቻልም ነበርና የመውረጃውን ገመድ (ጠፍር) ይዞ ይወርድ ዘንድ ጀመረ ጥንተ ጠላት ዲያቢሎስ ገመዱን ከካስማው ላይ ቆረጠው አባታችንም ይህን አስደንጋጭ ክስሀት ተከትሎ የተሰጣቸው የፀጋ ክንፍ በገዐድ ተገለጠ አበ ምኔቱና መነኮሳቱም ከገዳሙ አፈፍ ሆነው የሚሆነውን ያዮ ነበር ጻድቁም እንደ ሰማያዊ መላእክ በክንፉቸው በረው በደህና ከመሬት ደረሱ መነኮሳቱም መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁ ብለው አደነቁ::
ከዚህም ባለፈ ህዳር 24ቀን መላእኩ ከምድራዊ ቦታቸው ነጥቆ ወስዶ ከሱራፌል ጋር ቀላቀላቸው በልጅነት አንደበታቸው አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ብለው ያመሠገኑት አግአስተ ዓለም ቅድስት ሥላሴን ዛሬ ደግሞ በዙፋኑ ላይ እናዳለ እያዮት በከንፈሮቻቸው ሰለሱት ቀደሱት በወርቅ ማዕጥንትም ዙፋኑን አጠኑ ።ወደ ቀደመም ኑሯቸው መላኩ መለሳቸውና ተጋድሏቸውን ቀጠሉ።

በገዳመ አስቄጥስ ግብጽ እና ከኢየሩሳሌም።ጉብኝት በኃላ እየዞሩ ወንጌልን ለማስተማር ባይቻላቸው ስለዚህ በአንድ ቦታ መቆምን መረጡ ከፊት ከኃላ ከግራ ከቀኝ የሚያነቃ የሶር ሶማያ ስለው በመትከል በደብረ አስቦ በደብረ አስቦ ዋሻ ከዘረጉ ሳያጥፉ ከቆሙ ሳይቀመጡ ለ22 ዓመታት በጸሎት ጸኑ ጥር 4 ቀን 12 88ዓ.ም በ92 ዓመት ሲሆናቸው አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ከመቆም ብዛት ተሰብራ ወደቀች ጸሎታቸውንም ሳያቆርጡ በአንድ እግራቸው 7 ዓመት አክለው በጸሎት ተጎ በድምሩም 29 ዓመት በጸሎት ተጋደሉ :: ከፈጣሪ ዘንድም ብዙ ጸጋና ቃል ኪዳን ከተቀበሉ በኃላ በ99ዓመት ከ10ወር ከ10ቀናቸው ነሐሴ 24 ቀን በክብር አርፈዋል:: እንደ ሰው በምድር ተወልደው እንደ መላክት የኖሩ አዲስ መላክ ያልናቸውም ለዚሁ ነው።

የጻድቁ አባት የአቡነ ተክለ ሃይማኖት እረድኤት በረከታቸው በአማላጅነታቸው የምትገኝ ጸጋ ለዘለዓለሙ ከእኛ ጋር ትኑር .....አሜን!

ኃ/ማርያም
ጥቅምት 2013ዓ.ም
አ.አ ኢትዮጵያ
👇👇👇👇👇👇👇
#ዓውደ_ምሕረት የእናንተ
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Audio
ክ·ሥነምግባር001_2.amr
1.4 MB
Audio
ት·ሃይማኖት02_1.3gpp
1.9 MB
Audio