ዐውደ ምሕረት
3.69K subscribers
929 photos
24 videos
271 files
192 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
የሚከላከሉትና ጥቃት የሚያደርሱት በቀንዶቻቸው አማካኝነት ነው ስለዚህ ቀንዳቸው ኃይላቸው ሥልጣናቸው ነው :: ታዲያ ይህ ለአብርሃም በይስሐቅ ፈንታ ይሰዋው ዘንድ የተሰጠው በግ እንደማንኛውም የቀንድ ከብት እራሱን ከአራጁ የሚከላከልበት ኃይልና ሥልጣን ያለው ቀንዳም በግ ቢሆንም ቀንዱ ግን በ አፀ ሳቤቅ ስለተያዘ ያን ያደርግ ዘንድ አላስቻለውም ። በሕልውና ፣በሥልጣን ፣በኃይል ከባሕሪ አባቱ ከአብ እና ከባሕሪ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል (እኩል ፣የተተካከለ) ቢሆንም ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስም በሰው ልጆች የፍቅር እጸ ሳቤቅ ተይዟልና ከልዕልና ወደ ትዕትና ዝቅ አለ ባሕሪውንም ሰውሮ እንደኛ የተገዢ የሰውን አራዐያ ነሳ። ፍቅር ሰአቡ ኃያል ወልድ እም መንበሩ ወአብጽዮ እስከ እለ ሞት / #ፍቅር ኃያል ወልድን ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው"/ የበጉ ቀንድ በእጸ ሳቤቅ ስለተያዘ ከመታረድ እንዳልሸሸ ና በቀንዴም ተዋግቼ ላምልጥ ብሎ የቀንዱን ሥልጣን እንዳልተጠቀመ ሁሉ ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስም በፍቃዱ በሰው ፍቅር ተይዟልና ሥልጣን ሁሉ የእርሱ ሆኖ ሳለ ሥልጣኑን ሳይሆን ፍቅሩን ተጠቅሞ ለኛ ተሰውቶ አዳነን:: "ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም። በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?" ኢሳ 53፥7-8

#የአሮን በትር ዘኁልቁ 17÷8
ሙሴም ለእስራኤል ልጆች ተናገራቸው፤ አለቆቻቸው ሁሉ አሥራ ሁለት በትሮች፥ እያንዳንዱም አለቃ በየአባቱ ቤት አንድ አንድ በትር፥ ሰጡት፤ የአሮንም በትር በበትሮቻቸው መካከል ነበረች። ሙሴም በትሮቹን በእግዚአብሔር ፊት በምስክሩ ድንኳን ውስጥ አኖራቸው። እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ ወደ ምስክሩ ድንኳን ውስጥ ገባ፤ እነሆም፥ ለሌዊ ቤት የሆነች #የአሮን_በትር_አቈጠቈጠች_ለመለመችም_አበባም_አወጣች የበሰለ ለውዝም አፈራች። ሙሴም በትሮችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ፊት ወደ እስራኤል ልጆች ሁሉ አወጣቸው፤ እነርሱም አዩ፥ እያንዳንዱም በትሩን ወሰደ። እግዚአብሔርም ሙሴን፦ የአሮንን በትር ወደ ምስክሩ ፊት መልስ፤ ማጕረምረማቸው ከእኔ ዘንድ እንዲጠፋ እነርሱም እንዳይሞቱ ለሚያምፁብኝ ልጆች ምልክት ሆና ትጠበቅ አለው።
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የማክሰኞ እርሻ ትባላለች የማክሰኞ እርሻ ገበሬ ሳይኮተኩታት ውኃም ሳያጠጣት አብባ አፍርታ ተገኝታለች ይህች የማክሰኞ ዕለት እርሻ የመጀመሪያይቱ ምድር ወይም ጥንተ ምድርም እየተባለች ትጠራለች የሶሪያው ሊቅ ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊም አክሎ በውዳሴው እንዲ ብሏታል #ሳይተክሏትና ውኃ ሳያጠጧት የለመለመች የአሮን በትር ነበር እንቺ እንደርሷ ነሽ" #አባ ኤፍሬም ሶሪያዊ #ውዳሴ_ማርያም ዘ እሁድ

#የኖህ መርከብ ዘፍ 6፥14
በኖህ መርከብ ፍጥረት ከጥፋት እንደተረፈ በእመቤታችንም ከጥፋት ድኗል ። የኖህ መርከብ ሦስት ክፍሎች ነበሯት እመቤታችንም በሦስት ነገሯ ንጽሕት ነች በሥጋዋ ፣በነፍሷ፣ በሕሊናዋ የጋስጫ ፍሬ አባ ጊዮርጊስ "በመኑ ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ " ድንግል ሆይ በምንና በምን እንመስልሻለን ምሳሌን የለሽም" እንዳለ ምሳሌዎች ሁሉ እመቤታችንን አይመስሏትም(አይመጥኗትም)
#የኖህ መርከብ ስምንት ሰዎችና ብዙ ዐይነት እንሰሳት ገብተውባታል ወጥተውባታል
#በእመቤታች ግን ከኃያላ ከጌታ በቀር ወደ እርሷ ገብቶ የወጣ የለም
#በኖህ መርከብ ሲገባም ሲወጣም በሮቹአን ከፍተው ዘግተው ነው
#እመቤታችን ግን ማንም ለዘላለሙ የተዘጋች ገነት የታተመች ፈሳሽ ነችና ዘላለም እትዕምት ፣ዝግ ፣ድንግል ነች ። ጌታችንንም የጸነሰችው እንዲሁ ዝግ ሆና ነው ስትወልደውም እንዲሁ ዝግ ሆና ነው። " ወደ ምሥራቅም ወደሚመለከተው በስተ ውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም፦ ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፥ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል።" ሕዝ 44÷1-2
#ወደ ኖህ መርከብ የገቡት እንሰሳት እንሰሳዊ ጠባያቸውን ሳይለቁ ነው የወጡት ለምሳሌ ወደ ኖህ መርከብ የገባ አንበሳ ሲወጣም የአንበሳነቱን ሥጋ ቦጫቂነቱን ሳይለቅ ወጣ ፣ነብሩም ደም መጣጭነቱን ሳይተው ወጣ ፣በግም ውኃም መጎንጨቱን ሳር ጋጪነቱን ሰይለውጥ ወጣ ::

#በእመቤታችን ምልጃ አምኖና ተማምኖ አማልጂኝ ብሎ በሥሯ የተጠለለባት ሰው ግን እንዲሁ እንደ ኖህ መርከብ በቀደመ ግብሩ አይቆይም ንፉጉ ለጋሽ፣ጨካኙ እሩሩ ፣ ዘማዊው ድንግል ሆኖ ተለወጦ ይገኛል ስለዚህ እመቤታችን ከኖህ መርከብ በእጅጉ ትልቃለች ትበልጥማለች :: ዝም ብለን እንደ ሊቁ
......በመኑ ወበ አምሳለ መኑ ናስተማስለኪ........ እንበላት።
.............ይቆየን..............
እረድኤትና ቃልኪዳኗ አማላጅነቷም ለዘለዓለሙ ከኛ አይራቅ ...አሜን!
ኃ/ማርያም
👇👇👇👇👇
@YEAWEDIMERITE

#ዓውደ ምሕረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
👆👆👆👆👆👇