ዐውደ ምሕረት
3.66K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
#ሱባዔ

ሱባዔ በሰዋሰው ትርጉሙ ቆየ ሰነበተ ዘገየ ሰባት ማለት ሲሆን ምሥጢራዊ ትርጓሜውም ደግሞ አንድ ሰው ከዚህ ቀን እከዚህ ቀን ድረስ ፈጣሪዬን በጸሎት እገናኛለሁብሎ የሚያቅደው ዕቅድ ነው። ሰባት ቁጥር በእስራኤላዊያን ዘንድ በሥራም በቃልም የሚገለጥ ፍጹም ቁጥር ነው ፈጣሪ ዓለማት እግዚአብሔር በሰባተኛው ቀን ሥነ ፍጥረትን ከመፍጠር አረፈ እንዲል በጸሎት የሚተጉ ምዕመናንም በቀን ሰባት ጊዜ ማመስገናቸው የሰባት ቁጥርን ፍጹምነት ያመለክታል ። ሱባዔ የተጀመረው ከመጀመሪያው ሰው አዳም ውድቀት በኋላ ነው ቅዱሳን መላእክት አዳምን ጸሎት እንዴት እንደሚጸለይ እንዳስተማሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይናገራሉ። ለአዳምም የጸሎት ጊዜያትን አስተምረውት አስተምረውት ነበርና ጥፈቱን አምኖ ሱባዔ በመግባቱና በመጸለዩ እግዚአብሔርም በማይታበል ቃሉ ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ ከልጅ ልጁ ተወልዶ እንደሚያድነው ቃል ኪዳን ገባለት ።



ሱባዔ ለምንምክንያት እንገባልን ቢሉ የመጀመሪያው የሚሆነው የሰው ልጅ በባህሪው ኃጢአት የሚስማማው ነው በሥጋ ሰውነቱ ፈጣሪን ይበድላል በፈጸመው በደል / ኃጢአት/ ሕሊናው ይወቅሰዋል በዚህም ያዝናል ይጸጸታል በሰራው ኃጢአትም ልቡ ይደነግጣል በዚህ ጊዜ የፈጣሪን ይቅርታ ለማግኘት ሲል ሲል ሱባዔ ይገባል ።እግዚአብሔርን ለመማፀን የሚገባ ሱባዔ አለ ። ማንኛውም ሰው ሱባዔ በገባ ቁጥር ወደ ፈጣሪው የሚያቀርበው ተማጽኖ ሊኖረው ይገባል ምንም የምንለምነውና የምንጠይቀው ነገር ሳይኖር ሰባዔውን ብንገባ የምናገኘው ምንም አይነት መልስ አይኖርም
ስለዚህ ተማፅኖ ሊኖረን ይገባል ። ያለ ምንም ቅድመ ሆኔታና ዝግጅት ሱባዔ የሚገቡ ሰዎች ከሱባዔው በኋላ ምን እንደተመለሰላቸው የሚያውቁት ነገር ስለማይኖራቸው ሱባዔ በመግባታቸው የሚገኙት ነገር አይኖርም ይህን ተገንዝበው ከመግባታቸው በፊት የሚገቡበትን ምክንያት ራሳቸውን መጠየቅ አለባቸው ። ቅዱሳን አባቶችና ቅዱሳት እናቶቻችን ደማቸውን ካፈሰሱበት አጥንታቸውን ከከሰከሱበት ድንቅ ድንቅ ገቢረ ተአምራት የሰሩበት ቦታ ገዳማቸውና አድባራት ላይ የሚገባ ሱባዔ ከቅዱሳኑ ረድኤት ተካፋይ ይደርጋል ። ሱባዔ የተደበቀን ምሥጢር የሚገለጥበት ቁልፍ የቤተክርስቲያን ሥርዓት ነው ቅዱሳን አባቶቻችን ያዩት እራይ ምሥጢሩና ትርጉሙ አልገለጥ ሲላቸው ሱባዔ ይገቡ ነበር እግዚአብሔርም በንጽሕና ሆነ ነው የገቡትን ሱባዔ ተመልክቶ ምሥጢሩንና ትርጉሙን ይገልጥላቸዋል ። ነቢዬ ዕዝራ የመጽሐፍታት ምሥጢር እንዲገልጥለት ሱባዔ ገባ እግዚአብሔር አምላክም ሁሉን ገለጸለት የጠፉትን የብሉይ ኪዳን መጽሐፍታት ደግሞ ለመጻፍ ችሏል ይህ ምሥጢር የተገለጠለት በሱባዔ ነው ።

ከብሉይ ጀምሮ ያሉ የሱባዔ አባቶቻችን የገቡት ሱባዔ ሱባዔ አዳም ፣ ሱባዔ ሔኖክ ሱባዔ ነብያት
፣ሱባዔ ዳንኤል ሱባዔ ዳዊት በተጨማሪም የግል ሱባዔ የማኀበር ሱባዔ የአዋጅ ሱባዔ በመባል ይታወቃሉ በሐዲስ ኪዳን ከአራት ቀን በኋላ የምገባ ሐዋርያት የገቡት ሱባዔ ነው የፍልሰታ ሱባዔ በዚህ ሱባዔ ተሰውሮ የነበረውን የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ቅዱስ ሥጋ የተገኘበት ትንሣኤዋ እንዲገለጥላቸው የተገባ ሱባዔ ነው ። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን 14 ቀን ያክል በጻም በጸሎት ተማጽነው ትንሣኤዋን ገለጠችላቸው ። እንግዲህ ሱባዔ ከብዙ በጥቂቱ ይህንን ይመስላል ወቅቱ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የፍልሰታ ስባዔ እንደ መሆኑ መጠን እኛም የሐዋርያቱን ፈለግ በመከተል በንጹሕ ልቦና በትሁት መንፈስ ሆነን የእናታችን ትንሣኤ ይገለጥልን ዘንድ በሱባዔው እንትጋ ። ለሐዋርያቱ በሙሉ የልባቸውን መሻት የፈጸመች የጌታችን እናት ድንግል ማርያም የእኛንም የልባችንን ትፈጽምልናለች። ወቅቱን የጾም፣የጸሎት፣የስግደት፣ የምጽዋት፣ ስለ ሀገራችን ኢትዮጲያ የምናለቅስበት ነው ። ስለዚህ ሁላችን በሱባዔው እንበርታ

“በሐዋርያትም ትምህርትና በኅብረት እንጀራውንም በመቍረስ በየጸሎቱም ይተጉ ነበር።”
— ሐዋርያት 2፥42
#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit

.....ይቆየን.......
ምንጭ :-እናት ማህበሬ ምክሐ ደናግል ሰሌዴ መጽሔት ሐምሌ ና ነሀሴ2010ዓ.ም የተለጠፈ
#ሱባዔ ነቢያት

እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል ኪዳን መሠረት በማድረግ ቀደምት ነቢያት በተነሡበት ዘመን ቅደም ተከተል ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው መሆንና ዳግም መምጣት ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ሱባዔም ቆጥረዋል፡፡ ኢሳ.7.14፡፡ መዝ.49.3፡፡ ዘካ.13.6፤ ዘካ.14.1፡፡ የአንዱ ነቢይ ትንቢታዊ ንግግርና ሱባኤ በአነጋገርና በአቆጣጠር ከሌላኛው ነቢይ ጋር ይለያያል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ትንቢቱን ሲያናግር ምሳሌውን ሲያስመስል ጐዳናው ለየቅል በመሆኑ ነው፡፡ «ከጥንት ጀምሮ እግዚአብሔር በብዙ ዓይነትና በብዙ ጐዳና ለአባቶቻችን በነቢያት ተናገረ፡፡» እንዲል፡፡ ዕብ.1.1፡፡ የአቆጣጠር ስልታ ቸውና የሱባዔ መንገዳቸው ቢለያይም ዓላማና ግባቸው ግን አንድ ነው፡፡

#ሱባዔ አዳም

አዳም ትንቢት በመናገርና ሱባዔ በመቁጠር የመጀመሪያውን ሥፍራ ይይዛል፡፡ ምክንያቱም በገነት ሰባት ዓመት ከአንድ ወር ከዐሥራ ሰባት ቀን በተድላና በደስታ ከኖረ በኋላ ሕግ በማፍረሱና የፈጣሪውን ቃል በመጣሱ ያለምንም ትካዜና ጉስቁልና ከሚኖርበት ዔደን ገነት ተባርሯል፡፡ ዘፍ.3.24፡፡ እርሱም ፈጣሪው እንዲታረቀው፣ በዐይነ ምሕረት እንዲጐበኘው፣ ቅዝቃዜው ሰውነት ከሚቆራርጥ ባሕር ውስጥ በመቆም ለሠላሳ አምስት ቀን /አምስት ሱባዔ/ ሱባዔ ገብቷል፡፡ በባሕርዩ የሰውን ልጅ እንግልት የማይወድ ቸሩ ፈጣሪ የአዳምን ፈጽሞ መጸጸት ተመልክቶ «በኀሙስ ዕለት ወበመንፈቃ ለዕለት እትወለድ እምወለተ ወለትከ ወእድኅክ ውስተ መርህብከ ወእቤዝወከ በመስቀልየ ወበሞትየኸ በአምስት ቀን ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ» ብሎ ተስፋውን ሰጠው፡፡ አዳም የተሰጠውን ተስፋ ይዞ በዓለመ ሥጋ ለዘጠኝ መቶ ሠላሳ አመት ከኖረ በኋላ መከራና ችግር ከበዛበት ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
በወንጀል ተከሶ በወኅኒ የተፈረደበት ሰው ከእስር የሚፈታበትን ዕለት በማውጣት በማውረድ ወራቱንና ዓመታቱን እንደሚቆጥር፣ አዳምም በሞት ቢለይም በሲኦል የነፍስ ቅጣት ካለበት ሥፍራ ይኖር ስለነበር የተሰጠውን ተስፋ በማሰብ ሱባዔውን እየቆጠረ የተናገረውን የማያስቀር የማያደርገውን የማይናገር ጌታየ «እነሆ አድንኀለሁ» ብሎ የገባልኝ ዘመን ተፈጸመ፤ ሰዓቱ አሁን ነው፤ እያለ ሲያወጣ ሲያወርድ ቸር አምላክ ሰው ኾኖ ሥጋ ለብሶ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወርዶ፡- «ተንሥኡ ለጸሎት ለጸሎት ተነሡ፤ ሰላም ለኩልክሙ፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን» በማለት አዳምን ከነልጅ ልጆቹ ነጻ አውጥቶታል፡፡ አዳምን በመከተል ልጆቹም አበው ቅዱሳን ነቢያት ሱባዔ በመግባት የተስፋን ዘመን በመቁጠር በመልካም ግብር ተከትለውታል፡፡ በዚህም መሠረት በርካታ ነቢያት በተለያየ ስልት ሱባዔ ቆጥረዋል፤ እኛም ሱባዔ ከቆጠሩ ነቢያት የተወሰኑትን በዚህ ጽሑፍ እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

#ሱባዔ ሔኖክ

ጻድቁ ሔኖክ፣ የያሬድ ልጅ ሲሆን፣ በትውልድ ከአዳም ሰባተኛ ነው፡፡ እርሱም በሕይወቱ እግዚአብሔርን ደስ ለማሰኘት ቤት ንብረቱን በመተው በሱባዔና በትሕርምት እግዚአብሔርን አገልግሏል፡፡ ፍጹም አካሔዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ሰው በመሆኑ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን መልካም ግብር ተመስክ ሮለታል፡፡ «ሔኖክም አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ፡፡» ዘፍ.5.22፡፡ ይህም በመሆኑ እግዚአብሔር የሱባዔውን ዋጋ ቅዱስ መንፈሱን በረድኤት ስለ አሳደረበት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ በሰማይ ተሰውሮ ሳለ ስለ ቅዱሳን መላእክት፣ ስለ መሲሕ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ፀሐይና ጨረቃ አመላለስ /ዑደት/ የሚተርክ በስሙ የተሰየመውን መጽሐፍ ጽፏል፡፡ ዘፍ.5 21-24፡፡ ይሁዳ ቁ.14፡፡ ሔኖክ 1.9፡፡
ሱባዔ ሔኖክ የሚባለው ነቢዩ ሔኖክ በመስፈርት የቆጠረው ሱባዔ ነው፡፡ መስፈርቱ /ማባዣ ቁጥር/ 35 ሲሆን 35'19 ሲበዛ በውጤቱ 685 ዓመት ይሆናል፡፡ 685'12 ስናባዛው 7980 ይሆናል፡፡ ይኸውም ሐሳብ የሚያስረዳው ስለክርስቶስ ምጽአት ነው፡፡
ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ አሁን የደረስንበት ዘመን 7497 ይሆናል፡፡ ይህን ለማረጋገጥ በ5500 ዓመት ላይ 1997 ዓመትን መደመር ነው፡፡ በዚህን ጊዜ ከላይ ያስቀመጥነውን 7497 ዓመት ይሰጠናል፡፡ በነቢዩ ሔኖክ አቆጣጠር መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ በ7980 ይሆናል፡፡ ከላይ ሔኖክ የቀመረውን ቁጥር ይዘን ከ7980 ዓመት ላይ አሁን ያለንበትን ዘመን /1997/ ስንቀንስ 483 ዓመት እናገኛለን፡፡ ስለዚህ በሔኖክ ሱባዔ መሠረት ምጽአተ ክርስቶስ ሊሆን 483 ዓመት ይቀራል፡፡

#ሱባዔ ዳዊት

ነቢዩ ዳዊት ከእስራኤል ነገሥታት ሁሉ ታላቅና ተወዳጅ ንጉሥ ነበር፡፡ ዘመነ መንግሥቱ 1011-971 ከክርስቶስ ልደት በፊት እንደ ነበር ይታመናል፡፡ ነቢዩ ዳዊት ልበ አምላክ እንደ መሆኑ ትንቢት ተናግሯል፡፡ ሱባዔ ቆጥሯል፡፡ ይኽውም ቀመረ ዳዊት በመባል ይታወቃል፡፡ «እስመ ዐሠርቱ ምእት ዓመት በቅድሜከ፤ ከመ ዕለት እንተ ትማልም ኃለፈት፤ ሺ ዓመት በፊትህ እንዳለፈች እንደ ትላንት ቀን»፡፡ /መዝ.89.4/ የሚለውን መምህራን ሲቆጥሩት 1140 ዓመት ይሆናል፡፡ ይኸውም በጌታ ዘንድ 1140 ዓመት እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ ይህም ለዳዊት ሱባዔ መቁጠሪያ /መሥፈሪያ/ ሆኖ አገልግሏል፤ 1140’7= 7980 ዓመት ይሆናል፡፡ ይህም ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ በ7980 ዓመት ክርስቶስ ዳግም እንደ ሚመጣ የሚያመለክት ነው፡፡

#ሱባዔ ዳንኤል

ነቢዩ ዳንኤል ምድቡ ከዐበይት ነቢያት ነው፡፡ እስራኤል ወደ ባቢሎን ሲማረኩ ተማርኮ ወደ ባቢሎን ወርዷል፡፡ እርሱም ስለ ክርስቶስ መምጣት ትንቢት ተናግሯል፤ ሱባዔም ቆጥሯል፡፡ «ሰብአ ሰንበታተ አድሞሙ ለሕዝብከ፤ ሰባ ሰንበት ወገኖችህን ቅጠራቸው፡፡» ይኸውም ክርስቶስ ከ490 ዓመት በኋላ ሰው መሆኑን የሚያመለክት ትንቢት ነው፡፡ እንዲሁም «እስከ ክርስቶስ ንጉሥ ትትሐነፅ መቅደስ ወእምዝ ትትመዘበር፤ እስከ ንጉሥ ክርስቶስ ድረስ መቅደስ ትታነፃለች በኋላም ትፈርሳለች» ሲል ተናግሯል፡፡
የአቆጣጠር ስልቱም በዓመት ሲሆን ይኸውም ሰባቱን ዓመት አንድ እያሉ መቁጠር ነው፡፡ ይኽውም ሱባዔ ሰንበት ይባላል፡፡ ዳንኤል ሱባዔ ከቆጠረበትና ትንቢት ከተናገረበት ጀምሮ ክርስቶስ እስከ ሚወለድ 490 ይሆናል፡፡ መስፈርቱ /ማባዣው/ ሰባት ስለሆነ 7’70 ስናባዛው 490 እናገኛለን፡፡ ይኸውም ነቢዩ ሱባዔ ከቆጠረና ትንቢት ከተናገረ ከ490 ዓመት በኋላ የክርስቶስን መወለድ ያመለክታል፡፡
በአጠቃላይ ከላይ የተመለከትናቸው ቅዱሳን ነቢያት አካሄዳቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በማድረግ ሱባዔ ገብተው በትሕርምት በመኖራቸው ድንቅ የሆነውን የክርስቶስን ልደትና ዳግም ምጽአት ለመተንበይ ችለዋል፡፡ ሱባዔ መግባት የራቀን ለማቅረብ የረቀቀን ለማጉላት ብቃትን ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚያስገኝ መንፈሳዊ ጥበብ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

**** ይቀጥላል*****
#የሱባዔ ዓይነቶች

#የግል ሱባዔ/ዝግ ሱባዔ/

የግል ሱባዔ አንድ ሰው ብቻውን ሆኖ በቤትና በአመቺ ቦታ የሚይዘው ማንም ሰው ሳያየው በግሉ የጸሎት በኣቱን ዘግቶ በሰቂለ ኅሊና ሆኖ ፈጣሪው ብቻ እንዲያየው እንዲሰማው በኅቡዕ የሚፈጽመው ሱባዔ ነው፡፡ ማቴ.6፡5-13፡፡ በዚህ ዓይነት መልክ አንድ ሰው ሱባዔ ሲገባ ዘጋ ይባላል፡፡ ዝግ ሱባዔ የያዘ ሰው የሚያስፈልገውን ነገር ይዞ ወደ በኣቱ ከተከተተ በኋላ ሱባዔው እስኪፈጸም ድረስ ከሰው አይገናኝም፡፡ መዝ. 101-6-7፡፡

#የማኅበር ሱባዔ
የማኅበር ሱባዔ የሚባለው ካህናት፣ ምእመናን ወንዶችና ሴቶች፣ ሽማግሌዎችና ወጣቶች በአንድ ሆነው በቤተ ክርስቲያንና አመቺ በሆኑ ቦታዎች ሁሉ ተሰብስበው የሚገቡት ሱባዔ ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን የነበሩ ምእመናን ወደ እግዚአብሔር በመሄድ ይጸልዩ ነበር፡፡ 1ኛ ሳሙ.1፡9፤ መዝ.121፡1፤ ሉቃ.18፡10-14፡፡
በሐዲስ ኪዳንም የሐዋርያት ተከታዮች የኾኑ መነኮሳት፣ ካህናትና ምእመናን በገዳማት፣ በአድባራት፣ የሰንበት ት/ቤት ተማሪዎች፣ የጽዋ ማኅበርተኞች ስለ ማኅበራቸው ጥንካሬና ከማኅበርተኞቹ መካከል አንዱ ችግር ሲገጥመው የማኅበር ሱባኤ ይያዛል፡፡.

#የዐዋጅ ሱባዔ

የዐዋጅ ሱባዔ በአገር ላይ ድንገተኛ አደጋ፣ አባር ቸነፈርና ጦርነት ሲነደ እንዲሁም ለማኅበረ ምእመናን አስጊ የሆነ መቅሰፍት ሲከሰት፣ እግዚአብሔር መሽቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ የሚያዝ የሱባዔ ዓይነት ነው፡፡ ለዚህ ዓይነቱ ሱባዔ የነነዌ ሰዎችና በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ እስራኤላውያን ተጠቃሾች ናቸው፡፡ የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ለሦስት ቀን ከመብል ከመጠጥ ተከልክለው በመጾም በመጸለይ እግዚአብሔር መዓቱን በምሕረት ቁጣውን በትዕግሥት እንዲመልስ አድርገዋል፡፡ ሌላው በፋርስ በስደት ይኖር የነበረ አይሁድ በአስቴር ትእዛዝ የያዙት ሱባዔ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚያን ዘመን አርጤክስስ አይሁድ በያሉበት እንዲገደሉ በማዘዙ ከዚህ የጅምላ ጭፍጨፋ ለመዳን አይሁድ በዐዋጅ ሱባዔ ገብተዋል፡፡ አስቴር ገብታ ንጉሡን ስታናግረው ሌላው ሕዝብ በውጭ ዐዋጅ ዐውጀው ሱባዔ ገብተው ፈጣሪያቸውን ተማፅነዋል፡፡ አስቴር 4፡16 - 28፡፡
በአገራችንም ይህን የመሰለ የዐዋጅ ሱባዔ በዐፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ተደርጓል፡፡ ፋሽስት ጣልያን አገራችንን በመውረር ኢትዮጵያን ቅኝ ተገዥ ለማድረግ ድንበሯን አልፎ በመጣበት ወቅት ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ፡- «ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ጉልበት የሌለህ በጸሎትህ ርዳኝ» በማለት የዐዋጅ ሱባዔ መያዛቸው ይነገራል፡፡ በዚህም መሠረት በየገዳማቱ ምሕላ ተይዟል፤ ንጉሡም ታቦተ ጊዮርጊስን ይዘው ዓለምን እጅግ ያስደነቀ ጥቁሮችን ለነጻነታቸው እንዲነሣሱ የሚያስችል ፋና ወጊ የሆነ ድል አግኝተው አገራችንን ለቅኝ ግዛት ያሰበውን ፋሽስት ጣልያንን ማሸነፋቸው በከፍተኛ ስሜት የምናስታውሰው ነው፡፡

#ቅድመ ሱባዔ(ከሱባዔ በፊት) ዝግጅት

ሱባዔ መግባት የሚፈልግ ምእመን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ይኖርበታል፡፡ ያለምንም ዝግጅት ሱባዔ መግባት ለፈተና ያጋልጣል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/፣ ጊዜ ሱባዔ/ በሱባዔ ጊዜና ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/ ዝግጅት አስፈላጊ ነው፡፡
ቅድመ ሱባዔ /ሱባዔ ከመግባት አስቀድሞ/በመጀመሪያ ሱባዔ የምንገባበትን ምክንያት ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሰው ሱባዔ የሚገባበትን ዓላማ ለይቶ ካስቀመጠ ከሱባዔ በኋላ የሚጠበቀውን ነገር ማግኘት አለማግኘቱን ይረዳል፡፡ ይህ ሳይሆን ሱባኤ ቢገባ ከሱባኤው በኋላ የጠየቀው ነገር ስለሌለ ትርጉም ያጣል፡፡ ስለዚህ ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ለምን ሱባኤ ለመግባት እንዳሰብን ለይተን ማወቅ ይኖርብናል፡፡
ሱባዔ ለመግባት የወሰንበትን ምክንያት ከለየን በኋላ ምክንያታችንን ይዘን የንስሐ አባታችንን ማማከር ያስፈልጋል፡፡ ምክንያቱም በምክረ ካህን መጓዝ መጀመር ክርስቲያናዊ ግዴታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአባትነታቸውና በሕይወት ልምዳቸው ምን ማድረግ እንደሚገባን ምክር ለማግኘት እገዛ ያደርግልናል፡፡ ቅድመ ሱባኤ ከንስሐ አባት ጋር መመካከር ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው በሱባዔ ወቅት የተለያዩ ፈተናዎች ቢያጋጥሙት የተሰጠውን ምክር በመጠቀም ፈተናውን ለመቋቋም ይችላል፡፡ እንዲሁም የንስሐ አባቱ በሱባዔ ወቅት በጸሎት እንዲያስቡት መማከር የራሱ የሆነ ድርሻ አለው፡፡
ሱባዔ ለመግባት ስናስብ ለምን ያህል ቀናት መቆየት እንዳለብን መወሰን ያስፈልጋል፡፡ ሱባዔ ከዚህ እስከዚህ እቆያለሁ ብለን ዕቅድ የምንይዝበት ነው፡፡ እንደ አቅማችንና እንደ ችሎታችን ከዚህ ቀን እስከዚህ ብለን በመወሰን ሱባዔ መግባት ተገቢ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ፡- ምንም ዓይነት ልምድ ሳይኖረው አንድ ሰው «በዋሻ እዘጋለሁ» ቢል ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል፡፡ ምክንያቱም በሱባዔ ወቅት ፈተና ስለሚበዛ የሚመጣበትን ፈተና መቋቋም ባለመቻል ሱባዔው ሊቋረጥ ይችላል፡፡ ስለዚህ ቅድመ ሱባዔ ዐቅምንና ችሎታን አገናዝቦ መወሰን ተገቢ ነው፡፡
ሌላው ቅድመ ሱባዔ ለሱባዔ ተስማሚ የሆነ ወቅትና ቦታ መምረጥ ተገቢ ነው፡፡ በቤተ ክርስቲያን በአብዛኛው ሱባዔ የሚገባው አጽዋማትን ተከትሎ ነው፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንገባበት ወቅት የጾም ወቅት መሆን አለመሆኑን መለየት ያስፈልጋል፡፡ በአጽዋማት ወቅት የሚያዝ ሱባዔ ለተሐራሚ ጠቀሜታው እጅግ የጐላ ነው፡፡ ምክንያቱም በአጽዋማት ወቅት ብዙ አባቶች ሱባዔ ስለሚይዙ ከአባቶች ጸሎት ጋር ልመናችንና ጸሎታችን ሊያርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወቅትን ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
እዚህ ላይ «ከወርኃ አጽዋማት ውጭ ሱባዔ አይያዝም» የሚል አቋም ለመያዝ አይደለም፡፡ አንድ ሰው ፈተና ከአጋጠመው በማንኛውም ጊዜ ሱባዔ ሊገባ እንደሚችል እዚህ ላይ ለመጠቆም እንወዳለን፡፡ ከዚህም ባሻገር ሱባዔ የምንይዝበትን ቦታ መምረጥ አለብን፡፡ ለሱባዔ የምንመርጣቸው ቦታዎች ለፈተና የሚያጋልጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ ይኸውም ሱባዔ ከተገባ በኋላ ኅሊናችን እንዳይበተን እገዛ ያደርግ ልናል፡፡ ጫጫታና ግርግር የሚበዛበት ቦታ በሰቂለ ኅሊና ለመጸለይ አያመችም፡፡ ስለዚህ ሱባዔ የምንይዝባቸው ቦታዎች ከከተማ ራቅ ያሉ ገዳማትና አድባራት ተመራጭ ናቸው፡፡

#ጊዜ ሱባዔ /በሱባዔ ጊዜ/

በጸሎት ሰዓት ዓምድና ግድግዳ ሳይደገፉ መቋሚያ ሳይዙ በሁለት እግር ቀጥ ብሎ በመቆም መጸለይ ይኖርብናል፡፡ እንዲሁም ፊትን ወደ ምሥራቅ መልሶ መቆም ወዲያና ወዲህ ወደ ግራ ወደ ቀኝ አለመዟዟር በሰፊሐ እድ በሰቂለ ኅሊና ኾኖ መጸለይ ይገባል፡፡ መዝ.5፡3፤ መዝ.133፡2፤ ዮሐ.11፡41፡፡
በሱባዔ ወቅት በቅደም ተከተል መጸለይ አለብን፡፡ መጀመሪያ «በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አአትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀልኸ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አንዱ አምላክ መላ ሰውነቴን በትእምርተ መስቀል አማትባለሁ» እያለ ሰጊድን ከሚያነሣው ሲደርስ መስገድ መስቀልን ከሚያነሣ ላይ ስንደርስ ማማተብ ይገባል፡፡
በማስከተል አቡነ ዘበሰማያት፣ መዝሙረ ዳዊት፣ ውዳሴ ማርያምና ሌሎች በመዝገበ ጸሎት የተካተቱትን መጸለይ፤ ቀጥሎ አቡነ ዘበሰማያት፣ ጸሎተ እግዝእትነ ማርያምን፣ ጸሎተ ሃይማኖትን ከጸለይን በኋላ አቡነ ዘበሰማያት መድገም፤ ከዚያ 41 ጊዜ ኪርያላይሶን ይባላል፡፡ ሌላው በሱባዔ ጊዜ ከተሐራሚ የሚጠበቀው ነገር ኃጢአቱን እያሰበ ማዘን ማልቀስ ነው፡፡ ሲያለቅስም ለእያንዳንዱ በደል እንባ ማፍሰስ ያስፈልጋል፡፡
በመጨረሻም ሱባዔ የገባ ሰው ሱባዔውን ሳይጨርስ ወይም ሱባዔውን አቋርጦ ከማ
ንም ሰው ጋር ፈጽሞ መገናኘት የለበትም፡፡

#ድኅረ ሱባዔ /ከሱባዔ በኋላ/

ለቀረበ ተማኅፅኖ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን ነገር መጠበቅ ይኖርብናል፡፡ እግዚአብሔር ላቀረብንለት ምልጃና ጸሎት እንደ ልባችን መሻት እንደ እርሱ ቸርነት እርሱ በወደደ ጊዜ ያደርግልናል፡፡ ሱባዔ የገባ ሰው ሁሉ ራእይ ላያይ ይችላል፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መልስ አሰጣጥ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከሱባዔ በኋላ መጀመሪያ የምናገኘው የኅሊና ሰላምን ነው፡፡ ይህ ትልቅ የአምላክ ስጦታ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ሱባዔ ገብተን ያሰብነውን ካላገኘን ዳግመኛ ተዘጋጅተን እስከ መጨረሻው ሰዓት መማፀን መጽናት ይኖርብናል፡፡
ምንጭ:-Info:- Mk website
#ዓውደ ምህረት የኛ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
" #ቀርታ_ያስቀረችን_ምርጥ_ዘር "

ጊዜው ክረምት ወቅቱም የዘር የመከር ወቅት በመሆኑ ዘርና ፍሬ ዝናብና ጠል ገበሬና በሬ ያለ መነጣጠል ይነሱበታል ። የክረምት ወቅት ምሳሌያዊ ትርጉም ዘርፈ ብዙ ነው ። አንዱ ና ዋናው ግን የ5500 ዘመን ወይም የብሉይ ኪዳን ዘመን ፣ የመከራ ፣ የስቃይ ፣ የጨለማ ጊዜ ምሳሌ መሆኑ ነው :: ይኸውም ክረምት የ5ሺህ 500 ዘመን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው መባሉ በክረምት ጭጋግ ፣ ጉም ፣ደመና ይበረታሉ ነጎድጓዳት ይሰማሉ መባርቅት በርቀው ያስደነግጣሉ ይልቁኑ ደግሞ ውኃ ይሰለጥናል :: የክረምት ወቅት ሰቆቃ ይበዛዋል ይልቁኑ በስደት በደጅ ላሉ ሰውች ይብስባቸዋል “ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ፤”
የሚለው የጌታችን ምክርም የዚህን የክረምት ወቅት ጠንካራነት ያሳያል። ማቴ24፥20

የ5500ዘመንም ዘመነ ፍዳ ዘመነ መከራ ዘመነ ጨለማ ነውና በእግረ አጋንንት ተገዝተን በሲዖል እሳት ውስጥ ተግዘን ኖረናል ። በክረምት ውኃ እንዲሰለጥን በብሉይ ኪዳንም ውኃ ሰልጥኖ ፍጥረትን አጥፍቷል ገኃነመ እሳት በርትቷል በክረምት ምድር በውኃ እረክታ ትረሰርሳለች መሬት ትጨቀያለች በብሉይም ሰዎች በኃጢያት ዝናብ በስብሰው በሰዶም ግብር ጨቅይተው ነበር በዚህ ሰበብም ፈጣሪና ፍጡር ሰማይና ምድር ሰውና መላእክት ነፍስና ሥጋ ተጣልተው ከርመዋል በመሆኑም ዘመነ ብሉይ (5500 ዘመን) ከአሰቃቂው የክረምት ወቅት ጋር በእጅጉ ይመሳሰላል ። በመካከላቸውም የጠብ ግድግዳ ተገንብቶ ቆይቷል ቤተ ክርስቲያን በዚህ ወቅት ዘሪ ሊዘራ ወጣ እያለች የመንገድ ዳር፣ የጭንጫ ፣የሾህ ልቡና ያላቸውን ምዕመኖቿን ልብ በስብከተ መልካም መሬት አድርጋ በወንጌሏ ታቀናዋለች ቃል ዘርታ ሕይወት ታጭዳለች ።

ዛሬ ዛሬ ዓለማችን ነጭ ጥቁር ሀገራችን ደግሞ ኦሮሞ ትግሬ አማራ ጉራጌ በመባባል ተከፋፈለዋል። ሁሉም ዘሩ ምርጥ ዘር እንደሆነ ያስባል ሌላው ዘር ሁሉ እንክርዳድ የሚመስለው ነቀዝ ብዙ ነው ። ከሰዶምና ከጎሞራ ቅጣት የተረፍንባት ምርጥ ዘራችን ድንግል ማርያም ነች። ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችም መጀመራያ ብሎ እንደጠራት ትምክተ ዘመድነ የምትባል እመቤታችን ነች ። ከእርሷ በቀር ምርጥ ዘር የሚባል የለንም ።
ይህች ንጽሕት ዘር ወርቅ ነች ወርቅ ከጭቃ ይገኛል ግን ጭቃ አይደለም እመቤታችንም በኃጢያት ጭቃ ከወደቁት ከአዳም እና ከሔዋን ዘሮች የተገች ዳግማዊት ሔዋን ብትሆንም የበደል ጥንት አልነካታም የመተላለፍ እድፍ አላጎደፋትም ስለዚህ በአዳም ገላ ውስጥ ታበራ የነበረች ነጭ እንቁ ነች።

ነቢየ ልዑል ቅዱስ ኢሳይያስ “የሠራዊት ጌታ #እግዚአብሔር_ዘርን_ባያስቀርልን_ኖሮ፥ እንደ ሰዶም በሆንን እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።” ብሎ የተናገረላት ከኃጢያት መተዳደፍ በመንጻት ከከፋት ሥራ ሁሉ ቀርታ ከጥፈት ያስቀረችን ምርጥ ዘራችን እመቤታችን ነች። ኢሳ 1፥9 ይህችሁም ንጽሕይት ዘር በወርኃ ክረምቱ ማዕከላዊ ጊዜ በሆነው በነሐሴ 7 (ሰባት)በዛሬዋ ቀን ከሐናና ከኢያቄም ተጸንሳልናለች ይህ ቀን የእመቤታችን ብቻ ሳይሆን እያገዳደለን ካለው የዘረኝነት ግዳይ ዓለማችንንና የሀገራችንን ትንሳኤ የምታደርግበት የድኅነታችን ጽንስ መጀመሪያም ቀን ነው።

በክረምት ወቅት የሰማይ መስኮቶች ተከፍተው ዝናብ ለዘር ጠል ለመከር ይሰጣሉ ታዲያ ይህ ጊዜ ለትጉህ ገበሬ ምቹ ነው በሬውን ይጠምዳል መሬቱን ያርሳል ዘሩን ይዘራል ዝናቡን በጉድጓድ ያጠራቅማል መባርቅቱን ፣ ነፋሳቱን ይታገሳል። በመጨረሻውም የድካሙን ፍሬ አዝመራውን ያጭዳል በመከራ እንዳልዘራ በደስታ ይሰበስባል " በልቅሶ የሚዘሩ በደስታ ይለቅማሉ ። በሄዱ ጊዜ፥ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ፤ በተመለሱ ጊዜ ግን ነዶአቸውን ተሸክመው ደስ እያላቸው ይመጣሉ ። መዝ (125) 126 ÷5 ሰነፍ ገበሬ በአንጻሩ ብርዱን ቸነፈሩን ተሰቆ ቤቱ ይተኛል እገሌ ከኔ ወገን ነው ደግ ነው እገሊት ከወንዝ ማዶ ናት አትመስለንም ባለፈችበት እንዳታልፉ በዞረችበት አትዙሩ የሚል ነው የአጥንት እንጂ የእህል ዘር የማያውቅ :: ዘረኝነት ኃጢያት ነው ኃጢያት ደግሞ ማጣት ማለት ነው ባለ ብዙ ዘሮች ነን የሚሉ ዘረኞች ሃይማኖቱን፣ ምግባሩን ፣ ፖለቲካውን ፣ ሥልጣኑን ፣ ዕውቀቱን፣ ውበቱን ፣ ሙቀቱን ፣ድምቀቱን፣ ዝናውን ፣ተሰሚነቱን የያዙ ይመስላቸው ይሆናል ነገር ግን አንዱም እንኳ የላቸውም አጥተውታል። ሰው ኃጢያትን (ዘረኝነት) ዘርቶ እንዴት አንድነትን ሊያጭድ ይችላል ??? በእኩልነት ሰበብ በኩይ ከከፋፈሉን በኃላ በእንድነት ደግሞ እንምራቹ አሉን በአንድ ገመድ ሁሉንም ከብቶች አስሬ ልምራቸው የሚል እረኛ የለም ቢኖር ግን ይህ ምንደኛ እንጂ እረኛ አይደለም ምክንያቱም ከብቶቹን በአንድ ታስረው ወደ ሚፈልጉት የልማት ጉዳና የሥልጣኔ ማማ መድረስ አይቻላቸውምና። አንዱ ወድቆ ሊላውን የሚጠልፍበት የውድቀት ትርምስ ነው የሚሆንባቸው ። ከዛም አልፎ ከለመለመው መስክ ሳይሰማሩ በረፍትም ውኃ ዘንድ ሳይቀርቡ ከናፈቁት በረታቸውም ሳይገቡ የነጣቂ ተኩላ ሲሳይ የጅብ እራት ሆነው ይቀራሉ ። “ኃጢአትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፥ ”ምሳሌ 22፥8 " ማሰር መፍትኤ የሚሆነው ጠባቂ ከሌለ ብቻ ነው! " ። እረኛ ካለ ገመድ ለምኔ ?


........ ይቆየን.............

@YEAWEDIMERITE
አዘጋጅ :- ተርቢኖስ ሰብስቤ ኃ/ማርያም
ነሐሴ 7 ቀን 2012ዓ,ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
+++ ታማልደናለች +++

ሐዋርያው ስለ ቅዱሳን “ራሳቸውም ስለ እናንተ ሲያማልዱ፥ በእናንተ ላይ ከሚሆነው ከሚበልጠው ከእግዚአብሔር ጸጋ የተነሣ ይናፍቁአችኋል።” (2ኛ ቆሮ 9፥14) በማለት የተናገረውን ያነበበ የአምላክ እናት ምልጃን እንዴት ያስተባብላል?
+++++
እመቤታችን የነገሥታቱን ንጉሥ የጌቶቹን ጌታ የኃያላኑን ኃያል የጸጋ አማልክት የተባሉ የቅዱሳኑን አምላክ እርሱን የወለደች ውሆችን በእፍኙ የሠፈረ ሰማያትን በስንዝሩ የለካ የእርሱ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ናትና እንወዳታለን እናከብራታለን ።(ኢሳ 40:12 ራእይ 19:16 1ጢሞ 6:15) ጠላት የክርስቶስ እናቱ የድንግል ማርያም ወዳጆችን በባሕር አሸዋ በተመሰለ በዚህ ዓለም እንደ አሸን ፈልተው በተበተኑ እኩያን ሰዎች ልቡና አድሮ እንደሚዋጋቸው ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ መስክሯል። (ራእይ 12:17) ጥላቻ ደረጃ አለው ዲያብሎስ ሁሉንም የሰው ዘር ይጠላል ከፍ ሲልም ቅዱሳንን አምርሮ ይጠላል ለድንግል ማርያም ያለው ጥላቻ ግን ወሰን ገደብና ጥግ የለውም ። የጥላቻው መገለጫ ከሆኑ ነገሮች መካከል አንዱ ደግሞ ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጣትን ምሉዕ ጸጋ ማስተባበል ማጠራጠር ማስካድና እርሷንም መሣርያ ባደረጋቸው ሰዎች አንደበት ማሰደብ ነው:: የምልጃዋን ጣዕም የቀመሰ ደግሞ ስለ አማላጅነቷ ከሕይወቱ በላይ ምስክር የለውምና እንዲህ ይላል :-
++ ታማልጅን ዘንድ ላንቺ ይገባል ++
የእመቤታችንን አማላጅነት መቃወም እግዚአብሔርን መቃወም መጻሕፍትንም ማስተባበል ነው:: ለምን ? ቢሉ
፩. በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለሰዎች መማለድ መለመን ታላቅ ጸጋ ነው :: የእግዚአብሔር ጸጋ ያልተሰጠው ያልበዛለት በእርሱ ፊት ቆሞ እርሱን ሊለምን አይችልምና :: አባታችን አብርሃም በእግዚአብሔር ፊት ጸጋን ቢያገኝ በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለሰዶምና ለገሞራ እንደማለደ መጽሐፍ ይመሰክራል ። (ዘፍ 18:18-29) ሊቀ ነቢያት ሙሴም በእግዚአብሔር ፊት ቆሞ ለምኖላቸዋል ። (ዘጸ 32:1-32) ልበ አምላክ ክቡር ዳዊት ይህን ታሪክ አውስቶ ሲናገር "እንዳያጠፋቸው ቁጣውን ይመልስ ዘንድ የተመረጠው ሙሴ በመቅሠፍት ጊዜ ባይቆም (ባይለምን) ያጠፋቸው ዘንድ ተናገረ።" (መዝ 105(106)÷23) ማለቱ ሐሳባችንን ያጠነክርልናል:: የአምላክ እናት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ምሉዕ ጸጋን አግኝታለች:: ከሰማያውያኑ ቅዱስ ገብርኤል ከምድራውያኑ ቅድስት ኤልሳቤት "ማርያም ሆይ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ ።" (ሉቃ 1÷30:43) ብለው እንደመሠከሩ:: ድንግል ማርያም ያልተሰጣት የቀረባት ምን ጸጋ አለ? እርስዋ አታማልድም የሚሉ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በመቃወም ክብር ይግባትና "የሚጎድላት ጸጋ አለ" እያሉ እንደሆነ እንገንዘብ:: ይህ ደግሞ ራሳቸው ምን ያህል ከጸጋው እንደተራቆቱ ያሳያል:: ከቅዱሳን ሁሉ ክብር የማርያም ክብር ይበልጣልና ::
፪. በሐዲስ ኪዳን ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማማለድን ጸጋ ለቅዱሳን እንደሰጠ ሐዋርያው ሲመሠክር "ነገር ግን የሆነው ሁሉ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን ከእግዚአብሔር ነው:: እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ (ህልው ሆኖ) ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውንም አይቆጥርባቸውም ነበር :: በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ:: እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልእክተኞች ነን ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን ።" 2ቆሮ 5÷17-20 ብሏል:: ለሐዋርያት የተሰጠ ጸጋ በሙሉ ለእመቤታችን ተሰጥቷታል ለእርሷ የተሰጠ ጸጋ ግን ለሐዋርያት አልተሰጠም:: ከፍጥረታት ወገን " ጸጋን የተሞላሽ" የተባለ ከእርሷ ሌላ ማን አለ? ታዲያ ማማለድ ለሐዋርያት የተሰጠ ጸጋ ተልእኮም ከሆነ ድንግል ማርያም ደግሞ በጸጋ የተሞላች ከሆነች "አታማልድም" የሚሉ አያፍሩምን? የቅዱሳን ሐዋርያትን የማማለድ ጸጋ መጽሐፍ እየነገረን የእርስዋን ማማለድ ለመቀበል መቸገር ምን ይሉታል?
፫ . በሐዲስ ኪዳን ስለ ክርስቶስ በዓላውያን ነገሥታት የታረዱ በሰማይ በክብር የተገለጡ ሰማዕታት በክፉዎች ላይ እንደለመኑባቸው ቅዱስ ዮሐንስ መስክሯል ። (ራእይ 6÷9)ስለ ልጇ "በአንቺም ደግሞ በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል ።" (ሉቃ2÷35) የተባለች የሰማዕታት እናት ድንግል ማርያም ሰይጣን ክፉ ዓለም የሥጋ ፈቃድ ለሚፈትናቸው ክርስቲያኖች አትማልድምን ?
፬. ደፋሮች በድፍረትና በትእቢት በመናቅም እንደ ተራ ታሪክ ቢመለከቱትም ቅዱስ ዮሐንስ "የምልክቶች መጀመሪያ ጌታችንም ክብሩን የገለጠበት" ብሎ በመሠከረበት በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ልጅዋን ወዳጅዋን ኢየሱስ ክርስቶስን ለምና ተራውን ውሃ ወደሚጣፍጥ ወይን እንዲለወጥ አድርጋለች ። (ዮሐ ፪÷፩-፲፪)ክብርና ጸጋዋ ያልተገለጠላቸው ሰዎች የእርሷን የማማለድ ጸጋ እያስተባበሉ "እንጸልይላችሁ" "እናድናችሁ" "እንፈውሳችሁ" ሲሉ ማየትና መስማት " ከፍ ከፍ ያሉ ዓይኖች ያሉት ሽፋሽፍቶቹም ወደ ላይ የሚያዩ ትውልድ አለ ።" (ምሳ 30÷13) ተብሎ የተነገረው ትንቢታዊ ኃይለ ቃለ እንዲፈጸምባቸው እየተጉ መሆኑን ያሳየናል:: ዛሬም በኑሯችን በሥራችን በትዳራችን በትምህርታችን ጣዕም ያጣን ሁሉ በአማላጅነቷ በጥዑም ስሟና ከልጇ በተሰጣት ጸጋ አምነን እንቅረብ !! እርሷ ሰማይና ምድርን የፈጠረ የክርስቶስ እናቱ ናትና::

አዘጋጅ መምህር #ቢትወደድ_ወርቁ

ነሐሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
ለዳዊት ሦስት ልጆች ነበሩት አቤሴሎም፣አምኖን እና ትዕማር ። የዳዊትም ልጅ አምኖን ትዕማርን ወደዳት። አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ ታመመ፤ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር ።ለአምኖንም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ የሚባል ወዳጅ ነበረው፤ ኢዮናዳብም እጅግ ብልህ ሰው ነበረ።እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም፦ የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።

ኢዮናዳብም፦ ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ፤ አባትህም ሊያይህ በመጣ ጊዜ፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታዘጋጅልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በል አለው። እንዲሁም አምኖን፦ ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ፤ ንጉሡም ሊያየው በመጣ ጊዜ አምኖን ንጉሡን፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታደርግልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ አለው። ዳዊትም፦ መብልን ታዘጋጂለት ዘንድ ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት ሂጂ ብሎ መልእክተኞችን ወደ ትዕማር ቤት ላከ።

ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፥ ተኝቶም ነበር፤ ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፥ እያየም እንጎቻ አደረገች፥ ጋገረችም። ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም፦ ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ። አምኖንም ትዕማርን፦ ከእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው አላት፤ ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው። መብሉንም ባቀረበች ጊዜ ያዛትና፦ እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔም ጋር ተኚ አላት። እርስዋ መልሳ፦ ወንድሜ ሆይ፥ አይሆንም፤ እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ አይገባምና አታሳፍረኝ፤ ይህንም ነውረኛ ሥራ አታድርግ።እኔም ነውሬን ወዴት ልሸከም? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከምናምንቴዎች እንደ አንዱ ትሆናለህ፤ እንግዲህስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም አይነሣህም አለችው። ቃልዋን ግን አልሰማም፤ ከእርስዋም ይልቅ ብርቱ ነበረና በግድ አስነወራት፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ ። ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ ጠላት፤ አስቀድሞም ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም፦ ተነሥተሽ ሂጂ አላት።

እርስዋም፦ አይሆንም ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ አኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ አለችው እርሱ ግን አልሰማትም። የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ፦ ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን ዝጋባት አለው። ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፥ እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱ ነበርና፤ አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን ዘጋባት። ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች ሄደች።

#ትዕማርን_ቢሆኑ ምን ያደርጋሉ?
🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀🤦‍♀
👇👇👇👇👇👇👇👇
ሀሳቦን ያጋሯት
@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE


#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ትዕግስ ብሩ:-

ena behon bet mengest indemhonu metin keweti aderga echoe neber
Geche danaile

በያዝኩት ምግብ ማቅረቢያ አናቱን እለው ነበር
Forwarded from ሀኒቾ
ትእማርን ብሆን እሷ እንዳረገችዉ የልቤን ለሚያቅ ፈጣሪያ አልቅሼ እነግረዋለዉ እኔ ምንም ባደርገዉ የጠፋዉ ነገሬ እንደማይመለስ አዉቃለዉ ፈጣሪ ደሞ ለሱ አባት ለኔ የእንጀራ አባት ስላልሆነ በቀሌን እንደሚበቀልልኝ አምነዋለዉና ዋጋዉ እንዲሰጠዉ ዘወትር በፊቱ አለቅሳለዉ ::
በእውነት ቃለ ህይወት ያሰማልን መምህራችን እግዚአብሔር እድሜ ጸጋ ያድልልን

እኔ ብሆን ግን ከባድ ነው ምክንያቱም ወንድሜን ይህ ያደረጋል ብይ አላሰብም ለመፈረድ ይከብዳል በእውነት


እንደ አሁን ልጆች ብንሆን ግን ለምን ሰዎች ሁሉ እንዲወጡ ያደረገው የሚለው የሚጠይቅ ትውልድ ዘመን ነን ትዕማር ያልጠየቀችው ምክንያት በየዋህነት ወይም ወንድምዋ ሰለ ሆነ ብይ እወሰዳለሁ ግን አሁን ዘመኑ የከፈ ሰለ ሆነ እኛ ቢሆን አሁን ለምን ብለን እንጠይቃለን

ሁለተኛ ትዕማር ለምን ድምጸዋ ክፍ አደረጋ ብትጮኸ ቤተሰብ ይለም ወይ የሚለው ለእኔ ጥያቄ ነው ምክንያቱም ከእርሱ ጋራ እንተኛ ሲነግራት የእራሰዋ ትግል እና መጮኸ ነበረባት የሚል አለኝ

ይህ ሰል ግን ነገሩ ለመፈረድ ይህ ነው ለማለት ከባድ ነው ከማይጠብቁት ሰው ሲሆን

እግዚአብሔር ልብ ይሰጠን ከማለት ወጭ ከባድ ነው

ትምህርት አለ ቃሉ ላይ
Audio
#መልካም የደብረ ታቦር በዓል

የማህበረ #ፊሊጶስ መዝሙር
#ቡሄ በሉ ... ሆ

#ዓውደ ምህረት የእናንተ
👇👇👇👇👇👇👇
@AwediMeherit
@AwediMeherit
Audio
#መንፈሳዊ ውይይት

#በወንድማችን ብሩክ መልሳቸው እና
#በወንድማችን ተርቢኖስ ሰብስቤ
ይዘት :- #ደብረ ታቦር
👉የት ይገኛል?
👉በእርሱ ምን ምን ነገር ተገለጠ?
👉ለነማ ተገለጠ?
👉የቡሄ ታሪካዊ ድኃራ ምንድነው?
👉እንዴት እናክብረው?
@AwediMeherit
@AwediMeherit
ነሐሴ 13/2012