ብረው አይደለም።በተ
ለይ ይህን ከነገረ-ድኅነት (salvation) ጋር አያይዘው በለሰለሰ መልኩ ያስተማሩት የምዕራቡ ቤተ-ክርስቲያን አባት የሚባለው ቅዱስ አውግስጢኖስ (St. Augustine) ነው። እንዲህ ይላል - “ጸጋ የእግዚአብሔር ስጦታ እንጂ ሰዎች እግዚአብሔርን ስለመምረጣቸው የተሰጣቸው ሽልማት አይደለም። ጸጋ ክፍያ ከሆነ ሰዎች መዳናቸውን በጥሩ ሥራቸው ይገዙታል ማለት ነው።” ብሎ ይናገራል። ለዚህ ከሚጠቅሳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች መካከል የቅዱስ ጳውሎስ ዋነኛው ነው። (“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአል።” ሮሜ- 8፥29)። በእርሱ አስተምሮ “ሰው በራሱ ድኅነቱን ሊያገኝ ወይም በሥራው ሊድን አይችልም። ከኃጢአት የምንወጣበትን ጸጋ እግዚአብሔር ለመረጣቸው (elected) ለይቶ የሚያድል እንጂ ሁሉም የዚህ ጸጋ ተጠቃሚ አይደሉም።” “የእግዚአብሔር የማዳን ጸጋ ለዓለም ሁሉ (universally) የተሰጠ ሳይሆን ለአንዳንዶች ብቻ አስቀድሞ በተወሰነው መሠረት የተለገሰ ነው” ይላል። ቅዱስ አውግስጢኖስ ጨምሮ እንዲህ ይላል -“ይሄ ማለት እግዚአብሔር ለርግማን የሆኑትን አስቀድሞ ወስኗል ማለት ሳይሆን ከሚጠፉት መካከል የሚድኑትን ለይቶ መርጧል ማለት ነው።” (This did not mean that some were predestined to damnation but it meant that God had selected some from the mass of fallen humanity.)
ከዚህ በተጻራሪ የምስራቅ ኦሬንታል አብያተ ክርስቲያናት (የኢትዮጵያ ቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን ጨምሮ) በቅዱስ አውግስጢኖስ የቅድመ ውሳኔ ትምህርት (predestination doctrine) ፈጽመው አይስማሙም።
ቅዱስ አውግስጢኖስን ሲነቅፉት አንዳንዶችን ለማዳን መወሰን ማለት ሌሎችን ላለማዳን መወሰን ማለት ነው።(The decision to redeem some was also a decision not to redeem others.) ይሄ ደግሞ ከመጽሐፍ ቅዱስ የድኅነት አስተምሮ ጋር ይጋጫል ብለው ያስተምራሉ።
“እኔ ሕያው ነኝና ኃጢአተኛው ከመንገዱ ተመልሶ በሕይወት ይኖር ዘንድ እንጂ ኃጢአተኛው ይሞት ዘንድ አልፈቅድም ፥ይላል ጌታ እግዚአብሔር።” ሕዝ - 33፥11
“ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።” 1ጢሞ- 2፥4
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ዮሐ- 3፥16
“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ማር- 16፥15
እነዚህ ሁሉ እና ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ቅዱስ አውግስጢኖስ መሠረት ካደረገባቸው የቅዱስ ጳውሎስ ሀሳቦች ጋር አብረው መገናዘብ እንጂ ያለባቸው እነዛን ብቻ ተይዞ የሰው ልጅ ፍጻሜው (destiny) በእግዚአብሔር አስቀድሞ ተወስኗል፣ ነጻ ፍቃድ የሚባል ነገር የለንም፤ ስለዚህ የምንኖረው እሱ ያለልንን ነው ፥ ወደሚል ጽንፍ ወደተገፋ እምነት ሊወስደን አይገባም። ምክንያቱም በዚሁ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አምላካችን እግዚአብሔር የሰው ልጅ ነጻ ፍቃድ እንዳለው እና የእርሱ ሁሉን አዋቂነት በእኛ የነጻ ፍቃድ ውሳኔ ውስጥ ጣልቃ እንደማይገባ ይነግረናል።
“በፊታችሁ ሕይወትንና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በሕይወት ትኖሩ ዘንድ ሕይወትን ምረጥ ።” ዘዳ - 30፥19
“እሺ ብትሉ ለእኔም ብትታዘዙ የምድርን በረከት ትበላላችሁ፤ እንቢ ብትሉ ግን ብታምፁም ፥ ሰይፍ ይበላችኋል፤ የእግዚአብሔር አፍ ይህን ተናግሮአልና።” ኢሳ- 1፥19
“እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።” ማቴ9 16፥24
“ወደ ሕይወት መግባት ብትወድ ግን ትዕዛዛትን ጠብቅ።” ማቴ- 19፥17
“እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምጼን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ፥ ወደ እርሱ እግባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።” ራዕ- 3፥20
“ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ ፥ ነቢያትን የምትገድሉ ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግሩ ፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም ።” ማቴ- 23፥37
“መንግስተ ሰማያት ለልጁ ሰርግ ያደረገ ንጉሥን ትመስላለች። የታደሙትንም ወደ ሰርጉ ይጠሩ ዘንድ ባሮቹን ላከ ሊመጡም አልወደዱም ።”
“የእርሱ ወደ ሆነው መጣ ፥ የገዛ ወገኖቹም
አልተቀበሉትም።” ዮሐ - 1፥11
ከላይ የተዘረዘሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የሚነግሩን የሰው ልጅ የመምረጥ ወይም ነጻ ፍቃድ እንዳለው ነው። ሰው ማድረግ ወይም መሥራት የሚፈልገውን ነገር የሚመርጥ ፥ እግዚአብሔርን ወዶ እና ፈቅዶ መከተል ያለበት ክቡር ፍጥረት እንጂ እግዚአብሔር የወሰነለትን የሕይወት ጉዞ ያለ እርሱ ፍቃድ የሚጓዝ ሮቦት አይደለም። ለዚህም ነው ክፉ እና ደጉን፤ ዘላቂ የሆነውን ከጊዜያዊው የሚለይበትን ትልቅ ሀብት እሱም “አዕምሮ” የሰጠው። ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን ሳይቀር መረዳት እና መመርመር የሚችል ፤ ማንኛውንም ነገር የሚጠይቅ፣ ረቂቁን ነገር ሳይቀር ወደ እራሱ አቅርቦ የሚያስብ አዕምሮ የተሰጠው ፥ ምድር ላይ ካሉ ፍጥረት የሰው ልጅ ብቻ ነው። ሰው በተወሰነለት ጎዳና ብቻ ነው የሚሄደው ማለት ይህን ትልቁን የሰው ሀብት የሚንድ ነው። ሰው ከእንስሳት የተለየበት “የሀልዮት” ባህሪው ያለ ነጻ ፍቃድ የሚሰራ አይደለም።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
#ዓውደ-ምህረት የእናንተ
🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤🎤
📢 @AwediMeherit 📢

ሰንበት እኛም የታመሙትን መጎብኘት እንዳለብን የምንማርበት ነው፡፡
ይህ ሳምንት “መጻጉዕ” ጌታችን ድውያንን ስለመፈወሱ የሚነገርበትና እኛም ባለን አቅም በነፍስ በሥጋ የተቸገሩትን ሁሉ መርዳትና ማገዝ እንዳለብን የምንማርበት ሳምንት ነው፡፡ ሕሙማንን መጠየቅ፣ የታሰሩትን መጎብኘትና ማስፈታት፣ የተራቡትን ማብላት፣ የተጠሙትን ማጠጣት፣ የታረዙትን ማልበስ ያዘኑትን ማረጋጋት ከጌታችን የተማርናቸው ክርስቲያናዊ ምግባራት ናቸው፡፡ ይህንን በማስተዋል የሚያስፈልገንን ሁሉ የሰጠንንና ከክፉ ነገር የጠበቀንን አምላክ ውለታውን እያሰብን ልናመሰግነው ይገባል፡፡ መጻጒዕ መጀመሪያ የነበረበት ደዌ ሥጋ ነበር፣ ይህንንም ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አራቀለት/አዳነው፡፡ ይሁንና በጌታችን ስቅለት ከአይሁድ ጋር በመተባበሩ፣ ያዳነውን ባለማመኑ ግን ደዌ ነፍስ አገኘው፡፡ እኛም እንደ መጻጒዕ ደዌ ነፍስ እንዳያገኘን ያዳነንን አምላካችንን ልናውቀው፣ ልናምነው፣ በህጉና በትዕዛዙም ልንሄድ ያስፈልጋል፡፡ ያን ጊዜ ከደዌ ነፍስ እንድናለን፡፡ ያንን ተስፋ ያልነበረውን በሽተኛ ከደዌ ሥጋው ፈውሶ ሕይወትን የሰጠው አምላክ፣ እኛንም በውስጥ በአፍአ ካለብን ደዌ ሥጋና ደዌ ነፍስ እንዲፈውሰን፤ ቁስለ ኃጢአታችንን እንዲያደርቅልን፣ በሕይወትና በጤና እንዲጠብቀን የእርሱ የጌታችን ቅዱስ ፈቃድ ይሁንል አሜን🙏
ምንጭ :-አስተምህሮ
#ለከበረው ሀሳብዎ
👉@YEAWEDIMERITE
@YEAWEDIMERITE
ዓውደ ምህረት የእናንተ