ዐውደ ምሕረት
3.67K subscribers
932 photos
24 videos
271 files
195 links
"ቤተ ክርስቲያን ባሕረ ጥበባት
አትመረመርም እጅግ ጥልቅ ናት"
Download Telegram
+++ ታቦትና ጣዖት አንድ ሆነው አያውቁም።+++

ይልቁንም ታቦተ ጽዮን ዳጎንን (ጣዖተ ፍልስጥኤምን) ስትገለብጥና ስትቆራርጥ አንብበናል። (1ሳሙ 5:3)

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን "ኦሪታዊት ናት" ስትል ትቆይና መልሰህ ደግሞ "ታቦቱ ለምን የኦሪቱን አልመሰለም?" ብለህ ትሟገታለህ። የአዲስ ኪዳኑ መሥዋዕት በቤተክርስቲያን የምንቀበለው (የምንበላው የምንጠጣው) ክርስቶስ ከኦሪቱ መሥዋዕት ፍፁም የተለየ እንደሆነ እንዲሁ የአዲስ ኪዳኑም መሠዊያ ከኦሪቱ ልዩ ነው። "መሠዊያ አለን።" እንዲል ሐዋርያው። (ዕብ 13:10) ያ መሠዊያ ምንድነው? ያልክ እንደሆነ የሐዲስ ኪዳን መሥዋዕት የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ምእመናን ይበሉትና ይጠጡት ዘንድ የሚቀርብበት የአዲስ ኪዳን ታቦት ነው።

"ታቦት ለምን በዛ?" ይልሃል ደግሞ በዚያ በኩል፤ መልሳችን አጭር ነው። በብሉይ ኪዳን ቤተ መቅደሱ አንድ ብቻ እርሱም የሰሎሞን ቤተ መቅደስ አልነበረምን? በሐዲስ ኪዳን ግን ክርስትናው በዓለም ናኝቷልና ክርስቲያኖች በበቀሉበት ሥፍራ ሁሉ ይሠራል እንጂ "ለምን ቤተ መቅደስ በዛ?" አይባልም።

ሥልጣነ ክህነትስ ለአንዱ ነገድ ለነገደ ሌዊ ብቻ ይሰጥ የነበረ አልነበረምን? በሐዲስ ኪዳን ግን ነገር ተለውጦ በክህነቱ ለማገልገል ብቁ ለሆኑና መንፈሳዊውን መስፈርት ለሚያሙሉ አማኞች ይሰጣል። "ለምን ለሁሉ ይሰጣል?" አይባልም! (1ጢሞ 3:1-13፣ ቲቶ 1:7)

ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ በአዲስ ኪዳን “በሰማይም ያለው የእግዚአብሔር መቅደስ ተከፈተ፥ የኪዳኑም ታቦት በመቅደሱ ታየ፥ መብረቅና ድምፅም ነጐድጓድም የምድርም መናወጥ ታላቅም በረዶ ሆነ።” (ራእ 11፥19) በማለት ይነግረናል። ይህ ሲጠቀስለት ደግሞ በአንድምታ ትርጓሜ ያምን ይመስል "ይህ አገላለጽ Symbolic እንጂ ስለ ታቦቱ አይደለም።" ይላል።

፩. ታቦት ጣዖት ከሆነ እንዴት በሰማይ ሊኖር ቻለ?

፪. "Symbolic ወይም ምሳሌያዊ ነው።" ብትሉ እንኳን በሰማያዊት ኢየሩሳሌም ያለ መልካም ነገር እንዴት በጣዖት Symbolic ሆኖ ሊገለጥ ይችላል?

በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንም ይህች ታቦት:- ታቦት ዘዶር እንደምትባልና ምሳሌነቷም ለአማናዊቷ ታቦት ለድንግል ማርያም መሆኑን መምህራን ያስተምራሉ። የራሱን ሰውነት በመቅደስ መስሎ ስለ ተናገረ ጌታ ትንሣኤ ትንቢት የተናገረ ክቡር ዳዊት "አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት" ብሎ ትንቢት መናገሩን ልብ እንበል። (መዝ 131:8) የመቅደሱ (የእርሱ) ታቦት (ማደርያው) እናቱ ድንግል አይደለችምን? ለክርስቶስ ማደርያነት በዚህ መንገድ የቀረበ ታቦትን እንዴት ጣኦት ትላለህ?

የምድሩ ታቦት ነገር ሲነገረው የማይገባው ስለ ሰማዩ ታቦት ቢነገረው እንዴት ይቀበል ይሆን?

እኛስ የታቦት ሥራ አለብን!!


መምህር ቢትወደድ ወርቁ
++ የታቦት ምንጩ ማነው? ++

ታቦት "ጣኦት" ቢሆን “በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።” (ዘጸ 20፥4) ብሎ ያዘዘ እግዚአብሔር እንዲኽ ብሎ ባዘዘበት ቃሉ ሊቀ ነቢያት ሙሴን “ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ።” ብሎ ያዝ ነበርን? (ዘጸ 25፥10)፤

ዳግመኛስ ታቦቱን ጣኦት ስትል “በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።” ብሎ ለሊቀ ነቢያት ሙሴ የተናገረ እግዚአብሔርን ክብር ይግባውና ጣኦት ባለበት ይገለጣል ልትል አይደለምን? (ዘጸ 25፥22)

ምሥጢሩን ተወውና (በምሥጢር ስለ ማታምን) በሰማይ ስለታየው ታቦትስ ምን ትላለህ? ከዬት መጣ? ማን ሰማይ አወጣው? ታቦትን "ጣኦት" ካልክ "ጣኦት በሰማይ ምን ይሠራል?" ያን ታቦት ማን ቀረፀው? ቅርጽና ይዘቱስ ምን አይነት ነው? እስቲ በጨዋነት መልስልን!

ሲጀመር የታቦት ምንጩ እግዚአብሔር፤ የጣኦትም ምንጩ ዲያብሎስ አይደለምን?

"ታላቅንም ነገርና ስድብን የሚናገርበት አፍ ተሰጠው በአርባ ሁለት ወርም እንዲሠራ ሥልጣን ተሰጠው።እግዚአብሔርንም ለመሳደብ ስሙንና ማደሪያውንም በሰማይም የሚያድሩትን ሊሳደብ አፉን ከፈተ።" እንዳለው ሐዋርያው ራሳችንን ከአውሬው የስድብ ራሳችንን እንጠብቅ! (ራእይ 13:5)

መምህር ቢትወደድ ወርቁ
ታላቅ ደስታ !
በአዲስ አበባ ደብረ አሚን (ዳግሚት ደብረ ሊባኖስ) አቡነ ተክለሃይማኖት ቤ/ክ የቤተ መቅደሱ ጥንታዊነቱን የጠበቀ ከፍተኛ እድሳት ተጠናቆ ዛሬ ጥር 23 - 2016 ዓ.ም በታላቅ መንፈሳዊ በዓል ምርቃቱ ተከብሯል !
" ሁለቱም አንድ ይሆናሉ "


Photo credit

26 - 05 - 2016 ዓ.ም አቤቶ ፕሮዳክሽን
0953856891
ላይ ይደውሉልን
መርሃግብርዎትን ከእኛ ጋር በመሆን ያሳምሩት !!!