" #እነሆ_መንገድህ_በፊቴ_ጠማማ_ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ "
_________
#ዘኍ ፳ ፪ ÷፴ ፪
ይህን ኃይለ ቃል የተናገረው #ሊቀ_መላእኩ_ቅዱስ_ሚካኤል ነው ። የተናገረውም ለተራጋሚው በልዓም ስለተባለ ሰው ነው:: ቃሉን ጽፎ ያስቀመጠልን ሊቀ ነብያት ቅዱስ ሙሴ ነው::
#በልዓም ሃብተ መርገም ያለው የረገመው በቶሎ የሚደርስለት ሰው ነበር :: በዚህም ጸጋው ተጠቅሞ እስራኤልን ይረግም ዘንድ እጅ መንሻ ገንዘብን እንዲሰጡት ባላቅ ሰዎች ላከበት "፤ የሞዓብ ሽማግሌዎችና የምድያም ሽማግሌዎችም የምዋርቱን ዋጋ በእጃቸው ይዘው ሄዱ፤ ወደ በለዓምም መጡ፥ የባላቅንም ቃል ነገሩት። " #ዘኍ ፳ ፪÷ ፯
በልዓምም የተሰጠውን ሃብተ መርገም በገንዘብ ቀይሮ ሕዝበ #እግዚአብሔርን እስራኤልን ለመርገም በአህያው ላይ ተቀምጦ ሽማግሌዎቹንም ከዋላው አስከትሎ ጉዞ ጀመረ ::ጥቂት እንደሄደ ግን አህያው አንድ ባታ ላይ ቆማ አልንቀሳቀስም አለችሁ:: #የእግዚአብሔር_መላእክ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ ከፊቷ ቆሞ አይታዋለችና:: በልዓም ግን አህያይቱን አብዝቶ ደበደባት አህያይቱም ወደፊት ላለመሄድ ወደጉን ወደ እርሻው ተጠጋች
"፤ አህያይቱም #የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፥ የበለዓምንም እግር ከቅጥሩ ጋር አጣበቀች፤ እርሱም ደግሞ መታት። " #ዘኍ ፳ ፪÷፳ ፭
#እግዚአብሔር አምላክ የሚረግሙህን እረግማለው የሚባእኩህንም እባርካለው ብሎ ቃል የገባላቸው የነ አብርሃም የነ ይስሐቅ የነ ያዕቆብ ዘር ናቸውና ሕዝበ እስራኤል እንዲረገሙ አልፈቀደም::ዘፍ 12÷3
የበላዓም ዓይኖች አሁንም አልተከፈቱም ልቦናውም ከአህያይቱ ልብ አልተሻለም አሁንም አብዝቶ ደበደባት ይህን ጊዜ በሰው አንደበት እንዲ ብላ ተናገረችው ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው። "፤ በለዓምም አህያይቱን። #ስላላገጥሽብኝ_ነው_በእጄስ_ሰይፍ_ቢኖር አሁን በገደልሁሽ ነበር አላት።
"፤ አህያይቱም በለዓምን። ከብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም ። እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት። እግዚአብሔርም የበለዓምን ዓይኖች ከፈተ፤ የእግዚአብሔርን መልአክ በመንገድ ላይ ቆሞ የተመዘዘም ሰይፍ በእጁ ይዞ አየ፤ ሰገደም፥ በግምባሩም ወደቀ።
#የእግዚአብሔርም_መልአክ። አህያህን ሦስት ጊዜ ለምን መታህ? እነሆ፥ መንገድህ በፊቴ ጠማማ ነውና እቋቋምህ ዘንድ ወጥቼአለሁ፤ አህያህ አይታኝ ከፊቴ ፈቀቅ ባትል ኖሮ በገደልኩ ነበር አለው ደግሞም በለዓምን ከሰዎቹ ጋር ሂድ፥ ነገር ግን የምናገርህን ቃል ብቻ ትናገራለህ አለው። በለዓምም ከባላቅ አለቆች ጋር ሄደ መልአኩ እየነገረው እስራኤልን ሊረግም ሄዶ መርቆ ተመለሰ::
#የእግዚአብሔር ሥራ ይገርማል ። የበልዓም አህያ የመላእኩን ክብር በማወቋና በመገንዘቧ የበላህምን ሕይወት ታድጋለች ዛሬ የቅዱሳን መላእክትን ክብር የማያውቁ የጸጋ ስግደት የማይሰግዱ አማላጅነታቸውን የማይቀበሉ ከአህያ ያነሱ ሰዎች በዝተዋል እግዚአብሔር አምላክ እንደ በልዓም ዓይነ ልቦናቸውን ከፍቶ ክብረ መላእክትን አውቀው ቅዱሳንን መርገም ትተው አንገታቸውን ደፍተው እንዲሰግዱ ያድርጋቸው ... .....ሌላ ምን እንላለን ከጌታችን የተማርነው ይህን ነውና
"፤ #የሚረግሙአችሁንም_መርቁ፥ ስለሚበድሉአችሁም ጸልዩ። "
(ሉቃ ፮÷ ፳ ፰ )
....#ይቆየን......
በዛሬው ዕለት ለበልዓምና ለአህያው የተገለጠበት ዓመታዊ ክብረ በዓሉ የሚከበርለት የሊቀ መላእኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤትና ምልጃው አይለየን!
አ.አ ኢትዮጵያ
ተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
መጋቢት ፲ ፪ ቀን ፳ ፻ ፲ ዓ.ም የተጻፈ

#ምስጋና ቢስ ጤና
----------------------------
በሽታውን ለምዶ ለኖረ በጠና
መዳን መታመም ነው መቆየት በጤና
ሕመመ ለምዶ ለምዶ
እኸኸን ለምዶ ለምዶ
ወንጀል ይመስለዋል የዳነ ተገዶ
ከለመደው ሕመመ ካከረመው በደል
ማንም ቢነጣጠል ጸናበት ነው እንጂ
ተፈወሰ አትበል
ጤና ለራቀው ሰው ሕመም ነው ጤንነት
ከለመደው መኖር እኸኸ ከሚልበት
አለመታመም ነው የሱ መጻጉነት
ስለዚህ ወዳጄ
ማዳንን ስለቻልክ መፈወስ ስላወክ
ልፈውስ አትበለው ሕመሙን አርቀህ ጤናውን እያወክ
ያ ደጉ ጌታ እንኳ ለማዳን የመጣው
ልድን ተወዳለህ? ብሎ ያስፈቀደው
ላንዳንዱ በሽታው
ጤናው እንደሆነ አስቀድሞ አውቆ ነው
መዳን ጤና የሚሆን ላንዳንዱ ብቻ ነው
ጤናው ጤና ነስቶት በሽታ የሆነበት
ኁልቁ ሰው አለልህ ለቁጥር የሚያዳግት
ያዳነውን መድኅን ሽቅብ የሚያንጓጥጥ
ያዳነኝ ያ ሰው ነው ብሎ የጠቆመው
መድኅኑን በሰው ፊት ኮንኖ ያቆመው
ተኝቶኮ አይደለም በአልጋ ቁራኛ
መጻጉዕ ድኖ ነው የሆነ ሕመምተኛ
እናማ የታመምክም ብትሆ በአልጋ የወደክ
ጤናህን በማጣት በጅጉ የደከምክ
አታማር ግድ የለም
ያንተ ጤንነትህ በደዌክ ውስጥ ነው
መናልባት ሕመም ቀና ያልክ ቀን ነው
#ማስታወሻነቱ :- በደዌ ደኛ በአልጋ ቁራኛ ለተያዙ ሁሉ ይሁንልኝ!
#የምሕረት-እናት-ድንግል-ማርያም ምሕረቱን ትላክላችሁ:: የወይን ጠጅ አኮ የላቸውም ብሎ አዲስ የወይን ጠጅ ባሰጠ አንደበቷ ዛሬም ጤናኮ የላቸውም ብላ ከቀድሞው የበለጠ አዲሰ ጤናን ታሰጣችሁ ታሰጠን! አሜን!
አ.አ ኢትዮጵያ
ከተክለ ኤል ኃይለ ማርያም
መጋቢት ፲ ፫ ቀን ፳ ፻ ፲ ፬ ዓ.ም

ፍጥነቱ፦ ፈጥነቱ እንደ መብረቅ ነው። «መብረቅ ከምሥራቅ ወጥቶ እስከ ምዕራብ እንደሚታይ፥ የሰው ልጅ መምጣት እንዲሁ ይሆናል» (ማቴ 24፥ 27):: ተብሏልና።
ቀኑ አለመታዎቁ፦ እንደ ሌባ ነው። ያን ግን እወቁ፤ ባለቤት ከሌሊቱ በየትኛው ክፍል ሌባ እንዲሚመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ ቤቱም ሊቈፈር ባልተወም ነበር … የሰው ልጅም በማታስቡበት ሰዓት ይመጣል (ቁጥ. 43-44)።
ለታሪካዊ ማስገንዘቢያ የኖህ ዘመንም እንደዚሁ ባልታሰበ ሠዓት እንደሚመጣ ማስገንዚያ ሆኖ በጌታችን ቀርቧል። (ከቁጥ. 37-39)።
ወቅታዊ መልእክቱ
ተጠንቀቁ፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ (ቁጥ.4)።
ንቁ፦ጌታችሁ በምን ሠዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ (ቁጥ. 42)
ተማሩ እወቁ፦ እንዲሁ እናንተ ደግሞ ይህን ሁሉ [ከላይ የተናገራቸውን ምልክቶች ሁሉ] ስታዩ በደጅ እንደ ቀረበ እወቁ (ቁጥ. 33)።
አትደንግጡ፦ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ (6)
ትጉና ጸልዩ፦ ነገር ግን ሽሽታችሁ በክረምት ወይም በሰንበት እንዳይሆን ጸልዩ (20)
ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፦ ስለዚህ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።(44)።
ጽኑ፦ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል (ቁጥ.13)።
እነዚህን ሁሉ ምክሮች፣ ማስጠንቀቂያዎችና ማፅናኛዎች በአእምሮ ጽላት ቀርፆ በማስተዋል በሃይማኖት እና በክርስቲያናዊ ሥነ ምግባር ጸንቶ የኖረ የሕይወትን ቃል ሰምቶ የክብር፣የድልና የጽድቅ አክሊልን ተሸልሞ በዘላለማዊ ደስታ ይኖራል።
ሦስተኛ የሰው ዘር የጋራ ልደት እና ዕድገት
ከዚህ ሁሉ በኋላ በእግዚአብሔር ዘንድ ቀነ ቀጠሮ የተያዘላት ዓለም ወደ ፍጻሜዋ ታመራለች፣ ጣዕሟ፣ ለዛዋ ሁሉ ይሟጠጣል፣ ፍጻሜ ዓለም ይሆናል፡፡ ምድር ከመሠረቷ ትናጋለች፣ ፀሐይ ትጨልማለች፣ ከዋክብትም እንደ ቃርያ ፍሬ ከሰማይ ይረግፋሉ፡፡ (መዝ. 12፥ 2፤ ኢሳ. 13፥ 6-13፤ ኢዩ. 2፥ 10-11፣ 30-32፤ ማቴ. 24፥ 29-41፤ ራዕይ 6፥12-17)፡፡
በታላላቅ ድንጋዮች የታተሙ መቃብሮች በውስጣቸው የያዙአቸውን ሙታን ይሰጣሉ፣ የሙታን ሥጋ ከረጅም የእንቅልፍ ዓለም ይባንንና ሁሉም በአንድ ቀን ከመቃብር ተወልደው በአንድ ቀን አድገው ወደ ፍርድ አደባባይ ይሰበሰባሉ፣ ታላቁ ዘንዶ ለብዙዎች ስሕተት ምክንያት የሆነው ዲያብሎስ ከነሠራዊቱ ለዘላለም በማይፈታ በእሳት ሰንሰለት ታስሮ ወደ ገሃነመ እሳት ይጣላል፡፡ ፊተኞቹ ሰማይና ምድር ከፍጡራን ፊት እንደወረቀት ተጠቅልለው ያልፋሉ፣ ስፍራም አይገኝላቸውም ለዘለአለምም ያልፋሉ፡፡ (ኢሳ. 13፥ 6-13፤ መክ. 12፥ 17፤ 1ኛ ተሰ. 4፥ 13-18፤ 2ኛ ጴጥ. 3፥ 10)፡፡
በበጉ ደም የተዋጁና ሃይማኖታቸውን የጠበቁ ታማኝ የክርስቶስ ልጆች ገናናውንና ታላቁን አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን ሊቀበሉ በታላቅ ክብር በደመና ወደ ሰማይ ይነጠቃሉ፡፡ የአብ ልጅ የድንግል ማርያም ልጅ የባሕርይ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስም በታላቅና እጅግ አስፈሪ በሆነ መለኮታዊ ግርማ የብዙ ብዙ በሚሆኑ እልፍ አእላፋት ቅዱሳን መላእክት ታጅቦ ይመጣል፡፡ (ዘካ. 14፥ 6፤ ማቴ. 25፥ 31፤ 1ኛ ተሰ. 4፥ 16)፡፡
በዚያን ጊዜ በፊቱ ችሎ የሚቆም ማን ይሆን? (ኢዩ. 2፥ 11) አመጣጡም እንደቀደመው ከሐና ወደ ቀያፋ ከዚያም ወደ ጲላጦስ አደባባይ እያንገላቱ ሲወስዱት ዝም እንዳለ በዚህ ዓይነት አመጣጥ አይደለም፡፡ የሚመጣው በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ መለኮታዊ ግርማና ክብር ነው፡፡ (መዝ. 49፥ 2)፡፡ መጥቶም ዝም አይልም እሳት በፊቱ ይነዳል ኃጥአንን ከፊቱ ጠራርጎ ወደ ገሃነመ እሳት የሚጨምር ጥቅል አውሎ ነፋስም አለ፡፡ (ማቴ. 24፥ 30፤ ራዕይ 1፥ 7)።
እረኛ በጎቹን ከፍየሎቹ እንደሚለይ ጻድቃንን በቀኙ ኃጥአንን በግራው ለይቶ ያቆማቸዋል፡፡ በቀኙ ያሉትን “እናንተ የአባቴ ቡሩካን ወደ እኔ ኑ ወደ አባታችሁ መንግስተ ሰማያት ግቡ፡፡” ብሎ ለዘለዓለም ሕይወት ይጠራቸዋል፡፡ በግራው ያሉትን ደግሞ እጅግ በሚያስፈራና በሚያስደነግጥ የቁጣ ቃል “እናን ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀው ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” ይላቸዋል፡፡
ኢየሩሳሌም ሰማያዊት ለባልዋ እንደተሸለመች ሙሽራ ተዘጋጅታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ትወርዳለች ማለት ለምእመናን ትሰጣለች፡፡ ምእመናንም ርስት መንግስተ ሰማያትን ይወርሳሉ ብርሃን ለብሰው ብርሃንን ተጎናጽፈው ለዘለዓለም በደስታ ይኖራሉ፡፡ (ማቴ. 25፥ 31-46፤ ራዕይ 21፥ 1-2)፡፡
ኦርቶዶክሳውያን! ነቢዩ ኤርምያስ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡-በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደሆነች እወቁ በእርስዋም ላይ ሂዱ ለነፍሳችሁም እረፍት ታገኛላችሁ” (ት.ኤር. 6፣ 16)፡፡ በማለት እንደተናገረው በቀደመችው በመልካሚቱ የሕይወትና የጽድቅ መንገድ በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነታችን እስከ መጨረሻው ድረስ ጸንተን ልንኖር ይገባል፡፡

ዐውደ ምሕረት
Photo
#ሠላም_ለጽንሰትከ ተክለ ሃይማኖት ሐዲስ ነቢይ
“በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።”
— #ኤርምያስ 1፥5

ገብርሔር02
<unknown>
ውይይት
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሁለት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሁለት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
Audio
ውይይት
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሦስት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
#በእንተ_ገብርሔር
ክፍል ሦስት
በወንድሞቻችን
#ዮሴፍ_ዘለቀ
#ኢዮብ_ክንፈ
#ተርቢኖስ_ሰብስቤ
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit
👉 @AwediMeherit