አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
495 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሙሾ_ለከሰመች_ተፈጥሮ

#ያኔ
ዛፎች ሳይረሸኑ
ሣሮች ሳይመነጠሩ
መስኮች ሳይሸነሸኑ
በቆርቆሮ ሳይታጠሩ፤

#ያኔ
ሰጎንና የዱር ዝሆን
የሎተሪ ስም ሳይሆን፤

#ያኔ
ቤቶች በዝተው ተባዝተው
እንደከፉ አረም፥ መስኩን ሞልተው
ሐመልማሉን ቁጥቋጦውን፥ እንደባላጋራ ገፍተው
ግኡዝ ግሪሳ ሳይሆኑ፥ የምድርን እሸት ሚያበላሹ
በወንጭፍ የማይመቱ፥ በጠጠር የማይሸሹ፤

#ያኔ
እዚም እዚያም ችፍግ ያሰ፥ የበርና መስኮት ጭፍራ
የጭስ ጅረት የሚያመነጭ፥ የነተበ ድኩም ጣራ
በተፈጥሮ ውብ መልከ ላይ
እንደ ማድያት ሳይዘራ፤
#ያኔ
በጋ ክረምት ሳይሉ፥ ወንዞች ሲገነፍሉ
ምንጮች በየመሰኩ ላይ፥ እንደከረምት እግሲ ሲፈሉ፤
#ያኔ
ገዴ ስትዘፍን፥ የጫካ ቆቅ ሲያስካካ
ያዋፍ ያራዊት ማህሌት፥ በመኪና እሪታ ሳይተካ
ከጥቁር አፈር ጋራ፥ እድሜያችንን እየፈጨን
ከደስታ እንባችን ጋር፥ ጅረት እየተራጩን
ልጅነታችንን ቀጨን፤

አሁን በድሜ ጎልምሰን
አጭትን፥ ጎጆ ቀልሰን
ቀድመውን ላንቀላፉ፥ ወዳጆቻችን አልቅሰን፤

ለብሳናው ለግራሩ፥ ላለቀው በመጋዝ ታርዶ
ለተሰየፈው ዋርካ፥ ሰደድ ለበላው ሰርዶ
በቅጠሏ አየር ነዝታ፥ ጥኡም ፍሬዋን አብልታ
ላሳደገችን ሾላ፥ ለዚያች የዋህ የናት-ፋንታ
ምነው መሾ ማናወርድ
ምነው ደረት ማንመታ።