#ግን_አንድ_ሰው_አለ
እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ፥ እንዳስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንዳመዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ
ያይንሽ ከረጢቱ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሆነሽ
መጣፍሽን ከፍተሽ
ያለፈውን ዘመን፥ ገልጠሽ ስታነቢው
የኔን ቃል አስቢ፤
ስንቶች አፈቀሩት፥ በሐቅ በይስሙላ
የገጽሽን አቦል፥ የውበትሽን ኣፍላ
ግን አንድ ሰው አለ
ከሌሎች ወንዶች ጋር፥ ያልተመሳሰለ
በዕጹብ ድንቋ ነፍሰሽ፥ ፍቅር የነደደ
የመልክሽ ጸደይ ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ፥ ጥሎሽ ያልነጎደ።
እርጅና ሲጫንሽ
እድሜ ተጠራቅሞ፥ እንዳስም ሲያፍንሽ
ሽበት እንዳመዳይ
በጭንቅላትሽ ላይ
በድንገት ሲፈላ
ያይንሽ ከረጢቱ፥ በንቅልፍሽ ሲሞላ
ምድጃ ዳር ሆነሽ
መጣፍሽን ከፍተሽ
ያለፈውን ዘመን፥ ገልጠሽ ስታነቢው
የኔን ቃል አስቢ፤
ስንቶች አፈቀሩት፥ በሐቅ በይስሙላ
የገጽሽን አቦል፥ የውበትሽን ኣፍላ
ግን አንድ ሰው አለ
ከሌሎች ወንዶች ጋር፥ ያልተመሳሰለ
በዕጹብ ድንቋ ነፍሰሽ፥ ፍቅር የነደደ
የመልክሽ ጸደይ ሲያልፍ
ልክ እንደ መስቀል ወፍ፥ ጥሎሽ ያልነጎደ።