አትሮኖስ
286K subscribers
117 photos
3 videos
41 files
566 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮዛ_2


#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ (🔞)


#ኤርሚ_ጂግሎ

ዕሁድ ጠዋት…። ማንንም ማግኘት የማልፈልግበት የግል ክፍለ ጊዜዬ ናት። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ስሞኑን የጀመርኳትን መጽሐፍ እያነበብኩ ነበር። አብሮ አደጌ ፌሩዝ ናት ከለንደን የላከችልኝን። “fifty Shades of Grey” ይላል ርዕሱ፡፡ አንድ ክርስትያን ግሬይ የተባለ የ27 አመት ወጣት ቢልዬነር
የሚመራውን ድብቅ የፈንጠዝያ አለም የሚተርክ መጽሐፍ ነው። ዋናው ባለታሪክ በወሲብ ወቅት ሴቶችን በማሰቃየት እርካታን የሚያገኝ ካዲስት ነው። ፌሩዝ «ብዙ ሚሊዮን ፈረንጅ በሸሚያ ያነበበው
ነው ሲባል ሰምቻለሁ፤ እኔ እንደምታውቂው ማንበብ አልወድም፣ አንቺ መጽሐፍ ማንበብ ስለምትወጂ
ነው የላኩልሽ» ብላኛለች። ምን አይነት መጽሐፍ ቢሆን ነው ብዬ ነበር የጀመርኩት።
ከጀመርኩት በኋላ ግን ታሪኩ ለማቆም ቸገረኝ፡፡

ሞባይሌ ስታቃጭል ያቆምኩበትን ገጽ ከአናቱ ላይ አጥፌ ከአልጋዬ በመውረድ ስልኬን ቻርጅ ወደ ሰካሁበት ቡፌ አመራሁ። ስልኬን ማጥፋት ረስቼ እንጂ እሁድ ጠዋት ማንንም ባላናግር ደስ ይለኝ ነበር።

የሞባይሌን ስከሪኔ "Ermi Gigolo” እንደደወለ ነገረኝ። ፈገግ አልኩኝ። እንደዚያ ብዬ ስሙን ሴቭ ማድረጌ ልክ አልነበረም።
ጂግሎ(Gigolo) የሚለው ቃል ኤርሚያስን የሚገልፅ ቢሆንም ስልኬ ላይ በዚያ ስም ሴቭ ማድረጌ ትክክል እንዳልሆነ ታውቆኛል። ጂግሎ ማለት በእንግሊዝኛ ከሴቶች ገንዘብ ተቀብሎ የወሲብ አገልግሎት የሚሰጥ ወንድን የሚወክል ቃል ነው።ስለዚህ ኤርሚን ይገልፀዋል።ሆኖም ይሄ ደዋዮቼን በቀላሉ ለማስታወስ በሞባይሌ ላይ ከዋና ስማቸው አጠገብ የማሰፍረው ቅጽል ከዚህ በፊት ብዙ መዘዝ አምጥቶብኛል

ለምሳሌ አንድ ምሽት ዳንኤል ከሚባል የብስኩት ፋብሪካ ያለው ወዳጄ ጋ እየተዝናናሁ ሳለ ሽንቴ መጣ ተነስቼ ባዝ ሩም ሄደኩ። ለካንስ ሞባይሌን እዚያው ጠረጴዛው ላይ ረስቼው ነበር። ከመጸዳጃ ቤት ስመለስ ዳኒ እሳት ለብሶና እሳት ጎርሶ ጠበቀኝ። የሚያስጠላ የስድብ ናዳም አወረደብኝ። መፃዳጃ ቤት
በሄድኩበት ቅጽበት ለካ የኔን ስልከ አንስቶ የራሱን ቁጥር ሲደውል እኔ የሱን ስልክ ሴቭ አድርጌዋለሁ።ሴቭ ማድረጌ አልነበረም ችግሩ። ሴቭ ያደረኩት «ዳኒ ቦርጮ ብዬ ነበር።

እኔ ምን ላድርግ ታዲያ! ሺ ዳንኤል ነው የማውቀው። “ዳኒ ኮንትራክተር” ፣ዳኒ አርቲስቱ” ኢምፖርተር”፣“ዳኒ ካናዳ"፣"ዳኒ ቦርጮ፣"ዳኒ ዲዛይነር”፣”ዳኒ ሸፋዳ”፣” ዳኒ ሾርት”፣ “ዳኒ ቆለጥ፣ "ዳኒ ፓስተር"

ዳኒ የበገነበት ምክንያት ከቁጣውና ከስድቡ በኋላ ግልጽ ሆነልኝ፤

“ብሽቅ ሸርሙጣ ነሽ! ያ ሁሉ እንክብካቤ እያረኩልሽ ከኔ “ቦርጩ” ብቻ ነው ትዝ የሚልሸ? ይሄ ለኔ ያለሽን መራር ጥላቻ ያሳየኛል። ድሮም ከሸሌ ምን ይጠበቃል! እናንተ ከልብ የሚወዳችሁና
የሚንከባከባችሁት አትወዱም…አንቺ ደህና ሰው ትመስይኝ ነበር፤ የሸሌና የሰይጣን ደህና የለውም "እውነተሸ ነው።"

በንዴት ስልኬን ከመሬት አጋጭቶ ሊሰብረው ሁሉ ቃጥቶ ነበር። ስኮሳተርበት ነው የተወው።

ኤርሚ ጂግሎም ስሙን ምን ብዬ ስልኬ ላይ ሴቭ እንዳደረግኩት ቢያውቅ ምን ሊሆን እንደሚችል ስገምት ዘገነነኝ። ነገ ማታ በመኪናው ከክለብ አሪዞና ፒክ እንደሚያደርገኝ ከተነጋገርን በኋላ ስልኩን ዘግቼ ወዲያው ስሙን ቀየርኩት። Ermi Stud ብዬ ሴቭ አደረኩት። ከgigolo ይልቅ Stud ቢባል ያኮራዋል እንጂ አያሸማቅቀውም።

ኤርሚ ጂግሎ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ከክለብ አሪዞና ይዞኝ ወደ ዮድ የባሕል ምግብ ቤት ወሰደኝ።
ዬድ አሪፍ ክትፎ ከበላን በኋላ ከክለብ ክለብ እየገባን፣ እየጠጣን፣ እየጨፈርን አሪፍ የማይረሳ ምሽት አሳለፍን

ኤርሚ ደም ግፊት ካለባት ሹገር ማሚ ወዳጁ ኑኑሻ ጋ ዱባይ አንድ ዓመት ቆይቶ መመለሱ ነበር።ከኑኑሻ ጋር የተዋወቁት ኤርሚ ጀንግል ጂም ፊትነስ ሴንተር ውስጥ ኤሮቢክስ በሚሰራበት ወቅት ነበር ኑኑሻ የዱባይን መሬት ለመጀመሪያ ጊዜ ከረገጡ የሀበሻ ሴቶች ኣንዷ እንደነበረች ነግራዋለች።
ሃብታም ነጋዴ ናት። እኔና ኤርሚ ጂግሎን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስተዋወቀን ደግሞ ኡስማን ዘ ፒምፕ ነበር።

ኤርሚ ጂግሎ ፈረንጆቹ 'six pack የሚሉት የሚያምር የሆድ ቅርጽ አለው። ፈርጣማና ጡንቸኛ ሰውነቱ ከቁመናው ጋር ተደማምሮ የትኛዋንም ሴት ያፈዛል። አብረን በትዝናናንባት በዚያ ምሽት እንኳ
ብዙ ሴቶች ከቦይፍሬንዶቻቸው እቅፍ ዉስጥ ሆነው ኤርሚ ጂግሎን በስርቆሽ ሲያዩት ነበር።

ኤርሚን በአካል ሳላውቀው በፊት መጀመርያ ያወቅኩት በፎቶ ነው። አትላስ ኡስማን ዘ ፒምፕ የትራቭል ኤጀንሲ ቢሮ ዉስጥ ቁጭ ብዬ ኡስማንን እየጠበቅኩ እያለ ሼልፍ ላይ የሚያምር ካታሎግና
አልበም ተቀምጠው አየሁ። መዝዤ ስገልጠው ኤርሚ ጂግሎ የአልበሙን ግማሽ ሞልቶታል።በተለያዩ ፓንቶት፣ በቁምጣ፣ ጥብቅ በሚያደርግ ቦዲ፣ ወንድነቱጋ አበጥ ያለ ነገር እንዳለ በሚያሳብቅ የወንድ ታይት፣ ገጠር ውስጥ በሬ ጠምዶ ሲያርስ፣ ፈረስ ሲጋልብ.የሌለው አይነት ፎቶ…ያልተነሳው
አይነት አነሳስ የለም። መአት ፎቶ ነው ያለው። በሌላኛው አልበም ደግሞ የብዙ ሴቶችን ፎቶ የያዘ ካታሎግ ተመለከትኩ። እሱን ትቼ የኤርሚ ጂግሎን ካታሎግ በድጋሚ እያየሁ ሳለ ኡስማን ዘ ኪንግ
በሩን በርግዶ ገባ። ሰርቆ እንደተያዘ ሌባ ክው አልኩኝ። ምን እንዳስደነገጠኝ ገርሞኛል። ኡስማንም ድንጋጤዬ ገርሞት ምን እያረኩ እንደነበር ጠየቀኝ። ኤርሚ ጂግሎ ሞፈርና ቀንበር ተሸክሞ የሚያምር ገበሬ መስሎ ደረቱን አጋልጦ የተነሳውን እጅግ የሚያምር ፎቶ አሳየሁት። ኡስማን ነገሩ ገብቶት መሳቅ
ጀመረ። ምንድነው ሮዚ! በቆንጆ ወንድ ፎቶ ሴጋ መምታት ጀመርሽ ማለት ነው…” ብሎ የማያባራ ሳቅ ሳቀብኝ፣ በጣም ሳቀብኝ። ሲስቅብኝ ደግሞ ይበልጥ ተሸማቀቅኩ።

ፎቶው ላይ ስለተመለከትኩት ልጅ ጠየቅኩት። አጠር አድርጎ አብራራልኝ።

“ ኤርሚያስ ይባላል…ቱሪስት ሴት ክላይንቶቻችን ጠይም የሐበሻ ወንድ ካልወለድክ ብለው
እስጨነቁኝ፡፡ ጥያቄው ሲበረታብኝ ኤርሚያስን በስንት አደን አገኘሁት፡፡ እንደምታይው ጠይምነነቱና
ቁመናው ይማርካቸዋል ወንዶቻችሁ ጡንቻቸው ደቃቃ ነው» እያሉ ብዙ የመለመልኳቸውን
ወንደች አጣጥለውብኝ ነበር። ኤርሚያስ ነው በመጨረሻ የገላገለኝ…” አለኝ፡፡

ከዚያ በፊት እንደዚያ አይነት ነገር እዚህ እግር ዉስጥ ሰምቼ አላውቅ ስለነበር በጣም ተገረምኩ ኡስማንን አፍጥጬ ስመለከተው ሌላ ነገር የፈለኩ መስሎት
"ችግር የለውም ሮዚ፤ አንድ ምሽት እንዲቸገርልሽ ማድረግ እንችላለን” አለኝ። “ሂድ እዛ ሞዛዛ፣ አስቀያሚ” ብዬው ልወጣ ስል እጄን ይዞ
እስቀመጠኝ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኡስማን በኤርሚ ጉዳይ እንደሳቀብኝ ነው። “እኔ ቢሮ ዉስጥ በኤርሚ ፎቶ ሮዛ ምን ስታደርግ እንደያዝኳት ነገርኳችሁ?” እያለ ለነራኪ አሳልፎ ሰጠኝ። መሳቂያ አደረገኝ ።ራኪ እንኳን ይሄን ጮማ ወሬ አገኝታ....።

ከስንት ጊዜ በኋላ ኡስማን ደውሎ ጊዮን ቀጠረኝ። አብሮት መልአክ የመሰለ ጠይም ወንዳ ወንድ ልጅ
ተቀምጧል። ጥቁር መነጽር በማድረጉ ግን በደንብ አለየሁትም ነበር። ጠጋ ብዬ ሳየው ልቤ ቀጥ ልትል ምንም አልቀራት። ይህን ልጅ የት ነው የማውቀው ብዬ ስጨነቅ "ሮዝ ኤርሚያስ ይባላል...ተዋወቁ" አለኝ እየጠቀሰኝ። አሁን ማን መሆኑ መጣልኝ። ካታሎጎ ላይ ያየሁት ሰው ነው። ኤርሚ ጂግሎ

ኤርሚን ሰኡስማን ያስተዋወቀችው ደግሞ ሳቢ ናት። ሳቢ ከኡስማን ወፎች ሲኒየሯ ናት። አንድም ቀን ያለማቋረጥ ኤሮቢክስ ስፖርት የምትሰራ ንቁና ታታሪ ሴት ጥሪ ብባል ከሷ ሌላ የማውቀው የለም የማውቃቸው ሰዎች ሁሉ ጀምረ
👍51😁1