አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ማፍቀር_ወይስ_መለየት ?
:
#አጭር_ልብወለድ
:
ቅዳሜ ከሰአት በኋላ ፣ፀጥ ረጭ ብሏል፣ የቤታችን የግድግዳ ሰአት ብቻ . . .ችው . . . ችው
እያለ በዚህ ፀጥታ ውስጥ ይሰማል። ማንም የለም እኔና እኔ ብቻ። በውስጤ የብቸኝነት ስሜት ተሰማኝ። በዚህ በጠራራ ፀሐይ እቤት ውስጥ ለብቻ መቀመጥ ምን ያህል ይከብዳል እያልኩ ከራሴ ጋር አወራለው።

ዞር ብዬ ክላሲካል ሙዚቃ ሲያሰማ ወደ ነበረው ቴፕ ስመለከት መብራት ሄዶ ዝም እንዳለ ታወቀኝ። ሀሳቤን ሰበሰብኩና በእጄ ወደያዝኩት ልብ ወለድ መፅሀፍ አቀርቅሬ ማንበቤን ቀጠልኩ።

በጥሩ ተመስጦ ውስጥ እንዳለው ድንገት ከአጠገቤ የነበረው ስልክ ጮኸና ቀልቤን ገፈፈው።በጣም ደነገጥኩ። በራሴ መደንገጥ ተገረምኩና እራሴን አረጋግቼ የስልኩን እጀታ በጉጉት አነሳሁት።

<<ሃሎ>> አልኩኝ በትህትና
<<ሄሎ>> አለችኝ አንዲት ልጅ በሚያባባና በሚያምር የድምፅ ቅላፄ።
<<ማንን ፈለጉ ?>>
<<እ. . .ናሆምን ላገኘዉ እችላለሁ ?>>

በዚህን ግዜ የልብ ትርታዬ ፍጥነቱን ጨመረ።
ድምፆም አዲስና የሚማርክ ስለሆነብኝ ማን ልትሆን ትችላለች? በሚል ከራሴ ጋር ትንሽ ተሟገትኩና።

<<ነኝ. . . ማን ልበል?>>
<<. . . ሜሮን እባላለሁ >>
<<ሜሮን?.. .ይቅርታ. . . አላስታወስኩሽም፣ ሜሮን ማን ?>>
<<ሜሮን አለሙ>>

አሁንም ፈፅሞ ላስታውሳት አልቻልኩም።ሜሮን የምትባል ልጅ ፈፅሞ ማወቄን እርግጠኛ አልነበርኩም።

<<በ. .ጣም.. ይቅርታ የኔ እህት አላወኩሽም።>>
<<ይገርምሀል እኔም አላውቅህም።>>
<<የደወልሽው አንቺ መሰለሽኝ?>>
<<አልተሳሳትክም፤ ማለቴ ስልክህን የአስረኛ ክፍል ማስታወሻ ደብተሬ ላይ ከበስተጀርባው ተፅፎ ነው ያገኘሁት።ሁለት አመት እንዳለፈውና በራሴ እጅ ፅሁፍ ስለመፃፉ እርግጠኛ ነኝ ነገር ግን በምን ቀንና ሁኔታ እንደተፃፈ አላስታውሰውም
<<እና?>>
<<እናማ ብዙጊዜ ሲከነክነኝ የነበረ ስልክ ቁጥር ስለነበር ምን አልባት አንተ ካወከኝ በሚል ነበር የደወልኩት።

መልሶን ማመን አቃተኝ።ለሰኮንዶች ያህል በአይኔ የማውቃቸውን እንስቶች በአይነ ህሊናዬ እየቃኘኋቸው ድምፅን ከምስል ጋር ለማዛመድ ሞከረኩ።ሆኖም በፍፁም ልትመጣልኝ አልቻለችም ።በርግጥ ከሁለት አመት በፊት ስለተከሰተ ነገር ማስታወስ ይከብዳል።

የቀረን ነገር ቢኖር በግምት ልንተዋወቅበት የምንችልበትን ሁኔታ መመርመር ነውና ስለየግል ህይታችን መነጋገር ጀመርን።ስለ ት/ቤትና ስለመኖርያ ስፍራችን፣ ስለቤተሰብ እንዲሁም ስለ ቅርብ ጓደኞቻችን ሳይቀር በግልፅ ተወያየን።በሚገር ሁኔታ ግን አሁንም ከጥርጣሬ ያለፈ እዚህ ቦታ ይሆናል ብለን መወሰን ተቸገርን።

ለቀልድ ነው ብዬ እንኳን እንዳልጠረጥራት የምትሰጠኝ መልሶች ሁሉ ግልፅና ፈጣን ነበሩ።
በተለይ ከንግግሯ በራስ መተማመንና በሳልነቷን ለመገመት ይቻል ነበር።ሁኔታው ቢያስገርመኝም ቀስ በቀስ ምርመራውን ትተን ስለየጎል ህይወታችን ገብተነሰ መጨዋወት ጀመርን።

<<ምን አየሰራሽ ነው አሁን?>>
<<ያው አስረኛ ከጨረስኩ በኋላ የሁለት አመት አካውንቲንግ ፊልድ ተምሬ ነግል ድርጅት ውስጥ በመስራት ላይ ነኝ። አንተስ?>>
<<እኔ እንደምንም የመሰናዶ ትምህርት ተምሬ አ.አ.ዮ የአስተዳደር ትምህርት በመማር ላይ ነኝ>>
<<ኦው ጎበዝ ተማሪ ነሃ . . .!>>
<<ነኝ ብለሽ ነው . . . ለመሆኑ ግን ምን ከይነት ሰው ነሽ ማለቴ መልክሽን?>>
<<...እኔጃ ለመግለፅ ይከብዳል።>> ሳቅ እያለች።
<<ታድያ.... ለምን በአካል አንገናኝም፤ >>ምን አልባት በመልክ ልንተዋወቅ እንችላለን?
ጥያቄውን በድፍረት ነበር ያነሳሁት ፤ሆኖም በፍርሀቴ ልክ መልኳን ለማየት ጉጉቱ ነበረኝ። እርሷም በመግደርደር ይሁን አላውቅም።

<<..መገናኘቱ እንኳን የሚመች አይመስለኝም።>
<<ለምን?>>
<<እኔንጃ?>>
<<ፈራሽ እንዴ?>>
<<አይ መፍራት ሳይሆን ሰሞኑን ክፍት ሰአት ስለሌለኝ ነው።>>
ንግግሯ እንደማቅማማት አይነት ነበር ፤ እርግጠኛ አልነበረችም።

<<እሺ. . . ብዙ አላስጨንቅሽም ባይሆን ስልክሽን ስጭኝና ተደዋውለን ሌላ ግዜ እንገናኛለን።>>

ለተወሰኑ ሰኮንዶች ዝም አለች።የኔንም ግራ መጋባት ጥርጣሬ አጎላችው።

<<ምነው ዝም አልሽ?>>
<<...ስልክም አሁን ልሰጥክ አልችልም።>>
<<እህ..ያሁሉ የግል መረጃሽን በግልፅነት ስትነግሪኝ ቆይተሽ እንዴትስልክ መስጠት ከበደሽ?>>
<<በፍፁም መደበቄ አይደለም።በዚህን ሰአት እኔን የምታገኝበት ስልክ ምን አልባት ለሁለት ቀን ብቻ የሚቆይ ነው ። ሌላ ስልክ በሌላ ግዜ እንጂ አሁን ልሰጥክ አልችልም ወይም አላውቀውም።>>
<<አሀ ገባኝ፣ ቤት ልትቀይሩ ነው አይደል?>>
<<አረ አይደለም >>ሳቅ እያለች ነበር።
<<ምንድን ነው እሱ ግልፅ ሁኚ እንጂ የደበቅሽው ነገር ኦንዳለ ይሰማኛል።>>
<<በቃ ለምን ነገ ወደ ማታ አንገናኝም?>>
የአቋም ለዉጧ አስገርሞኛል፣አስደንግጦኛልም።
አሁን ለመናገር ያልፈለገችው ሚስጥሯም ከልብ አጓጓኝ።
<<ጥሩ የት እንገናኝ?>>
<<ፒያሳ ያለው ቤቲ ካፌ ይመችካል?>>
<<ደስ ይለኛል ስንት ሰአት?>>
<<አስራ ሁለት ሰአት።>>
የሰአት ምርጫዋ ወደ ማታ መሆኑ አይናፋርነቷን ቢያስገምተኝም ለኔም ጥሩ ግዜ ስለነበር ወድያው ምልክቶቻችንን መለዋወጥ ጀመርን ።
የሷን አንድ በአንድ ከሰማሁ በኋላ ፣ የኔንም እንዲሁ ነገርኳት።እንደምልክት አገላለጿ በጣም ውብ ልጅ እንደምትመስል ገምቻለው ።ነገር ግን ከዚህ በፊት ያየኋት ትሆናለች የሚል ሀሳብ አልነበረኝም።

ይቀጥላል

Like 👍 Like 👍

አስተያየት ካሎ በ @atronosebot አድርሱን
👍13
#ማፍቀር_ወይስ_መለየት(የመጨረሻ ክፍል)
:
..ሰአቴን አስር ጊዜ አያለው፤ከካፌው በረንዳ ላይ ሆኜ ሜሮን ምን ልትመስል እንደምትችል አሰላስላለው።ፍርሃቴም እንዳለ ነው።አይኔ ግራና ቀኙን ካሁን ካሁን መጣች በሚል ያለመታከት ይማትራል።ብዙ ሴቶች ሲያልፉ እያየሁ እደነግጣለው።በተለይ አንዷማ ራሷ መስላኝ ከመቀመጫዬ ብድግ ለማለት ምንም አልቀረኝ።መልሼ ደግሞ ሰአቱ እየገፋ ሲሄድ የምሞኝ መሰለኝ።
<<ቆይ እስቲ አንድ ሰው እየተጫወተብኝ ቢሆንስ?>> እያልኩ እራሴን በጥርጣሬ እሞግታለሁ ።

ብዙም አልቆየ አይኔ ሳያስበዉ ከአንድ ሰው አይን ጋር ተጋጨ።ሁሉ ነገር በሰከንድ ውስጥ ተቀያየረ።
ዞማ ፀጉር፣ጠይም መልከመልካም፣ቁመናዋ የሚማርክ በተለይ አይኗ! ምንም እንኳን በትክክል ምልክቶቿን ብታሟላም፣እርሷም ቢሆን ወደኔ እየቀረበች ቢሆንም እሷናት ብዬ ለማመን አልቻልኩም ነበር።

<<ባልሳሳት ናሆም የምትባል አንተ ነህ?>>
በካፌ ውስጥ ብዙ ወንዶች እያሉ እኔን ለይታ ማወቋ ገርሞኛል።
<<አልተሳሳትሽም . . .እራስሽ ነሽ ግን?>>
<<አይ እህቷ ነኝ!>> ስትል ቀለደችብኝ።
ፈገግታዋ ልዩ ነበር።
ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው ጉንጭ ለጉንጭ ተሳሳምን።
የካፌው ሰዎች ሁሉ ወደኛ በመመልከታቸው ኩራት ኩራት አለኝ።
እንድትቀመጥ ከጋበዝኳት በኋላ አስተናጋጁን ጠራሁት።
<<. . . እሺ አስታወስከኝ ?>> በአትኩሮት እያየችኝ ነበር።
<<አረ በፍፁም!ለመሆኑ እንዳንቺ አይነት ሰው እዚህ ከተማ አለ?>>
<<እኔም እንዳተው ነኝ ግን እርገጠኛ አይደለሁም እንጂ መልክህ አዲስ አልሆነብኝም>>
<<ታድያ ስልኩ ከየት ተፃፈ ይባላል?>>
<<እኔም ደንቆኛል...ምን አልባት መንገድ ላይ ይሆን?>>
<<የምታስታውሽው አጋጣሚ አለ?>>
<<ኦው . . ይከብዳል ።>>
<<በርግጥ ልክ ነሽ . . .የእግዜር ስራ ይገርማል።>>
ለጥቂት ሰኮንዶች ዝምታ ሰፈነ።በካፌው ውስጥ ለስለስ ብሎ የኤፍሬም የድሮ ዜማ ተከፍቷል።ትንሽ እንደቆየን ፀጥታውን ሰብርን ስለየግል ህይወታችን ፣ስለመሀበራዊ ጉዳይ መጨዋወት ጀመርን።ቀስ በቀስ ፍርሀቴ ተጠራርጎ ወጣና ስለምንወደውና ትርፍ ጊዜን ስለምናሳልፍበት ሁኔታ ሳይቀር ተነጋግርን።በደቂቃ ውስጥም አንድ ስንሆን ተሰማኝ።ፍቅር እንዳይዘኝም ሰጋሁ።ግን ፈርቼም እንደማይቀርልኝ አውቃለው።ብቻ ቆይታችን በጣም ስለተመቸኝ ጊዜው እንዳይሮጥ አምላኬን ተማፀንኩት።ንግግሯም ጣፋጭ ስለነበር ፈፅሞ ፀጥታ እንዲገባ እድል አልሰጠሁም።
<<ጓደኛ አለሽ >> የሚለው ጥያቄ በውስጤ ይብሰለሰል ነበር።ነገር ግን መቸኮሉ ጥሩ እንዳልሆነ አሰብኩ።እንዲህ እንዲህ እያልን ከምሽቱ አንድ ሰአት ሲሆን ሂሳብ ከፈልኩና ከካፌው ወጥተን በእግራችን የፒያሳን ጎዳናን ማቋራጥ ጀመርን።
ምሽቱ ለኔ ውድና መቼም ልረሳው የማልችለው ትዝታን እንደጫረብኝ እርግጠኛ ነበርኩ
ለሷም ቢሆን ከዚህ የተለየ ይሆናል ብዬ አለገምትም።
<<ትላንት ለምንድን ነው ስልኩን የከለከልሽን>>
<<አልተረዳክኝም ማለት ነው>>
<<አዎ ምንም ግልፅ አልሆነኝም።>>
<<ቆይ እንግርሀለው>>
<<መቼ?>>
<<አሁን>>
<<አሁን እኮ አሁን ነው>>
<<ትንሽ ቆይቶ አሁን?>>
ምን እንደሆነ አላውቅም ልቤ ስጋት እየተሰማው እጅ ለእጅ እንደተያያዝን ከሰፈሯ ደረሰን።መለያየታችንም ግድ ነውና ካንድ ቦታ ቆም ብለን ፊት ለፊት በስስት ተያየን።
<<ልንለያይ ነው ማለት ነው?>>አልኳት በሀዘን
<< ምን ይደረግ>>
<<መቼ እንገናኛለን?>>
<<መቼም. . .።>>
<<ለምን?>>
ዝምት ሰፈነ።አምላኬን <<እባክህ ፈጣርዬ ሆይ የሰጠከኝን እድል መልሰህ እንዳትነፍገኝ>> ስል ተማፀንኩት።
<<ይቅርታ አድርግልኝ ናሆም በሰልክ ያልነገርኩክ ድምፅህ እንዲሁም ብስለትክ ሰለማረከኝ ሳላይህ አልሄድም ብዬ ነዉ።ከነገ ወድያ ለኑሮ አባቴ ጋር ወደ ካናዳ መሄዴ ነዉ።እስካሁንም ያልነገርኩህ ጫወታችን እንዳይቀዘቅዝ ሰግቼ ነው። >>
<<. . .ምን! . . . እየቀለድሽ ነው? >>
ነገሮች ሁሉ ሲገለባበጡ ተሰማኝ።የምሰማውን ማመን አቃተኝ።
የሰጋሁት ነገር እውን መሆኑን ስረዳ ተናደድኩ።ህልምም መስሎኝ ለመባነን ቃጣኝ።
<<እየቀለድኩ አደለም ናሆም፤ባንተ ውስጥ ያለው ስሜት በኔም ውስጥ እንዳለ እወቅልኝ። ስልኩን የደወልኩልህ ከስልክ ደብተሬ ላይ ያሉትን ወዳጆቼን ሁሉ ተሰናብቼ የቀረኝ ያንተ ብቻ ነበር። እኔም ቅር እያለኝ ከምሄድ ብዬ ነው የደወልኩት>>
<<ልክ አይደለሽም. . .።>> ሀሞቴ ፍስስ እንዳለ ነበር።
<<እንዴት ናሆም?>>
መልስ መስጠት ከበደኝ፤አንደበቴም ተሳሰረ።ምን እየሆነ እንዳለ፤ምን እንደማደርግ ሁሉ ግራ ገባኝ።ትንሽ እንደቆየን ከሜሮን ጋርም ምንም የቀረኝ ነገር እንደሌለ ተረዳሁ።የመጨረሻ የምትሆነኝን ቃል እንደምንም አምጬ ሰነዘርኩለት።
<<እስቲ አሁን ምን አለበት . .ሳትደውዪ ዝም ብለሽ ብትሄጂ !?. . .>>
ሳልሰናበታት ከቆመችበት ጥያት ወደ ቤቴ ማዝገሜን ቀጠልኩ።
አይኔ ላይ ብዥ ብዥ እያለብኝ ትንሽ እንደተጓዝኩ ከኋላዬ ደርሳ እጄን አጥብቃ ያዘችው።
<<እባክህን ናሆም ተረዳኝ . . .እኔ ምን አጠፋው ምንስ ማድረግ ነበረብኝ። ይሉቁንስ እግዜር ያለመክናይት አላገናኘንምና ልነደሰት ይገባናል።>>
መልስ አልሰጠኋትም።አይኖቼ አይኖቿን ሲመለከቱ ፈዝዤ ቀረሁ ።በዛ ምሽት እንደኮብ ያበራሉ።የምሰማው ድምፅዋ በደምስሬ ሰርፆ መንፈሴን ሲያድሰው ተሰማኝ ።እኔም ከፊትዋ ቆሜ አይን አይኖን እያየው አዳምጣታለው መልስ መስጠት ግን አልፈለኩም።
<<ተረዳከኝ ?ሆን ብዬ ያደረኩት አይደለም።ለምንስ ሆን ብዬ አደርጋለው።ልክ እንዳተው ሁሉ የስልክ ቁጥሩ ሚስጥር ለኔም ሚስጥር ነው። ደግሞ እግዜር በፈጠረው አጋጣሚ አትማረር፤ ሁሉም ለበጎ ነውና።. . .ተናገር እንጂ ለምን ዝም ትላለህ ? በዚ ላይ ስሜታችን አንድ እንደሆነ እገምታለሁ።>>
በረጅሙ ተነፈስኩና ለደቂቃ ሰማይ ሰማዩን ስመለከት ጨረቃን አገኘኋት።በትዝብት ተመለከትኳት።ከዛም ወደራሴ ተመለስኩና በርጋታ ማሰላሰል ጀመርኩ።ምንም እንኳን አጋጣሚው አስገራሚና አሳዛኝ እንዲሁም የማይታመን ቢሆንም፤እውነታውን ተቀብዬ በሰላም መለያየቱ ጥሩ እንደሚሆን አሰብኩ።ሜሮን ላይም ምንም ስህተት ፈልጌ አጣው።
<<ማክሰኞ ጠዋት ነው የምትሄጂው?>>
<<አዎን>>
<<ታድያ ለምን አልሸኝሽም?>>
<<አይሆንም ከቤተሰብ ጋር ስለሆንኩ እንደገና መጨነቅ የለብንም። እዛው እንደደረስኩ በደቂቃ ውስጥ እደውልልካለው >>
<<እርግጠኛ ነሽ?>>
<<አትጠራጠር ላንተ ሳይሆን ለራሴ ስል ነው የምደውለው።>>
<<እጠብቃለው።>>
<<በቃ ደህና ሁን፤በግዜ ቤትክ ግባ።>>
እቅፏ ውስጥ ስታስገባኝ ይባስ ነፍሴ ተደሰተች።ጠረንዋ ካፋንጫዬ ሲቀር ታወቀኝ።ጡቶቿ ከደረቴ ጋር ሲነካኩ ስሜቴ ጣርያ ደርሶ ተመለሰ።በረጅሙ ተነፈስኩና ዳግም የምነገናኝበትን ቀን መናፈቅ ጀመርኩ።
አንድ ነገር ተሰማኝ....አዲስ ህይወት፤አዲስ እስትንፋስ፤ዳግም ውልደት....ግን ምን ያደርጋል የወደድኳት ለት ተለየኋት.....የናፍቆቷን ኑሮ ''ሀ'' ብዬ ልጀምር ነው።

▪️▪️▪️▪️
👍82