አትሮኖስ
280K subscribers
113 photos
3 videos
41 files
475 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_ሦስት

....ዩኒቨርስቲ ውስጥ የነበረኝ ሕይወት የአንድ መልካም ተረት ፍፃሜ ይመስል ነበር፡፡ ልክ
ከዛም በሰላምና በደስታ ይኖሩ ጀመር” ተብሎ እንዳለቀ ተረት፡፡ ብር አልቸገርም ነበር እድሜ
ለዛፒ፡፡ ጊዜ ባገኘሁበት ቀን ሁሉ አቲዬን አያታለሁ፡፡ በየቀኑም እደውላለሁ፡፡ አቲዬን በስልክ
ማውራት ከባድ ነው፡፡ በቃ ጥያቄዎቿ አንድ ዓይነት ናቸው፤ “
እንጀራው ጥሩ ነው ?”፣ “ልብስህ
አልቆሸሽም ?”፣ “ንባብ አታብዛ፣ በጊዜ ተኛ፤ ራስህን ያምህል፣ ማታ ማታ ጋቢ ልበስ፣ አሹ..
ደሞ እጅህን ወጣ ወጣ አታድርግ የሰው ዐይን ጥሩ አይደለም ሁሉንም በጥሞና አዳምጣታለሁ፥
ስለራሷ ስጠይቃት “እኔ ምን አለብኝ ብለህ” ብቻ ነው መልሷ፡፡ አቲዬ የሚያሰቃይ የወገብ ህመም
እንዳለባት እንኳን ያወቅኩት ከተመረቅኩ ከሁለት ዓመት በኋላ ነበር፡፡ እንዳልጨነቅ ደብቃኝ፤
ፍፁም በተረጋጋ ሕይወት ውስጥ ትምህርቴ ላይ ብቻ መሉ ሐሳቤን ሰብስቤ እንዳጠና:: የሰው አፈጣጠሩ እየገረመኝ፣ የበሽታ መከሰቻው ምክንያት ብዛት እና መነገድ እያስደነቀኝ፣ ለዛውም የሰው ልጅ ምህረቱ ባይበዛለት በቀናት እድሜ ከምድር ተጠራርጎ የሚጠፋ ትበያ መሆኑ እያስደመመኝ፣ ሰው የምጠላው እኔ የሰው ጠላት የሆነ በሽታ ጋር ድብብቆሽ ስጫወት ወደ መመረቂያዬ ተቃረብኩ፡፡

ሴት አይቀርብም" ይሉኛል፡፡ ይሄም እንደ ጨዋነት ተቆጥሮልኝ ነበር፡፡ እኔ ባጠቃላይ ሰው
ነው የማልቀርበው፡፡ ለምን ለይተው፣ “ሴት አይቅርብም' እንደሚሉኝ ይገርመኛል፡፡ ሲጀመር
ማንም ጋር የሚያገናኘኝ የትምህርትና መሰል ጉዳዮች ከሴትም ይሁን ከወንድ ርቄ አላውቅም፡፡

ዩኒቨርስቲ ውስጥ ለዛውም የሕክምና ትምህርት ላይ ብቸኛ መሆን ቀላል ነገር አይደለም፡፡
ቢሆንም ከማይረባ መጠላለፍና በሕይወቴ አንድ እርምጃ እልፍ በማያደርገኝ ጉዳይ ውስጥ ገብቼ
የመዳከር ፍላጎቱ አልነበረኝም፡፡ ለምሳሌ ፆታዊ ፍቅር !! ወንድ እና ሴት ቆመው ወይም አንድ
ጥግ ተቀምጠው ያንን ሁሉ ሰዓት ሲቆዩ ምን ጉድ እንደሚያውሩ ይገርመኛል፡፡ ፍቅር ለምን
አይይዘኝም ብዬ ያሰብኩት አንዲት ልጅ እንዳፈቀረችኝ የነገረችኝ ጊዜ ነው፡፡ ማህሌት ነው
ስሟ መጀመሪያ ስታፈጥብኝ አጋጣሚ መስሎኝ ነበር፣ ሲደጋጋም የሆነ ነገር ፈልጋ ይሆናል ብዬ ችላ አልኩት። ከዛ ከበበችኝ፡፡ አየር ሆነች፡፡ ላይብረሪ ካለሁ አለች፡፡ የሆነ ቦታ ከተቀመጥኩ ከሆነ ቦታው ፊትለፊት፣ ከኋላ ወይም ከጎን አለች። ባለፍኩበት ታጋጥመኛለች፡፡ ከሰላሳ መንታ
እህቶቿ ጋር ወደ ዩኒቨርስቲው አብራ የገባች እስኪመስለኝ በዛችብኝ፡፡ በመጨረሻ ወደድኩህ
አለችኝና እርፍ !!

እንደው አጋጣሚውን አልለፈው ምንስ ኣባቴ ቢክደኝ ባባቴ ወንድ አይደለሁ አልኩና ልሞክር
ወሰንኩ፡ ግን ልጅቱ በቀጣዩ ቀን ሰለቸችኝ !!

በቃ እግዚኣብሔርን ባፈቅር ይሻላል የሴት ፍቅር አያዋጣም' አልኩ፡፡ ሳይቆይ ግን ዓለም እግዜርን የሚያፈቅርበት አካሄድ እኔ ከማፈቅርበት ጋር አልገጥም አለኝ፡፡ አንድ እግዜርን በስንት መንገድ እንደሚያፈቅሩት ስመለከት አፈቃቀሬ የተሳሳተ ይሆን እንዴ ብዬ ፈራሁ፡፡

አንድ ቀን ከግቢ ወጥቼ የተማሪው ኪስ ሞላ ሲል የሚያዘወትራት ሬስቶራንት ሄድኩ፡፡ ምሳዬን
ኣዝዤ ስጠብቅ የዲፓርትመንቴ ልጆች መጡና ፊት ለፊት ተቀመጡ ሦስት ሴታች፡፡ ብዙ
ሴቶች ሲሰበሰቡ ኀብረተሰቡ የጫነባቸውን የፆታ ተፅእኖ ቀንበር የሰበሩት ይመስላቸዋል መሰል
ድፍረት ይጨምራሉ ጮክ ብለው ማውራት መሳቅ ምናምን…፡፡

ያዘዝኩት ምግብ ጭሱን እያግተለተለ መጣ፡፡ አስተናጋጇ ገነትን በስሀን ይዛልኝ የመጣች ነው የመሰለኝ፡፡ ርቦኝ ስለነበረ የምግቡ ሽታ የተለየ ሆንብኝ፡፡ አንገቴን ዝቅ እድርጌ ዐይኖቼን ጨፈንኩ፣ጸሎት ይመስላል፡ ግን አልነበረም:: በጭራሽ ! መቼ እንደጀመርኩት ባላስታውስም፡ በተለይ ርቦኝ የሚበላ ነገር ሳገኝ፡ ደሰ የሚል ምግብ ሲቀርብልኝ ሁልጊዜም እንዲህ አደርጋለሁ፡፡ ጥልቅ የሆነ ስሜት ውስጤን ይሞላውና የሚያስገርም የአፍታ ዝምታ ውስጥ እገባለሁ፡፡ ለሞተው
የረሀብ ዘመኔ አጭር የህሊና ጸሎት !

ቀና ስል ሴቶቹ በግርምት አፋቸውን ከፍተው ያዩኛል፡፡ ፊታቸው ላይ ማክበር፡ መቀራረብ መፈለግ ነበር፡፡ ልክ እንደማላውቃቸው ሰዎች ችላ ብያቸው መብላት ጀመርኩ። በልቼ እንደጨረስኩ ቡና አዘዝኩ፡፡ እንዷ ወደኔ መጣች…ኤጭጭጭጭ !

“ሰላም ላንተ ይሁን፣ አሸብር!”

“ሃይ” አልኳት ባጭሩ፣ ስናገር ሊያገሳኝ ነበር፡፡

“መቀመጥ ይቻላል ?” አለች ለመቀመጥ መንገድ ጀምራ፡፡ ከዛም እንደ እኔ ቡና አዘዘችና ወሬ
ጀመረች፡፡ “ስታመሰግን አየንህ ክርስቲያን እንደሆክ አናውቅም ነበር” አለች ፈገግታዋ ፊቷ ላይ እየተንተገተግ፣
አልመሰስኩሳትም፡፡

“ፈሎሽፕ አለን ብንጋብዝህህህ ደስ ይለኛል፡፡ በቃ አብረን ጌታን ማምለክ ነው አላማው፡፡ ዕሮብና
ቅዳሜ ከሰዓት ነው ፕሮግራሙ” የሆነች ወረቀት ሰጠችኝና አመሰግናኝ ቡናዋን ሳታጋምሰው
ሄደች፡፡ ከጓደኞቿ ጋር ተያይዘው ወጡ፡፡ ተመራርጠው ጓደኛ የሆኑ ይመስል ሦስቱም በቁመትም
በቅጥነትም አንድ ዓይነት ነበሩ፡፡

እንግዲህ ይሄ ምግብ ሲቀርብ ማቀርቀሬ ነው የአብረን እናምልክ!” ግብዣ ያመጣብኝ፣ ወላ ያመጣልኝ፡፡ ዝም ብዬ ሳስብ ከእነዚህ ልጆች ጋር እንዴት ነው በጋራ የምናመልከው?" ብዬ
ገረመኝ፤ እኔ ለየትኛውም እምነት፣ ለየትኛውም አምልኮ ግድ ያለኝ ሰው አይደለሁም፡፡ በሕይወቴ
ሙሉ የፀለይኩበት ቀን ኖሮ አያውቅም፡፡ እግዚአብሔር የእኔ ብቻ ስለሚመስለኝ ሌሎች ጋር
በጋራ ማምለኩም፣ መዘመሩም ምኑም ትዝ ብሎኝ አያውቅም፡፡
እግዚእብሔር እኔ ጋር በመተባበር አዲስ አበባን ድራሽዋን ለማጥፋት እስከመረቅ እየጠበቀኝ
አልያም እንደ ኖህና ቤተሰቡ እኔና አቲዬ ወደ መርከበ እንድንገባ ፈልጎ የጥፋት ውሀውን
ያዘገየው ስሰሚመስለኝ ማንም ጋር ማምለክ ፈልጌ አላውቅም፡፡ ስለዚህ ቀተጋበዝኩበት ቀን
ቀረሁ፡፡ ንዝንዛቸው ግን መቆሚያ መቀመጫ ኣሳጣኝ፡፡ አንድ ቀን፣ “ይቅርታ የምትሉቀት ቦታ
መሄድ ስለማልፈልግ ካሁን በኋላ በዚሁ ብናቆም' አልኳት አንዷን በቁጣ፡፡

አዎ ተቆጥቼ ነበር " እግዚአብሄርን በምቾት የሚያውቁት ሞልቃቆች የቻፕስቲክ መግዣ ሲያጡ፣
“አግዚአብሔር ማነው?” የሚሉ..እግዚአብሄርን እንዲያስተዋውቁኝ አልፈልግም፡፡ አይቻቸዋለሁ በዩኒቨርስቲ ቆይታዬ፣ ዶሮ ሦስት ጊዜ ሳይጮህ ጴጥሮስ ጌታን ሦስት ጊዜ እንደካደው የሚያትት መዝሙር እያንጎራጎሩ እነሱ ራሳቸው የሃብታም መኪና ጡሩንባ ባምባረቀ ቁጥር ከራሳቸው ሰላሳ ጊዜ ሲካካዱ፡፡ አይቻቸዋለሁ
የጌታ የማዳን ድንበር አቃቂና ኮተቤ ድረስ ብቻ ይመስል የአዲስ አበባ ልጆች ብቻ ተጠራርተው፤ “በጌታ ፍቅር” ምሳ ሲገባበዙ፣ ቸርች ሲሄዱ - የፅንፍየለሽ ከታማያዊ ዘረኝነት የሚነበብ ነገር ሲዋዋሱ፡፡አይቻቸዋለው በየእምነቱ ተቧድነው ሲናቆሩ ሲጠዛጠዙ፡፡ እኔ እና እናቴ እግዚእብሄርን ገደል ጫፍ ላይ እንደተንጠለጠለ ገመድ የሙጥኝ ብለን ሕዝብ ከዛ ከዚህ ሲገፋን፣ ድህነት እጃችንን እየቀጠቀጠ የመዳኛ ገመዳችንን ሊያስለቅቀን ሲታገል፣አንለቅም" ብለን የተረፍን ሚስኪኖች ነን፡፡ ሰው አትመልከት እግዜርን እንጂ” ይሉኛል፣
አብረን እናምልክ! ብሎ ጠርቶ 'ሰው አትመልከት፣ ማለት ምንድን ነው?
👍39