አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
479 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#አስራ_ሁለት


...ጠላትህ የትም የሚገኝ እንደ ትቢያ እያፈስክ የትም የምትበትነው ገላባ ነው። አስተማሪ ብትሆን ከጠመኔህ ስር ጠላትህ አለ። ጥላቻ አእምሮው ውስጥ እየዘራህ ሰይጣን ታፈራለህ፡፡ ሹፌር ብትሆን የጠላትህ ነፍስ በእጅህ ነው፣ ይዘኸው ገደል ልትገባ ትችላለህ፡፡ ግንበኛ ወላ አናፂ ብትሆን
ምትሰራለት ቤት በላዩ ላይ ፈርሶ እንዲቀብረው የማድረግ ስልጣን በእጅህ ነው፡፡ ባለሰልጣን ከሆንክማ፥ እባቡም ከእግርህ፣ ዱላውም ከእጅህ ብትፈልግ ቀይሽብር ወንጀለኛ' ምናምን
ቅብርጥስ ብለህ በየመንገዱ ትደፋዋለህ፡፡ ካሻህ እድሜ ልኩን በድህነት እንዲማቅቅ ታደርገዋለህ፡፡

ደግሞ ለበቀልህ ማን ይተባበረኛል?' ብለህ አትሰጋም፣ ሕዝቡ ራሱ ለመባረክ ስትቆም ነጠላውን አጣፍቶ ከጎንህ ነው፡፡ ለማረድ ስትቆምም ቢላውን ስሎ ከጎንህ ነው፡፡ ከሌላ ዓለም ረዳት
መጥራት ሳያሻህ፤ ወንድሙ ላይ የሚጨከን ፈሪሃ እግዚአብሄር ያለው ሕዝብ ጠላትህ ከሆነ
አደግድጎ ለበቀልህ ታዛዥ ነው

ደነዝ ሕዝብ፣ ደነዝ መሪ እንደሚወልድ እስኪገባው ትጫወትበታለህ፡፡ ጭራቅ ሕዝብ፣ ጭራቅ መሪዎች እንደሚፈለፍል እስኪያውቅ ታሸዋለህ፡፡ አዎ ጠላትህ ሕዝብ ከሆነ በቀልህ ቦታ እና ጊዜ ሳይመርጥ የትም ሊፈፀም ይችላል፡፡ ደግሞ ታዝበህ ከሆነ ከልብህ የሕዝብ ጠላት ከሆንክ ሕዝብ ይወድሃል፡፡ ስላንተ ይዘምራል፡፡ ጀግና! እያለ ሲያወሳህ ይኖራል፡፡ ለምን መሰለህ፤
ውስጡ ያለው ጭካኔ ነው በአደባባይ ያሳየኸው !

ወዳጁን እየካደና እየቀረጠፈ ውለታውን ትቢያ የሚያለብስ ሕዝብ የትናቴን ጉልበት እንደምስጥ መጥጦ እንጨቷን አስቀረ ብዪ አላዝንም፡፡ ሰው እሆናለሁ፡፡ በእኔ ሰው መሆን ትላንት ፍሬ የምትሰጥ ለምለም ዛፍ የነበረች ሕዝብ ያደረቃት እናት የምትባል እንጨት ከማገዶነት አፋፍ ተመልሳ እንደ እሴይ በትር ትለመልማለች፡፡

ያኔ በልጅ ልጆቿ ልብ ውስጥ ከቅዱስቅዱሳኑ ለዘላለም በከብር ትቀመጣላች፡፡ ቱ! አሸብር
አይደለሁማ !

አዎ ታጋይ ነኝ !! ታጋይ በሴት አይፈትንም፡፡ ሴቷ ቀይ እግር ቢኖራትም፤ አይኗ ቢያምርም፣
ተንጠራርታ ብትስምም፣ ስሟ ዮርዳኖስ ቢሆንም፣ ማታ ማታ ትዝ ብትልም፣ ከነድሪቶቹ
ብትቀርበኝም የጠላት ልጅ ያው ጠላት ነው !! ዮርዳኖስን ርግፍ አድርጌ ተውኳት !

ከባድ አልነበረም፡፡ እንዲያውም ዐይኔን ስገልጥ ዮርዳኖስ ለእኔ ሸክም ነበረች፡፡

በብልጣ ብልጥ ሴትነት ነገን አሻግራ ያየች፣ መረቧን ተሽክማ ግራ በገባው አሳ ዙሪያ የምትሸከረከር ብልጥ ሴት፡፡ እሾሁን አራግፋ ልትቀረጥፈው !! ተውኳት፡፡

“ልብሱን ሲቀይር ተወኝ አለች ተባለ፤ እሷ የድሮ ልብሷን የሆነች ይመስል፡፡ ብዙ ፆታዊ
ግንኙነቶች ላይ ኣለመፈለግ ክህደት ተደርጎ ይታያል፡፡

አስራ ሁለተኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት አምጥተው ዩኒቨርስቲ ሲገሱ ከትዘጋጁ ጥቂት ተማሪዎች
መካከል አንዱ እኔ ነበርኩ አራት ነጥብ : አራት ነጥብ የሚባል አንድ ጠመንጃ ይዤ ለትጥቅ
ትግል ዩኒቨርስቲ ወደሚባል ጫካ ልዘምት ተዘጋጀሁ፡፡

ዛፒ እንጅ የናጠ የሃብታም ልጅ ሊኖረው ከሚችለው በላይ ልብስና ጫማ፣ ለሎችም ቁሳቁሶችን
ከአገር ዉስጥ ብቻ ሳይሆን ከቤተሰቦቿም ጭምር አስመጥታ አምባሻበሻኝ፡፡ ምርር ያለ ቤተሰባዊ ፍቅር ውስጥ ገብተን ነበር፡፡ ዕይኗ ይወደኝ ነበረ ያስታውቃል፡፡ በተለይ አስራ ሁለተኛ ከፍል ተፈትኜ ውጤት ስጠብቅ ከዛፒ ጋር ያሳለፍነው ጊዜ የማይረሳ ነበረ፡፡
ያልዞርንበት መዝናኛ አልነበረም፡፡ የትም ስትሄድ ከ አለሁ፡፡ እኔን “ወንድሜ ብላ ማስተዋወቅ
እንዴት እንደሚያኮራት ዐይቼ ራሴን ለወንድምነት አሳልፌ ሰጥቻለሁ፡፡ የእውነትም ደግሞ
ወንድሟ እመስል ነበረ፡፡ ዛፒ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለአቲዬም ደግነቷ ተንሰራፍቶ ነበር፡፡ ማታ
ማታ ቡና ተፈልቶ በረንዳ ላይ ወይም ሳሎን ደስ የሚል ጊዜ ሦስታችንም እናሳልፋለን፡፡

ዛፒን ከምቾት ጋር ያገለለ ዓለም እኔና አቲዬንም ከጉስቁልና ጋር የተፋ ሕይወት በምን ሂሳብ
እንዳቀሳቀሰን ባይገባኝም ቅልቅሉ ግን ከልብ የሆነ ቤተሰባዊ ትስስርን ፈጥሮ ነበረ፡፡

አንድቀን “አቲዩ!አልኳት፣

“አቤት!”

“ምን ብሆን ደስ ይልሻል?”

“ኧረ እኔ ምን አውቄ፣ እኔ ትምርት የለኝ አላቀው“ ብላ ሳቀች፡፡

“ግዴለሽም ተምሬ እኔ ልጅሽ ምን ብሆንልሽ ደስ ይልሻል?”

“እሷን አማክራት እስቲ“ አለችኝ ዛፒን ማለቷ ነበር፡፡

“አቲ ዛሬ ካልነገርሽኝ አልለቅሽም ራስሽ ንገሪኝ"

ትንሽ አሰበችና፣ “ዶፍተር” አለችኝ በሳቅ፡፡ ሁለታችንም ባሳቅ ፍርስስስስ አልን።

አነጋገሯ በዕርግጥም ያስቅ ነበር፡፡ ህክምና የመማሬ ብቸኛ ምከንያት ይሄው ነው!! ሕዝቤንና
ውገኔን ከበሽታ ለመታደግ ምናምን በዬ አልነበረም!! እናቴ፣ የምወዳት እናቴ፡ የእዕምሮዋ ጥግ
የታላቅነት መጨረሻ የመሰላትን ነገር ለመሆን እንጂ!!

የዩኒቨርስቲ ቆይታዬ የደስታና የቅንጦት ነበረ፡፡ ዛፒ ውብ ሆና ግቢ ስትመጣ ዐይኑን የማይጥልባት ተማሪ አልነበረም፡፡ ብዙ ሰው እናቴ ያደርጋት ነበረ፡፡ ሴቶቹ የዛፒ ጫማና ልብስ ላይ ዐይናቸው ይጎለጎላል፡፡ ከዚህ የቆንጆ ዘር በረከቱን ሊካፈሉ የቋመጡ፣ በስልምልም ዐይን፣ በጨዋ መሳይ ፈገግታ ሲቀርቡኝ ሲዞሩኝ ነበር፡፡ 'ፀዳ ያለ ልጅ ይሉኛል፡፡ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ! አላልኳችሁም፣በድፍን ግምት ወደድን ብለው ከሰልፍ ሊያስወጡ መሞከር ይሄ ነው እኮ፣

የወደዱኝን ያከበሩኝን ሁሉ ቁምነገር ባለመቁጠር በቀሌን አንድ ብዬ ጀመርኩ፡፡ ኮተታሞቹ
የግቢ ልጆት ራሳቸውን ችለው መቆም ይፈራሉ፡፡ ሴቶቹ ወንድ ታዛ ስር ካልተጠለሉ ሰው የሆኑ
አይመስላቸውም፡፡ ወንዶቹ የተፈጥሮን ጾታዊ መፈላለግ
ሳይንስ ሊያደርጉት ጅራት ሲቆሉ፣ ግራ የገባቸው የከተማ ልጆች ጭልጥ ወዳለው ማሕበራዊ እንስሳነት ሲወርዱ፣ በግቢያችን ውስጥ እንደሰው መኖርን ያጣጣምኳት እኔ ከፍ ባለ ክብር እየተማርኩ ሁሉንም ተማሪ ፅንፍ በሌለውጥላቻና ንቀት እመለከት ነበረ፡፡

የናቀውን የሚወድ ሕዝብ ግን ከጎኔ ነበር! አሹዬ፣ እሹጎት፣ ሹ፣ .ሸቢ፣ ሹሹ፣ ከቤተሰቦቻቸው
የወረሱት እባብነት የስም ግንድ ላይ ሲጠመጠም ላለመነደፍ ልቤን ቆዳ አልብሼው ነበረ፡፡
ማቆላመጥ የሚወድ ሰው ጤነኛ አይመስለኝም፡፡ አጭበርባሪ ነጋዴ ነው የሚመስለኝ። በየስሙ ላይ ዬ' መለደፍ የፍቅር ሃዋሪያ መሆን ይመስላቸዋል፡፡

የቤተሰቦቻቸው መርዝ አልሰራ ሲል፣ (የተመረተበት ጊዜ አልፎ እንዳይሆን ሰግተው) ከፊልምም
ከመጽሄትም አዳዲስ መርዝ እየተሸከሙ ብቅ ይላሉ፡፡ በአነጋገር፣ በአለባበስ፣ በአስተያየት፣ በእግር፣ በዳሌ፣ በጣት፣ በፀጉር እናም በመጨረሻ በሃሜት፣ “ይሄ ልጅ ሴት አይመቸውም እንዴ? ማን ያውቃል? ዘመኑ ክፉ ነው እናትዬ፣ እንትን እንዳይሆን::

እነሱ ጋር ያልሆነ፣ እነሱን ያልፈለገ ጭራ አለው፤ ደብቆት ነው እንጂ፡፡ ቀንድ አለው፣ ጥፍር አለው፡፡ በዚህች ምድር ላይ እንደመናቅ የሚያም ነገር የለም፡፡ ንቀቴ አመማቸው !!

ቡምምምምምምምምም እውነት ፈነዳ !! “ይሄ ቀብራራ እዚህ ይኮፈሳል እናቱ እኝጀራ ጋጋሪ፣
ልብስ አጣቢ ነች አሉ”፡፡ ጮማ ወሬ ተገኘ፡፡ ዳሌያቸውን እየናጠጡ ፀጉራቸውን እየነሰነሱ፣ ጅራታቸውን ከሚቆሉላቸው ወንዶቻቸው ጋር አወሩ፡፡ ተሳለቁ፡፡ ሲያሸማቅቁኝ ሞከሩ፡ ራሳቸውን
ችለው መቆም ሲፈሩ፣ የእፉኝት ልጆች በልብስ አጣቢ ልጅ ሳቁ፡፡ የቤታቸውን አጠራቅመው
ለዘመን መለወጫ ቤታቸውን የሚያፀዱ ሁሉ፣ ሰው ሰራሽ ጠጉራቸው ራሳቸው ላይ ጀልቶ በጾም በጸሎት የሚፈታ ሁሉ፣ ተብረቅርቀው ሰው ነን ሊሉ፡፡ ልክ ለልክ ከተዋወቅን ቆየና ይሄም ጥይታቸው ከሸፈ፡፡
👍383👎1🥰1