አትሮኖስ
281K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
482 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ዶክተር_አሸብር


#በአሌክስ_አብርሃም


#ዘጠኝ

የአስቴር ትልቋ ልጅ ዛፒ ትባላለች፡፡ ትርጉሙ ምን እንደሆነ አላውቅም፡፡ ምናልባትም 'ሰይጣናዊ መዝገበ ቃላት የሚባል ነገር ካለ፣ ትክከለኛ ትርጕሙ እዛ ላይ ሳገኝ አይቀርም፡፡ እስከዛው
ግን በግምት “ዋጋ ቢስ' ብዬ ተርጉሜዋለሁ።

ዘር ከልጓም ይስባል እንዲሉ ቁርጥ እናቷን (ለነገሩ አባቷን የት አውቄው?)እኔ ከስምንተኛ ክፍል
ወደ ዘጠነኛ ክፍል ሳልፍ እሷ የሀያ አምሰት ወይም የሀያ ስድስት ዓመት ወጣት ነበረች፥ ተስፋ
የቆረጠች ወጣት፡፡ እናቷ አስቴርና ትንሽ እህቷ ጓዛቸውን ጠቅልለው ወደ ውጭ አገር ሲመለሱ
እሷ እዚሁ እኛ የነበርንበት ግቢ ውስጥ ከንድ ደስ የሚል የተረጋጋ ወጣት ጋር መኖር ጀመረች፣

ምናልባት እዚሁ የቀረችው ልጁን ስለወደደችው ይሆናል፡፡

መጀመሪያ መኪናውን ውጭ ጋር ያቆምና ተያይዘው ይሄዱ ነበር፡፡ ከመሄዳቸው በፊት ዋጋ ቢሷ ትጠራኝና አሸብር ኛ እችን መኪና ወልውል!” ትላለች፡፡

ዛፒዩ አሁን እኮ ነው ያሳጠብኳት!” ይላታል፡፡ እርሱ የዋጋ ቢሷ መልዕክት ተንቀጥቅጦ
የሚታዘዛት ሚስኪን መኖሩን ማሳየት መሆኑን መቼ አውቆ፡፡

ቆይታ እቤት እየገባ መቆየት ጀመረ፡፡

“አሽብር ና ለስላሳ ግዛ! ና ቢራ ግዛ” ብታምኑም ባታምኑም ኮንዶም ሁሉ ታስገዛኝ ነበር፡፡
መላላኬ ሳይሆን በዛ እድሜ ፋርማሲ ሂዶ ኮንዶም መግዛት ያሳቅቀኝ ነበር፡፡ ፋርማሲስቶቹ
በትዝብት ያዩኛል፣ “የተቀደደ ሱሪውን ሳይቀይር…” በሚል ግርምት…ሱሪው የተቀደደ ሰው
እንትን አያደርግም የተባለ ይመስል፡፡

ከዛ ማደር ጀመሩ፡፡ በጨለማ በዛ በኮረኮንች መንገድ ቢራ ተሽከሜ እጀን የፌስታሉ እጄታ እየከረከረኝ የተላላኩበት ጊዜ መቼም አይረሳኝም (እስከዛሬ እቃ በፌስታል መያዝ አልወድም፡፡ አቲዩ የግቢው በር ላይ ብርድ እያቆራመታት ቆማ ትጠብቀኛለች፤
ገብቼ ቢራውን ስሰጥ ዛፒ ልክ ከፍሪጅ ያወጣችው ያህል ከእጄ ላይ ትወስድና፣ እንካ ሁለት ፓኬት ሮዝማን ግዛና ና” ትላለች፡፡
በመጨረሻ ጠቅልሎ ገባና አብረው መኖር ጀመሩ፡፡ መኪና ማጠብ ቋሚ ስራዬ ሆነ፡፡ እውነቱን
ለመናገር ጥሩ ባል ነበር፡፡ ዋሲሁን ይባላል። ቤቱ የባለትዳር ቤት እንዲመስል የተቻለውን ሁሉ
ይጥር ነበረ፡፡ ዛፒ ግን የሚቋቋማት ዓይነት 'ሚስት አልነበረችም፡፡ ጉራዋ ፀጉር ያስነጫል፣ በውበቷ ስትመካ ልክ የላትም፡፡ የእናቷ ጫማ ውስጥ ዘላ የገባች ጉረኛ ! አቤት ጉረኛ ሴት እንዴት እንደምትቀፍ፡፡ ከምትናገራቸው አስር ዓረፍተ ነገሮች፣ አስራ አንዱ ስለራሷ ውበት፣ ስለቆዳዋ ጥራት፣ ስልጣቶቿ አለንጋነት፣ ስለልብስና ሽቶዎቿ ብራንድ በቀጥታ አልያም በተዘዋዋሪ ይተርካሉ ፡፡

ዘላ የተዘፈቀችበት ትዳር ከጭፈራ ቤት መዳራት በምን እንደሚለይ ገና ያልገባት አካሏ ብቻ
ህሊናዋን ጥሎ ያደገባት ከንቱ ነበረች፡፡ ዋሲሁን ውጭ መመገብ አይወድም፡፡ የታሸጉ ምግቦችን
ገና ሲመለከታቸው ያንገሸግሸዋል፡፡ እንጀራ በሽሮ ወጥ ነፍሱ ነው:፡ ዛፒ ታዲያ ቤት ውስጥ ለባለቤቷ ምግብ አብስሎ ማቅረብን በሴት ልጅ ላይ የሚፈፀም ታላቅ በደል አድርጋ ነበር የምታየው፡፡አበሻ ወንድ ጓዳለጓዳ ካልተንደፋደፈች ሚስቱ ሚስት አትመስለውም፡፡ ሴት አደባባይ መውጣቷ ያማቸዋል” የምትለው ከእናቷ የወረሰችው ዘይቤ አላት፡፡ በጓዳም በአደባባይም ምንም የማትፈይድ የወሬ ቋት፡፡ ኩኪስ አልያም ጭማቂ ነገር ከፍሪጅ ታወጣና ሶፏዋ ላይ እግሯን አጣጥፋ ቴሌቪዥን እያየች ትበላለች፣ ትጠጣለች፡፡ ስለፋሽን ሳታቋርጥ ትቀባጥራለች፤ በዓለም ላይ ስላሉ የቅንጦት ሆቴሎችና ጌጣጌጦች ዋ.….ው” እያለች ትቋምጣለች፡፡ ቤትም የለችም፡ የምትመኘውም ቦታ የለችም፡፡ የትም የሌሎች የውሀ ላይ ኩበት ነገር!!

ዋሲሁን ያደበትን የቤተሰብ ስነስርዓት፣ የኢትዮጵያዊነ ወግ ምሳ ተዘጋጅቶ፣ ቡና ተፈልቶ፣ ቤቱ
ሞቅ ብሎ እንደሚጠብቀው በማመን እንደ ኣባወራ
ምሳ ሰዓት ላይ ሲመጣ ዛፒ ጠረጴዛው ላይ እግሯን ሰቅላ ዙሪያዋን የጥፍር ቀለም ጠርሙሶች ከበዋት ቤቱ በአልኮል ሽታ ታፍኖ ስትቆነጃጅ
ያገኛታል፡፡ ማታ ሲመጣ ዛፒ ለባብሳ ኣንዲወጡ ስትጠብቀው ይደርሳል፡፡

ሀኒ ዎከ እናድርግ ትለዋለች፣ ባል ጋር መታየት እንጂ የባልን መሻት ማየት አልፈጠረባትም፣
የሆሊዉድ ተረቶች ባዶ ጭንቅላቷን ሞልተውት ነበር፡፡ ከንዱን ይዛ መንገድ ላይ ስትውረገረግ ብጤዎቿ፣ “ዋው ምናይነት ጥምረት ነው? ማች ያደርጋሉ" እያሉ ያወሩላታል፡፡
ሚስኪን ዋሲሁን ሳይወድ በግድ እግሩ እስኪቀጥን ሲዞር አምሽቶ እኩለ ሌሊት ላይ ስልችት
ብሎት ይመለሳሉ፡፡ የተሰቀለችበት ባለ ተረከዝ ጫማ ለመራመድ ስለማይመቻት ክንዱ ላይ
ተዘፍዝፋ ትወናገራለች፡፡

“ሃኒ ዲጄው ሽቶሽ ብራንዱ ምንድን ነው?' ሲለኝ ሰምተኸዋል?”

“አልሰማሁትም ይላል ትክት ብሎት፡፡

"ሃሃሃሃሃሃሃ ጠጥተህ ነበር ብዙ.ሰካራም ሃሃሃሃሃ” ትላለች እየተለፉደደች፡፡ አብሯት አይስቅም፡፡

"በናትህ ቀሚሴ ላይ ዋይን ደፋብኝ ያ ወልካፋ አስተናጋጅ" ትላለች ረዥም የራት ቀሚሷን
እያሳየችው::

“ይታጠባል.ደግሞ አንቺ ስታልፊ እኮ ነው የገጨሽው” ይላታል ስልችት ብሎት፡፡

“እዚህ አገር ምን ላውንደሪ አለ? ሰባት መቶ ዶላር የወጣበት ቀሚስ እንደቀልድ - ምን አይነት
አገር ነው? ብላ ቀሚሷ ባአደባባይ ባለመከበሩ አስራ አምስት ቀን ታወራለች፡፡ ስለ ተራ ቀሚስ
ሳይሆን ስለ ባንዲራ መደፈር የምታወራ ነው የምትመስለው::
ጧት ተነስቶ በተሳሳት መንፈስ ወደ ስራ ሲሄድ ዛፒ አትሰማም አትላማም ተኝታለች፡፡ ምሳ
ሰዓት እንደገና ጓደኞቿ ጋር እንደሄደች ትደውልለትና፣ “ምሳህን ውጭ ብላ ሃኒ" ትለዋለች፣ በዛውም አያችሁ ባሌን ሳዘው!' እያለች በከንቱ ጓደኞቿ፡፡ ምሳ፣ ራት፣ ቁርስ በአበሻ ባህል
ከምግብ የዘለለ ፋይዳ ያለው ጉዳይ መሆኑ ለዛፒ አልታያትም ነበር፡፡

የቤተሰብ እትብት ከእናት ማዕድ ጋር እንደሚያያዝ ማን ይመከራታል? ዋሲሁን ለአንድ ዓመት አብሯት ቆየና ከፉ ደግ ሳይናገር፣ አንቺ ጋር እንግዲህ በቃኝ ብሏት ሄደ...!! መሄድ ብቻ
አይደለም፡ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ድል ባለ ሰርግ ሌላ ሴት አገባ፡፡ ዛፒ መጀመሪያ፣ “ጥርግ
ይበል! ለሞላ ወንድ!" አለች፡፡ ቆይታ፣ “ይሄ ችጋራም ፒዛ እንኳን መብላት ያለማመድኩት እኔ
ነበርኩ፡ ጥጋበኛ የደሀ ልጅ” ማለት ጀመረች፡፡ በመጨረሻ ፎቶውን እያየች ማልቀስ ሆነ ስራዋ፡፡

ዛፒ ሲበዛ ቆንጆ ናት፡፡ ልብሶቿ ጌጣጌጦቿ የብዙ ሴቶች የቁም ቅዠት፡፡ ግን ዋሲሁን ከሄደ በኋላ
ወንድ የሚባል አልቀርብ አላት፡፡ ይፈሯታል፡፡ የተጋነነ ቁንጅናዋና ውድ ጌጣጌጦቿ የማትደፈር
ግዛት ስለሚያስመስሳት የሚመኛት እንጂ ድፍሮ የሚቀርባት ጠፋ፡፡

የአበሻ ወንድ ተመካከሮ ሸሸ

ዛፒ ታዲያ የለየላት ስካራም ሆነች። ማታ ማታ ሰክራ ትመጣና፣
በምን አባታችሁ ዕድላችሁ ነው እኔን የምትስሙት!? እዛ የጉራጌ ጫማ ደንቅረው የቻይና ሱሪ ውስጥ የተቆጠሩ ኋላ ቀር ሠራተኛ ሴቶቻችሁ ጋር ኑሩ! ጎ ቱ ሄል ቆሻሾች! ቦርጫሞች! ቀ'ጂም'
አጠገብ አልፋችሁ የማታውቁ” እያለች በረንዳዋ ላይ ቆማ ድፍን የአበሻን ወንድ ትሳደባለች ።

በጣም ስከር ብላ ጨርቅ ሆና ያመጣት ባሰታከሲ ግቢ ውስጥ ደግፎ አስገብቷት ሲመለስ
ትጠራኛለች፣

“አሸብር ና ጫማዩን አውልቅ!”
👍26👏1