አትሮኖስ
280K subscribers
112 photos
3 videos
41 files
474 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የመደርደሪያው_ጫፍ


#በአሌክስ_አብርሃም

“አብርሃም !"

“አቤት”

“ስምህ ማነው ?” አለኝ ፊቴ የተቀመጠው ደግ ፖሊስ፡፡ ፊቱን ሳየው ማፏጨት ጀምሮ መሐል
ላይ ሲደርስ ሊያፏጭ የፈለገው ዜማ የጠፋበት ጎረምሳ ይመስላል፡፡ ስሜን ጠርቶ ስምህ
ማነው? ሲለኝ ቢጎርመኝም በትህትና ተናገርኩ፡፡

“አብረሃም”

“አ.ብ.ር.ሃ.ም”ፊደል የቆጠረ ፃፈ፡፡

የአባትህ ስም" ነገርኩት ጻፈ፡፡
“አብረሃም ! ለምንድነው የሰው ባል ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በሚዛን ስሀን የፈነከትከው”
አለኝ፡፡ አጠያየቁ 'ባትመልስልኝም ግድ የለም” የሚመስል ሰሜት ነበረበት፡፡

ኧረ ስላበሳጨኝ ነው እንጂ እኔ ሰው ጋር ተሰዳድቤ እንኳን አላውቅም፤ እንኳን በጭካኔ..
ዓረፍተ ነገሬ እየተወለጋገደ መለስኩ፡፡

“እሱማ ታስታውቃለህ፡፡ ጨዋ ልጅ ነህ፡፡ ጨዋ ባትሆን ኖሮ ሰሀኑ ላይ የተቀመጠውን አንድ ኪሎ መመዘኛ ብረት ትተህ በሰሃኑ ብቻ ኣትፈነከተውም ነበር፡፡ ጎበዝ ራስህን መግዛትህ ትልቅ ነገር ነው:: ራሱን የሚገዛ አገር ከሚገዛ ይበልጣል ይባላል፡፡ ቢሆንም ግን አብረሃም ዋስ ትጠራለሁ፡፡

“እሺ አልኩና ትዝ ሲለኝ የሚዋስ ሰው የለኝም፡፡

እንካ ደውልና ጥራ !" ብሎ ቅድም ወደ ማረፊያ ቤት ስገባ የተቀብለኝን ስልኬን ወደ ፊቴ
ገፋልኝ፡፡

ወደ አእምሮዬ የመጣችው ሂሉ ነበረች፡፡ ግን ሀሳቡ በራሱ ሳቁን አመጣብኝና ተውኩት፡፡ ባሏን
ፈንክቼ ሚስቱን ዋስ ሁነኝ ማለት በእርግጥ ያስቃል፡፡ ዝም ብዬ ዋስ የሚሆነኝ ሰው ሳወጣና ሳወርድ ቆየሁና "ዋስ የለኝም !" አልኩት ለደጉ ፖሊስ፡፡

እንዴት ዋስ አይኖርህም? ከሰው አልተወለድክም ? ጓደኛ የለህም? ወይም ጎረቤት ” አለ ፖሊሱ፡፡ እንዲህ ሲለኝ ዘመድም ጓደኛም የምለው ሰው እንደሌለኝ ትዝ አለኝና እንባዬ በዐይኔ
ግጥም አለ፡፡

“ደህና እስቲ የአንድ ሰው ስም ንገረኝ አለ ለመፃፍ እየተመቻቸ፡፡

“የአንድ ሰው ማለት?

"በቃ ዝም ብለህ የአንድ ሰው ስም ንገረኝ” አለ፡፡

"እበራ " ማረፊያ ቤቷ ውስጥ አበራ አንበሳው ! የሚል ስም በተወለጋገደ የእጅ ጽሁፍ አይቼ
ሰለነበር አፌ ላይ ድንገት መጣልኝ፡፡

“የአባቱ ስም ማነው ?"

"እኔ ንጃ ተገርሞ አየኝና ፈገግ ብሎ አጉተመተመ፡፡

“በቃ አበራ ቀለጠ ብዬዋለሁ - ዋስሀ ነው:: አብረሃም አምንሃለሁ፤ ጥሩ ልጅ ነህ፤ ይሄ መቼም
የዕለት ግጭት ነው:: ከአሁን በኋላ እዛ ሱቅ አካባቢ ብትደርስ ግን ዋስህን እቀፈድደዋለሁ፤

' ነግሬያለሁ” አለ እየሳቀ፡፡
እዚች ምድር ላይ ይኑር አይኑር በማይታወቅ ዋስ ከእስር የወጣሁ ሚስኪን ሰው፣ ቀበቶዬን
ተቀብዬ ከታጠቅኩ በኋላ ወደ ቤቴ አዘገምኩ፡፡ ፖሊሱ ያሳየኝ እምነት በጣም ነው የገረመኝ፡፡
ለምን እንደሆነ ባላውቅም ሰው ከመሬት ተነስቶ ያምነኛል፡፡ ሌባ ብሆን መቼም ባንዴ ሃብታም
ነበር የምሆነው፤ ሰዎች እንዲያምኑህ እና እንዲዘናጉ ማድረግ ትልቁ የሌብነት ጥበብ ነውና፡፡
ሰፈሬ ስደርስ ወደ ህሊና ሱቅ መንገድ ጀመርኩና ትዝ ሲሰኝ ደንግጬ መንገዴን ቀየርኩት፡፡ ሱቅ አካባቢ እንዳልደርስ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶኛል፡፡ ወይኔ ከሁሉም ከሁሉም ህሌናን ሳላይ መዋል እንዴት ያስጠላል?! ህሊናን እንዳላይ በህግ ተከልክያለሁ፡፡ ያ ፖሊስ በሕግ አላስፈራራኝም
ሕጉን ነው አእምሮዬ ውስጥ ተክሎ በፍቅር ያጠረው፡፡

ሂሉ እስካሁኝ በዱቄት የተበከለ ጋውኗን ስብሳ ፊቷ በሚነድ ሻማ የሆነ ነገር እያደረጋች ይሆናል፤
ወይም የለስላሳ ሳጥን ላይ ቆማ እንደ ነብር ሽንጧ ተመዞ የላይኞቹ መደርደሪያዎት ላይ ሳሙና
እየደረደረች ይሆናል፡፡ ስትንጠራራ እኮ ስታምር! ሰማይ ላይ በተቀመጠ ገብታ በሚያማምሩ
ጣቶቿ እግዜር ጋር ቼዝ የምትጫወት ነው የሚመስለኝ፡፡
ሂሉ የኔ ውብ ! የኔ ቆንጆ! የግርማ
ሚስት ፤ ሰው እንዴት ግርማን ያገባል በእግዚኣብሔር

ብቸኛ ነኝ ! ሁሉም ነገር የሰለቸኝ የሃያ ሰባት ዓመት ወጣት፡፡ ቤቴ እገባለሁ፤ እወጣለሁ ሶስት ዓመት ሙሉ እዚህ ሰፈር ስኖር የማውቃት ህሌናን ብቻ ነው፡፡ መንገዴ ላይ ሱቅ አላት፣ድምቅ ያለ ሱቅ፡፡ የሱቁ ድምቀት ህሊና ራሷ ሳትሆን አትቀርም፡፡

ህሊና ጨዋ ሴት ነበረች። እኔም ጨዋ ልጅ ነበርኩኝ፡፡ የህሊና ባል ግን ጨዋ ስላልነበረ ሊያሳሰተኝ
ሞከረ፡፡ ይሄ አሳሳች ደስ ይበለው፤ ተሳክቶለት ተሳሳትን፡፡ በእርግጥ ስሀተታችን ጣፋጭ ነበር፡፡

ለሚስቱ ሱቅ ከፍቶ ወንድ ደንበኛ በመጣ ቁጥር 0ይኑን ማጉረጥረጥ ተገቢ ነው? ገበያተኛ በመጣ ቁጥር የሚስቱን ፈገግታ መለካት እና ማታ ማታ በልክ ፈገግ በይ እያለ መነትረክ
እግዚር ይወደዋል? እሽ ይሄ ይሁን ግዴለም…ግን አብረሃም የሚባል ልጅ እዚህ ሱቅ ለምን ይመጣል ለሞላ ሱቅ?!” ብሎ መጠየቅ ከአንድ ባለ ሱቅ ይጠበቃል? ... መንግስት ሳያዳላ ሕዝብ
እንዲያገለግልበት በሰጠው ንግድ ፈቃድ እከሌ ይምጣ እከሌ ይሂድ ብሎ ሰው ይመርጣል?
እሺ (ሂሂሂሂ…ኧረ ይሄስ ያሳፍራል) ግን ሚስቱ ጋር፤ ቆንጅዬ ሚስቱ ጋር እቅፍቅፍ ብሎ ከመተቃቀፍም አልፎ መርፌና ክር ሆነው ሌላ ዓለም ውስጥ ሲዋኙ ድንገት የማይቋረጥ ነገር
አቋርጦ፣ “ለምንድን ነው አብረሃም ቲማቲም የሚገዛው? ማን ሊያበስልለት?” ብሎ ሚስቱን
ይጠይቃል፥ እንዲህ ይደረጋል ?

ሂሉዬ ብስጭት ብላ “ራሱ ይሰራላ” ስትለው፣ ራሱ እንደሚሰራ በምን አወቅሽ ?” ይባላል ?ለጥያቄና መልስ ይሄ ቦታው ነው ? ሰዓቱስ ነው ?

ባሏ ቀልቡ አይወደኝም፥ እቀፈዋለሁ፡፡ እኔ ሱቁ በር ላይ ስቆም ዐይኔን ላለማየት የማያየው ነገር የለም፡፡ የተደረደረውን ሳሙና፣ የተሰቀለውን ሙዝ፣ የተለጠፈውን "ዱቤ ክልክል" ነው የሚል ማስታወቂያ...ብቻ ማየት የቻለውን ሁሉ ፌቱን እጨፍግጎ ይቃኛል፡፡ አናቴን ሊፈነከተኝ ፈልጎ
ደህና መፈንከቻ ያጣ ነው የሚመስለው:: በዛ ላይ ሆነ ብሎ ህሊናን በወሬ ያጨናንቃታል፡፡
እንዳናወራ መከላከሉ እኮ ነው፡፡

እጃክስ አለቀ እንዴ?” ይላታል፤

ኧረ አለ!"

"ለስላሳ ዛሬ አላወረድሽም ?"

“ገና ትላንት እኮ ነው ያወረድኩት !”

በቃ የማይቀባጥረው ነገር የለም፡፡

እንግዲህ ስገባና ስወጣ ሰላም የምላት ብቸኛ ሴት ባለ ሱቋ ህሊና ነች፡፡ ሱቋ መንገዴ ላይ
ስለሆነች አስቤዛዬን የምሸምተው ከሷው ነው፡፡ ታዲያ ህሊና ጥሩ ልጅ ስለሆነች ነው መሰል
ከደንበኝነት ከፍ ያለ ቅርርብ ነው ያለን፡፡

ዛሬም ልክ ደመወዝ እንደተቀበልኩ ሄድኩ፤ ባሏ የለም፡፡ ሁለታችንም ደስ አለን፡፡

አንተ?" ትለኛለች፡

በቃ ስሜን ጠርታኝ አታውቅም፡፡ አንተ ነው የምትለኝ፡፡ እውነቱን ለመናገር ህሊና 'አንተ'
ስትለኝ ስሜን ያቀናጣችው ነው የሚመስለኝ፡፡ አብርሃም ሲቀናጣ 'አንተ ! በእኔ ጆሮ ብትሰሙት
በጣም ይገጣጠማል !!

ሰላም 'ሂሉ' ባሏ ከሌለ ሂሉ ነው የምላት፤ በእርግጥ አንዳንዴ እሱም እያለ ያመልጠኛል፡፡

“ምን ሆነህ ነው ዐይንህ የቦዘዘው” ትላለች በትልልቅ ዐይኗ እያየችኝ፡፡ ዐይኖቿ ዐይኔን
ይስሙኛል፡፡

“ዱቤ ልከፍል ስለሆነ ይሆናላ !”

በዚህ ሁኔታ መቀለድ መቻሌ ግዴላችሁም ብርቱ ሰው ብሆን ነው!

ሂሂሂሂሂሂሂሂ….ውይ አታስቀኝ ከምሬ ነው!” ትላለች፣ ስቃ ከወጣላት በኋላ እኮ ነው፡፡ ከዛም
የወሩ እዳዩን እንተሳሰባለን፡፡
"ዱቤ ክልክል ነው" ከሚለው ጽሑፍ ስር ያስቀመጠችውን የዱቤ መጻፊያ ደብተር ታወጣና
ቁልቁል በእስክርቢቶዋ እየጠቆመች “ካርድ የ 100 ብር ግን መቶ ብር ካርድ ምን ያደርግልሃል?
ወሬ እንኳን አታበዛ” ትላለች፤

ዳቦ

ዳቦ

ዳቦ ሰነፍ ስለሆንክ እኮ ነው ዳቦ የምትበላው ! ብቻ አንጀትህ እንዳይደርቅ ፤ ምናለ እንደ
ወንዶቹ እንቁላል እንኳን ብትጠብስ …" ትቀጥላለች፡፡

“…የተፈጨ ቡና…!
👍23👏1😁1
#የመደርደሪያው_ጫፍ

፡(የመጨረሻ ክፍል)
#በአሌክስ_አብርሃም


....ሳሙናዬን ተቀብዬ ወደ ቤቴ አዘገምኩ፡፡ በቀጣዩ ቀን ቅዳሜ ሂሉ እንባዋ ጠብ እስኪል እየሳቀች ሳሙናውን ገዝቼ ከሄድኩ በኋላ ከግርማ ጋር የተባባሉትን እንዲህ ስትል ነገረችኝ፡፡.አወራሯ
ድራማ ነው የሚመስለኝ። ሂሉ ሲበዛ ነፃ ነች፡፡

እንተ ” በሳቅ ፍርስርስ አለች፤

“ምን ያስቅሻል?”

"እይውልህማ…ብታይ…ትላንት ሳሙና ስጭኝ ስትለኝ ሰጥቼህ (ረዥም ሳቅ )..ሰጥቼህ ከሄድክ
በኋላ ግርምሽ ብስጭት ብሎ ሲነዘንዘኝ አላመሽ መሰለህ! ሆሆ!”

“ምን አነዛነዘው ?”

ነገረችኝ፤ ልከ እኔ እንደወጣሁ ግርማ ሂሉን ጠየቃት፣

".…እኔ የምልሽ! አብረሃም 'ሳሙና ስጭኝ' ነው ያለሽ አይደለም እንዴ?”

“እዎ እና እኔስ ሌላ ምን ሰጠሁት?”

“ምን እንደሰጠሽውማ አንችው ታውቂያለሽ”

“እንዴ! ግርምሽ ምን ማለትህ ነው?”

“የሳሙናውን ዓይነት አልተናገረም፡፡ እንዴት ዘለሽ እዛ ትንጠላጠያለሽ? እዚህ የገላ ሳሙና አለ፥ እዛጋ አጃክስ አለ፤ ላርጎ ፈሳሽ ሳሙና አለ፤ ምን እንደፈለገ በምን አወቅሽ ?”

ሂሉ ደነገጠች፡፡ ቢሆንም ኮስተር ብላ መለሰችለት፡፡

“ሁልጊዜ የሚወስደው ይሄንን ነዋ!"

“እስኪ እሱን የዱቤ ደብተር አቀብይኝ አለ፤ አቀበለችው፡፡ የወሰድኩትን ዝርዝር አየና የታለ
ሳሙና ወስዶ የሚያውቀው?” አላት በብስጭት፡፡

“እየከፈለ ነው የሚወስደው"

“ያሁኑን መቼ ከፈለ ?

“ኤጭ እንግዲህ አትጨቅጭቀኝ ! ወይ 'ሱቁን ዝጊና ቤት ተቀመጭ! በለኝ አለች ብስጨት ብላ፤

በዱቤ ደብተሩ ወርውሮ ሳታት፡፡ ከፀያፍ ስድብ ጋር “ሸርሙጣ!"

ይህን ሰትነግረኝ ሁለታችንም ከልባችን ሳቅን፡፡ ስቃ ስቃ ሲወጣላት “እንተ ምናለብህ ሳቅ ገብተህ በሰላም ለጥ ትላለህ፤ የሰው ትዳር እየበጠበጥክ ልክ ስለሌላ ሰው ትዳር የምታወራ ነበር የምትመስለው።

ባሏ ግርማ ከሌለ ወሬያችን መቆሚያ የለውም፡፡ እንደማልወደው ታውቃለች፡፡ እሱም እንደማይወደኝ ታውቃለች። ይሄ ነገር ሳያስቃት አይቀርም፡፡ ሰው ከመሬት ተነስቶ ይጠማመዳል?ሆሆሆ ትላላች። ከዛም ልክ የመጀመሪያው ወሬ አካል እስኪመስለኝ ሌላ ርዕስ ውስጥ ትገባለች፡፡

"አንተ እቺ ሸሚዝ አሁንም አለች?” አለችኝ ድንገት የለሰስኳትን ሸሚዝ በግርምት እየተመለከተች፡፡

"አዎ የት ትሄዳለች ?”

የመጀመሪያ ቀን እዚህ ሱቅ ስትመጣ እችን ነበር የለበስከው..ፀጉርህ ጨብረር ብሎ እዚች ጋ ቆመህ.ወረፉ ነበር፣ ሰው ሁሉ እያለፈህ ገዝቶ ሲሄድ እንተ ዝም ብለህ ቆመህ ..ሂሂሂሂ
ሌባ መስለከኝ፣ ስልኬን አንስቼ መሳሲያዩ ውስጥ አስቀመጥኩት ሃሃሃሃ…ከዛ በአንድ ዐይኔ አንተን
እያየሁ፡ በአንድ ዐይኔ ደንበኞቼን ሳስተናግድ ነበር፡፡…ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ !” አወራሯ ያስቃል፡፡ ሌባ ትመስላለህ እያለች እንኳን ታስቃኛለች።.ደግሞ የሚገርመኝ አሳሳቋ ሳቁ
እንሳቅ ዓይነት ግብዣ ነው በቃ !

ግርምሽም ሌባ ነበር የምትመስለው አሁንም ሐሳቡን የቀየረ አይመስለኝም፡፡
ሃሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂሂ…” ሁለተኛዋን አረፍተ ነገር ስራዬ ብላ እኔን ለማብሸቅ የጨመረቻት
ብትሆንም እያውቅኩም ተበሳጨሁ፡፡

"እናትክን በይው እሺ!”

"ሃሃሃሃ አንተ ባለጌ ስድ ባሌ እኮ ነው! ሂሂሂሂሂሂሂ…»

"እኮ ባልሸን እናትክን በይው!.…ማታ እቅፍ አድርገሽ ጉንጩን እየሳምሽ : መቼም ይሄ ማቀፍም
መሳምም አይገባው…'የኔ ቆንጆ አብርሃም እናትክን ብሎሃል እሽ ! በይው"

ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃም የሚያልፈው ሰው እየዞረ እስኪመለከት ሳቋን ለቀቀችው፤
እየሳቀች እንባዋ ሲፈስ ገርሞኝ ነበር፡፡ በቀጥታ እየሳቀች ማልቀስ መጀመሯን ያወቅኩት ወዲያው
ነበር፡፡

እንዴት እንደመረረኝ!” አለችኝ፡፡ ደነገጥኩ፡፡ ብሶቷን ዘረገፈችው፡፡

የሐረር ልጅ ናት፡፡ ዘጠነኛ ክፍል እያለች ይሄ ያሁኑ ባሏ ግርማ ወታደር ሆኖ ሰፈራቸው የነበረ
ካምፕ ውስጥ ይኖር ነበር፡፡ ያኔ ተጫዋች፣ ወንዳወንድ፣ በቃ የሚፈቀር ሰው ነበር፡፡ ለጓደኝነት
ሲጠይቃት አላንገራገረችም፡፡ “
ይዤሽ ልጥፋ!” ሲላት አምናዋለች፡፡ ካለ እናት ያሳደጋትን አንድ አባቷን ጣጥላ ይሄን መዶሻ ራስ ተከትላ እዲስ አበባ ገባች፡፡ እናቱ፣ እህቶቹ፣ ወንድሞቹ
ሳይቀሩ አተካኗት፡፡ ለጎብረት ያገቧት ይመስል በትዳሯ እየገቡ መፈትፈት ጀመሩ፡፡ ነፃ ሆኗን
አለሌነት፣ ሳቋን የሽርሙጥና ደውል አድርገው ዐይንሽን ላፈር አሏት፤ እንደ አዲሳባ ሰው በሯንም
ጥርሷም በልኩ መከፈት ያላደገባትን፡፡ ሚስኪን ! ልለማመድህ ብትለውም አልሆነላትም፡፡

" ኤጭጭ አቦ እንደፈለጉ ይሁኑ!" ብላ ሳቋንም ነፃነቷንም ተያያዘችው፡፡ ይባስ ብሎ ሳቋ ማርኮት እንዳልወደዳት “ሳቅሽን አቁሚ!“ አላትና አረፈው!! ብዙ ባሎች የባል ድንበሩ የት ድረስ እንደሆነ አያውቁም፡፡ ትንሽ ባሎች ደግሞ ድንበራቸው ላይ ሳይደርሱ ይቆማሉ፡፡

አባቷ እሷን ፍለጋ ተከራትቶ ተንከራትቶ ሲሞት አፈር አላለበሰችውም፡፡ የሐረር ሰው ውሎ ይግባ አልቅሶ ቀበረው፡፡ በምድር ላይ የነበራት አንድ መሸሻ ዋሻ ተደፈነ፡፡አሁን ግርማ መድረሻ
የሌላት ከንፏ የተሰበረ ወፍ አደረጋት። “በየመንገዱ ስታገጭ ነው ያገኘሁሽ" አላት ፣ እንደ
ሚስት ሳይሆን እንደ ሰራተኛ ከፍ ዝቅ አድርጎ ያዝዛት ጀመረ፡፡ ያኔ ካስቀመጠባት መንበር ጎትቱ
አወረዳዳት፡፡ ለሴት ልጅ ትልቁ ከብሯ ቤተሰቧ መሆኑን አመነች፡፡ ለምን አፈር ጠርጎ የሚተኛ
ደሃ አይሆንም ቤተሰብ አለኝታ ነው ! ፍቅር ይወጣል፣ ይጠልቃል፡፡ እቃ ! የሰው ፍቅር እንደ ፀሐይ ምስራቅና ምዕራብ አለው:: እየጣፈጠ ወጥቶ፣ እያቃጠለ ይጠልቃል! ቤተሰብ ግን ሰማይ ነው:: የሕይወት ፀሐይና ጨረቃ ሰፈራረቅ የማይቀያየር፣ የማይጠልቅ፣ የማይጠቀለል ቦታውንም
የማይቀይር ሰፊ ሰማይ ማለት ቤተስብ ነው፡፡ ሂሉ ቤተሰብ የላትም፡፡ ሰማይ የለም፡፡ ቀጥ ስትል ኦና ነው ባዶ ነው ! ኮከብ የለም፣ ጨረቃ የለችም፣ ፀሐይም የለችም፡፡ ሰማይ በሌለበት
ምንም የለም፡፡ እግዜር የት ይሆን መቀመጫው ? የት ሆኖ ይሆን ይህን ጉድ የሚመለከተው?!

የአዲስ አበባ ኑሮ አንሸገሻት። ለምሬቷ ጣዕም ኮሶ የጨመረው ባሏ ነው:: “ታምናለህ…. ከሳመኝ
ስንት ጊዜው ? አለችኝ፡፡ ግን እወደዋለሁ ! ስድቡ፣ ማቃለሉ እያቃጠለኝ እንኳን እወደዋለሁ !

ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አንተ እስለፈለፍከኝ :" አለችና ሳቋን ለቀቀችው:: የኔ ሚስኪን !!
ባለፈው ሐሙስ ደግሞ ሂሉ ወደኔ ጠጋ ብላ ፊት ለፊቴ ቆመች::መሐላችን ላይ ሚዛኑ አለ፡፡ ፊቷ ልክ አልነበረም፡፡ ቶሎ እንድሄድባት መፈለጓ በግልፅ ያስታውቃል፡፡

አንድ ትንሽ ልጅ መጥቶ "ሳሙና ስጭኝ ! ቢጫውን አላት፤
“የለም " አለች፣ ግን ፊት ለፊት ተደርድሮ ነበር፡፡
ሌላ ሴት መጣችና “ስኳር ስጭኝ ሕሊና ኣለቻት፡፡
“የለም !" ፈት ለፊት ኩንታል ስኳር ተቀምጧል፡፡ ገርሞኝ ጠየቅኳት፡፡
“ሂሂሂ.አንተ ካልሄድhልኝ በስተቀር ምንም ነገር አልሸጥም ዛሬ እየቀለደች መስሎኝ ነበር።
“ማሪያምን !" ስትለኝ የላፕቶፕ ቦርሳዬን እንስቼ፣ “በይ ቻው !” አልኳት፡፡
“ቻው አብርሽ !" አለችኝ በቅሬታ ፈገግታ፡፡ “አብርሽ ብላኝ አታውቅም፤ ግራ ገባኝ፡፡
በቀጣዩ ቀን ሂሉ የለችም ነበር፤ ባሏ ተገትሯል፡፡

"ሰላም ዓርማ"
“ምን ልስጥህ?” አለኝ ኮስተር ብሎ፣
"ኮካ"
"የለም"
"እሺ ቀዝቃዛ ሰፕራይት አድርገው"
"የለም"
👍32👎2