አትሮኖስ
280K subscribers
110 photos
3 videos
41 files
462 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ትኩሳት


#ክፍል_አንድ


#በስብሐት_ገብረ_እግዚአብሔር


ስብሃት ለትምህርት ወደ ፈረንሳይ በተላከበት ጊዜ ከጓደኞቹ ጋር በፓሪስ ያሳለፈውን ጊዜ የሚተርክ። በእውነተኛ ታሪክ ላይ ተመስርቶ የተጻፈ ከኢትዮጵያ ባህልና ስርአት ወጣ ያለ ልቦለድ ነው በርግጥ ከላይ ከላይ ለሚያነበው ከወሲብ ቀስቃሽ መፅሀፍነት ላይዘል ይችላል ነገር ግን በማስተዋል ብናነበው የብዙ ነገር ትኩሳቶች ያነሳልና ስናነብ በጥሞና ይሁን ያው ሁሉንም ይመቻል ተብሎ አይጠበቅምና ከዚህ ውጪ ወደ ላይ ብዙ ድርሰቶች አሉና ያላነበባችሁ ከሆነ እስከዚያው በነሱ አሳልፉ። አሁን ወደ #ትኩሳት እንሂድ።👇
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ከውብ ሰማይ በታች

ባህራም
ከሩቅ

ይሄ ሁሉ የሆነውና የተደረገው ኤክስ ውስጥ ነበር.....
ኤክስ (ኤክስ-አን-ፕሮቫንስ) በፈረንሳይ ደቡብ ከማርሴይ አጠገብ የምትገኝ ትንሽ የዩኒቨርሲቲ ከተማ ናት፡ ህዝቧ ግማሽ በግማሽ ተማሪ ነው
የኤክስ ሰማይ አብዛኛውን ጊዜ ብሩህ ሰማያዊ ነው፡ አንዳንድ
ጊዜ ውሀ አረንጓዴ ይሆናል፣ ወደ ማታ ላይ እንደ ልጃገረዶቹ
ጉንጭ ይቀላል።

የኤክስ አየር ጠባይ የተመሰገነ በመሆኑ፣ ሀብታም በሽተኞችና
ሽማግሌዎች በሐኪም ምክር ወደ ኤክስ መጥተው ይኖራሉ፡፡ ስለዚህ
«ኩር ሚራቦ» የተባለው የኤክስ ዋና ጎዳና ላይ ሽማግሌዎች፣
አሮጊቶችና ባለሻኛዎች
እግራቸው ረዣዥም ቀጫጭን የሆነ፣የተነፋ ደረታቸው ውስጥ አንገታቸው የተቀበረ ባለሻኛ ሰዎች በቀስተኛ እርምጃቸው ሲዘዋወሩ ይታዩበታል። ባቡር መንገድ ዳር የተደረደሩት አግድም ወምበሮች ላይ የአሮጊትና የሽማግሌ መአት ቁጭ ብሎ ሹራብ እየሰራ ወይም ጋዜጣ እያነበበ ፀሀይ ይሞቃል፡
ወይም ዝም ብሎ ባዶ ብርጭቆ መሳይ ፈዛዛ አይኑን አተኩሮ (ምን
ያይ ይሆን?) ከንፈሩን ያለማቋረጥ ያንቀሳቅሳል (ምን ይል ይሆን?)

በጣም ይቀፋሉ የፈረንጅ ሽማግሌዎችና አሮጊቶች። ጨምጻዳ ቆዳቸው የተሰነጣጠቀ ደረቅ ሰም ይመስላል። ቀጥቃጣዎች::ዝምተኞች። አገጫቸው ተገንጥሎ ወደታች የወደቀ፣ ከንፈራቸው
የተንጠለጠለ፣ ጥርሳቸው የፈራረሰ ሽማግሌዎች፡፡ ጥርሳቸው አልቆ አፋቸው ወደ ውስጥ የጎደጎደ ፂማም አሮጊቶች፡፡ የመኖር ጊዜያቸው
አልፎ፤ የሞት ጊዜያቸውን ዘመናዊ ህክምና ከልክሏቸው፤ ታችኛው
ከንፈራቸውን እንደ ጡጦ እየጠቡ ሞትን ሲጠብቁ ሚውሉ
የህይወት ኦናዎች። ዝምተኞች፡፡ ለአይን ብቻ ሳይሆን ላፍንጫም
ይቀፋሉ፡፡ የልዩ ልዩ መድሀኒት፣ የእርጅና፣ የሞት ሽታ
ሳይቀበር መግማት የጀመረ ስጋ

ደሞ መብዛታቸው ከተማሪው እኩል ሳይሆኑ ይቀራሉ? ማታ
መቸስ ፀህይዋ ሙቀቷን ይዛ ስትሄድ ወደየአልጋቸው ይከተታሉ።
ቀን ግን የትም ይገኛሉ፣ ኤክስን ይወሯታል። ኩር ሚራ ግዛታቸው ነው፡ ዩኒቨርሲቲው አጠገብ ያለው መናፈሻ ቤት መንግስታቸው ነው! ካፌዎቹ ቅኝ ሀገራቸው ናቸው። ቀን ሲኒማ የገባህ እንደሆነህ በጭለማው ሳይታወቅህ፣ ሳይተኛ ከሚያንኰራፉ ሽማግሌ፣ ወይም በየሶስት ሰከንዱ አክ!» ከምትል አሮጊት አጠገብ ትቀመጣለህ. . .

ደግነቱ ይሄ ታሪክ ስለአሮጊቶችና ስለሽማግሌዎች አይደለም።
ስለኛ ስለወጣቶቹ ነው፤ ስለባህራም፣ ስለኒኮል፣ ስለሲልቪ ስለሉልሰገድ፣ ስለሌሎችም ወጣቶች ....

ጥሩ ነው ወጣት መሆን። ገንዘብ ባይኖርህም ጤና ይኖርሀል፡ መልክ ባይኖርህም አንጎል
ይኖርሀል! እውቀት ባይኖርህም ጉራ ይኖርሀል፡ ፍቅር ባይኖርህም
ተስፋ ይኖርሀል፤ ደስታ ባይኖርህም ንዴት ይኖርሀል መጨቆን ቢበዛብህ ሪቮሉሽን ታነሳለህ. .. መኖር ቢያስጠላህ ወይም ቢያቅትህ ራስህን ትገድላለህ....ሰው ባያውቀውም ቅሉ ታሪክ ይኖርሀል፤ወጣት ነህና

የኤክስ የበጋ ሙቀት እየከበደኝ አላስራ ስለሚለኝ የከሰአት
በኋላውን ተኝቼ ውልና ሌሊት ስሰራ ለማደር 'ሞክራለሁ።
አንዳንድ ሌሊት ስራው እምቢ ሲለኝ፣ ከሆቴሌ ወጥቼ በእግሬ
እዘዋወራው ደስ ይለኛል በሌሊቱ ኤክስን መዞር፡፡ ትንሽ ከተማ
ስለሆነች ሰባት ሰአት ሲደርስ ሁሉ ነገር ተዘግቷል (ከካፌ «ሰንትራ»
እና ከላ ፓሌት ናይት ክለብ በቀር) በቀን ጠባቦቹን መንገዶች
የሚያስጨንቃቸው ህዝብ በሙሉ ተኝቷል፡ እነዚያ የሚያስፈሩኝ፣ መምጫቸው የማይታወቅ እብድ ፈረንሳይ ነጂዎች
በየአልጋቸው ተከተዋል! ኤክስ-አን-ፕሮቫንስ ሰላም ነው፡፡ ቤቶቹ ሁሉ ጨልመው፣ የመንገድ መብራት በርቶ፣ በፀጥታው የጫማዬን ድምፅ ብቻ እየሰማሁ ስራመድ፣ ባዶ ከተማ ውስጥ እንዳለሁ ሆኖ ይሰማኛል። አልፎ አልፎ በየአደባባዩ የሚገኙት ሰው ሰራሽ ምንጮች ወደ ኮከቦቹ በኩል እየዘለሉ ከሌሊቱ ጋር ይንሾካሾካሉ

አንድ ሌሊት ወደ ስምንት ሰአት ላይ አንዱን መንገድ ይዤ
ስራመድ ቆይቼ ወደ ግራ በኩል ስታጠፍ፣ ከፊቴ አራት የሚታገሉ
ፈረንጆች ድንገት ብቅ አሉ። ብቅ ያልኩትስ እኔ ነበርኩ፣ ግን እነሱ
ብቅ ያሉብኝ መሰለኝ፡፡ በበጋው ሙቀት ምክንያት አራቱም በሽሚዝ ናቸው፣ ይታገላሉ። በሌሊቱ ፀጥታ ጫማዎቻቸው ከአስፋልቱ ጋር ሲፋተጉና ትንፋሻቸው ሲቆራረጥ ይሰማል። ለጊዜው ማን ከማን ጋር
እንደሚታገል ለማወቅ አልቻልኩም። ዝም ብዬ ስመለከት፣ ሶስት ግዙፍ ሰዎች አንዱን ደቃቃ ብጤ ገጥመውት ኖሮ፣ ከጥቂት ትግል በኋላ ሁለቱ በቀኝና በግራ በኩል ያዙት። ሶስተኛው ከፊቱ ቆመ::
ሁሉም ቁና ቁና ይተነፍሳሉ፡፡ ደቃቃው ሰውዬ ይፍጨረጨራል፣
ግን ድምፅ አያሰማም፡፡ ለምን ኡ ኡ እንደማይል እንጃለት

ከፊት የቆመው ግዙፍ አንዴ በጥፊ መታውና፣ ዘወር ብሎ አጠገባቸው ካለው ግድግዳ ስር አንድ ትንሽ ነገር አንስቶ መጥቶ፣ በዚህ
በጨበጠው ነገር የትንሹን ሰውዬ ግምባር ፈተገው። ትንሹ ሰውዬ
ተፋበት። ግዙፉ በሹክሹክታ እየተሳደበ ወይም እየተራገመ ከሱሪ ኪሱ መሀረብ አውጥቶ ፊቱን ጠረገና ሲያበቃ፣ ደቃቃውን አንድ ቃሪያ ጥፊ አላሰው፡፡ ጥፊው ጧ ሲል ቀሰቀሰኝ፣ ገና አሁን ከመፍዘዜ ነቃሁ። ዘወር ስል፣ አጠገቤ ለመንገድ መጠገኛ ይሁን ለቤት ማስሪያ የተከመረ ኮረት አየሁ። በፍጥነት አንድ ሰባት ከባድ ጠጠር አነሳሁና
እያነጣጠርኩ ሰዎቹ ላይ መወርወር ጀመርኩ (ስወረውር የሀበሻ ነገር!» የሚል ሀሳብ በሀይል አሳቀኝ) ከት ከት ብዬ እየሳቅኩ የወረወርኩት ድንጋይ (ሶስተኛዋ) በጥፊ ተማቺውን ሰውዬ ደረቱን ደለቀችው፣ አራተኛዋ የአንዱን ትክሻ መታች። ድንጋዩና ሳቁ አስደንግጧቸው፣ ትንሹን ሰውዬ ለቀቁትና ተፈተለኩ፡፡ ለምራቂ ያህል እጄ ውስጥ የቀሩትን ድንጋዮች ወረወርኩባቸው። በድንጋዮቼ
ሸኚነት ጥቂት እንደሮጡ ወደ ቀኝ በኩል ታጠፉ፣ ጠፉ።

ሳቄም ድንገት ጠፋ። የፍርሀት ሳቅ ኖሯል። አጠገባችን ምንጭ
ሰማሁ። ገና አሁን ሰማሁት! ለካስ «ፕላስ ዴ ካትር ዶፈን» እተባለው
አደባባይ ውስጥ ነን

ትንሹ ሰውዬ ግራ ገብቶት መንገዱ ጋር ቆሞ አኔን ያየኛል
እጄን እያራከፍኩ ወደሱ ሄድኩ።
ይህን ያህልም ደቃቃ አደለም ከኔ ትንሽ ተለቅ ይላል። ደቃቃ የመሰለኝ ጠላቶቹ በጣም ግዙፍ ስለነበሩ መሆን አለበት።

«Bon soir» አልኩት (ቦን ሷር)
«Bon soir! አንተ ነህ እንዴ? ሀለላሲ ሙት!» አለኝ እየሳቀ

ባህራም ነው፡፡ ከዚህ በፊት ከሀበሾቹ ጋር ብዙ ጊዜ
አይቼዋለሁ። ግን ያን ጊዜ ያገሬን ልጆች በብዙ ስለማልጠጋቸው፣
ይህን ባህራም ተዋውቄው ወይም አናግሬው አላውቅም ነበር።

ድምፁ ወፍራም ሆኖ ለጆሮ ደስ ይላል ፈረንሳይኛው የፈረንሳዮቹ አይደለም፣ መልኩ ግን ትንሽ የደቡብ ፈረንሳዮችን ይመስላል። ፊቱ እንደ ፈረንጅ ነጭ ሳይሆን፡ ፀጉሩ በጣም ጥቁር ነው:: «ሀለሰላሴ ሙት!» ያለኝ ሀበሻ መሆኔን ስላወቀ ነው።
አብሯቸው የሚሄድ ሀበሾች ብዙ ጊዜ ሀይለስላሴ ይሙት!» ሲሉ
ሰምቷል
👍37