#ተሸከመናታል !!
፡
፡
#በአሌክስ_አብርሃም
እናቴ ሁልጊዜ እንድናጠና ስትመክረን እንዲህ ትላለች፡-
እናንተ ልጆች አጥኑ፣ ተማሩ እባካችሁ ! ..እኔ ባለሙማሬ ነው ጉዴን ተሸክሜ የዋልኩት፤”
ማንበብም መፃፍም ስለማትችል ንግግሯ በቁጭት ነበር፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ይሄ ተሸክማ የዋለችው ጉድ ምን እንደሆነ ለማወቅ ጓጉቼ ጠየቅኳት፣
“ማሚ የምን ጉድ ነው ተሽከመሽ የዋልሽው ?”
አወራችኝ…
በደርግ ጊዜ መስከረም ሁለት ቀን ሕዝቡ በግድም ሆነ በውድ የድጋፍ ሰልፍ ይወጣ ነበር፡፡
መስከረም ሁለት ደርግ ንጉሱን ገልብጦ ሥልጣን የያዘበት ቀን ነው፡፡ በአጭር አገላለፅ መስከረም ሁለት የደርግ ግንቦት ሃያ ነበር፡፡ ያሁኑ እንኳን መቼ እንደሆነ እኔንጃ ካወቃቹ ንገሩኝ ታዲያ እናቴ በወቅቱ የነበረውን የግዳጅ ውትድርና በመፍራት
የመጀመሪያ ልጇን ወታደር ቤት እንዳይወስዱባት ከከተማው ወጣ ያለ አክስታችን ቤት ደብቃ፣
ሁለተኛ ልጇንም ገጠር እናቷ ጋር ልካ፣ ሦስተኛውን ልጇን አልጋ ስር አስቀምጣ፣ አባቴንም
“ታምሜያለሁ በል!' ብላው፣ እሷ ግን ነጭ ልብስ ለብሳ ሰልፍ ወጣች፡፡ ግዴታ ነዋ!
ቀበሌ ስትደርስ ሴት ወንዱ ያለውን ለብሶ ተሽቀርቅሮ፣ ቀበሌውም በተለያዩ መፈክሮችና በባለ ቀለም
መብራቶች አጊጦ ጠበቃት፡፡ የቀበሌው የኢሴማ ኃላፊ የነበረች ሴት በባለእጀታ የጣውላ ሰሌዳ ላይ ተፅፈው የተዘጋጁ በመቶ የሚቆጠሩ መፈክሮችን ለእናቴ እያሳየቻት፣“ምረጭና አንዱን ያዥ” አለቻት፡፡
እናቴ ቀለል ያለችና በደማቅ ቀይ ቀለም የተሽሞነሞነች መፈከር መርጣ አነሳችና ወደ ሰልፉ
ተቀላቀለች፡፡ ከለበሰችው የሚያምር የአበሻ ቀሚስ እና ከራሷም ቁንጅና ጋር ተዳምሮ የኦሎምፒክ መከፈቻ ላይ ኢትዮጵያ የሚል ምልክት ይዛ ሰልፉን የምትመራ ቆንጆ የአበሻ ሴት ትመስል ነበር፡፡
በዕለቱ መስቀል አደባባይ ላይ እናቴን በርካታ ሰዎች በግርምትና በአድናቆት ሲመለከቷት ዋሉ፡፡
ታዲያ በዚያ ሰሞን ማታ በቴሌቪዥን ደጋግመው እናቴን ከነመፈክሯ ያሳይዋት ጀመረ፡፡ ምን ይሄ ብቻ፣ ዓመቱን ሙሉ ፎከረውም እናቴን ማሳየት፣ ኢህአፓ ብለውም እናቴን፣ መኢሶን ብለውም እናቴን፣ ቀይ ሽብር ብለውም እናቴን፣ ጓድ ሊቀመንበር ተናግረው ሲያበቁም እናቴን ማሳየት፡፡
ጭራሽ ብሔራዊ ውትድርና ተብሎ ምድረ ወጣት ሲጋፈ ፣ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቀፍ ዓርማ የእናቴ ፎቶ ሆኖ በየቦታው ተለጠፈ፡፡ በነጭ ልብስ ተውባ መፈክር ይዛ የቆመች እናቴ የብሔራዊ ውትድርና አገር አቅፍ አርማ ሆነች፡፡አንድ ጋዜጣ ላይ የእናቴ ፎቶ ስር እንዲህ የሚል ጽሑፍ ሰፍሮ ነበር፤
“አብዮታዊት ሶሻሊስት ኢትዮጵያ ነጭ ቀሚስ ለብሳ”
እናቴ ታዲያ መጀመሪያ አካባቢ በቴሌቪዥን በታየች ቁጥር በቁንጅናዋ የተመረጠች መስሏት
አባቴ ላይ በኩራት ትነሰነስበት ነበር፣ “ጓዳ ለጓዳ ስውል ቀላል ሰው አድርገኸኝ፣ እግሬ ወጣ ካለ አገር ነው የሚሰግድልኝ!” ትለዋለች ኮራ ብላ፡፡ አባቴ አፉን ሸርመም አድርጎ፣ “እዩኝ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ደብቁኝ ያመጣል ” ይላታል::
“የቅናት ወሬ ነው ይሄ” ትልና ሆነ ብላ ለማበሳጨት በቴሌቪዥን ደጋግሞ የሚታየውን
ምስሏን አተኩራ እየተመለከተች፣
“አንዲት ፍሬ ልጅ እኮ ነኝ” ትላለች፡፡ አባባ ታዲያ “ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ…” ብሎ በረዥሙ ይሰቅና “ሰልፍ ላይማ መንግስትም አንድ ፍሬ ነኝ ነው የሚለው” ይላል፡፡
“ኤዲያ እንግዲህ ቦለቲካህን ልትጀምር ነው…” ብላ ወደ ጓዳዋ ትገባለች፡፡
ይሁንና እናቴ እየቆየች በቴሌቪዥን መታየቱ እና ስለ እርሷ መወራቱም ሲደጋገምባት ፈራች፡፡
በተለይም ጓድ መንግስቱ ኃይለማሪያም መስቀል አደባባይ በትልቁ የተሰቀለውን የእናቴን ፎቶ
ለተሰበሰበው ሕዝብ እያሳዩ በደም ፍላት፣
“እንደነዚህ ዓይነት ጀግና እናቶች ያሉባት አገር በማንም ወመኔ ከሃዲ ስትወረር እንዴት
ወንዶቿ አልጋ ስር ይደበቃሉ? እነዚህን ቦቅቧቃ ወንዳገረዶች ቂጣቸውን በሳንጃ…” እያሉ
ንግግር ካደረጉ በኋላ እናቴ ስጋቷ ከፍ አለ፡፡
ስጋቷን ለማስታገስ፣ “ኧረ ይሄ መፈክር ምንድን ነው የሚለው?” ብላ የተማረ ሰው ጠየቀች፡፡
መስከረም ሁለት ሰልፍ ላይ ይዛ ስለወጣችው መፈክር ተሸክማው ስለነበረው ጽሑፍ ሚያዚያ
ላይ “ምንድን ነው?” ብላ ጠየቀች፡፡ ሲነበብላት አመዷ ቡን አለ ፤ ብርክ ያዛት፡፡ መፈከሩ እንዲህ ነበር የሚለው
“የአብዮት ጠላቶችን ለማደባየት እኛ እናቶች ልጆቻችንን፣ ካስፈለገም ባሎቻችንን በደስታ እናዘምታለን!”
✨አለቀ✨

👍36😁18❤9👏2