#የፍቅር_ሰመመን
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ
፡
፡
#ድርሰት_ሲዲኒ_ሼልደን
፡
፡
#ትርጉም_ብርሃኑ_በላቸው
....ሎው ጉድማን ስታር ተብሎ ከሚጠራው የሎስ አንጀለስ መንገድ ላይ መኪናውን ሲያስገባ ፀሐይ መጥለቅ ጀምራ ነበር። የሴንቸሪ ሲቲ ትልቅ ፎቅ
ደግሞ በሎስ አንጀለስ ሐምራዊ ብርቱካናማ የምሽት ፀሐይ የሆነ ህልም
ውስጥ የሚገኝ ፎቅ መስሎ ቆሟል።
በመንገዱ ዳር እና ዳር የሚገኙት
የዘንባባ ዛፎችም በሞቃታማው ንፋስ ልክ እንደሰከረ ሰው ይወዛወዛሉ።
የፖሊስ ባጁን እንደያዘም የህንፃው እንግዳ ተቀባይ ዴስክ አጠገብ
በመድረስ “መርማሪ ፖሊስ ሉው ጉድማን የግድያ ወንጀል ምርመራ ፖሊስ
ነኝ፡፡ ክፍል ቁጥር 706 ን ለማየት ነው የመጣሁት እና ቁልፉን ትሰጪኝ”
አላት ላላቲኖዋ እንግዳ ተቀባይ ፈገግ እያለ፡፡ ልክ እንደሁልጊዜው የፍርድ
ቤት ማዘዣ ወረቀት ሳይዝ እንደሚያደርገው ማለት ነው፡፡
ልጅቷም የአፀፋ ፈገግታዋን ለግሳው እና በውስጧም ኮሌምቢያ ውስጥ ከምታውቃቸው ፖሊሶች የተሻለ መልካም ፀባይ እንዳለው እያሰበችም “ አለኝ፡፡ ግን አያስፈልግህም፡፡ ዶክተር ሮበርትስ ቢሮዋ ከገባች አንድ ሰዓት አልፏታል። አሁንም ቢሮዋ ውስጥ ትገኛለች፡፡ በግራ በኩል ያለውን አሳንስር መጠቀም ትችላለህ አለችው።
"አመሰግናለሁ” አላት መብሸቁን ለመደበቅ ፈገግ እያለ፡ ጉድማን የኒኪ
ቢሮ ውስጥ ብቻውን በመግባት ቢሮዋን መበርበር ነበር የፈለገው፡፡ በዚህ
ሰዓት ምን ትሰራለች? ብሎ ራሱን ጠየቀ፡፡ ግን ቢሮዋ ውስጥ እሷ መኖሯ ጥሩ ነው ብሎም አሰበ፡፡ ምክንያቱም ቀን ላይ ባልደረባው ጆንሰን እሷን ስላበሸቃት ብዙ ልትነግራቸው የምትፈልጋቸውን ነገሮች መናገር ትታ ነበር::ምናልባት አሁን እሱ ብቻውን ስለሆነ ይበልጥ ግልፅ ሆና ልታወራኝ ትችላለች ብሎ አሰበ እና ተረጋጋ።
በአሳንሰሩ ሰባተኛው ፎቅ ድረስ ወጣና በኮሪደሩ ላይ እየተራመደ የዶክተር ኒኪ ሮበርትስ ቢሮ ጋ ሲደርስ ቆመ፡፡ በሩ ገርበብ ብሎ ስለተከፈተም ወደ ውስጥ መሰስ ብሎ ገባ፡፡ ኒኪ ጀርባዋን ሰጥታ በወረቀት መክተፊያው ማሽን ውስጥ ወረቀቶችን እያስገባች ወረቀቶችን እየከተፈች ነበር፡፡ እግሯ ሥር ካስቀመጠችው ካርቶን ውስጥ ዶክመንቶችን እያነሳች ወደ ማሽኑ እየከተተች እና እየከተፈች ልትጨርስ ስትል
“እንዴት ነሽ?” የሚል ሰላምታን ስጣት፡፡
ኒኪም ድምፁን ስትሰማ በከፍተኛ ድንጋጤ ቀለሙ የተለወጠውን ፊቷን
ወደ እሱ በማዞር ፍርሃት በተሞላ አይን ተመለከተችው፡፡
“በእግዚአብሔር! በፍርሃት ነፍሴ ልትወጣ ነበር!” አለችው፡፡
“ይቅርታ” አላት እና እጇ ላይ የቀረውን ለማሽኑ ልታጎርሰው ያዘዘችውን
ፋይል በጉጉት እየተመለከተ
“ምንድነው የያዝሽው?” አላት፡፡
“ምንም አይደለም። ፅዳት እያካሄድኩኝ ነው::” አለችው እና ወረቀቱን ወደ ማሽኑ አፍ ከተተችው:: ማሽኑም ወረቀቱን እየሸረካከተ በዚያኛው ጎን
በኩል ሲተፋው ኒኪ “አታስብ ጠቃሚ የሆኑ የታካሚዎቼ ፋይሎች አይደሉም። ባልደረባህ መጥቶ ይህንን ሲያይ ይበልጥ የማያምንበት ነገር እንዳገኘ እንዳያስብ እና ይበልጥ እንደ ወንጀለኛ
ሌላ እኔን እንዳይመለከተኝ ደግሞ”
“እውነቱን ስለነገርሺኝ አመሰግናለሁ::” ብሎ ፈገግ አለ። ደግሞስ እንዲ
ዶክተር ኒኪ ያሉ ቆንጆ ሴቶች ፊት ሥርዓት ያለው ፖሊስ ሆኖ መተወን እንዴት ያቅተዋል?
“እና ቅዳሜ ምሽት እዚህ ምን እግር ጣለህ መርማሪ ፖሊስ ጉድማን?”
ብላ ማሽኑን እያጠፈች ጠየቀችው።
“ጠዋት ላይ ስለተፈጠረው ነገር ይቅርታ ልጠይቅሽ ነው የመጣሁት” አላት እና ውሸቱን በመቀጠልም መርማሪ
ፖሊስ ጆንሰን አንቺን እንደዚያ መናገር
አልነበረበትም።” አላት።
“መልካም” አለች እና ኒኪ በመቀጠልም “ግን እኮ ለጥፋቱ ይቅርታ መጠየቅ ያለበት እሱ እንጂ አንተ መሆን አልነበረብህም። አይመስልህም?”
ጉድማንም ትከሻውን ሰብቆ “እኔ እና እሱ ባልደረቦች አይደለንም። በዚያ
ላይ ደግሞ ለጥፋቱ ይቅርታ መጠየቅ አንደኛው የእሱ ችግር ነው እና እኔ
ልጠይቅለት ብዬ ነው” አላት።
ኒኪም ሳቀች እና “አሁን ገባኝ” አለችው። መርማሪ ፖሊስ ጉድማን ለማውራት ቀለል የሚል ሰው ስለሆነ ደስ ብሏታል “መቼስ እየዋሸሁ እንዳልሆነ ይገባሃል ብዬ አስባለሁ።” ብላ በማስከተልም “ባለፈው ምሽት እኔ የምኖርበትን ቦታ የሚያውቅ ሰው መኖርያ ሰፈሬ ድረስ መጥቶ በመኪና ገጭቶ ሊገድለኝ ነበር” አለችው፡፡
አምንሻለሁ” አላት እና ጉድማን በማስከተልም “ጆንሰንም ቢሆን
ያምንሻል። ምክንያቱም የምርመራ ቴክኒሽያኖችን ብዙ ብዙ ማስረጃዎችን
ከአካባቢው ላይ ሰብስበዋል”
“እውነትህን ነው?” ብላ ኒኪ የመገረም ፊት እያሳየች “ታዲያ ለምንድን ነው እኔን የቀን ቅዠተኛ እያለ የሚወነጅለኝ? እኔ ምን አድርጌ ነው?”
“እሱን እንኳን አላውቅም” ብሎ ለሰኮንዶች ያክል ዝም ብሎ ቆየ፡፡
ከዚያም “ምናልባት እኔ እና አንቺ ሆነን እሱ አንቺን ለምን እንደዚህ
እንደሚመለከትሽ ኋላ ላይ እንደርስበታለን፡፡ መጠጥ ልጋብዝሽ ዶ/ር
ሮበርትስ?”
ሎስ አንጀለስ ውስጥ ብዙ ሰው ወደማይበዛበት ጎዳና ታናስ ወደ ተባለ
ባር ይዟት ሄደ:: ኒኪ ጃክ ዳንኤልን አዘዘች እና ሲቀዳላት ብርጭቆውን
( ጉድማን አስተናጋጁ ሙሉውን ጠርሙስ ጠረጴዛው ላይ ትቶት እንዲሄድ
ሙሉውን መጠጥ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠችው። በዚህም የተበረታታው
በምልክት ነገረው እና ትቶላቸው ሄደ፡፡
“ባለፈው ምሽት ላይ እኔን መኪና ገጭቶ ሊገድለኝ የነበረው ሰው ሊዛን እና ትሬይን የገደለው ሰው ነው ብለህ ታስባለህ?” ብላ በቀጥታ ጠየቀችው።
“ምናልባት እራሱ ወይንም እነርሱን ከገደለው ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ሰው ነው ብዬ አስባለሁ ብሎ ጉድማን
መጠጡን ተጎንጭቶ ከመጀመሪያው ጊዜ ጀምሮ ገዳዩ አላማ ያደረገው አንቺን ነው ብዬ ነው የማምነው።” አላት፡፡
ኒኪ ለሊዛ ፍላንገን ባዋሰቻት የዝናብ ኮቷ የተነሳ ኒኪን መስላቸው በስህተት እንደገደሏት ጭምር ግምቱን ነገራት፡፡ በዚያ ላይ ባለፈው ማክሰኞ የተሞከረባት ግድያ የሚያመለክተው ኒኪ ከሊዛ እና ከትሬይ ጋር ባላት ግንኙነት ምክንያት ግድያዎቹ እንደተከወኑ ጭምር አስረዳት፡፡
“ልክ ነህ እንበል እሺ” ብላ ኒኪ በእርጋታ መለሰችለት እና “እሺ እነዚህ ሰዎች እኔን ለመግደል እየተከታተሉኝ ነው ልበል። ግን እነዚህ ሰዎች እኔን ለመግደል ለምንድነው የሚፈልጉት? ምንድነው ምክንያታቸው?”
“አሁን ላይ አንቺን ለመግደል ምክንያታቸው ምን እንደሆነ አላውቅም”
ብሎ ጉድማን በመቀጠልም “ግን ሊዛን እና ትሬይን የገደሉት ሰዎች ሁለቱንም ሰዎች አሰቃይተዋቸው ነው። ሰዎቹ ደግሞ ሰዎችን የሚያሰቃዩት
የሆነ መረጃን እንዲሰጧቸው ስለሚፈልጉ ነው። አይመስልሽም?” ብሎ
ጠየቃት፡፡
ኒኪም ለአፍታ ያህል ስታስብ ቆይታ “እኔም እንደዚያ አስቤው ነበር።
ግን ደግሞ ገዳዮቹ በሰዎች ስቃይ የሚደሰቱ ሳዲስቶች ቢሆኑስ?” ብላ
ጠየቀችው፡፡
ጉድማንም መጠጡ ያለበት ብርጭቆ ላይ እንዳፈጠጠ ይህም ሊሆን
ይችላል ብሎ አሰበ፡፡
“የሞቱት ሰዎች ላይ የሌለ የሞተ ሰው ህዋስ ተገኝቷል የሚባለው ነገር
እውነት ነው?” ብላ ኒኪ ጠየቀችው፡፡
ጉድማንም በጥያቄዋ በጣም ደንግጦ “ይህንን ደግሞ ማነው የነገረሽ?”
“ከኢንተርኔት ላይ አንብቤው ነው” ብላ ኒኪ በመቀጠልም “የዞምቢ ገዳይ በሚል ርዕስ ዙሪያ በኢንተርኔት ላይ ሰዎች ዜናውን እየተቀባበሉት ነው” አለችው፡፡
ጉድማንም በሰማው ነገር በጣም በሸቀ። ይህን የመሰለ መረቅ መረጃቸው ከእነርሱ አፈትልኮ ከወጣ በኋላ ደግሞ ነገሩ እየሰፋ ይሄድ እና የአሽሙር ጋዜጣ ገፆች ላይ ይወጣል ብሎ አሰበ፡፡
“እውነት ነው ነገሩ” ብላ ኒኪ ተጭና ጠየቀችው፡፡

👍1