#ምንም_አልል...
እኽ..ሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የደቂቅ እድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ፥ ጊዜዬን እያሠላሠልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር ፥ እየደገምኩ እያሠለሥኩ
ሳልሰለች እየመላለስኩ......
እኽ ሺ እንግዲህ በፀጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለች እየደጋገምኩ
በእግረ ህሲና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ......
እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አመሰክርም
አልልም። ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያሰጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያዳውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጂ ፥ ሌላ ምንም ምንም አልል።
ጥቅምት ፦ ፲፱፻፷፫ ፒያሳ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን
" እሣት ወይ አበባ "
እኽ..ሺ እንግዲህ በዝምታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የደቂቅ እድሜን ትዝታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
እያዳመጥኩ እያስታመምኩ ፥ ጊዜዬን እያሠላሠልኩ
ሳልናገር ሳልጋገር ፥ እየደገምኩ እያሠለሥኩ
ሳልሰለች እየመላለስኩ......
እኽ ሺ እንግዲህ በፀጥታ
የልቤን ደም ሥር ትርታ
የእስትንፋሴን ቃል ጉምጉምታ
ትር ስትል አፍታ ለአፍታ
ሳልሰለች እየደጋገምኩ
በእግረ ህሲና እያደቀቅኩ
እየቋጠርኩ እየቆጠርኩ......
እሺ እንግዲህ አልናገርም
በአንደበቴ አልተነፍስም
በልሳኔ አመሰክርም
አልልም። ምንም አልልም
እንዲያው ዝም እንጂ ዝም ዝም
የልቤ ደም ሥር ሲያቃጭል
ልሳኔን ሲያስነሳ ሲያሰጥል
ቃላቴን ሲቃኝ ሲያጋግል
ትንፋሼን ሲያንር ሲያዳውል
ክል ሲል ትር ድም ሲል
ማዳመጥ ማስታመም እንጂ ፥ ሌላ ምንም ምንም አልል።
ጥቅምት ፦ ፲፱፻፷፫ ፒያሳ
ሎሬት ፀጋዬ ገብረ መድሕን
" እሣት ወይ አበባ "