አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#አታውቃት #እንደሆን
ሰው እንደ ሰው ቢቆም ፥ በእናት ሐገር ምድሩ
ያለዋጋ አይደለም ፥ ወዲህ ነው ምሥጢሩ
አያት ቅድመ አያቱ ፥ ጠላትን ሲመቱ
እንደዝናብ ሲወርድ ፥ የጥይት መዓቱ
ሲንጣጣ ሲያሽካካ ፥ ጦር አውርዱ ኹላ
ያፈገፈገ የለም ፥ ከቶም ወደ ኋላ።
ከኋላ ምሽት አለች ፥ ከአንድ ወንዝ የተቀዳች
ከቀሚሷም ወርዶ ፥ የሚድኹ ልጆች
የእርሻም መሬት አለ ፥ በላብ ወዝ የራሰ
የሽምብራ ጥርጥር ፥ በወግ ያደረሰ
የቤተስኪያን ደውሉ ፥ የመስኪድ አዛኑ
ኢምንት እምነቱ ናት ፥ የሰው ማዕዘኑ።
አይሸሽም አይፈራም ፥ ያቅራራል ቀረርቶ
ሽለላ ያሰማል ፥ ዘራፍ ደረት ነፍቶ
ግዳይ እንደ ጣለ ፥ በሞት ነው የሚፈካ
ከጠላ ጠላ ነው ፥ ከማረም አይነካ
ጀግና ዕድሜ እየተጫነው ፥ ምን በመልኩ ቢጃጅ
ፈርቶ ሞት አያውቅም ፥ ጦር ቀምሶ ነው 'ሚባጅ።
ቆመህ ስትራመድ ፥ ዛሬ በነጻነት
ደፍረህ ስትናገር ፥ ቀና ብለህ ካንገት
ትርጉሙ እንዲገባህ ፥ ውሉን እንዳትስተው
ኢትዮጵያዊነትህን ፥ ሀ ብለህ መርምረው።
የማንነት ካስማዋ ፥ የአንድነት ማማዋ
አታውቃት እንደሆን ፥ ይህቺው ናት ዓድዋ።

🔘እሱባለው አበራ🔘