#የፈጣሪ_ልሳንእጆቼን ዘርግቼ . . .
ልጸልይ፣ ልማልድ ፣ ከደጅኽ ተገኘኹ፤
አንጋጥጬ ሽቅብ በሐሳቤ ዋኘኹ።
ተንበርክኬ ለምሕላ በግንባሬ ተደፍቼ
ቀና ማለት ተዘነጋኝ ፤ የቃል ጸሎት ረስቼ።
ያ'ንደበትኽ
ልሳን ከየት ተሠወረ?
ቃል ከምላሴ ላይ እንደምን ታወረ ?
ዝም ...!
ዝም ዝም . . .!
እንደው ዝም! ዝምታዬ ቀረ ፤
ሰምተኸኛል አንተ ፤
በዝምታ
ልሳን ጸሎቴም ሰመረ።
🔘ተስፋሁን ከበደ
🔘