አትሮኖስ
286K subscribers
118 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሰው_አፈር

አዕዋፍ በሰማይ ላይ ሲበሩ
በማራኪ ዜማቸው ሲዘምሩ፤
ውብ ተፈጥሯቸው ይደንቀኛል
እኔም ወፍ በሆንኩ ያሰኘኛል፡፡

እንስሳትም በየፊናቸው
ተመሳስለው ከአካባቢያቸው ፤
በጎጡ በስርጓጉጡ
ሲሽሎከሎኩ ሲሮጡ፤
ውብ ተፈጥሯቸው ይስበኛል
ፈጣሪ ስራው ይደንቀኛል፡፡

አንዱ ከዛፍዛፍ ሲዘል - ሌላው በመሬት ሲንፏቀቅ
አንዱ በሰማይ ሲበር - ሌላው ውሐ ውስጥ ሲሞላቀቅ፤
አንዱ ጮማውን ሲቆርጥ
ሌላው ደግሞ ሳሩን ሲግጥ፤
ልዩነታቸውን መመልከት - ሲሽቀዳደሙ ማየት
አቻ የሌለው ቲያትር - ተፈጥሯዊ ድንቅ ተውኔት።

ታዲያ
ከዚህ ሁሉ ውብ ተፈጥሮ - ከዚህ ሁሉ ትዕይንት
ለተመልካች የሚደንቀው - የሚገርመው አስቂኝ ትርዒት
አፈር -አፈርን ሲንቅ
አፈር - ከአፈር ሲተናነቅ፣
አፈር - በአፈር ላይ ሲያሴር
አፈር - ለአፈር ሲቆፍር..
..እንደ አፈር ቁጭ ብሎ ማየት።

🔘?🔘