#ሰው_መሆን_ምንድን_ነው???
..እናልሽ ቆንጅቴ
የሆነ ዕለት ማታ
ገና አይኗ ያልበራ - የውሻ ቡችላ
ከእናቷ ተነጥቃ - መንገድ ዳር ተጥላ፣
ያውም በክረምቱ
ያውም በምሽቱ፣
እናቴን፣
ሙቀቴን፣
ህይወቴን እያለች
ቱቦ ስር ተኝታ - ታለቃቅሳለች፡፡
ምናልባት ሌሊቱን
ዝናብ ከዘነበ - ጎርፉ ይወስዳታል
ጎርፍ ካልወሰዳት
ራቱን ፍለጋ የወጣ ቀበሮ - ራት ያደርጋታል፡፡
ይህንን ስታይ - መኖር ይገርምሻል
ህይወት ግን ምንድን ነች?- ያፈላስፍሻል፡፡
ደግሞ በሌላ ቀን
አያቴ 'ሚሆኑ - እድሜ ጠገብ ባልቴት
በጠራራ ፀሐይ - ጥላ በሌለበት፣
ከአካላቸው ሚገዝፍ - የእንጨት ክምር አዝለው
ገዢ ይመኛሉ - ገንዘብ ተስፋ አድርገው፡፡
አንዲት ወጣት መጥታ - እየተቻኮለች
እንጨቱን ለመግዛት - ባልቴቷን ጠየቀች፤
“ስንት ነው?” ጠየቀች ወጣቷ
“ሃያ ብር” መለሱ አሮጊቷ፣
“ቀንሱልኝ ማዘር?”
“አስራ ስምንት አርጊው”
“አስራ አምስት ልውሰደው?”
“አላነሰም ልጄ?”
“ይህንም ማደርገው- ከምዞር ብዬ ነው!”
“በ...ይ እሽ ውሰጅው”::
ይታይሽ እንግዲህ
ሌሊቱን በሙሉ - የተጓዙበትን
መቼም ላይቃኑ - የጎበጡበትን፣
ከአራዊት ጋር ታግለው - ያመጡትን እንጨት
በአንድ ቢራ ዋጋ - አስራ አምስት ብር ሽጡት፡፡
አስራ አምስት ብር ብቻ!!!
አየሽ ያቺ ወጣት የ'ሷ ድካም እንጅ የባልቴቷ ኑሮ
አላስጨነቃትም
የምታወጣቸው አምስት ብሮች እንጅ - የአሮጊቷ ድካም
አላሳሰባትም፡፡
ይህንን ስታይ እንባ ያስወጣሻል
“መተዛዘን የታል?” ግራ ያጋባሻል፡፡
ትላንትና ደግሞ
በአንድ ቴሌቪዥን - ሰበር ዜና አይቼ
ሲያስታውከኝ አደርኩ - ከእንቅልፍ ተፋትቼ፤
ምን አየሁ መሰለሽ :-
አንድ የሰዎች ቡድን - ሰዎችን አግቶ
ሁሉንም በአንድ ላይ - ጠባብ ቤት ውስጥ ዘግቶ፣
እንደ በቆሎ እሸት - እያንከባለለ
ከነህይወታቸው - በእሳት አቃጠለ፡፡
በስመ አ..........ብ!!!
ይህንን ስታይ ህይወት ያስጠላሻል
የሰው ልጅ ምንድን ነው?' ያወዛግብሻል::
ታዲያ ግን አለሜ፤
ስንቱን ጉድ አይቼ፣
ስንቱን ጉድ ሰምቼ፣
በብዙ ቆስዬ፣
በብዙ ነድጄ፣
ነድጄ
ነድጄ........
አንቺን እንዳገኘሁ
ያስከፋኝን ሁሉ በአንዴ ረሳውና-
«ይህች ዓለም ጣፋጭ ነች - ቆንጆ ነች!› እላለሁ፡፡
እውነቴን ነው ምልሽ
አንቺን እንዳገኘሁ፡-
ባገባኋትና - አይኔን በአይኔ አይቼ
እስከፍፃሜየ - በኖርኩ ተደስቼ!
እያልኩ አመኛለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ምኞቴ - ለኔም ይገርመኛል
'ሰው መሆን ምንድን ነው?” - ውስጤ ይጠይቀኛል፡፡
ምስኪኗን ቡችላ - በቆፈኑ ክረምት - ቱቦ ስር የጣሏት
ደካማዋን ባልቴት - ከእንጨት አሳንስው - ጣል ጣል ያረጓት፣
ስውን ሚያህል ፍጡር- ከነህይወታቸው - በእሳት ያጋዩዋቸው
እውነት ሰዎች ናቸው?
እኔ ራሴስ ብሆን?
ይህን ሁሉ ህመም - እያየሁ ያስቻለኝ
በምችለው መጠን - ርዳታ ፈላጊን - መርዳት የተሳነኝ
ጭራሽ ከአንቺ ጋራ - ሁሉን ረስቼ - መቦረቅ የሚያምረኝ
እውን እኔ ሰው ነኝ ??
ልጠይቅሽ እስኪ፡-
የምስኪኗን ጩኸት፣
የባልቴቷን ብሶት፣
የንፁሃንን ሞት፣
የሰውን ልጅ እክል፣
የምድርን ምስቅልቅል፣
አንቺ ካስረሳሺኝ
ጠቀምሽኝ?
ጎዳሽኝ?
ገደልሽኝ?
አዳንሽኝ?
መልስ እፈልጋለሁ
ሰው መሆን ምንድን ነው???
🔘መሉቀን ሰለሞን🔘
..እናልሽ ቆንጅቴ
የሆነ ዕለት ማታ
ገና አይኗ ያልበራ - የውሻ ቡችላ
ከእናቷ ተነጥቃ - መንገድ ዳር ተጥላ፣
ያውም በክረምቱ
ያውም በምሽቱ፣
እናቴን፣
ሙቀቴን፣
ህይወቴን እያለች
ቱቦ ስር ተኝታ - ታለቃቅሳለች፡፡
ምናልባት ሌሊቱን
ዝናብ ከዘነበ - ጎርፉ ይወስዳታል
ጎርፍ ካልወሰዳት
ራቱን ፍለጋ የወጣ ቀበሮ - ራት ያደርጋታል፡፡
ይህንን ስታይ - መኖር ይገርምሻል
ህይወት ግን ምንድን ነች?- ያፈላስፍሻል፡፡
ደግሞ በሌላ ቀን
አያቴ 'ሚሆኑ - እድሜ ጠገብ ባልቴት
በጠራራ ፀሐይ - ጥላ በሌለበት፣
ከአካላቸው ሚገዝፍ - የእንጨት ክምር አዝለው
ገዢ ይመኛሉ - ገንዘብ ተስፋ አድርገው፡፡
አንዲት ወጣት መጥታ - እየተቻኮለች
እንጨቱን ለመግዛት - ባልቴቷን ጠየቀች፤
“ስንት ነው?” ጠየቀች ወጣቷ
“ሃያ ብር” መለሱ አሮጊቷ፣
“ቀንሱልኝ ማዘር?”
“አስራ ስምንት አርጊው”
“አስራ አምስት ልውሰደው?”
“አላነሰም ልጄ?”
“ይህንም ማደርገው- ከምዞር ብዬ ነው!”
“በ...ይ እሽ ውሰጅው”::
ይታይሽ እንግዲህ
ሌሊቱን በሙሉ - የተጓዙበትን
መቼም ላይቃኑ - የጎበጡበትን፣
ከአራዊት ጋር ታግለው - ያመጡትን እንጨት
በአንድ ቢራ ዋጋ - አስራ አምስት ብር ሽጡት፡፡
አስራ አምስት ብር ብቻ!!!
አየሽ ያቺ ወጣት የ'ሷ ድካም እንጅ የባልቴቷ ኑሮ
አላስጨነቃትም
የምታወጣቸው አምስት ብሮች እንጅ - የአሮጊቷ ድካም
አላሳሰባትም፡፡
ይህንን ስታይ እንባ ያስወጣሻል
“መተዛዘን የታል?” ግራ ያጋባሻል፡፡
ትላንትና ደግሞ
በአንድ ቴሌቪዥን - ሰበር ዜና አይቼ
ሲያስታውከኝ አደርኩ - ከእንቅልፍ ተፋትቼ፤
ምን አየሁ መሰለሽ :-
አንድ የሰዎች ቡድን - ሰዎችን አግቶ
ሁሉንም በአንድ ላይ - ጠባብ ቤት ውስጥ ዘግቶ፣
እንደ በቆሎ እሸት - እያንከባለለ
ከነህይወታቸው - በእሳት አቃጠለ፡፡
በስመ አ..........ብ!!!
ይህንን ስታይ ህይወት ያስጠላሻል
የሰው ልጅ ምንድን ነው?' ያወዛግብሻል::
ታዲያ ግን አለሜ፤
ስንቱን ጉድ አይቼ፣
ስንቱን ጉድ ሰምቼ፣
በብዙ ቆስዬ፣
በብዙ ነድጄ፣
ነድጄ
ነድጄ........
አንቺን እንዳገኘሁ
ያስከፋኝን ሁሉ በአንዴ ረሳውና-
«ይህች ዓለም ጣፋጭ ነች - ቆንጆ ነች!› እላለሁ፡፡
እውነቴን ነው ምልሽ
አንቺን እንዳገኘሁ፡-
ባገባኋትና - አይኔን በአይኔ አይቼ
እስከፍፃሜየ - በኖርኩ ተደስቼ!
እያልኩ አመኛለሁ፡፡
ታዲያ ይህ ምኞቴ - ለኔም ይገርመኛል
'ሰው መሆን ምንድን ነው?” - ውስጤ ይጠይቀኛል፡፡
ምስኪኗን ቡችላ - በቆፈኑ ክረምት - ቱቦ ስር የጣሏት
ደካማዋን ባልቴት - ከእንጨት አሳንስው - ጣል ጣል ያረጓት፣
ስውን ሚያህል ፍጡር- ከነህይወታቸው - በእሳት ያጋዩዋቸው
እውነት ሰዎች ናቸው?
እኔ ራሴስ ብሆን?
ይህን ሁሉ ህመም - እያየሁ ያስቻለኝ
በምችለው መጠን - ርዳታ ፈላጊን - መርዳት የተሳነኝ
ጭራሽ ከአንቺ ጋራ - ሁሉን ረስቼ - መቦረቅ የሚያምረኝ
እውን እኔ ሰው ነኝ ??
ልጠይቅሽ እስኪ፡-
የምስኪኗን ጩኸት፣
የባልቴቷን ብሶት፣
የንፁሃንን ሞት፣
የሰውን ልጅ እክል፣
የምድርን ምስቅልቅል፣
አንቺ ካስረሳሺኝ
ጠቀምሽኝ?
ጎዳሽኝ?
ገደልሽኝ?
አዳንሽኝ?
መልስ እፈልጋለሁ
ሰው መሆን ምንድን ነው???
🔘መሉቀን ሰለሞን🔘