አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ከዕለታት_ስምንት_ቀን (የሳምንት ፍቅር)

ከዕለታት አንድ ቀን፡-
እኔና ልጅቷ - ገና እንደተያየን
(ተዋደድን መሰል)
በጥቅሻ ተግባብተን - ስልክ ተቀያየርን፤

ከዕለታት ሁለት ቀን
ተቀጣጠርንና - ስልክ ተደዋውለን
ሻይ ቡና ልንል - ካፌ ውስጥ ተገኘን፤

ከዕለታት ሶስት ቀን
(እንደተገናኘን)
ብዙ ሳናወራ - ትንፋሽ ተቀያየርን
አንሶላ ተጋፈፍን፡፡

ከዕለታት አራት ቀን
ከዕለታት አምስት ቀን
ከዕለታት ስድስት ቀን
እየተጠራራን
ትንሽ እያወራን
ብዙ ፍቅር ሰራን፡፡

ከዕለታት ሰባት ቀን
(አንሶላ ውስጥ ሆነን)
“አንተ ማነህ?” አለች -
አንቺስ ማነሽ?” አልኳት
እሷን ነገረችኝ -
እኔንም ነገርኳት፤

ከዕለታት ስምንት ቀን
እኔም አልጠራኋት - እሷም አልደወለች
በሰባት ቀን ውሎ - ፍቅራችን አለቀች፡፡