አትሮኖስ
282K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
495 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ፍቅር_አያሸንፍም

ህፃን
ልጅ
አዋቂው
ወጣት ሽማግሌው ፥ ረጋሚ መራቂው
በአንደበቱ ማህፀን
ፍቅር ያሸንፋል”
የሚል ጥቅስ አርግዞ ፥ በምላስ ይወልዳል
ፍቅር ግን ሁል ጊዜ
እየተሸነፈ ፣ መሸነፍ ይወዳል።

አቅመ ቢስ ነው አቅሙ ፥ ወዋረድ ነው ልኩ
ሁሌም መሽነፍ ነው
ሁልጊዜ መውደቅ ነው ፥ የፍቅር ታሪኩ።
ርሐብተኛ ነው
አይበላም አይጠጣም ፣ ንብረት አያፈራም
አይደፍርም አይፈራም
አይጠፋም አይሰራም
ፎቅ አይደረድርም ፥ ቪላ ቤት አይሰራም
ማደሪያው በረት ነው ፥ ሲታይ ስጋ ለብሶ
ባሪያ ነው አንግሶ
ሁሌም ዝቅ ያለ ነው ፥ ከፍታ ላይ ደርሶ።

ፍቅር ይሸነፋል!
መንገድ ምራን ላሉት ፥ መንገድ ሆኖ ያርፋል
ሁሉ ይረግጠዋል
መልኮት ኋይል አለው ፥ በሰው ይገረፋል
በሰማይ ሲሾሙት ፥ ወደምድር ይጠፋል
አንድ ሀገር የለውም
የትም ቦታ አለ ፥ እየተሰደደ
ሁሌ እንደተገፋ ፥ እንደተዋረደ
ዝቅ ይሎ ይኖራል
ዝቅ ብሎ ያድራል
ቃል አይናገርም ፥ ስንጥለው ጠልፈን
እርቃን ስናስቀረው
ልብሱን ከአደባባይ ፥ ከገላው ላይ ገፍፈን
ፀሐይ ላይ ተጥደን
ውርጭ ስናስመታው ፥ ስናለብሰው ቆፈን
ከሀገር ስናስወጣው ፥ ካንጀት ተፀይፈን
ጥለነው ስንሔድ ፥ ስናገኘው አልፈን
ትንፋሽ አይወጣውም
ለሁሉ መንገድ ነው ፥ መሔጃ የለውም።
ሁሉን ይከተላል
ለሁሉ ዝቅ ይላል
እረኛ ሲያደርጉት ፥ በግ መሆን ይመርጣል
ዘጠና ዘጠኝ በግ
ሜዳ ላይ በትኖ
አንድ የጠፋ በጉን ፥ ፍለጋ ይወጣል
አይቀድም ይሮጣል
አይሸሽም ያመልጣል
አይተኛም ያደፍጣል
ሲሰድቡት ቃል ያጣል
ቃል ሆኖ ይመጣል
ህያው ነው ስንለው
መቃብር ይወርዳል ፥ በሙታን ተገድሎ
ይነሳል ሲቀብሩት ፥ ከሞት ተነጥሎ
ባሪያ ነው ለሁሉ
መንግስቱን የሚያወርስ ፥ ከምንዱባን ውሎ።

አቅሙ አቅመ ቢስ ነው ፥ ሽንፈት ነው እድሉ
ወርዶ መገኘት ነው
ማጎንበስ ነው እጣው ፥ መረታት ነው ውሉ
ዝቅ ብሎ መኖር ነው ፥ እቅድና አቅሉ
ዝም ነው ስንገርፈው
ዝም ነው ስንዘልፈው
ጭጭ ነው ስንጠልፈው
ቃላት አይወጣም
ራሱ ግን ቃል ነው ፥ የቃሉ እስረኛ
ፍቅር ሲሸነፍ ነው
ፍቅር ያሸነፈ ፥ የሚመስለን ለኛ!

ያንሳል ስናገዝፈው
ቀድሞ ይጠብቃል ፥ ትተነው ስናልፈው
እየተሸነፈ
በመሸነፉ ነው ፣ ፍቅር ያሸነፈው።

🔘በላይ በቀለ ወያ🔘