አትሮኖስ
281K subscribers
111 photos
3 videos
41 files
480 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ሮሜዎና_ዡልዬት


#ክፍል_አስራ_ሶስት

#በአባ_ሎራ_ቤት

አባ ፡ ዮሐንስ ፡ (ከውጭ ፡ መጣ) ።
ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው ፡ አባቴ ፡ አባ ፡ ሎራ ?

#አባ_ሎራ
ተሳሳትኩ ፡ ብዬ ፡ በልቤ ፡ ባልፈራ ፡
በድምፅህ ፡ መሰልከኝ ፡ የኛ ፡ አባ ፡ ዮሐንስ ።

#አባ_ዮሐንስ
ዐውቀሃል ፡ እኔ ፡ ነኝ ።

#አባ_ሎራ
አንተ ፡ እስክትመለስ ፡
እጠብቅህ ፡ ነበር ፡ ቸኩዬ ፡ ባሳቤ ፡
ፈጥነህ ፡ ደረስክልኝ ፡ ስሥጋ ፡ በልቤ ፡
መልሱን ፡ ከሮሜዎ ፡ ለጻፍኩት ፡ ደብዳቤ አመጣህልኝ ፡ ወይ ?እስቲ ቶሎ ፡ ስጠኝ፤

#አባ_ዮሐንስ
የሆንኩትን ፡ ነገር ፡ ልንገርህ ፡ አድምጠኝ
ደብዳቤህን ፡ ቶሎ ፡ ለመስጠት ፡ ወስጄ
አንዱን ፡ የኛ ፡ ካህን ፡ ልፈልገው ፡ ሄጄ ፡
ወደ ፡ ሮሜዎ ቤት፡ እንዲወስድኝ መርቶ :
እሱም ፡ እሺ ፡ ብሎ ፡ ሊወስደኝ ፡ ተነሥቶ
ዘበኞች ፡ መጡና ፡ ከቤት ፡ እንዳንወጣ ፡
ዘግተውብን ፡ ሄዱ፤ ከውጭ ፡ የመጣ ፡
በሽታ ፡ ስላለ ማንም ፡ ከሌላ ፡ አገር፡
ሲመጣ ፡ አስቀድሞ ፡ ለካ ፡ እስቲመረመር
ለብቻው ፡ እንዲሆን ፡ የመጣው ፡ ሥራቱ፡
የሚያስገድድ ፡ ኖሮ ፡ ሳልሄድ ወደ ፡ማንቱ
ሮሜዎን ፡ ሳላገኝ ፡ ሳላየው ፡ ደርሼ
ያንተንም ፡ ደብዳቤ ፡ አመጣሁ ፡ መልሼ
ልልከው ፡ አስቤ ፡ ብሞክር ፡ ብለፋ:
ብጠይቅ ባስጠይቅ የሚላክ ሰው ፡ ጠፋ፡
አልሆንልህ ፡ አለኝ ፡ ነገር ፡ አልሳካ ፤
ይቅርታ ፡ አድሮግልኝ ፡ ደብዳቤህን፡እንካ ። (ሰጠው)

#አባ_ሎራ
ምንኛ ፡ መጥፎ ፡ ነው ፡ያመጣኸው ወሬ !
አይ ፡ አባ ፡ ዮሐንስ ፡ ጉድ ሰራኸኝ ፡ ዛሬ ።
መልክቴ ፡ በውነቱ፡ ትልቅ ጕዳይ ፡ ነበር ፤
በጣም ፡ የከበደ ፡ ከፍ ያለ'ቁም ፡ ነገር ፡
ባለመፈጸሙ ፡ የመልክቴ ፡ አደራ ፡
እጅግ ፡ የሚያሳዝን በጣም የሚያስፈራ፡
ነገር ፡ ለማስከተል ፡ ይችላል ፡ ወዳጄ ፤
ጽፌ ፡ የሰጠሁህ ፡ ያ ፡ ወረቀት ፡ በእጄ ፡
ለሮሜዎ ፡ ቶሎ ፡ መድረስ ፡ ነበረበት ፤
አይ ፡አባ ዮሐንስ ጕድ ሠራኸኝ በውነት !
እባክህ ፡ አሁንም ፡ ቶሎ ፡ እንረዳዳ ፤
ጕጠት ፡ ፈልግና ፡ አምጣልኝ ፡ ከጓዳ ።

#አባ_ዮሐንስ
ሳልችል ፡ ቀርቼ ፡ ነው ፡ በጣም ፡ ተቸግሬ ፡
ምን ፡ ሁን ፡ ትለኛለህ ፡ ስቀመጥ ፡ ታስሬ ፡
እንዴት ፡ ብዬ ፡ ልሂድ እንደ ፡ ምን ፡ አድርጌ
መልካም ነው ጕጠቱን ላምጣልህ ፡ ፈልጌ
(አባ ፡ ዮሐንስ ፡ ወደ ፡ ጓዳ ፡ ገባ) ።

#አባ_ሎራ ፡ (ብቻውን) ።
ከዡልዬት ፡ መቃብር ፡ ብቻዬን ፡ ገሥግሼ ፡
መዝጊያውን ፡ ልከፍተው ፡ በቶሎ ፡ ደርሼ
መድረስ ፡ ይገባኛል ፡ በቶሎ ፡ በቅጽበት
ጊዜው ፡ ደርሷልና ፡ የምትነሣበት ።
በተነሣች ፡ ጊዜ ፡ ሮሜዎን ፡ ስታጣ ፡
እንደ ፡ ምን ፡ ትረግመኝ ፡ በንዴት ፡ በቍጣ
አምጥቼ ፡ ላስቀምጣት ፡ በቤቴ ፡ ሸሽጌ ፤
ከዚያም ፡ እንደ ፡ ገና ፡ አንድ ፡ሰው ፡ ፈልጌ
ደግሞ ፡ ለሮሜዎ ፡ ሲሆን ፡ ዛሬ ፡ ማታ ፡
ጽፌለት ፡ ይመጣል ፡ ሁሉንም ፡ ሐተታ ።

(ፓሪስ ፡ ካሽከሩ ፡ ጋር ፡ አበባና 'መብራት ፡ ይዞ ፡ ወደ ፡ ዡልዬት ፡መቃብር ፡ መጣ) "

#ፓሪስ
መብራቱን አጥፋው እንግዲህ ይበቃል
ሰው የመጣ፡እንደሆን ምናልባት ማን ያውቃል
እዚህ ፡ ሰው ፡ እንዲያየኝ ፡ አልፈልግምና
በል ፡ ቅረብ ፡ተጠጋ ፡ አንተም ወደዚህ ፡ና።
ጀሮህን ፡ አቁመህ ፡ ተጠንቅቀህ ፡ ስማ ፤
ኰሽታ ፡ ስትሰማ ፡ ወይም ፡ የሰው ፡ ጫማ
ምልክት እንዲሆን አፏጭተህ አስታውቀኝ ፡
አስቀድሜ ፡ እንዳውቀው ፡ ፈጥነህ ፡ አስጠንቅቀኝ፤
በል ፡ እንግዲህ ፡ አሁን ፡ አበባውን ፡ ስጠኝ ።
(ፓሪስ ፡ ሄደ) ።

#አሽከር ፡ (ብቻውን) ።
የተሻለ ፡ ስፍራ ፡ ባገኝ ፡ ደግ ፡ ነበር ፤
ይህ ፡ ቦታ ፡ ቀፈፈኝ ፡አልወድም ፡ መቃብር
(እልፍ ፡ ብሎ ፡ ሄደ ) ።

#ፓሪስ ። (በዥልዬት ፡ መቃብር ፡ ላይ) ።
ይህንን ፡ አበባ ፡ መርጨ፡ ፈልጌ ፡
ላቀርብልሽ ፡ መጣሁ ፡ በረከት ፡ አድርጌ
ገጸ ፡ በረከቴ ፡ ጸጸት ፡ ነው ፥ አበባ ፤
ሐዘን ፡ ነው ፡ ለቅሶ ፡ ነው ፡ የመረረ ፡ እንባ
ትተሽኝ ፡ ብትሄጂ ፡ ብቻዬን ፡ ቀርቼ ፡
ልጐበኝሽ ፡ መጣሁ ፡ ሌሊት ፡ ተነሥቼ ።
(አሽከሩ ፡ አፏጨ) ።
እንሆ ፡ አፏጨ ፡ ሰማሁት ፡ አሽከሬ ፤
አሁን የሚመጣ ሰው፡ ነው ወይስ አውሬ ?
ሰላም ፡ የሚነሳኝ ማነው፡ ባሁን ፡ ሰዓት ?
እንዴት ? ደግሞ ፡ ያውም፡ይዟል ፡ በእጁ ፡ መብራት!
እስክረዳው ፡ ድረስ ፡ ምስጢሩን ፡ ዐውቄ ፡
ከለላ፡ፈልጌ፡ልየው ፡ተደብቄ (እልፍ፡ ብሎ ተደበቀ)

(ሮሜዎና ፡ ቤልሻጥር ፡ መብራትና ጉጠት ፡ ይዘው ፡ መጡ) ።

#ሮሜዎ
በል መብራቱን ስጠኝ፤ አንተ ግን ተመለስ
እገባለሁ ፡ እኔ ፡ መቃብሯ ፡ ድረስ ፤
አንተ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ እንዳትንቀሳቀስ ፡
ዦሮህን ፡ አቁመህ ፡ ሰው ፡ ሲመጣ ፡ ስማ
ተደብቀህ ፡ ጠብቅ ፡ እዚህ ፡ በጨለማ ።
ያየህ ፡ እንደ ፡ ሆነ ፡ ሰው ወዲህ ሲመጣ፡
ከተደበቅህበት ፡ ቦታ ፡ ሳትወጣ ፡
በፉጨት ፡ ምልክት ፡ እኔን ፡ አስጠንቅቀኝ
ምናልባት ፡ ሰው ደርሶ ድንገት ፡ እንዳያየኝ
የዡልዬት ፡ ሬሳ ፡ ካለበት ፡ ገብቼ ፡
በመቃብሯ ፡ ውስጥ ፡ እሷን ፡ ተመልክቼ ፡
ካየኋት ፡ በኋላ ፡ ከልቤ ፡ አልቅሼ ፡
አንብቼ ፡ ሲያበቃኝ ፡ ሐዘኔን ፡ ጨርሼ ፡
የጣቷን ፡ ቀለበት ፡ አውልቄ ፡ ከሷ ፡ ላይ ፡
ልወስድ ፡አስቤያለሁ ላንድ ብርቱ ጕዳይ
ከወጣሁ ፡ በኋላ ፡ እኔ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡
ይህንን ፡ ደብዳቤ ፡ ጨምረህ ፡ ሰላምታ ፡
ላባቴ ፡ ስጥልኝ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ ተጠንቀቅ ፤
ምን ፡ ይሠራል ፡ ብለህ፡ አሳቤን ፡ ለማወቅ
መሰለል ፡ አስበህ ፡ ወደ ፡ እኔ ፡ አትጠጋ ፤
ያገኝሃልና ፡ የመሞት፡ አደጋ ፡
በውነቱ ፡ ባገኝህ ፡ ይህንን ፡ ስትሠራ ፡
እጄም ፡ አያዝንልህ ፡ መንፈሴም ፡ አይራራ
ልብ ፡ በል ፥ተጠንቀቅ ለሕይወትህ ፡ ፍራ

#ቤልሻጥር
እኔ ፡ ከዚህ ፡ ቦታ ፡ አልንቀሳቀስም !
ስታስጠነቅቀኝ፡ትእዛዝ ፡ አላፈርህም። (ሮሜዎ'ሄደ)።

#ሮሜዎ ፡ (የዡልዩትን መቃብርዋን ' በር
ሊከፍት ፡ ይታገላል) ።
ከጥንት ፡ ጀምረህ ፡ ብትበላ ፡ ብትበላ ፡
ጠገብኩኝ ፡ የማትል ፡ ሆድህ ፡ የማይሞላ
መቃብር ፡የሚሉህ አንተ መጥፎ ከርሣም
ለወጣት ፡ አታዝን ፥ ለቆንዦ ፡ አትሣሣም
ዡልዬትን ፡ ከጥርስህ ፡ ፈልቅቄ ፡ ላወጣ ፡
መጥቻለሁና ፡ የዋጥከውን ፡ አምጣ ፡
አንዴ ፡ ልያትና ፡ እንባዬን ፡ አፍስሼ ፡
እርሜንም ፡ አውጥቼ ፡ ተራዬን ፡ አልቅሼ ፡
ሐዘኔን ፡ ገልጬ ፡ ከበቃኝ ፡ በኋላ ፡
እኔንም ፡ ከሷ ፡ ጋር ፡ አብረህ ፡ እንድትበላ

#ፓሪስ
መብራት ፡ በጁ ፡ ይዞ ፡ የመጣው ፡ ከደጅ
ሮሜዎ ፡ ይመስላል ፡ ያ የሞንታግ ፡ ልጅ፡
ጐበዙን ፡ ቲባልትን ፡ የዡልዬትን ፡ ዘመድ ፡
አሁን ፡ በቅርብ ፡ቀን ተጣልቶት ፡ በመንገድ
ገድሎ ፡ ተፈርዶበት ፡ ተሰዶ ፡ የወጣ ፡
አሁን ፡ ደግሞ ፡ እዚህ ፡ ምን ፡ ሊፈጥር፡ መጣ?

💫ይቀጥላል💫