አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
568 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ተፈጥሮን #ደጅ #ልጥና
" እኔ ልሙትልሽ እያልኩኝ አልምልም
ቃላቴን መንዝሬ፣ለሞት ቀብድ አልከፍልም
ያኔ ትዝ ይልሻል
"ራስህን ግደል" ብለሽ በረኪና የላክሽልኝ ጊዜ
እድሜ ለስጦታሽ፣ ታጠበ ሸሚዜ
ገደብ ጫፍ በሌለው፣ በልቤ መጋዘን
ቢታጨቅ መከራ፣ ቢጠራቀም ሀዘን
"ባለፈልኝ" እንጂ "በሞትኩ ብየ አላቅም
ካልጋ ላይ ነው እንጂ፣ ከፎቅ ላይ አልወድቅም
በሀኪሙ ስተት ፣በቁሜ ብከፈን
በወርድ በቁመቴ፣ ሳጥኔ ቢደፈን
ከጭስ እቀጥናለሁ፣ እኔ መውጫ አላጣም
በጠጅ በወይን አገር፣ሽጉጤን አልጠጣም።
የተመደበልኝ ዘመን ከባከነ
የተሰፈረልኝ ፣ቀን አልቆ ከሆነ
ተፈጥሮን ደጅ ልጥና
ባዲስ መንገድ ትስራኝ፣ባዲስ የፍጥረት ውል
መስኮትሽ ላይ ሆና
ስትዘምር የምትውል
ድንቢጥ ወፍ ታድርገኝ
ብኖር አንቺን አየሁ፣ ከመሞት ምን ሊገኝ?
➛ገጣሚ ፦በእውቄ