አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
567 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
Re.Post
#ለመለስ #የተፃፈ #ደብዳቤ
፨ ፨
.
.
እንደምን ነህ ጋሼ ፣እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ፣ ቀረህ ሳትመለስ?!
.
እኛማ ይሔውልህ
ባንተ ሌጋሲና ባንተ ትልቅ ራዕይ
በየአደባባዩ ስንል ነበር ዋይ ዋይ
አዎ ትዝ ይለናል
ጀነራልህ ሁሉ ፣ ተኩስ ነው ትእዛዙ
ወገን ይጥል ነበር ፣ የግፍ አፈሙዙ
ለምንድን ነው ስንል? ስምክን አስቀድመው
ከክርስቶስ በላይ ፣ምስልህን አትመው
ቅዱስ መፅሐፍ ይመስል
ባንተ ራዕይና በሌጋሲህ ምለው
ቢረፈርፉንም አላለቅንምና
ደብዳቤ ላክንልህ ከሞት የተረፍነው!
~
የሆነስ ሆነና ግን አንተ ደህና ነህ
እኛማ ይኸውልህ
ደርሰህ ስትናፍቀን
አይሞትም የምትል ሙዚቃ ሞዝቀን
መቃብርህን ልንስም ፣አበባ ልናኖር ፣ስላሴ ብንመጣ
ፌደራል ያይሃል ፣ እስረኛ ይመስል ፣ ሾልከህ እንዳትወጣ
መቼም ስላሴ ውስጥ...
ባለስም ነውና ፣ የሚቀበርበት
አንተን አየት አርገን ፣ ዞር ስንል ድንገት
እነፊታውራሪ
ግራ'ዝማች
ቀኝ'ዝማች
ፊተኛ ባለስም ፣ የሆኑት አባቶች
ያለዘብ ቆመዋል ፣ እነ አብዲሳአጋ
ጀግና መሃል ሳለህ ፣ ምነው በድንህ ሰጋ?!
~
የሆነስ ሆነና
ሃየሎም ደህና ነው
እዛም ትግል ይመራል?
እስር ቤት ሰባብሮ ፣ታራሚ ያስፈታል
እዛም ከፊት ሆኖ ፣ ጭቁን ያታግላል
እዛም በጀግንነት ፣ በለኮሳት ሻማ
ነፃ ነኝ ባለባት ፣ ርዕሰ ከተማ
ትንሽ ግሮሰሪ ፣ ይገባ ይሆን ደፍሮ?
እዛስ ጀማል ያሲን ፣ ፈጠረ አምባጓሮ?
ሃየሎምን ሰዋው ፣ በሐሺሽ ናላው ዞሮ?
።።
እኛማ ይኸውልህ
ብዙ ሃየሎሞች ፣ ፈጥረን ስናበቃ
እልፍ ጀማል ያሲን ፣ ይሆናል ጥበቃ
ይኸው ባደባባይ
የጀግኖቻችን ደም ፣ በየቦታው ፈሶ
አለ ጀማል ያሲን ፣ ሞት ሚበይንበት ፣ ፍርድ ቤቱ ፈርሶ!!
~
ግን አንተ ደህና ነህ
አቡነ ጳውሎስስ ፣ብፁው እንዴት ናቸው
እዚያም እንደምድሩ
አንድ አንቀፅ ያክላል ፣ መጠሪያ ስማቸው?
ደረታቸው ግድም "ሽጉጥ" የሚያደርጉት ፣ አለ መስቀላቸው?
።።።
እኛማ ይኸውልህ
ጳጳሳት አስታርቀን ፣ ሾመን በአደባባይ
ቃላቸውን እንጂ ፣ ዘራቸውን ሳናይ
አለን በአንድ ላይ።
የሆነው ሆነና...
አቡነ ጳውሎስ ፣ ጳጳሱ እንዴት ናቸው
ደረታቸው ግድም ሽጉጥ የሚያደርጉት አለ መሥቀላቸው?
እዛም ትውልድ ሲያልቅ
ወገን ደሙ ሲፈስ
እምነትሲተራመስ ፣ አያውቁም ግሳጤ?
እዛም ታጋይ ናቸው?
ቆባቸው የጳጳስ ነብሳቸው የአጤ?
~
እንደምን ነህ ጋሼ እንደምን ነህ መለስ
ትመጣለህ ስንል ቀረህ ሳትመለስ
~
~
~
ከቻልክ ፃፍልን ለደብዳቤያችን መልስ!!
👍1👎1