#ለምን #መጣህለምን መጣህ ትይኛለሽ
ለምን እንደሆን እያወቅሽ
ለምን ብለሽ አጠይቂ ይሄንን ብቻ እወቂ
መምጣት ለኔ ያኖረኛል
ከሰፈርሽ እያመሸዉ መዋል ማደር ያረካኛል
ከሰፈርሽ ዉሾች መሀል እኔ ብቻ የምጮህዉ
ሂድ ብለሽኝ ካጠገብሽ ከጥላሽ ስር የማርቀዉ
ጠዋት ማታ ልሳለምሽ ደጅሽ ድረስ የምቆመዉ
ከእልፍ ሰዉ መሀል አንድ የኔ ቸግሮኝ አንችን
ፍለጋ ነዉ
ለምን ማለት ምንድን
ለምንስ ምድን ነዉ።
*በባንቻየሁ አለሙ*