አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የውበት_ጀርባው

አንተ እሚታይህ፣ የሚያምር ፈገግታ
ያበባ ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ፣ ውብ ገጽታ ብቻ።

ጥርሷን ጉራማይሌ፣ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፣ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን፣ በሾህ ስትበሳ
የበላችው ፍዳ፣ ያየቺው አሰሳ
የዋጠችው ሕመም፣ ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፣ ከሷ በስተቀረ?

አያንዳንዱ ታላቅ ውበት በስተጀርባ
ሲንዠቀዠቅ ኑሯል፣ ብዙ ደምና እንባ።

ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ሥዕል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፣ እንደ መና ወርዶ
ሥቃይ ያቃልላል፣ ከሥቃይ ተወልዶ።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘