#ከዛፍ_የተቀሰመ_ዜማ
ካ'ለም እቅፍ ወጥቶ
ካ'ለም እቅፍ ሸሽቶ
ወደ ገዳም ሲሄድ
ደክሞት ተዝለፍልፎ
ብላቴናው ያሬድ ካ'ንድ ዛፍ ሥር ዐርፎ
ከዛፉ ግንድ ሥር ትል ሲሸልል ሰማ
እንዲህ በሚል ዜማ
ዛፉ ነው ሕይወቴ
ቅጠሏም እራቴ
ሰባት ጊዜ ልውደቅ
ሰባቴ እንድወጣ
የኋላ ኋላ ራቴን ኣላጣ”
ይህን ስትሰማ ቅጠሊቱ ራደች
መሸሽ ባይኾንላት ሙሾን አወረደች
ዛፉ ሕይወቴ ነው
ግን ኀያል ቢመስልም
ተራራ ቢያክልም
የማታ የማታ
ከትል አያስጥልም”
ያሬድ ይኼን ሰምቶ
ትሉ በጥረቱ ራት ሲበላ አይቶ
ተስፋውን አጸናው
በቅጠሏ ዕጣ ግን ተነካ ልቡናው
ከዚያም ተመልሶ
የትሉን ፉከራ
የቅጠሏን ለቅሶ
ባ'ንድ ላይ ለውሶ
ዜማውን ቀመረ
ዜማው ተዘመረ
ከሰው ነፍስ ተስማማ
በሰው ድምፅ አማረ።
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
ካ'ለም እቅፍ ወጥቶ
ካ'ለም እቅፍ ሸሽቶ
ወደ ገዳም ሲሄድ
ደክሞት ተዝለፍልፎ
ብላቴናው ያሬድ ካ'ንድ ዛፍ ሥር ዐርፎ
ከዛፉ ግንድ ሥር ትል ሲሸልል ሰማ
እንዲህ በሚል ዜማ
ዛፉ ነው ሕይወቴ
ቅጠሏም እራቴ
ሰባት ጊዜ ልውደቅ
ሰባቴ እንድወጣ
የኋላ ኋላ ራቴን ኣላጣ”
ይህን ስትሰማ ቅጠሊቱ ራደች
መሸሽ ባይኾንላት ሙሾን አወረደች
ዛፉ ሕይወቴ ነው
ግን ኀያል ቢመስልም
ተራራ ቢያክልም
የማታ የማታ
ከትል አያስጥልም”
ያሬድ ይኼን ሰምቶ
ትሉ በጥረቱ ራት ሲበላ አይቶ
ተስፋውን አጸናው
በቅጠሏ ዕጣ ግን ተነካ ልቡናው
ከዚያም ተመልሶ
የትሉን ፉከራ
የቅጠሏን ለቅሶ
ባ'ንድ ላይ ለውሶ
ዜማውን ቀመረ
ዜማው ተዘመረ
ከሰው ነፍስ ተስማማ
በሰው ድምፅ አማረ።
🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘
👍1