አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#መልክአ_እናት

ሰላም ለኪ እናታችን
ባለሽበት እንዳለሽ
ከዘመኑ ሴቶች ተለይተሽ
አንቺ የተባረክሽ ነሽ
ሰላም ለዐይኖችሽ
ከጭስ ጋራ ለሚሟገቱ
ከእንቅልፍ ጋራ ለተፋቱ
ተቅበዝባዥ ፍጡር ኾኜ ኑሮዬን ከምገፋ
ምነው እንባሽን በኾንኩ
ካይኖችሽ ሥር እንዳልጠፋ፡፡
ሰላም ለከንፈሮችሽ
ትላንት ለማውቃቸው
ዛሬ ለምናፍቃቸው
ውዳሴ ክብር ምርቃት
ጭብጨባ ሙገሳ ሽልማት በተረፈበት ቀዬ
ምነው ያንቺን እርግማን - ይናፍቃል ጆሮዬ
ከሌሎች ውዳሴና ክብር እልፍ ጊዜ የተሻለ
ለካ በ'ርግማንሽ ውስጥ እናትነትሽ አለ፡፡
ሰላም ለጣቶችሽ
ለሰዎች የቀረቡ፣ ከራስሽ ግን የራቁ
መስጠት መለገስ እንጂ መቀበልን ለማያውቁ
ሰላም ለኪ!
ባለሽበት እንዳላሽ።

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘