አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ግዞት

እፍኝ ተበድሮ ነፍሱን ሊያድናት
ባርያ ሆኖ ሞተ ያባቴ አባት
እዳው ተጭኖት
ባርነት ሲመረው ሲያቅት ለግዞት
የጭሰኛ ክብር ሰጡት ለኔ አባት
አርሶ፣ ዘርቶ፣ አጭዶ ጭሰኛው አባቴ
ምርቱን ሲገብረው ለመሬት ከበርቴ
መሬት ለአራሹ ” መፈክር አንስቼ

ታግዬ አሸነፍኩ ከጫካ ገብቼ
ወገኖቼ ሁሉ ቀድመው የተገፉት
በኔ በልጃቸው አሁን ገና አረፉት
ብዬ በተስፋ ስንቅ ቃላት ስደረድር
አንደበት ሳደድር
ከኔም ለካ አልጠፋም የጭቆናው ቀንበር
ካ'ብታም ግዞት ስር ነኝ ተብዬ “ወዝ አደር”
መደብ ከታች እላይ ጎባጣው ሳይቀና
ነጻነት ከቃላት መቼስ አልፎ ያቅና፡፡

🔘በዕውቀቱ ስዩም🔘