አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
569 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#የሚሰሙ_ህልሞች

እረፍ ልል ተኛሁ
በአልጋ ጎዳና ፥ እንቅልፌ ወሰደኝ
ከማይዳሰሱ
ከማይታዩ ህልሞች ፥ አድርሶ አላመደኝ።
ጨለማ አይደለም
ብርሃንም አይደለም ፥ ድምፆች ይሰማሉ
እንደ ነፋስ አይነት ፥ የወንድም ያልሆኑ የሴትም ያይደሉ
ሚታይ አካል የለም
የሚሰሙ ህልሞች ፥ ኬ'ትም ይመጣሉ፡፡

ይመስለኛል በህልሜ
የሚታዩን ህልሞች
ዓለም እያለመ ፥ ሊያስፈታ ሲባትል
ከጫጫታ መሃል
አንድ ህልም ሰማሁ ፥ ተፈተሃል ምትል።
እላት ይመስለኛል ፥ “ከምን ነው ምፈታው?”
“መልስህ ታስሯል” የሚል
ሌላ ድምፅ ይመጣል ፥ ወጥቶ ከጫጫታው።
“ምን ነበረ መልሱ?”
የምል ይመሥለኛል ፥ ታፍኜ በሲቃ
ከጫጫታው መሃል
ሌላ ድምፅ ይለኛል ፥ “መልስ የለም ሳትነቃ።”

🔘በዕውቀቱ ስዪም🔘