አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
570 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አንድ ባለቀለም ጉርድ ፎቶግራፍ ብቻ ነበር ውስጡ ያኘሁት፤አንዲት እድሜዋ ሦስት ዓመት የሚሆናት ቆንጅዬ ሕጻን ልጅ ፎቶ፡፡ከፎቶው ጀርባ
በእንግሊዝኛና አማርኛ ቅልቅል እንዲህ የሚል ጽሁፍ ተጽፏል የሎዛ የእጅ ጽሁፍ ነው፡፡
hello,uncle! guess what ...My name is "ማምሻ ዳግማዊ!!

ሟርት ነው አልኩ ለራሴ፡፡ ግን ደግም አይገርምም፣ ሎዛ እብድ ናት እብድ ቤተሰብ
መመስረትም ትችላለች፡፡ እናም ዓለም ፈውሷን ለመቀበል የሎዛ ዓይነት ብዙ እብዶች ሳያስፈልጓት አይቀም፡፡

ጨረስን

አረ ተዉ #MUTE ያደረጋቹ #UNMUTE አድርጉ ምንም አልሰማም አላችሁ እኮ😡 ምን ይሻለኛል ወይ እስቲ ስለድርሰቱ አስተያየት ስሰጡ #UNMUTE የማታደርጉበትን ምክንያት ምንድን ነው??? እባካችሁ ንገሩኝ..Post የሚደረጉትን ብዙ ሰው የማያነበው ከሆነ ማዘጋጀቱም ይደብራል..ሌላ ድርሰት ለመጀመር ወይም ለማቆም አስተያየታችሁን (ምክንያታችሁን) እፈልጋለው...በዛሬው ቀን ብቻ እንኳን #381 ሰው ቻናሉን #MUTE አድርጓል አስተያየት ይስጡ

@atronosebot ን ይጠቀሙ
ተንተርሳ የደረቱን ጠጉር እያፍተለተለች በወጣትነት ትኩስ ገላው ውስጥ እንደ ቅቤ ለመቅለጥ... እንደ ውሃ ለመፍሰስ... በእጅጉ ጓጉታለች፡፡

ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ሆነ፡፡ ጌትነት በዚያ ከጥጥና ሲባጎ በተሰራ ምቹ ሶፋ ወንበር ላይ በጀርባው ተለጥጦ እየተዝናና ጠላውን መኮምኮሙን ቀጥሏል። ሸዋዬ ሁኔታውን ስትመለከት ፈነጠዘች። ጠላዋ ስራውን በሚገባ በመስራት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን አረጋገጠች። ሁሉም
ነገር በእቅዷ መሰረት እየተቀላጠፈ ነው። ሚስኪኑ ባጠመደችለት ወጥመድ ውስጥ ያለችግር ሰተት እያለ በመግባት ላይ መሆኑን እንዳወቀች ያንን ከተዳፈነበት ተቆስቁሶ እንደ ነበልባል ሲለበልባት የቆየ፣ ውስጥ ውስጡን ያሰቃያትን፣ ቀን ከለሊት እረፍት ያሳጣትን ችግሯን ለማስወገድ ቸኮላች፡፡ የወሲበ ክብሪቷን ጭራበት በዚያ እንደ ፈረሰኛ ውሃ ሽቅብ በሚጋልበው ዳሌዋ ላይ አፈናጣ እያስጋለበች በጭኖቿ መካከል አስገብታ ልቡ እስከሚጠፋ ድረስ ልታሸውና ትኩስ የወንድነት ወኔውን ጨምቃ ልታጣጥመው ተጣደፈች፡፡

“እጅህን ታጠብ ጌቱ?” ከፊት ለፊቱ ከሞላ ጎደል ዳንስ በሚመስል ሁኔታ እየተውረገረገች የእጅ ማስታጠቢያውን አስጠጋችለት። ድሮ ጌትነት ብላ ነበር የምትጠራው።ዛሬ ግን ከወዲሁ ስሜቱን ለመስረቅ ለየት ያለ ስሜት ልታሳድርበት ፈለገችና ጌቱ ብላ አቆላመጠችው። በዚያ ላይ ደግሞ አድርጋ የማታውቀውን እጁን ልታስታጥበው ተነሳች። ጌትነት ድንግር
ግር አለው፡፡ “እንዴ! ጋሼ ቶሎሳ ሳይመጣ እራት ልበላ?”በፈዘዙ ዐይኖቹ ሽቅብ እየተመለከታት ጠየቃትና ማስታጠቢያውን ከእጇ ሊቀበል ሞከረ።
“ውይ አልነገርኩህም ለካ! የነገርኩህ መስሎኝ፡፡ ስልክ ደወለልኝ እኮ! የጓደኛዬ ልጅ ሞታ ቀብር አለብኝ እያስተዛዘንኩት ነው ብሎ ደወለልኝ”
አምሽቶ ስልክ የደወለ አስመስላ ነገረችው። ጌትነት ቅር ቢለውም እጁን
ለመታጠብ የወንበሩን መደገፊያ ተመርኩዞ ብድግ ሊል ሞከረ።
“እስቲ ለዛሬ ክብሩ ይቅርብኝና ቁጭ ብለህ ታጠብ” ከመቀመጫው እንዳይነሳ በግራ ክርኗ ትከሻውን ወደ ታች ደገፍ አድርጋ አስታጠበችው። እጁን ካስታጠበች በኋላ እንጀራ የተጉዘጉዘበት ሰፊ ትሪ አመጣች። ያንን ሰፊ ትሪ ደግሞ በጥልፍ ባሸበረቀው ትልቁ ሌማት ላይ
ካስቀመጠች በኋላ ያንን በቅመምና በቅቤ ያበደ የዶሮ ወጥ ልታመጣ
ተመልሳ ወደ ጓዳ ገባች። ወጡን ይዛ ስትገባ ረሃብ የሽረሽረው ሆዱ በነጎድጓድ ድምጽ አፍ አውጥቶ ጩኽቱን አቀለጠው..!! የወጡ ሽታ መጣፈጥ
ለጉድ ነበር። ሽዋዬ ጊዜ አላጠፋችም። በፍጥነት ከዋንዛ እንጨት የተሰራውን ኩርሲ ሳብ አድርጋ ከጐኑ ልጥፍ ብላ ተቀመጠችና በአፍ በአፉ ትለቅበት ጀመር፡፡ የጉርሻዋ ክብደት አይጠየቅም፡፡ 'ፍቅርና ጉርሻ ሲያስጨንቅ ነው ባይዋ ሸዋዬ በላይ በላዩ እየጠቀለለች ባጎረሰችው ጉርሻ ሆዱ ተወጠረ። የእራት ሥነ ሥርዐት ጨዋታው በአንድ ቋሚ የጉርሻ ተቀባይና በአንድ ቋሚ አጉራሽ መካከል ሲካሄድ ከቆየ በኋላ“ወደ ማሳረጊያው ላይ ለኔስ አታጎርሰኝም እንዴ?” አለችው እንደማቀፍ እየቃጣት።

“ማጉረስ ስለማልችል እኮ ነው እትዬ ሸዋዬ?” ከመፍዘዛቸው ብዛት ያንቀላፉ የሚመስሉ ዐይኖቹን በግድ ከፍቶ ዐይን ዐይኖቿን ሽቅብ እየተመለከተ።
“ሂድ! ጉረኛ! ይሄኔ የምትወዳት ውሽማህ ብትሆን ኖሮ በጉልበትህ ተንበርክከህ አደግድገህ ነበር የምታጎርሳት” በመቀመጫዋ ጎሽም አደረገችው።

ጌትነት አፈረና አንገቱን አቀረቀረ።
“ምን አንገትህን ትደፋለህ?! አንገት ደፊ አገር አጥፊ አሉ?! እኔ እንደሆንኩ እሳት መሆንህን ያወቅኩት ገና እንዳየሁህ ነው። ነቃሁብ አይደል?” አሁንም በመቀመጫዋ ቡጢዋን ደገመችው። ጌትነት ግራ
ተጋባ፡፡ ያከብራትና ይፈራት የነበረችው ሸዋዬ መሆኗን ተጠራጠረ፡፡ ከሷ
እንደዚህ ያለውን አቀራረብና ቅብጠት ፈፅሞ ያልጠበቀው ነበር። ስሜቱ
በመጠኑ ተረበሽ፡ ወደ መጨረሻ ላይ በግድ ልታጐርሰው ስትታገለው “በቃኝ”ብሉ እጆቿን ይዞ ተማፀናት። ከሚገባው በላይ ሲሆን እህልም ዱላ
ነው። በቁንጣን እንዳይታመም ፈራ።

“ጌቱ ይህቺን ብቻ በሞቴ!!” ሄዳ አንገቱን እቅፍ አድርጋ በግድ አጎረሰችው። የመጨረሻው ጉርሻ እንኳን ሆን ብላ አንገቱን ለማቀፍ እንጂ እንደጠገበ ሳይገባት ቀርቶ አልነበረም፡፡ በአንድ ቋሚ አጉራሽና በአንድ ቋሚ ጎራሽ መካከል ሲካሄድ የቆየው ጨዋታ አብቅቶ ገበታው ሲነሳ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ሆኖ ነበር፡፡
አንድ ሰዓት ሙሉ የፈጀ የእራት ሥነ
ሥርአት... ከገበታው በኋላ ሸዋዬ ለራሷም ጠላ በዋንጫ ሞላችና ኩርሲውን የበለጠ አስጠግታ ልጥፍ አለችበት።......

ይቀጥላል

እባካችሁ #MUTE አድርጋችሁ የምትጠቀሙ #UNMUTE አድርጉ በየቀኑ የሚለቀቁትን መከታተል አትችሉም
በድርሰቶቹ ላይም ያለውን አስተያየታችሁን በመወያያ ግሩፑ @dertogadaa እና @atronosebot ላይ ማስፈር ትችላላችሁ
👍1