አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አትሮኖስ pinned «#ብቸኝነቴን_መልሺልኝ የተሰኘው ምርጥ የፍቅር ታሪክ #በፍቅር_ቤት እየተለቀቀ #የመጨረሻውን_ክፍል ይዞላችሁ ቀርቧል ያልጀመራችሁት እታች ባለው ማስፈንጠርያ ገብታችሁ አንብቡ የጀመራችሁትም መጨረሻውን ክፍል እንሆ። 👇»
#በእቅፍሽ_ውስጥ_ያለው_ሰላም

በደጃፌ
ያዱኛ ጅረት ይፈስሳል
ሲዘረጋ መዳፌ
አልማዝ አፍሶ ይመለሳል።

ድህነትን አልቀድስም፣ ሀብታም መሆን አልጠላም
ግና ገንዘብ ኪስን እንጂ፣ የልብን ክፍተት አይሞላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።

በጉልምስና ዘመኔ፣ ወደ ልጅነት ተዛውሬ
የወይን ፅዋየን ወርውሬ
እልፍ ጡቶችን ብጠባ
ካንዲት ሽንቁር ተመዝዤ፣ ሌላይቱ ውስጥ ብገባ
ብለዋውጥ ማህደር
ብቀያይር ሰገባ
ምን አገኘሁ? ምን አተረፍሁ? ምን ፈየድኩኝ? ምኔ ረባ?

ሥጋ በሥጋ ቢሞረድ፣ የደነዘ ነፍስ አይሰላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👍2
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስር


#በሜሪ_ፈለቀ

አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ ጊዜው በትክክል
መቼ መሆኑን ባላውቅም። በሞቅታ ስለምታወራ ከመስማት ውጪ አፌን አላላቀኩም።

"ታውቃለህ ለሷ ብለህ ምንም ለመስዋት የተዘጋጀህላት ህፃን ልጅህ ምርጫ ቢሰጣት እሱን እንደምትመርጥ ማወቅ
የሚጠዘጥዝ ቁስል ስሜት እንደሚሰጥ? አታውቅም!! ህፃን ናት በሷ እኮ አልፈርድም፡፡ የሚሰማኝን ፍርሃትና ህመም ግን ልታውቀው አትችልም። ስታድግ አባቷን መርጣ ብትሄድስ? ለእርሷ ብዬ የከፈልኩላት ሁሉ ባይገባትስ? አባቷን ስላሳጣኋት ብትወቅሰኝስ? ለነገሩ አንተ የምትሳሳለት ሰው ኖሮህ አያውቅም::" አለችኝ።

ኖሮኝ አያውቅም፡፡ እስከገባኝ ድረስ በአንዲት ክስተት ስለእርሷ
የተገለጠልኝ ስስት ግን የሶስት ዓመት ጥርቅም እንጂ የዛች ቅፅበት ብቻ አልነበረም። ሶስት ዓመት ሙሉ በእያንደንዷ የስራ ቀን የቀኑን መንጋት ያህል ስምሪት የተለመደ ክስተቴ ነበረች፡፡
ቡና አብሪያት ስጠጣ፣ ስትናደድ ጉንጫ ሲቀላ ደስ ስለሚለኝ ሳበሳጫት፣ ለማንም የማላወራውን ስሜቴን ሳወራት፣ እሷ
እንደማውቃቸው ሴቶች አልነበረችም:: አሁን ያን ላስረዳት አልሞከርኩም፡፡ ከብዙ ወሬዋ እና ከ'ታውቃለህ? አታውቅም!በኋላ አልጋው ላይ ተጋድማ ማውራቷን ቀጠለች፡፡ እያወራች እንቅልፍ ይዟት ሄደ፡፡ አልቀሰቀስኳትም አጠገቧ ተጋደምኩ።

"እናትህ ማገገሚያ ነው ያሉት::" አለችኝ ጠዋት ቀድማኝ ተነስታ ያበሰለችውን ቁርስ እየበላን፡፡ ዝም አልኩ፡፡ ቀጥላ
በምትጠቀማቸው ሱሶች ምክንያት መግባቷን አከለችልኝ።ደነገጥኩ? አዘንኩ? ላያት እፈልጋለሁ? ስሜቴ ድብልቅልቅ አለ፡፡
ከስምሪት ጋር ከነጋ ከተወሰኑ ቃላት በላይ አልተነጋገርንም። ልቤን ከብዶኛል፡፡ ምንም የማውራት ፍላጎት የለኝም።ብዙ ዝም ካልኩ በኋላ የረባ ቃላት ሳንለዋወጥ ያለዚያ ቀን መኖሩን ወደማላውቀው የግል ማገገሚያ ሆስፒታል ደረስን፡፡ ሳያት ምን እንደምላት አላውቅም። ባታውቀኝስ ? ጭንቅላቷ የተቃወሰ
ቢሆንስ? እንደልጅነቴ ዞር በል ብላ ብትሰድበኝስ? ቆምኩ።የተዘጋጀሁ አልመስል አለኝ፡፡ ስምሪት ገብቷታል፡፡ እየደጋገመች እጄን ትጨምቀኛለች፡፡ እሷም ተጨንቃለች፡፡ አልጋው ላይ
ተጋድማ ሳያት ልጨብጣት? ልቀፋት? ፈገግ ልበል? ላልቅስ?የትኛው ላለሁበት ቦታና ስሜት እንደሚመጥን አላወቅኩትም።ስታየኝ ከአልጋዋ ወርዳ ማምለጥ ብትችል ፈልጋ ነበር፡፡
የለበሰችው ስስ የአልጋ ልብስ ውስጥ ተሸጎጠች፡፡ ስምሪት ቀድማ ሄዳ አቀፈቻት፡፡ ምንም ሳልናገር አጠገቧ ሄጄ ተቀመጥኩ፡፡ሳላገኛት በፊት ብዙ ጥያቄዎች ብትመልስልኝ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ከእድሜዋ በላይ አርጅታለች። ሰውነቷ ተጎሳቁሏል፡፡ ማለት የቻልኩት ዝም ብቻ ነው።

"ትልቅ ሰው ሆነሃል!" አለችኝ ፊቷን ከኔ አዙራ:: እያለቀሰች እንደሆነ አውቃለሁ። ላባብላት እፈልጋለሁ ግን አላደርገውም። ሳላስበው እጇን ያዝኳት። መልሼ ወዲያውኑ ለቀቅኳት፡፡

የቱንም ያህል ብትጠላኝ አልፈርድብህም። ይገባሃል::" አለችኝ
ፊቷን ደብቃኝ፡፡

“አልጠላሽም:: ባታወሪኝ እንኳን ትንሽ ደቂቃ አጠገብሽ ልሁን፡፡"አልኳት:: ድምፅ አውጥታ እያለቀሰች ፊቷን ወደእኔ መለሰች።ስምሪት አብራት ታነባለች፡፡ የማደርገው ጠፋኝ፡፡
“እያስጨነቅሽኝ ነው። እባክሽ አታልቅሺ፡፡” አልኳት አቅፌ ባባብላት ደስ ይለኛል። የሚሰማኝ ግን እሩቅነት ነው፡፡ እጄን ሰድጄ መለስኩት።በዝምታ ብዙ ካወራን በኋላ ተነሳሁ።

"መጥቼ አይሻለሁ::" አልኳት። ብርግግ ብላ ተቀመጠች፡፡ አንድ እርምጃ ጀርባዬን ሰጥቻት እንደተራመድኩ።

"ባቢሾ?" ብላ ጠራችኝ፡፡ የቤት ስሜ ነበር፡፡ አጠራሯ የፈለገችው ነገር ኖሮ ልትጠይቀኝ የፈራች ይመስላል። ምን ቸግሯት ይሆን ብዬ እያሰብኩ ተጠግቻት "ምነው?" አልኳት፡፡

በጣም እያመነታች እያየችኝ እጇን ወደ ፊቴ እያስጠጋች "አንዴ ልንካህ?" ስትለኝ ጭንቅላቴ በከባድ ነገር የተመታ መሰለኝ፡፡ ያ ስሜት ለዘመናት የያዝኩባትን ቂም የማጠብ አቅም ነበረው።ልጇን ለመንካት ያስፈቀደች እናት ህመም የእኔ እናት ህመም ብቻ ነው።ይሄ ስሜቷ ከጥላቻ ዋልታ ወደ ፍቅር አርያም
የማምጠቅ ምትሃት ነበረው። የዘረጋቻቸውን እጆቿን ሳምኩላት። እናትነት እንዲሰማት ማድረግ ተመኘሁ።

"ልጅሽ እኮ ነኝ! ብትቆነጥጪኝ እንኳን በኔ ላይ ስልጣን አለሽ!” አልኳት በእጁ አንገቴን ፀጉሬን ፊቴን ደባብሳኝ ስታበቃ በቀስታ እጇን ሰበሰበች። ከሆስፒታሉ እንደወጣሁ ብቻዬን መሆን ፈለግኩ፡፡ ስምሪትን ተሰናብቻት ማሰብ እስካቆም ጠጣሁ።በሚቀጥሉትን ቀናት የተለመደው ዓይነት ህይወት ቀጠልኩ።
አዲስ ነገር እናቴን እየሄድኩ አያታለሁ። አንዳንዴ ከስምሪት ጋር እንሄዳለን፡፡ ስላለፈው አናነሳም፡፡ ልጠይቃት የምፈልገው ብዙ ጥያቄ ቢኖርም አጠገቧ ስሆን ዝም ማለትን እመርጣለሁ።
ከስምሪት ጋር ልክ እንደበፊቱ ሆንን፡፡ ምንም እንዳልተፈጠረ፣ሳያት ምንም እንደማይሰማኝ፣ ስታረፍድ እንደማልንቆራጠጥ፡፡

አንድ ቀን ባሏ ሲመጣ ሳትኳኳል እንደጠበቀችው እና አስጠሊታ
መሆኗን ነግሯት ልጁን ይዞ እንደሄደ ነገረችኝ፡፡

በተደጋጋሚ ይሄን በማድረጓ አብረው መተኛት ማቆማቸውን ነገረችኝ፡፡ ከሳምንታት በኋላ እናቴ ከሱሷ ከማገገሟ በባሰ በጉበት በሽታ እየተሰቃየች ስለነበር ለከፍተኛ ህክምና ወደ ሌላ ሆስፒታል ተዛወረች።መታመሟን ስታውቅ ዘመዶቿጋ ስልክ ደወለች። እስከዛሬ መኖራቸውን እንኳን አስቤ ከማላውቃቸው
ቤተሰቦቼጋ ለመግባባት መሞከር ያልተለመደ ደባሪ ነገር አለው፡፡
የወንድ አያቴን፣ አጎቴንና አክስቴን ተራ በተራ እየመጡ ሲከርሙ ተዋወቅኳቸው። አክስቴ እዚሁ አዲስ አበባ መኖሯን
ማወቄ ገረመኝ፡፡ እንዴት አይጠያየቁም? አጎቴና አያቴ ከክፍለሃገር ነበር የመጡት: የገባኝ ነገር እናቴ ከቤተሰቦቿም ጋር ቢሆን የጠበቀ ግንኙነት ያላት አይመስለኝም:: ልጅ እንዳላት
እንኳን ያወቁኝ አሁን ነው። አልተገረምኩም እንኳን እነርሱ
አብሬያት ኖሬ የማውቀው ልጇ እንኳን ብዙ የማይፈታ እንቆቅልሽ እንዳላት አውቃለሁ፡፡

“አባትህ የምሰራበት የነበረ ሆቴል ያረፈ ቱሪስት ነበር። በጣም ጥሩ ሰው ነው። ፈረንሳዊ ነው:: የምትኖርበትን ቤት የገዛልኝ እሱ ነው።ሀገሩ ሚስትና ልጆች ስለነበሩት ተመልሶ ወደ ሀገሩ
ሄደ፡፡ አድራሻውን አላውቅም፡፡ ልጅ እንዳለው አያውቅም።አንተን ማርገዜን አልነገርኩትም።እሱ ባከበረኝ ልክ ማንም
ወንድ አክብሮኝ አያውቅም።እሱን ነው የምትመስለው::" አለችኝ ብቻዬን ሆስፒታል ያደርኩኝ የሆነ ቀን ማታ። ዝርዝር አድርጋ እንድትነግረኝ ልጠይቃት አስብና ማስታወስ የማትፈልገው
ታሪኳ ከሆነ ብዬ እየፈራሁ እተወዋለሁ። ማወቄ ለእኔ ከሚፈይደው ቁም ነገር ጋር ሳነፃፅረው ማስታወሷ የሚፈጥርባት
ህመም የሚያመዝን እየመሰለኝ አለማወቄን መረጥኩ። ይሄን
የነገረችኝ ጠዋት ለአክስቴና ከእናቴ ስር ለማይጠፋው የነፍስ አባቷ ቀኑን ለቅቄላቸው ወደ ስራ ልገባ እስኪመጡልኝ
እየጠበቅኳቸው ሳለ አንድ መልከ መልካም ወጣት ገራገር የመሰለች ሴት እጅ ጣቶች በጣቶቹ ቆልፎ ሆስፒታል መጣ። እናቴ ስታየው ግራ ተጋባች። የእርሱ ግድ የለሽነት እና የእናቴ
መቁነጥነጥ ሌላ የማላውቀው ታሪክ ክር ጫፍ መሆኑን ነገረኝ። አብራው የነበረችው ገራገር ሴት ወደ እናቴ ተቅለብልባ ሄዳ እየሳመቻት።
"እንዴት ነሽ ወለላ? መታመምሽን አባ ናቸው ትናንት የነገሩን?አሁን ተሻለሽ?" መልስ አትጠብቅም።ወዲያው ወደ ወጣቱ ዘወር ብላ "ና ሳማት እንጂ! ምን እዛጋ ይገትርሃል?" መልስ ሳይሰጣት በተገተረበት መቆሙን አይታ በዓይኗ ማባበልም ቁጣም የቀላቀለው ማጎረጥረጥ ታጉረጠርጣለች፡፡ ወንበር ላይ ያለ ንግግር ተቀመጠ፡፡
👍41
ወለላን እንደሚጠላት ያስታውቅበታል።
መፋጠጣቸው ግራ ያጋባኝ እኔ ራሴን አስተዋወቅኳቸው።

"ኪሩቤል እባላለሁ። የወለላ ልጅ ነኝ።" ከአፌ የወጣው ቃል እነሱ ጆሮ ጋር ሲደርስ ሌላ የሚያስደነግጥ ነገር እስኪመስለኝ ሁለቱም ደርቀው
እናቴ ምንም የወሬው አካል
እንዳልሆነች ሁላ ኮርኒሱ ላይ አፈጠጠች፡፡ ልጅቷ "ልጅ? ልጅ
ልጅ? ማለቴ የወለደችህ? ሲገርም::" እያለች ተራ በተራ ታየናለች። እንደመቅበጥበጥ ሲያደርጋት ከእድሜዋ በታች ህፃን ትመስላለች፡፡

"አዎን ልጂ ነኝ ምነው?" አልኳት።

"እሱ ወንድምህ ነው። ስህተት ይባላል፡፡ ማለቴ የወለላ ልጅ ነው።እኔ ረድኤት እባላለሁ:: ፍቅረኛዬ ነው::" ብላኝ ብዙ ጊዜ እንደምታውቀኝ ተንደርድራ አቀፈችኝ፡፡ ምን ማሰብ እንደነበረብኝ
ግራ ገባኝ:: በደመ-ነፍስ ጨበጥኩት። ስሙ ገርሞኛል።

እውነት ነው? ወንድሜ ነው?" አልኳት እናቴን፡፡ ምንም የገረመው የማይመስለውን ወንድሜን እያየሁት። አረጋገጠችልኝ፡፡ ለደቂቃዎች ዝም አልኩኝ፡፡ ማድረግ የፈለግኩት
እርሷን መውቀስ ነበር ወንድም እንዳለኝ ለምን እንደደበቀችኝ ግን አላደረኩትም።ሀያ ሁለት ዓመቱ ነው በስምንት ዓመቴ ጥላኝ የሄደች ጊዜ ሌላ ቤት መስርታ እንደ ነበር የእድሜው
ቁጥር ነገረኝ፡፡ ለወንድሜም ጥሩ እናት እንዳልነበረች ምንም ሳይናገር ገብቶኛል፡፡ ስልክ ተለዋውጠን ስለረፈደብኝ ወደ ስራ
ገባሁኝ፡፡ቀኑን ሙሉ እያሰብኩ የዋልኩት ስለእናቴ ተመዘው የማያልቁ ታሪኮች እና ልወጣ ስል ወንድሜ ስለጠየቀኝ ጥያቄ
ነበር።

"ደብዳቤዎች የምትፅፍላት አንተ ነበርክ?" ብሎኛል፡፡

ከስራ ስወጣ ስለወንድሜ እየነገርኳት ስምሪትን ልሸኛት እቤቷ ስንደርስ ባሏ አለመኖሯን አይቶ ሲመለስ ደረስን። ብዙ ስድብና ጥቂት ጥያቄ ቀላቅሎ አምባረቀ፡፡ ልትከላከል በማያስችላት ፍጥነት በጥፊ አላት።በምን ፍጥነት እንዳደረግኩት አላውቅም።በቡጤ ጉንጭና አገጩን አጎንኩት፡፡ ስምሪት መሃል መግባቷን ሲያይ ካልገደልኩት ብሎ ተወራጨ፡፡ እንደፈራ
ያስታውቅበታል።

ሴት የሚማታ ወንድ ከወንድ ጋር የመደባደብ ወኔ የለውም።ሽንታም!!" ካልኩት በኋላ ስምሪትን ያስከፋኋት ስለመሰለኝ አየኋት። ጥርሶቿ ባይስቁም ዓይኖቿ ሲስቁ አስተዋልኩ።ከብዙ
ድንፋታ በኋላ ሄደ። እቤቷ አስገብቻት ልሰናበታት ስል " ኪሩ ሳመኝ?" አለችኝ፡፡ ሰምቻታለሁ:: ዝም አልኳት።
"
ኪሩ?"

"ወዬ?" ስላት ጉንጯ ቀላ፡፡

አላስደገምኳትም። እየሳምኳት
አቋረጠችኝ፡፡

"ምነው?" አልኳት፡፡

"ቆይ የሚቀጥለውንም እኔ ካልጠየቅኩህ አታደርግም?" አለችኝ።

የመጀመሪያ ቀን ከወለሉ ላይ እንዳነሳኋት ተሸክሜ ክንዴ ላይ አቆየኋት፡፡ ከማውቃቸው ውብ ነገሮች ሁሉ የተለየች ድንቅ ፍጥረት ናት:: ወዲያው ስልኬ ጠራ። ከሆስፒታል ነበር፡፡ ምኑ
ነው ያልገባኝ? ጭራሽ ምንም አልገባኝም!! ይህቺ ሴትዮ እንቆቅልሼ ተቆለለሳ? እናቴ ሞታለች! ከመሞቷ ይብስ ለጆሮዬ አዲስ የሆነው ዜና እህትህ...... የሚለው ነበር። እህት አለኝ!
በአንድ ቀን ጠዋት እና ማታ የደበቀቻቸውን ወንድምና እህቴን
ዱብ ያደረገች እናት የኔ እናት ብቻ ናት!!
"ምን ሆነህ ነው? ምንድነው የሰማኸው?" ትለኛለች ስምሪት
በቆምኩበት መደንዘዜ አስደንግጧት።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
1👍1
አትሮኖስ pinned «#ቀላውጦ_ማስመለስ ፡ ፡ #ክፍል_አስር ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ ጊዜው በትክክል መቼ መሆኑን ባላውቅም። በሞቅታ ስለምታወራ ከመስማት ውጪ አፌን አላላቀኩም። "ታውቃለህ ለሷ ብለህ ምንም ለመስዋት የተዘጋጀህላት ህፃን ልጅህ ምርጫ ቢሰጣት እሱን እንደምትመርጥ ማወቅ የሚጠዘጥዝ ቁስል ስሜት እንደሚሰጥ? አታውቅም!! ህፃን ናት በሷ እኮ አልፈርድም፡፡ የሚሰማኝን…»
#ሚሊዮን_ፀሐዮች_ሚሊዮን_ጨለሞች

ጨረቃ ብቅ አለት፣ ፀሐይ ስትከስም
ያው እንደ ወትሮ ነው
የምሽት የንጋት፣ ፈረቃው አይፈርስም!

የኔ ግን ይለያል
ልቦናየ ቢማስ
ሚሊዮን ፀሐዮች፣ ሚሊዮን ጨለሞች!
ሺ ሰማይ፣ ሺህ አድማስ
ተገልጦ ይታያል።

ስንቴ በጽልመቴ፣ ዙርያየን አዳፈንሁ
ስንቴ በጨረሬ፣ የምድርን ዐይን ወጋሁ
ባንድ ቀን ውስጥ ብቻ
ስንት ጊዜ መሽቼ፣ ስንት ጊዜ ነጋሁ!
#የመገፋት_ጣዕም

ነግጄ ሸቅጬ
ማትረፍ ባይሆንልኝ
ብርርርርርርርርርርር ...
ሳልል ቀርቼ
ከተስፋ ጋር ብገኝ
ከፊታቸው እንድገል .
ሲገፉኝ ሲገፉኝ
ሲገፉኝ ሲገፉኝ
ሲገፉኝ ሲገፉኝ
ካናት የሚቀቡት
ለጋ ቅቤ ሆንኩኝ።
#ሰው_ከቀየው_እንጂ

ወጥቼ ከቀሳው
ለጊዜው ታግየ
ሞትን ድል ብነሳው
መኖር አሸነፈኝ
ቤቴ ተደፍቶብኝ፣ ሁለት ወር አለፈኝ።

ተፈጥሮየ ከዳኝ፣ ፈሊጡን ቀየረ
አካሌ ሸፈተ፣ አዲስ ወግ ተማረ
ገላየ በቁሙ፣ ሳር ማብቀል ጀመረ።

እንዳልቆይ መታከት፣ እንዳልወጣ ሽብር
ሳይደከመኝ ተኝቼ
እንቅልፍ አንገቴ ላይ፣ ቀንበሩን ሳይሰብር
ካልጋ ተነስቼ
እየተደናገርሁ
እየተደናበርሁ
በምሳ ሰአቴ፣ ራት እየጋገርሁ
ኑሮ እንደ ሳር ጉንጉን፣ እያደናቀፈኝ
ሁለት ወር አለፈኝ!

ዛሬ ኮበለለ
ትላንትናን ቀድሞት፣ ባምባላይ ፈረሱ
ቀኔና ሌሊቴም፣ ሰልፍ እያፈረሱ
ይተራመሳሉ
ይርመሰመሳሉ

አርባም እድሜ ሆና
ያችን ለማሳጠር

ነፋስ በሰው ሲያድም፣ ከሞት ሲመሳጠር
ወዴትስ ይኬዳል
ሰው ከቀየው እንጂ፣ካለም ይሰደዳል?"
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ
---------------------------------------------------
ሁሉም የሕይወት ገፅ መጨረሻ ላይኖረው ይችላል ለህይወት መጨረሻ ብሎ ነገር የለም።የአንዱ ቀን መጨረሻ የሌላው ቀን መጀመርያ ነውና።የሰኞ ማለቅ የማክሰኞ መጀመር እንደሆነው የምድር መጠቅለል ለሰማያዊ ህይወት መጀመር እንደሚሆነው....ሌላ ፅንፍ ግን አለው።

=========================

"እናትሽ በጠና ታማለች፡፡ እባክሽ ልታይሽ ትፈልጋላች...ለአራተኛ ጊዜ የተላከልኝ መልዕክት ነው።

“እስካሁን አልሞተችም እንዴ? ለምን ታጓጓኛለች? አንዳችሁ እንኳን ምናለ ሞተች የሚል ብስራት ብታሰሙኝ?"

"በስመ አብ ወ ወልድ ወ መንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ!! (ገዳዳ መስቀል በሰራ እጁ እያማተበ) ምነው ልጄ? ምን የሚሉት ጭካኔ ነው? ደግም አይደል! እግዜርም አይወደው::" መልሴ
አንገሽግሾታል። ሀምሳ ዓመት የሚያልፈው ሰውዬ ነው።የወለደችኝ ሴትዮ የነፍስ አባቷ ነው።

"በናትህ ከቤቴ ውጣልኝ!!"
"ምነው ልጄ? እግዜር የሰጠኝን ሹመት ባታከብሪ በእድሜ አባትሽ አልሆንም?" የሚናገረው ቃል የለዘበ ይሁን እንጂ ቀይ
ወጥ የመሰለ ግለታም ዓይኑ እንደተጠየፈኝ ያሳብቅበታል።

እድሜውን ሳይሆን የለበሰውን የቤተ ክህነት ልብስ ባከብር ደስ ባለኝ ግን ለባሹ ልብሱን እንጂ ልብሱ ለባሹን እንዴት ሊያስከብረው ይችላል? ልብሱ ይሄን ከንቱ ሰውዬ እንዴት ክቡር
ሊያደርገው ይችላል? መሆን የነበረበት ልብሱ ተገፎ ለተከበረ ሰው መደረብ ነበር። ያኔ ልብሱም ለባሹም ይከበራሉ።
መጎናፀፊያ አካልን ይሸፍን ይሆናል፤ ምናልባትም የአካል እንከንን የነፍስ ሴሰኝነት ግን በልብስ አይሸፈንም፡፡ ዝቃጭ ምግባር ግን ለቅድስና ሌት ተቀን ለሚታገሉ ልበ ብርቱዎች በተዘጋጀ መደረቢያ አይከለልም። በሱ ቤት እኔ ከእናቴ ጋር የሚስራውን ብልግና አላውቅበትም። የናቴ ውሽማዋ ነው።

ይሄኔ በየመቅደሱ ሰው የዘራውን ያጭዳል' እያለ ይቦጠለቃል፡፡

ሴሰኝነትን እየዘራ መከበርን ለማጨድ ማጭድ ይስላል፡፡ ከንቱ!!
ይሄኔ ስንቶች ስንጥር ለምታክል በደላቸው ንስሃን ሽተው ከፊቱ
ሲመጡ ዋርካ የሚያክል ስድነቱን በብብቱ ሸሽጎ ልባቸው ለንስሃ
እንዲሰበር ዘክሯል። የዘቀጠ!

የእናቴን ጣር ላይ መሆን ሊነግሩኝ እንደመጡት ሶስቱ እሱም እየተፀየፈኝ ቤቴን ለቆ ወጣ፡፡ የመጀመሪያዋ የእናቴ ብቸኛ እህት ነበረች፡፡ እዚሁ አዲስ አበባ ብትኖርም ገጠር እያለሁ በልጅነቴ ለበዓላት ስትመጣ ነበር ያየኋት፡፡ ጠይቃኝም ጠይቄያትም የማንተዋወቅ አክስቴ ናት።

“ምን አገባኝ ታዲያ? ለምን ፍግም አትልም?" ስላት ብታንቀኝ ደስ ባላት።

"ጨካኝ! አረመኔ!" ብላኝ ወጣች። ሳስበው የኔ ዘመዶች ግን የሆነ
የዛገ የማሰቢያ ክፍል ሳይኖራቸው አይቀርም::እንደወለደችኝ ከነእሪታዬ ጥላኝ አሸሼ ገዳሜዋን ልትል ስትሄድ ዞራ ልታየኝ እንኳን የሚራራ አንጀት ያልነበራትን ሴትዮ ጨካኝ! አረመኔ
ያላሏት ዘመዶቼ በወተት ምትክ ክፋት፣ በእናት እቅፍ ፈንታ ጥላቻ፣ በልጅነት ቡረቃ ልዋጭ መገፋትን ሲግቱ ፍቅርና
ጥላቻን ካምታቱበት ልቤ ርህራሄ ይናፍቃሉ፡፡

ሁለተኛው የእናቴ ብቸኛ ወንድም ነበር፡፡ ታላቋ ነው። አጎቴ የቤታቸው አድባር!!

"እንዴት እናትሽ መታመሟን ሰምተሽ ትቀሪያለሽ? ሞታም ቢሆን እኮ ይኸው ነው::" አለኝ በወቀሳ እፍረት የሚያሲዘኝ
መስሎት፡፡

“እሷ ብቻ ትሙት እንጂ ለሞቷ እንኳን አልዘገይም! ደስ እያለኝ መጥቼ እቀብራታለሁ።” ያልኩት አንቀጠቀጠው። ቅንጣት ርህራሄ እንደሌለኝ አስቦ ጥሎኝ ሄደ፡፡

ሶስተኛው አያቴ ነው:: የእናቴ አባት።
........…
"አባባ እኔን ለማናገር ሀገር አቋርጠህ መጥተህ ባላስቀይምህ ደስ
ይለኝ ነበር፡፡ እንዳደርገው እያስገደድከኝ ነው።እናቴ አንድ ሞት አይደለም አስር ሞት ብትሞት አልፀፀትም::" አልኩት::
"እናትሽ በህይወት ሳለች አግኝታሽ ገንዘብ ልትተውልሽ ትፈልጋለች። ካልደረስሽ ለሌላ ሰው ለማውረስ እያሰበች ነው።"

ብሉኝ ከፊቴ ላይ ስሜቴን መበርበር ጀመረ።

"ሃሃሃሃ ጥሩ ነዋ፡፡ በመኖሯ ማንንም ጠቅማ ማወቋን እኔንጃ በሞቷ እንኳን እስኪ ትጥቀም!" ስለው ደነገጠ፡፡

ንብረት ያሳሳታል ብሎ ማሰቡ ገርሞኛል፡፡ ምክንያቱም በኮልኮሌ ስብስብ ሀሴት የምቃርም ሴት አይደለሁም። የጮቤዬ ምንጭ ገንዘብ ቢሆን እንኳን ከዚህ በኋላ ምንም የገቢ ምንጭ ባይኖረኝ እድሜዬን ሙሉ ጮቤ እየረገጥኩ መኖር የምችልበት ሀብት ላለው ሀብታም የሸጠኝ እራሱ አያቴ ነው:: አያቴ ብቸኛው
በህይወቴ የተከሰተ ለጥሩ የተጠጋጋ ክስተት ነው።እናቴ ጥላኝ ስትሄድ የተቀበለኝ እሱ ነው:: ምንም እንኳን የልጁ ልጅ መሆኔን ሳያሳውቀኝ ባድግም፣ ምንም እንኳን ከሚያኖራቸው አገልጋዮች እንደ አንዷ ራሴን እየቆጠርኩ ስኖር
እንደልክ ሁሉ ቢያስችለውም፣ ምንም እንኳን እናቴ ማን እንደሆነች ሊነግረኝ ሳይፈልግ ባድግም፣ለጨለመ ልጅነቴ አንዱ ምክንያት ቢሆንም፣ ምንም እንኳን
በቅጡ ለማያውቀው ሀብታም ነጋዴ ቢሸጠኝም።ከብዙ ክፉ የኑሮዬ ገፅታዎች ውስጥ ደብዛዛው ክፉ እሱ ነው።

አልጋ ቢኖረኝ እንደ ፍጡር ለሊት ነበረኝ፡፡

ቅዠት ባይሆኑብኝ እንቅልፍ ነበረኝ፡፡

ቢያስተኙኝ ብዙ ህልም ነበረኝ።

ለሁሉም ርህራሄ አልባነቴን ብነግራቸውም ሁሉም የማይገባቸው ሀቅ ግን ሴትየዋን አልጠላትም በገፋችኝ ጥግ ወደርሷ የሚያስወነጭፈኝ ስበት አላት፡፡ የማስታውሰው ቅንጣቢ
የእናት የሚመስል ነገር አሳይታኝ አታውቅም፡፡ በክፋቷ ክምር ልጠላት እፍጨረጨራለሁ። ከንቱ መንፈራገጥ ብቻ ይሆንብኝና ለምትሰራው ቅጥ ያጣ ግፏ ምላሽ ከቀናት ንዴት በኋላ
በማልቆጣጠረው የእናት ፍቅር ጥም ሲቃጠል ራሴን አገኘዋለሁ።ብሽቅ እኔ! ልረሳት እመኛለሁ:: አልችልም።
ልጠላት አጥብቄ እፈልጋለሁ። አልችልም:: ልገላገላት እፈልጋለሁ። የሆነ ፍንትው ያለች ፀሃይ በደመቀችበት ማለዳ
ሞቷን የሚያበስረኝ መላዓክ በፈገግታ ታጅቦ "እነሆ እልልልልል የምትይበት ቀን መጥቶልሻል፡፡ እናትሽ በወዳጇ ሳጥናኤል እቅፍ ትገኛለች:: በክፋቷም በፍቅሯም የምትነጂበት ጊዜ አበቃ!" ቢለኝ ያ የተወለድኩበት ቀን የሚሆን ይመስለኛል። እናቴን መፈለግ ትቼ ራሴን የምፈልግ፡፡

በቁሟ አምርራ የምትጠላኝ እናቴ በሞቷ ዋዜማ ላይ ለንሰሃዋ መጫወቻ ጠጠር ልታደርገኝ ልታየኝ ትፈልጋለች፡፡ ኩነኔን
ፈርታ እንጂ እኔ አሳስቤያት አይደለም፡፡ ምናልባት ይቅርታ ልትጠይቀኝ እንኳን ከሆነ (አታደርገውም እንጂ!) ኀጢአቷን በኔ ይቅርታ ልትቀንስ እንጂ የሰበረችውን ልቤን ፍንክትካች ልትገጣጥም አስባ አይደለም፡፡

ከእያንዳንዱ ክፋት ጀርባ መሪር በደል አለ እያልኩ አስባለሁ።ጥያቄው የሚሆነው በደልን ይቅር ያለ በጎነት የለም ወይ? የሚለው ነው አንዳንዴ የወለደችኝን ሴት ሳስባት ለመራራነቷ ምክንያት እያበጀ በሚጃጃል ልቤ ልረዳት እሞክራለሁ።
ምክንያቷን ማወቅ እመኛለሁ። ከዛ ባዝንላት፣ ደሞ ያደረገችኝን
ሁሉ ብረሳላት፣ ደግሞም እድል ብሰጣት... በልፍስፍሱ እኔነቴ
ራሴን ለምወቅስበት መጠን ያህል ጊዜ ሞክሬያለሁ። አንድ እርምጃ ስጠጋት በመቶ ትሸሸኛለች፡፡ ይቅር ባልኳት እጥፍ
በደሏን ትከምርብኛለች፡፡ እንደቆሻሻ እየተፀየፈችኝ እንኳን እቅፏን እናፍቃለሁ። በሚያቆስል ምላሷ እየገሸለጠችኝ እንኳን
ፀጉሬን እየደባበሰች እንድታባብለኝ እቃዣለሁ። ራሴን ሳየው በርሷ የተለከፍኩ ይመስለኛል። የመኖር ትርጉም ቁልፌ በእሷ እናትነት ውስጥ ያለ ይመስለኛል፡፡ ሰውየው(የነፍስ አባቷ) ገስፀውኝ ከቤቴ ከወጡ ከሰዓታት በኋላም ይሄ ቄጤማ ማንነቴ ስለርሷ ማሰብ እንዳቆም
👍4
አልፈቀደልኝም። ምናልባት በፈጣሪ እጅ
ተይዛ ጥያቄዎቼን ትመልስልኝ ይሆን? ከዓመታት በፊት የነበራት ድንዳኔ ቀልጦ ይሆን? በሚዋልል ሀሳቤ እየበገንኩም
ቢሆን ተኛች የተባለበት ሆስፒታል መጓዝ ጀመርኩ፡፡

የጭካኔ መርዟ ሰውነቴን ሁሉ እንደሚመዘምዘው እያወቅኩ
የተኛችበት ክፍል ደረስኩ፡፡ አጠገቧ የነበሩት ዘመዶቿ ዘመዶቿ መሰሉኝ! ከነፍስ አባቷና ከአክስቴ ውጪ
አላውቃቸውም፡፡ ምናልባትም ጓደኞቿ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ሲያዩኝ አውሬ እንዳየ ታዳኝ መፈርጠጥ ቃጣቸው።ለሰላምታ እንኳን እጃቸውን ሳይዘረጉልኝ ክፍሉን ለቀው ወጡ። ስለእኔ ምን ብትላቸው ነው ሰው እንዳልሆነ ፍጡር የሚያዩኝ? እያልኩ አስባለሁ፡፡ አምጣ የወለደቻት እናቷ የምትፀየፋትን ልጅ ከሌላ
ጠፈር እንደመጣች ፍጡር ማየታቸው ተጨማሪ ማብራሪያ እንደማያስፈልገው አስብኩና ቅር አልተሰኘሁባቸውም። እኔና
እሷ ብቻ ተፋጠጥን። ፊቷ ጎረባብጦ እና አመዳም ሆኖ አህያ የፈነጨበት ሜዳ መስሏል። አጥንቷ ፊቷ ላይ ገጧል፡፡ ስትንቀሳቀስ በሰቀቀን ነው።

"እንዴት ነሽ?" ያልኳት የመሆኗ አኳኋን ግድ ሰጥቶኝ አልነበረም፡፡ ባትመልስልኝም ያለችበት ሁኔታ በግልፅ ይታያል።

"አልሞትኩም::" ያለችኝ መሞቷ እንደሚያፍነከንከኝ ሁሉ እርግጠኛ በመሆን ጥርሷን ነክሳ ነው:: በፍፁም ዓይኔን በሙሉ ዓይኗ አታይም።

"ምን ልትነግሪኝ ነው ልታገኚኝ የፈለግሽው? የሚጠቅም ነገር
መሆን አለበት::" በምትሰጠኝ መልስ ላለመብሸቅ ራሴን እያስናዳሁ መልሱን ጠበቅኩ።

"አልሰጠሽኝም እያልሽ የምትወቅሽኝን የእናትነት ፍቅር ማሳያ ከሆነሽ ብዬ ያለኝን ገንዘብ ልሰጥሽ ነው::" አለችኝ፡፡

አንቺ የሰይጣን ታላቅ እህት ከዚህ ሁሉ ኮልኮሌሽ ይልቅ አንድ የፍቅር ቃል፣ አንድ የይቅርታ ቃል፣ አንድ መሳም፣ የአንዴ
የእናት እቅፍ..አንዳቸው ብቻ እንኳ ልኬት በሌለው መጠን እንደሚበልጡ መገንዘብ የሚችል ልብ የለሽም ልላት ነበር ያሰብኩት።ዳሩ እሷ አጥፍቻለሁ ብላ ይቅርታ ከምትጠይቅ፣ተፀፅቻለሁ ብላ ከምታቅፈኝ፣ ናፍቀሽኛል ብላ ከምትስመኝ ሲኦል ሰባት እጥፍ ቢነድ ወደ እሳቱ ዓይኗን ጨፍና መወርወር
ትመርጣለች።

ከልብሽ የእናትነት ፍቅርሽ እንዲገባኝ ትፈልጊያለሽ?"

አይገባሽም እንጂ!" ስትናገር አለማፈሯ እኔን ያሳፍረኛል፡፡ እናት ሆና የምታውቅ ይመስል።

"እኔ ገንዘብሽን አልፈልገውም ለምትፈልጊው ሰው ስጪዉ ለኔ ግን ለጥያቄዎቼ መልስ ስጪኝ....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ቀላውጦ_ማስመለስ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ --------------------------------------------------- ሁሉም የሕይወት ገፅ መጨረሻ ላይኖረው ይችላል ለህይወት መጨረሻ ብሎ ነገር የለም።የአንዱ ቀን መጨረሻ የሌላው ቀን መጀመርያ ነውና።የሰኞ ማለቅ የማክሰኞ መጀመር እንደሆነው የምድር መጠቅለል ለሰማያዊ ህይወት መጀመር እንደሚሆነው....ሌላ ፅንፍ ግን አለው።…»
#አንድነት_ማለት

አንድ አካል ማለት
አንድ አምሳል ማለት
እንደ ጎፈርና ሰው ..
ከማርትሬዛ አካል ተጣብቀው እንዳሉት
በድንን መጋራት
አይደለም አንድነት

አንድ አካል ማለት
አንድ አምሳል ማለት
እንደ ሃገሬ ተክል እንደ አክሱም ሃውልት
አካልን ለማቅረብ ለመጓዝ ቢያቅት
በአይን ውሃ ተያይቶ ካለ መግባባት
ይህ ነው አንድነት፡፡
#አግርሞት

ለምንድን ነው ሃብቴ ሰማይ ያልደረሰው ?
አንሶ አንሶ አንሶ እንዲህ የኮስሰው?
እንዴትስ ነው ደስታ ከኔ የራቀብኝ ?
መሳቅ መሳቅ ብቻ ለኔ ያልሆነልኝ?
ለምንስ ነው የድል መስመሩ የጠፋብኝ ?
ስኬት ስኬት ብቻ ሆኜ የማልገኝ?
ብዬ መገረሜ ራሱ ገረመኝ
ለካ ስፈጠርም ራቁት ነበርኩኝ።
#ያው_እንደኛው_ናቸው

በሰማይ አዋፋት፣ አይዘሩም አያጭዱም
አገር አቆራርጠው፣ ሲራራ አይነግዱም
ግን ከኛ ኑሮ ምን ልዩ አረጋቸው?
ለእፍኝ እድሜ ሲባል፣ የሳር ጎጆ ማልማት
ሞላሁ ለማይል ሆድ፣ እህል በመሻማት
ያው እንደኛው ናቸው።

ያለም ከበርቴዎች
በፈጣን ጀታቸው፤ ሰማዩን ቢገምሱም
ርካታ ካለበት፣ ቀድመውን አይደርሱም
ሻርክ ተፈናጠው፣ ከባህር ቢጠልቁም
መንኰራኩር ጋልበው፣ ከጠፈር ቢመጥቁም
እኛን ከሚያሰጋን፣ አንድ ርምጃ እይርቁም።

የምድሪቱ ጌቶች
ለሰው ዐይን ሞልተው
ትልልቅ ቢመስሉም፣
በኩራት ተነፍተው
ተራራ ቢያከሉም፣
ከተሸከሸኩ፣ አንድ እፍኝ አይሞሉም።

ፍትወትና ፍራት፣ የሚጎትታቸው
ያው እንደኛው ናቸው፣
ባለስትንፋስ ሁላ፣ ቢታይ ተመንዝሮ
በቁመት አይበልጥም፣ ጎልያድ ከስንዝሮ
ለየቅል መሳዩ፣ ያው ነው ዞሮ ዞሮ።
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ሁለት


#በሜሪ_ፈለቀ

"እኔ ገንዘብሽን አልፈልገውም፡፡ ለምትፈልጊው ሰው ስጪው።ለኔ ግን ለጥያቄዎቼ መልስ ስጪኝ፡፡ ያኔ በመጨረሻ የእናትነት ፍቅርሽን ያለስስት እንደቸርሽኝ በልቤ እፅፍልሻለሁ።" አልኳት የተቃጠለ ውስጤን እና የሚለበልብ ትንፋሼን ለመደበቅ በለዘበ
አነጋገር። ከእርሷ ጠብታ ፍቅር እንደማላገኝ ገብቶኛል፡፡ ቢያንስ ግን ጭንቅላቴ ውስጥ የሚርመሰመሱ
ጥያቄዎቼን እንድትመልስልኝ ተስፋ አደረግኩ፡፡ በስልችት ከንፈሯን ወደጎን
ከፈት አድርጋ አሽሟጠጠች።

"አባቴ ማነው? ከማን ነው የወለድሽኝ?"

“ሰይጣን ነው። አባትሽ ጭራቅ ነው::" ተመሳሳይ መልስ ከዚህ በፊትም መልሳልኛለች። ከሰይጣንነቱ፣ ከጭራቅነቱ ያለፈ አታብራራልኝም። የገባኝ ነገር አባቴ ማንም ይሁን ማን
በድሏታል፡፡ በምሬት ትጠላዋለች።

"እሱ ለበደለሽ በደል ለምን እኔን አስከፈልሽኝ? ለምን ከዳሽኝ?
እኔ ምን በበደልኩሽ ነው የበቀል ጅራፍሽን እኔ ላይ ያጮህሽው?"
ድምፄ እየጨመረ ሲሄድ ጥያቄዎቼ የማይረቡ እንደሆኑ ሁሉ ፊቷ በንቀት ሲሸረድደኝ ዘለሽ ተከመሪባት የሚል ስሜት ተፈታተነኝ።

"ለማንም የማይበጁ ጥያቄዎችሽን.. ብላ እስክትጨርስ መታገስ አቅቶኝ አዞረኝ፡፡ አነቅኳት፡፡ የእጄ ፍጥነት ከቁጥጥሬ
ውጪ ነበረ።

"ከቋጥኝ የከበደ በደልሽን ለመቻሌ ቢያንስ መልስ ይገባኛል፡፡መልሺልኝ፡፡ መልሺልኝ አባቴ ማን ነው?" እጆቼ አንገቷ ዙሪያ ሲከሩ የፊቷ ደምስሮች ተወጣጠሩ።
አላውቀውም።" አለችኝ ከእጄ ለማምለጥ እየሞከረች፡፡ እውነቷን
አው ያለችኝ፡፡ እውነቷን መሆኑን ለማወቅ ዓይኗ እና ድምፀቷ በቂ ነበር፡፡ ሴትየዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውስጧ ስታወራ
ሰማኋት። አላውቀውም።በሚለው ቃሏ ውስጥ ምስጢራት እንደታጨቁ ሁሉ በመላው ሰውነቴ ፊደሎቹ ተሰራጩ፡፡ በሩ
ተከፍቶ ሰው ገባ፡፡ ካላወቀችው ሰይጣን ነው የምትለኝ ማንን እንደሆነ ልጠይቃት
ምላሴ ጫፍ ላይ ቃላቶቹ አንገዋልላቸዋለሁ።ለመተንፈስ ስትንፈራገጥ ነው ያደረግኩት የገባኝ ግርግር ተፈጥሮ ሁከት ደራ።ክፍሉ መሀል ተገትሬ ዘመዷቿ የመሰሉኝ ሰዎች ሲጯጯሁ እሰማለሁ እየደነፉብኝም ይመስለኛል ፖሊስ ሊጠሩም ሲንደፋደፉ፡፡
ከደራው ብጥብጥ አይሎ ጆሮዬ በአንድ ድምፅ ተደፍኗል።
አላውቀውም ሌላ ድምፆች የሚሾልኩበት ቀዳዳ የለም።የአክስቴ የስድብ ናዳዎች ሾልከው ሊገቡ ሲገፋፉ በተደፈነው ጆሮዬ የሚሰርጉ ፊደላትን ስገጣጥም ስድብ ወይ እርግማን
መሆኑን እጠረጥራለሁ።እየገፈታተሩ ከተኛችበት ክፍል ሲያስወጡኝም የሚሉትን አልሰማቸውም። በገፈታተሩኝ
ውክቢያ ፍጥነት እየተራመድኩ ከሆስፒታሉ ወጣሁ። መኪናዬን
ያቆምኩበትን ማስታወስ አልቻልኩም።
ቁልፉን በጣቴ እያሽከረከርኩ አራት እርምጃ በማትሞላ ቦታ ደጋግሜ በፈጣን
እርምጃ እመላለሳለሁ።መኪናዬን የቱጋ ነበር ያቆምኩት? ምንም እያሰብኩ አይደለም፡፡ ጭንቅላቴ ውስጥ የመቃብር ቦታ የመሰለ ረጭታ ነው የሚሰማኝ መኪናዬን ትቼ ለምን ታክሲ ተሳፈርኩ? ለታክሲ ነጂው በየትኛው ደቂቃ የቤቴን አድራሻ ነግሬው ነው ደጄ ላይ የጣለኝ? ምንም ቃል መተንፈሴን አላስታውስም።

መኪናሽስ?" ይለኛል ተፈሪ የአጥሩን በር እንደከፈተልኝ በሌባ ጣቴ እያሸከረከርኩት ያለሁትን የመኪና ቁልፍ እና ያመጣኝን
ታክሲ እያፈራረቀ እያየ። አልመለስኩለትም፡፡ የአጥሩ በር ቁልፍ
እጄ ላይ እያለ ለምን መጥሪያ ተጫንኩ? በቀጥታ ወደ መኝታ ቤቴ ገባሁ።ልብሴን አውልቄ እዚያና እዚህ ወርውሬ መታጠቢያ ቤት ገባሁ:: በቁሜ ውሃው እላዬ ላይ ሲፈስ ምን ያህል
እንደቆየሁ እንጃ፡፡ ተፈሪ መኝታ ቤት ሲያወራ ይሰማኛል። ምን እንደሚል አልሰማውም፡፡ ለአስራ ስድስት
ዓመት በቆየ ትዳራችን በድምፁ ብቻ ሲፈልገኝ አውቀዋለሁ።በምንም ስሜት ሆነ በየትኛውም ሰዓት ልብሴን አውልቄ ካየኝ እንዲህ ያደርገዋል፡፡ ያን ድምፁን እጠላዋለሁ:: በክረምት የሚጮሁ ብዙ እንቁራሪቶች ፂፂስታ ይመስለኛል። እንደዛ
ሲያወራ ስሰማው ጆሮዬን ይበላኛል። በጣቴ ጆሮዬን ደጋግሜ እኮረኩራለሁ። እላዬ ላይ ሰፍሮ ላቡንና የወንዴ ፈሳሹን
እስካላንጠባጠበ እንደ ቆስለ ውሻ ማላዘኑን አያቆምም።ሙሉ ቀን የመሰለኝን ያህል ሰዓት ከውሃው ስር ቆሜ ብሰነብትም ተፈሪ ማላዘኑን አላቆመም።እየተንጎራደደ መሆኑን ድምፁ
የሚመጣበት አቅጣጫ ያስታውቃል። ፀጉሬና ገላዬ የተሸከመውን ውሃ እያራገፍኩ ወደ መኝታ ቤት መጣሁ። ቆሞ እየቀላወጠ ያየኛል። መጨቃጨቁ ልቤን ዝቅ ከማድረግ ያለፈ ፋይዳ እንደማይኖረው አውቃለሁ፡፡አይተወኝም:: መገላገል ነው አቋራጩ መንገድ፡፡ አልጋው ላይ እየተሳብኩ በጀርባዬ ተጋድሜ እግሬን ከፈትኩለት፡፡

አንዳንዴ ሳስበው እንኳን ትንፋሽ ኖሮኝ እየሰማ ሞቼ እግሬ ተከፍቶ ቢያገኘኝ በድኔ ላይ ሰፍሮ መወዛወዙን የሚያቆም
አይመስለኝም፡፡ እየገለፈጠ ልብሱን አወላልቆ ከላዬ ሆነ። ስልት የሌለው ውዝዋዜ ከቦርጩ እየታገለ ይወዛወዛል፡፡ በኮርኒሱ ላይ አምፓሉን ከምትዞር ትንኝ ጋር ዓይኖቼ አብረዋት ይዞራሉ።
ለአፍታ ዓይኔን ነቅዬ ስመለስ ወደኋላ ተመልሳ ይሁን ዞራ መጥታ በአምፓሉ ዙሪያ ከነበረችበት ወደ ኋላ መጥታ አገኛታለሁ እስካሁን አልጨረሰም ሰውነቴ ላይ የተንጠባጠበው ላቦቱ ሰውነቱና ሰውነቴ ሲነካካ የሲኦል ማስጠንቀቂያ ደወል የሚመስለኝን ድምፅ ይፈጥራል፣ ሰውነቴ በላቡ ሲጠባበቅ ላቡን የቀመስኩት ይመስል አፌን ጨው ጨው ይለኛል ሁሌም እንዲህ ነበርን።እሱ ተወዛዋዥ እኔ የውዝዋዜው መድረክ፡፡ አለቀ! አስራ ስድስት ዓመት። ዛሬ ግን
በተለየ ሰለቸኝ እንዲወርድልኝ ናፈቅኩ፡፡ መልሼ ዓይኖቼን ወደ አምፖሉ እልካለሁ። የምትዞረዋ ትንኝ የለችም:: ዙሯን ጨርሳ ወይም ሰልችቷት ሄዳለች።የእኔም መንገድ እንደትንኟ ይመርለኛል ዙር መዞር ፤ አንድን መንገድ እየደጋገሙ መርገጥ፡፡ ዓለም ራሷ ክብ አይደለች? ኑረትም እንደዛው መሰለኝ። አንድ ዒላማ ላይ መሽከርከር፡፡ ሽክርክሪቱ ያው ቢሆንም ሁሉም ሰው የሚሽከረከርበት መሃለኛ ነጥብ አለው።የታደሉት የሽክርክሪታቸው መሃለኛ ነጥብ ስህተት መሆኑ ሲገባቸው ወይም ሲሰለቻቸው አልያም ተስፋ ሲቆርጡ ዒላማቸውን ይቀይሩትና አዲስ ሽክርክሪት ይጀምራሉ።
ኡፍፍፍፍ እስካሁን አልጨረሰም? ዛሬ ደግሞ የላቦቱ ብዛት!

እናቴን ቀብሬያት ነው የመጣሁት!" ስለው ራሴን ሰማሁት።ውስጤ ወንድነቱ ሲሟሽሽ ተሰማኝ፡፡ አፍጦ እንደ እብድ እያየኝ ከላዬ ላይ ኩምሽሽ ብሎ ወደ ጎኔ ወደቀ።በስመአብ ወወልድ መቼ ሞተች? ለምን አልነገርሽኝም? እንሂድ እንዴት አትይኝም?"የጣር በሚመስል ቀሰስተኛ ድምፅ ጠየቀኝ፡፡

“ቅድም ሞተች፡፡ እናት የለኝም:: ቀብሬያታለሁ።” ስለው ግራ ተጋብቶ በድንዙዝ ስሜት ከተጋደመበት ተነሳ።
"መች ሞታ ነው? ቄሱ የመጡት የእናትሽን ሞት ሊያረዱሽ ነው? የት ነው የተቀበረችው?"

"እኔ ልብ ውስጥ!" ስለው ጤነኛ አልመስልኩትም። ብዙ ጥያቄ አከታትሎ ጠየቀኝ፡፡ አልመለስኩለትም፡፡ ጭራሹኑ ያልሰማሁት ይበልጣል፡፡ አወላልቆ እንደፍየል በጠጥ የበታተነውን ልብሱን
እየሰበሰበ ትቶኝ ወጣ፡፡ለምን ያህል ሰዓት
እንደዛው እንደተጋደምኩ ለማወቅ ብሞክር እሩቅ ሆነብኝ፡፡ አስባለሁ:: ምን
እንደማስብ ውሉን አልይዘውም:: ለራሴ እየደጋገምኩ "እናት የለኝም።አባቴም አይታወቅም::" እላለሁ። ቃሌን አላመንኩትም:: እደጋግማለሁ:: የአባቴን
ማንነት ማወቅ ያለመቻሌ በተወሰነ መልኩ እረፍት መሰለኝ፡፡ ሌላ ፍቅር ፍለጋ
መፋተጉ አቁሳይ ሊሆንብኝ ይችላል:: ፍፁም ሊገባኝ አልቻለም።እናቴ ስላልተቀበለችኝ ዓለም ሁላ ያልተቀበለኝ ርካሽ እንደሆንኩ እየተሰማኝ አንገቴን የምደፋው ለምን ይሆን? የሷ ጥላቻ የዓለም ሁሉ ጥላቻ ሆኖብኝ የተፈጥሮ ሁሉ
👍2
ልብ ጥላቻ እንዳቆረብኝ የሚታወቀኝ ለምንድነው? ፍጥረት ሁሉ ለሷ አሸብሽቦ
የማይፈልገኝ አላስፈላጊ ፍጡር መሆኔ በርትቶ የሚጠዘጥዘኝ እንዴት ይሆን?

እንድትሞትልኝ የምፈልገው ዘመዶቼ እና እራሷም ጭምር እንደሚያስቡት ስለምጠላት አይደለም፡፡ በተቃራኒው ነው።ስለምወዳት ነው:: ካለእርሷ ትርጉም ያለው ቀን ስለማልችል ነው፡፡ የሽክርክሪቴ መሀለኛ ነጥብ እሷ ናት።
የምስቅልቅሌ ሁሉ ቁልፍ እሷ ናት:: የጣዕም አልባ ውሎዬ ጨው የእሷ ፍቅር ነው:: በፍጥረት ሁሉ ላይ ለያዝኩት ቂም
ማስተሰርያ የእሷ እቅፍ ነው:: መኖር የምጀምረው እንደገና በፍቅሯ ስትወልደኝ ነው:: እሷ ግን በፍፁም ያን አታደርግም፡፡
በፍፁም!!! ዘመኗ በረዘመ ቁጥር እሷን መዞሬን አላቆምም፡፡
እሷም እንድጠላት ልቤን መቧጠጧን አታቆምም። በሰበረችኝ መጠን ራሴን ችዬ መቆም የማልችል ደካማ እሆናለሁ:: መደገፍ የምፈልገው ግን እሷኑ ይሆናል፡፡ ከእሷና ከመረረ ጥላቻዋ ውጪ እወድቃለሁ። ማነኝ? ከየት መጣሁ? የማን ዘር ርጭት ነኝ?
ካልፈለገችኝ ለምን ዘጠኝ ወር ሙሉ በሆዷ ተሸከመችኝ? ከምን ብፈጠር ነው አምጣ የወለደችኝን ልጇን ከነደሜ ጥላኝ የሄደችው?

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ቀላውጦ_ማስመለስ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_ሁለት ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ "እኔ ገንዘብሽን አልፈልገውም፡፡ ለምትፈልጊው ሰው ስጪው።ለኔ ግን ለጥያቄዎቼ መልስ ስጪኝ፡፡ ያኔ በመጨረሻ የእናትነት ፍቅርሽን ያለስስት እንደቸርሽኝ በልቤ እፅፍልሻለሁ።" አልኳት የተቃጠለ ውስጤን እና የሚለበልብ ትንፋሼን ለመደበቅ በለዘበ አነጋገር። ከእርሷ ጠብታ ፍቅር እንደማላገኝ ገብቶኛል፡፡ ቢያንስ ግን ጭንቅላቴ ውስጥ የሚርመሰመሱ…»
#ስምና_ስያሜ

አብራክን አካፍለው
ከምድር ሲመጡ
ምግባረ ስራቸው
ሳይታይ በቅጡ
ወላጅ እንዲጦሩ
ፍስሃ እንዲጠሩ
በንግስና ሹመት
የሃገር መሪነት
በጦር አዝማችነት
የድል አድራጊነት
መጠሪያ ስያሜ
በቃል ከተሰጡ
ስመ ትንሾቹ
ተግባር ግን በለጡ፡፡
#እድሜና_እኔ

እድሜዬና እኔ እንዳሻን ስንጓዝ
እኔ እየኮሰስኩ እሱ ግን ሲኮፈስ
አግኝቼው አንድ ቀን ውስጤን ብጠይቀው
ለምን እንደሆነ ቀድሞኝ የሚሮጠው
ግዜ የለኝም ብሎኝ ከፊቴ ሄደብኝ
እኔ እያነባሁ እሱ ግን ሳቀብኝ

🔘በፋሲል ሃይሉ🔘
#ኗሪ_አልባ_ጎጆዎች

#አያቶች!
በባዶ መስክ ተመራምረው
ጥበባቸውን
ዕድሜአቸውን
ገብረው
የጎጆ ንድፍ ሲያበጁ
አረጁ
ዘመናቸውን ፈጁ

#አባቶች!
መላ ዘመናቸውን
ጎጆ በመቀለስ አሳለፉ
ሳይኖሩበት አለፉ

#ልጆች!
ጎጆውን ለመውረስ ሳይከጅሉ
እንዲህ አሉ
"ያ'ባቶቻችን ጎጆ
ይሁን ባዶ ይሁን ኦና
በ'ኛ ቁመት
በ'ኛ መጠን
አልተቀለሰምና።"

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_አስራ_ሦስት


#በሜሪ_ፈለቀ

በእርግጥ እናቴ እሷ መሆኗን እስካወቅኩበት ቀን ድረስ እናትና አባቴ ሞተውብኝ ከሩቅ ሀገር አምጥተው የሚያሳድጉኝ ጥያቄ አልባ
ቀኖች የነበሩኝ ህፃን ነበርኩ:: አባባ የምለው አሳዳጊዬ እግዚአብሔርን በመፍራቱና በደግነቱ ትንሿ ያደግኩባት የገጠር ከተማ ድፍን ነዋሪ የመሰከረለት፣ ሚስቱ የምትኮራበት፣ ልጆቹ የሚመፃደቁበት፣ እኔን ጨምሮ ቤቱ የምንኖር አገልጋዮቹ የምንመካበት ሰው ነበር፡፡ በልጅነቴ ውስጥ ያለው አሳዳጊዬ ይህ ነው፡፡ የልጅነትን ቡረቃ ተሰናብቼ መብሰልና ህልም ማለም ስጀምር ለክብሩ እንጂ ለእኔ ግድ ከሌለው አያቴ ጋር ተዋወቅን፡፡በእርግጥ በቸርነታቸው ከሚያሳድጉኝ መልካም አሳዳጊዎቼን
ላሳዩኝ በጎነት በልቤ የማመሰግን፣ ለውለታቸው ክፍያ በአቅሜ
የማገለግል አገልጋያቸው እንጂ ለጎደለው
የማማርርበት መብትም ሆነ ይገባኛል የምለው አንዳች ያልነበረኝ ትንሽዬ ልጅ ነበርኩ። ቢቆጡኝ፣ ቢሰድቡኝ፣ ቢያንቋሽሹኝ ትምህርት፣ ቢሰድቡኝ ትምህርት እንድማር ሳይፈቅዱልኝ ከማንበብና መፃፍ የዘለለ ባላውቅም፣ እንደልጅ ለመጫወት ባይፈቅዱልኝ
መሄጃ የለሽ ወላጅ አልባ ህፃን ለሚያሳድጉ ደግ አሳዳጊዎቼልክ ነገር መሆኑ ነበር የሚገባኝ፡፡

በአስራ አራት ዓመቴ ገደማ ለአዲስ ዓመት መለወጫ በዓል ሁሉም ቤተሰብ ተሰብስቧል። አክስቴና እሷ ከአዲስ አበባ ነበር የመጡት:: ሴትነቴ ያበበበት ወቅት ነው።የሰፈራችን ጎረምሶች
በአጠገቤ ሲያልፉ ቂጤን ገፍተር፣ ያጎጠጎጠ ጡቴን ቆንጠር እያደረጉ ያሽኮረምሙኛል፡፡ አመሻሹን ከብቶች ከሜዳ ይዤ ስመለስ ችፍ ያለው የሰንሰል ተክል አጠገብ አዳነ ቆሟል። ጎትቶ
ወደራሱ አስጠጋኝ፡፡ የመጀመሪያ ጊዜው አይደለም:: ጡቴን እንዳስነካው ያባብለኛል። ብዙ አላስለምነውም:: ሲነካካኝ ደስ ስለሚለኝ እፈቅድለታለሁ።

"እረፍ አዳነ ቤት ሁሉም አሉ። እየጠበቁኝ ነው ልቀቀኝ" ብዬው ነበር አልሰማኝም። እንደሌላ ቀኑ አላባበለኝም:: ወደ ሰንሰሉ
ውስጥ ይዞኝ ገባ፡፡ ከላዬ የለበስኩትን ልብስ ወደ ላይ ሰብስቦ ጡቴን ሲነካካኝ የምከለክልበት አቅምም ምክንያትም ከዳኝ። ሳሩ ላይ አጋድሞኝ ጡቴን በአፉ ሙሉ እየጎረሰ ሲተፋው እያቃሰትኩ
ነበር። ድንገት አቁሞ ሲበረግግ የጨፈንኳቸውን ዓይኖቼን ገለጥኳቸው።ያየሁትን ደግሜ ላለማየት ዓይኖቼን ጨፈንኳቸው። መልሼ አጮልቄ አየሁ። ከተጋደምኩበት ሆኜ ሳየው ጋሼ (የአባባ ብቸኛ ወንድ ልጅ) ከሰማይ ላይ ተወርውሮ የተንጠለጠለ መስሎ ዓይኑን ጎልጎሎ አፍጥጦብናል። አዳነ ፓንቱ እስኪቀደድ እግሬ አውጪኝ ብሎ ሲሮጥ ጋሼ ማጅራቴን ጨምድዶ ይዞኝ ወደቤት ገባ። በቤቱ ጣራ ስር ያሉትን ሁሉ
በጩኸቱ ስብስቦ እንደ ክፉ ወንጀለኛ ፊትለፊታቸው አቆመኝ፡፡የት እንዳገኘኝ እና ምን ስሰራ እንደነበረ በሚዘገንን ፀያፍ ቃል ለሁሉም ተናግሮ እንዳበቃ ተራ በተራ የምላሳቸውን መርዝ ተፉት። እሷ ምንም አልተናገረችም።ዓይኖቿ ውስጥ የነበረው መፀየፍ ግን ከእነርሱ ስድብ በላይ ህመም ነበረው።የሚያውቁትን ስድብና ቁጣ ሁላ ጨርሰው ፀጥ ሲሉ ወደ ጎዳ ገባሁ።እሷም ሲጋራዋን ልታጨስ ወደ ውጪ ወጣች።ጋሼም ተከተላት።በጎሮ በር አድርጌ ወጣሁ።ልሰማቸው ፈልጌ ባይሆንም ሲጯጯሁ ይሰማኛል። የመደናቆራቸው መንስኤ እኔ መሆኔን ሳውቅ ጆሮዬን ጥዬ መስማት ጀመርኩ፡፡

እንቺ የወረወርሻትን ዲቃላ እድሜ ለአባቴ በይ አሳደግንልሽ፡፡ እሷ ይዛብን የምትመጣውን ዲቃላ ማን ሊሸከምልሽ ነው?ካንቺም ብሶ እንዳለማች ቆጥረሽ ዝም ትያታለሽ? ባንቺ ነው የወጣችው! ገና ቂጧን ሳትጠርግ በየሳሩ ትሸረሙጣለች፡፡ ከዚህ በኋላ እግሯን እየጠበቅኩ የከፈተችውን እግሯን አልገጥምም።ከፈለግሽ ወስደሽ የምታደርጊውን አድርጊያት:: " ከእውነታው እኩል የመረጣቸው ፀያፍ ቃላት አስደነገጡኝ፡፡ የሰማሁት
እውነት መሆኑን መቀበል አቃተኝ፡፡ እሷ አትመልስለትም።አጎቴ አንዴ እህቱን አንዴ እኔን እየሞለጨ ደቂቃዎች አለፉ፡፡
ደጋግሞ ከተናገረው እሷ እናቴ መሆኗን እና ለእነሱ ጥላኝ እንደሄደች ገባኝ፡፡

"እናቴ አንቺ ነሽ? አባባ አያቴ ነው?" አልኩኝ ተኮራርፈው ሳሎን እንደተቀመጡ ሁሉም ነብር እንዳየ ጥንቸል ዓይናቸው
ተጎልጉሎ ጆሮአቸው ቆመ።የመለሰልኝ የለም፡፡

ውጪ ያወራችሁትን እንዳለ ሰምቻለሁ::" አልኳቸው፡፡

እና የሰማሽ እንደው ምን ይሁን? እኔ እናትሽ አይደለሁም ስትለኝ እናቴ መሆኗን ስሰማ ተንሰራፍቶ የነበረውን
ብልጭታ ደስታ በተነችው:: አጠገቧ ተጠግቼ እጇን ስይዛት መንጭቃ ገፈተረችኝ፡፡ እናቴ መሆኗን ሳላውቅም በፊት ይዣት አውቃለሁ፡፡ እንደዚህ አስጠልቻት አይቻት አላውቅም፡፡ እነ አባባ ጋር የምትመጣው ከስንት
ዓመት አንዴ ቢሆንም የምትለብሳቸው ልብሶች፣ ሲጋራ አጫጫሷ፣ ቁመቷ፣ አካሄዷ...
ባየኋት ቁጥር እንደርሷ መሆን የምመኝላት ነበረች::ስትመጣ እንግዳ ሲመጣ እንደማደርገው እግሯን የማጥባት እኔ ነበርኩ፡፡ ከስንት ዓመት አንዴ ለአዲስ ዘመን መለወጫ ስትመጣ
አዲስ ልብስ እቤት ላለነው ሁሉ ስትገዛ ለእኔም ገዝታልኝ ታውቃለች:: እንደዛ ቀን በጥላቻ አመናጭቃኝ አታውቅም።

በእርግጥ የምትፈልገውን ነገር ልታዝዘኝ ካልሆነ በቀር በፍቅር ወይ በክብርም አናግራኝ ማወቋን አላስታውስም፡፡
በደስታ፣በተስፋ እና ግራ በመጋባት መሃል ዋለልኩ:: በጥያቄ መዓት ተበታተንኩ፡፡ ተራ በተራ አፍ አፌን ብለው አባረሩኝ፡፡
ዓይኗን እንኳን መልሼ ሳላየው ተመልሳ ወደ አዲስ አበባ ሄደች።

ባልገባኝ ምክንያት ከዚያን ቀን በኋላ ከአባባ በቀር ሁሉም ያመናጭቀኝ ጀመር። ለምን የስጋቸው ክፋይ መሆኔ
እንዳሳፈራቸው ግራ ተጋባሁ:: ምንስ ቢሆን ደግሞ የእኔ ጥፋት ምኑ ላይ ነው? ከቀናት በኋላ አባባን እያለቀስኩ እውነቱን
እንዲነግረኝ ጠየቅኩት። የአስራ ሁለተኛ ክፍል ተማሪ ሳለች ከሆነ ጎረምሳ ጋር ተጣልታ ከባድ ጉዳት ስላደረሰችበት አስር ወር ተፈርዶባት መታሰሯን ነገረኝ። ማንም የተፈጠረውን አያውቅም፡፡ ሊጠይቋት ሲመላለሱ ማናቸውንም ለማግኘት ፈቃደኛ አልነበረችም። ፍርዷን ጨርሳ ወደ ቤት ስትመለስ መንገድ ላይ ነበር ምጥ የጀመራት:: ማናቸውም ማርገዟን ሳያውቁ እቤት እንደደረሰች ወለደችኝ፡፡ አባቷ ወግ አጥባቂ እና
ክብሩን ወዳድ ስለነበረ ተዋረድኩ ብሎ ያዙዙኝ ልቀቁኝ አለ፡፡
(ይሄን ሲነግረኝ በቁጭት ነበር) አንዲትም ቀን አላደረችም፡፡ለማንም ምንም ሳትል ከነደሜ ጥላኝ ጠፋች:: ከቤተሰቦቿ ጋር
መልሳ ስትገናኝ አድጌ በእግሬ ድክ ድክ እል ነበር። ሁሉም በዲቃላነቴ ደስተኛ ስላልነበሩ እናቴ መሆኗን እንዳላውቅ
የሰጠችው ማስጠንቀቂያ ተስማማቸው:: አብዛኛዎቹ የቤት አገልጋዮች እንደሚጠሩት ከስሜ የማስከትለው የአባባን ስም ነው:: የእኔ መወለድ ሌላ ሴት እንድትሆን እንዳደረጋት አባባ ሲነግረኝ ለቤተሰቡም ሆነ ለእናቴ ክፉ እጣ እንደሆንኩ ደጋገመልኝ እናቴ እኔን ከመውለዷ በፊት ከወንድ ልጁ ይልቅ በራስ መተማመኗ የሚያስተማምነው፣ ጎበዝ ተማሪ ስለነበረች ቤት ተከራይቶላት ከተማ የሚያስተምራት መኩሪያው፣ ትልቅ
ቦታ ትደርስልኛለች ብሎ የሚመካበት የዓይኑ ማረፊያ፣ ማንም ደፋር ቀና ብሎ የማያያት ጉልበተኛ እና ደፋር እንደነበረች
በትካዜ ፊቱ ደብዝዞ አወራኝ፡፡ እኔን ከወለደች በኋላ ጠፍታ ስትመለስ የማያውቋት ሌላ ሴት ሆና መምጣቷን ጨመረልኝ፡፡

"አባባ አባቴ ማን ነው?" አልኩት:: ምናልባት አባቴ ልጁን በፍቅር ክንዱን ሊዘረጋልኝ ይችላል ብዬ እያሰብኩ፡፡

"አናውቀውም:: ከእርሷ ውጪ የሚያውቅ የለም:: ስለአንቺም ሆነ ስለአባትሽ ጥያቄ ሲነሳባት ጣረሞት እንዳየ ሰው
ትንፈራገጣለች::” አለኝ፡፡

አባባ ከነገረኝ ያልተሟላ ታሪክ
👍2