አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
ለእርሷም እንደዛው፡፡ አስረኛ ክፍል ስደርስ እሱ በጉበት ካንሰር ሞተ፡፡እናቴ ድንገት ካለችበት መጣች።

"ርቄ ልሄድ ነው።

" አለችኝ ከለቅሶው በኋላ፡፡

የት? ወዴት? ለምን? አላልኳትም፡፡ ምክንያቱም ወትሮም አልነበረችም፡፡ የነበረችባቸውንም ጊዜያት ቢሆን ህልውናዋ የለገሰኝ የማስታውሰው የጠራ ስሜት አልነበረኝም:: ትምህርት ቤት ደርሼ ስመለስ የለችም።አልጋዋ ላይ የተወሰነ ገንዘብ እና ደብዳቤ አስቀምጣልኛለች፡፡ የፃፈችልኝ እንዳልፈልጋት፣ ትምህርቴን እንድማር፣ ጎበዝ ልጅ እንድሆን፣ ሱስ እንዳቆም
እና እናት ስላልሆነችልኝ ይቅር እንድላት ነበር:: አልከፋኝም፡፡ ደስም አላለኝም።

ክልስ ነኝ፡፡ አባቴ ምናዊ እንደሆነ አላውቅም:: እንዴትስ ላውቅ
እችል ነበር?

"ይሄኔ እኮ የዘጋ ሀብታም ፈረንጅ ይሆናል አባትህ:" ይሉኛል አብሮ አደጎቼ በቀልድ: የሚጎፈንነኝ ቀልድ መሆኑ አይገባቸውም። የሚያውቁኝ ሰዎች ስለእናቴ ሲያጉረመርሙ እሰማለሁ።
ስለሽርሙጥናዋ፣ ስለቀያየረቻቸው ወንዶች፣ ስላገባቻቸው ባሎች፣ ስለሰራችባቸው ትልልቅ ሆቴሎች...።
ያስጠላኛል: ያስጠሉኛል፡፡ ሀሜትና እውነታውን መለየት አልችልም::
ምክንያቱም ስለእናቴ የማውቀው እውነትም የለኝማ! ከወንዶች በነበራት ግንኙነት ዛቢያ የሚውጠነጠነውን ሀሜት ግን እሷ አታደርገውም ማለት ይከብዳል። ምክንያቱም እናቴ
ሴሰኝነት መክሊቷ ነበር።
ከማላያት ወንድ ጋር አልነበረም። ስለቤተሰብ ትስስር ተያያዥ ነገር መስማትም ማየትም አልፈልግም። አንዳንዴ እውነት ግን አባቴ ክዶኝ ነው? ወይስ ጭራሽ መፈጠሬን አያውቅ ይሆን? ብዬ አስባለሁ። አላውቅም። የራሱ ጉዳይ!! ባሏ ከሞተ በኋላ
ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን ጓደኛም የሌለኝ ሆንኩ፡፡ ከሱሴ ተጋባሁ።ከሱሶቼ ጋር በፍቅር ተቆራኘን። ከእንጀራ አባቴ ሱስ፣ ከእናቴ ሽፍደት፣ ከራሴ ቅጥ ያጣ ግድ የለሽነት አወጣጥቼ የአሁኑ ኪሩቤል ተሰራ።

"ኪሩ? አንተ ኪሩ?" ትከሻዬን እየወዘወዘች ጠራችኝ :: ስምሪት ናት። ቡና ልንጠጣ ተቀምጠናል።

"ፊትህ እኮ ደም መስሏል። ምን እያሰብክ ነው?" አለችኝ መልሳ።ከዚያን ቀን በኋላ በተገናኘን ቁጥር ደህና መሆኗን ልጠይቃት አስባለሁ። ልክ ሳያት
እተወዋለሁ፡፡ ልትጠይቀኝ የምትፈልገው ነገር ያላት ይመስለኛል:: ግን አትጠይቀኝም።እንደበፊቱ መጫወት አቃተን።

"ሴት ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለየ ስሜት ሳትሰጠኝ አልቀረም::" አልኳት፡፡"

ተመስገን ነው:: እንዴት የተለየች ብትሆን ነው?" አለችኝ ምንም ጉጉት ሳያድርባት፡፡

"በማላውቀው ምክንያት እናቴን መሰለችኝ።"

"እናትህን እኮ አትወዳቸውም።" አለችኝ ሰውነቷ እየፈሰሰ እስኪመስለኝ ተኮማትራ።

"አዎን አልወዳትም::" የሚሰማኝን መግለፅ ከበደኝ።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
#እጣ_ፈንታ

መዳፍ አስገልጬ
መስመሩን መርጬ
ያንቺና የኔ ጉዞ
እስከዚህ ነው ያልኩሽ
ባለማወቄ ነው
ስቼ አሳሳትኩሽ
የሰው እጣ ፈንታ
ቀድሞም የሚጻፈው
ከመዳፍ አይደለም
ለካስ ከግንባር ነው፡፡

🔘በፋሲል ሃይሉ🔘
#የምሬት_ምስጋና

በቁርጥ የጠገበ ሲያቀርብ ምስጋና
ቆሎ ካፉ ያለ ይሄንን አየና
ቢያሰማ 'ሮሮ
በ'ድሉ ተማሮ
አምላክ ተደሰተ ከምስጋና ቆጥሮ
ፍላጎቱ ሞልቶ ካንገቱ ባይቀና
የአምሳሉ ፍጡር ነፍሱ ተርፏልና።

🔘በፋሲል ኀይሉ🔘
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ስድስት


#በሜሪ_ፈለቀ

ግፈኛዋ እናቴን መሰልሽኝ፡፡ ግን በተለየ ወደድኩሽ፡ ነው የምላት? እንኳን ለርሷ ለራሴ የተደበላለቀ ነገር አለው። ለርሷ
ላስረዳት ቀርቶ ለራሴም አልገባኝም፡፡ እኔም አልገባኝም። ስምሪት ለምን እናቴን አስታወሰችኝ? “ስምረት ሞተች የሚለው
የአርሴማ ጥሪ የፈጠረብኝ ድንጋጤ እንዴት ብሽቅ ለሆነው የአሁኑ ስሜቴ ጎታች ምክንያት ሆነ? በውል ያልለየሁት
ለስምሪት የተሰማኝ ስሜት በምን ስሌት ወደልጅነት ትዝታዬ አሽመጠጠኝ? አላውቅም!! ምናልባት እስከማስታውሰው ለሰው ግድ የሰጠኝ በዚህ ክስተት ስለሆነ? ምናልባት ሰው መሆን ለሰው ማሰብን ያካትት ይሆን? ምናልባት ሰው ሆኜ ይሆን? ምናልባት ሰው በሆንኩ ቅፅበት እንደሰው ግድ ሳይሰጡኝ
ያለፍኳቸውን ክስተቶች ማሰላሰል መጀመሬ ይሆን? አላውቅም!!
ብቻ ምንም ሽራፊ ስሜት አይሰጠኝም ያልኳቸው ስንጣቂ የኑሮ ሰበዞቼን ሳይቀር ሳልፈልግ እያሰብኳቸው ነው።

"እያስጨነቅኩህ ነው?" አለችኝ ስምሪት ደጋግማ የማልወዳትን እናቴን እና የተለየ ስሜት የፈጠረችብኝን ሴት ምን
እንዳመሳሰላቸው ስትጠይቀኝ ቆይታ።

"እናቴን እንደማልወዳት እርግጠኛ እየሆንኩ አይደለም።" መለስኩላት። በእርግጥ የሚሰማኝ የትኛው እንደሆነ
አልለየሁትም። አቅፋኝ ታለቅስ ለነበረችው እናቴ ይሁን ቁብ ለማትሰጠኝ እናቴ የማልለየው ሀዘን ይቦረቡረኛል፡፡ ደግሞ
ተመልሶ የሚያንገሸግሽ ንዴት እና ጥላቻ ይግተለተልብኛል፡፡
ስምሪት ፀጥ አለችኝ፡፡ ዓይኖቿን አጥብባ ስታየኝ ቆየችና።

"ለምን አታረጋግጥም?" አለችኝ፡፡

"ምኑን?"

"ለእናትህ የሚሰማህን ስሜት?"

"እንዴት? በምን?"

“ፈልጋቸዋ!! ፈልገህ አግኛቸው።"

“የት ብዬ? ትሙት? ትኑር? እንኳን ማወቅ
ይከብዳል፡፡ብዙ ዓመት አልፏል።" ይሄን ለሷ ስመልስላት ራሴን ሰማሁት።ጥያቄዬ ልፈልጋት? ወይስ አልፈልጋት? የሚለውን እርከን አልፏል። 'አልፈልጋትም'የሚለውን
ጭራሽ አለማሰቤ አስገረመኝ። እሷም ይህ የገባት መሰለኝ፡፡ ፈጠን ብላ።

"ራስህን ዝግጁ ካደረግክ ፍንጭ የምናጣ አይመስለኝም::" አለችኝ
ዝግጁነቴን ለማረጋገጥ ነው መሰል ከአፌ የሚወጣውን ቃል አፏን ከፍታ እየጠበቀች፡፡ ፀጥ አልኩ። ፀጥ አለችኝ፡፡ እያየኋት እንደሆነ ሲገባት ታቀረቅራለች፡፡ እያየችኝ እንደሆነ ሳውቅ ዓይኖቼን በሌላ አቅጣጫ አርቄ እልካቸዋለሁ።

"ስምሪት?"

"አቤት?"

“እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ?" ራሷን በመነቅነቅ እንድቀጥል ተስማማችልኝ፡፡

"ለምንድነው ከሌላ ሰው በተለየ የምትቀርቢኝ? የምትሰሚኝ?
የምታወሪኝ?" የጠበቀችው ሌላ ጥያቄ እንደሆነ ሁሉ ፊቷ ረገበ።

ከአይምሮ ይልቅ ልብ ይማርከኛል፡፡" መልሷ እርግጠኛነት ነበረው፡፡

"ማለት?"

| “ከእውቀት ይልቅ ለቅንነት ዋጋ እሰጣለሁ ማለት ነዋ!! ቅንነት የሌለበት እውቀት በዜሮ ይባዛብኛል፡፡ቅንነት የሞላበት አለማወቅ እንኳን ይገዛኛል። ልብህ ቅን ነው::" ብላኝ ከኔ መልስ
እንደማትጠብቅ ተደላደለች። እሷ በገለፀችኝ ልክ ልበ ቅን መሆኔን እጠራጠራለሁ። ምክንያቱም ቅንነት ይመነዘራል ይመስለኛል፡፡ እኔ ስለራሴ እስከማውቀው ከራሴ ውጪ ለማንም
ግድ ኖሮኝ ለሰዎች ቀና ለማድረግም ሆነ ቀና ለማስብ ተጨንቄ አላውቅም። ማንም ጉዳዬ አይደለም።እሷ ሁሌም እንደዚህ ናት፡፡ ስለእኔ ስታወራ ባለቤቱ እርግጠኛ ከሆንኩት በላይ እርግጠኛ ናት፡፡ ምናልባት እኔ ራሴን ከማዳምጠው በላይ እሷ ስለምታዳምጠኝ ይሆናል። ሁሌም የምትጠቁመኝ ኪሩቤል መድረስ የሚችልበትን ጫፍ እንጂ ሰዎች ወይ እሷ መዳረሻ ብለው የሰቀሉትን ጫፍ አይደለም።

"ስምሪት?" ባልጠራትም እየሰማችኝ እንደሆነ አውቃለሁ።ከእስከዛሬው ሁሉ በተለየ እንድትሰማኝ ፈለግኩ፡፡

"አቤት?"

“ከዛን ቀን በኋላ አንቺን እንደአለቃዬ ወይም እንደጓደኛዬ ማሰብ እየቻልኩ አይደለም።" አልኳት። ከአፌ እስኪወጣ እየጠበቀችው ያለ ንግግር እንደሆነ ሁሉ መገረምም መደንገጥም ሳይታይባት

"አንድ እርምጃ ጠልቀህ ያወቅከኝ ስለመሰለህ ነው?" መልስ
የምትፈልግም አትመስልም።

“ማለት?" አልኳት ያለችው ሳይገባኝ ቀርቶ ሳይሆን የማስረዳት አቅም ከድቶኝ፡፡

"ኪሩ ልብሳቸውን ስትገፍ ያወቅካቸው እንደሚመስሉህ ሴቶች እርቃኔን ስላየኸኝ ገበናዬን የገለብክ አይምሰልህ፡፡"
የምታወራበት ቅላፄ የማላውቀውና ምሬት የተቀላቀለበት ነው፡፡ ምን
እንደምላት እና ለሷና ለማውቃቸው ሴቶች የሚሰማኝን የአንድ ጤፍ ፍሬና የተራራ ያህል የገዘፈ የስሜት ልዩነት ማስረዳት ባለመቻሌ ተናደድኩ።

"እንደዛ አይደለም የተሰማኝ። ውስጤ የቀረውን የገላሽን ምስል ሳስበው አብሬሽ መተኛት አይደለም የሚሰማኝ፡፡ ተሰምቶኝ በማያውቅ መልኩ ከወለሉ ላይ አንስቼሽ አልጋ ላይ ያደረስኩሽ ቅፅበት የእድሜ ዘመኔን ያህል ረዥም እንዲሆን ነው የሚሰማኝ፡፡ ክንዴ ላይ እንዳቀፍኩሽ የተከደኑ ዓይኖችሽን በስስት እያየሁ ዘመኖቼ ቢያልቁ ነው የተሰማኝ፡፡” ይግባት አይግባት እንጃ ከዚህ በላይ ማስረዳት ግን አቃተኝ፡፡ ደቂቃዎችን ትንፋሽ ያጠረኝ እስኪመስለኝ ፀጥ አለች፡፡
ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች "የለውጥ ኩርባ" አለችው።አስተሳሰቡ ወይ ስሜቱ፡ ወይ ድርጊቱ የሚቀየርባት።ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍበት ወይም ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርበት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት፡፡ለውጥ ወደ ተሻለ ማደግ ብቻ አይደለምና ኩርባውን ሲታጠፍ
ውድቀትም ሊሆን ይችላል፡፡ ያቺ የለውጥ ኩርባ አንድ የሆነች ኢምንት ክስተት ልትሆን ትችላለች ወይም ዓረፍተ ነገር ወይም አንዲት ቃል ምናልባት አንዲት መሳም ወይም የአንዲት ደቂቃ
መታቀፍ ወይም...

የኔ የለውጥ ኩርባ ያቺ ቀን ነበረች።

"ልክ አይሆንም። እኔና አንተ ከዚህ ቀደም ከነበረን የዘለለ ግንኙነት ሊኖረን አይችልም::" አለችኝ፡፡

"ቅድም 'ከአእምሮ ይልቅ ልብ ይማርከኛል አልሺኝ አይደል?

" እህ... " የምቀጥለውን ለመስማት እየሰገገች።

"ሲገባኝ ሌላ ፍቺው ከስሌት ይልቅ ለስሜት ቅርብ ነኝ ማለትሽ መሰለኝ፡፡ ልክና ስህተቱን በስሌት ልቀምርልሽ አልችልም። ባንቺ ፍቅር ከመውደቅ በላይ ልክ የሆነ ስሜት ተሰምቶኝ እንደማያውቅ ግን ላረጋግጥልሽ፡፡" አልኳት አሁንም ምን ያህል እንተረዳችኝ ባይገባኝም።

"ምናልባት እስክጋደምልህ ይሆናል። ፍላጎትህ እስኪረግብ!"ከአፉ የሚወጣው ቃልም ድምፀትም የሷ አይመስልም:: ጥርሷን እያፏጨች ነው የተናገረችው። በመጀመሪያ ደነገጥኩ፡፡ ስምሪት
እንዲህ ስትናገር ሰምቼ አላውቅም:: በመቀጠል ተናደድኩ።በፍፁም እየተረዳችኝ አልነበረም።በመሰለስ ግን ስለዚህች ሴት የማላውቀው ብዙ ነገር መኖሩን ማሰብ ጀመርኩ፡፡

ስደነግጥ

ለኔ ሳይሆን ለእርሷ ማንነት የማይመጥናት የመሰሉኝን ቃላቶች
በማውራቷ ዓይኖቼን ጎልጎዬ አፈጠጥኩባት።

ስናደድ

“እየገባሁሽ አይደለም።ስለሴክስ እያወራሁ አይደለም። እዚህ ጋር(ልቤን በእጄ ደግፌ) ስለሚሰማኝ ስሜት ነው እየነገርኩሽ የነበረው።" አልኳት በአፏ አልመለሰችልኝም:: ፊቷ ግን ስልችት
አሳየኝ፡፡

ማሰብ ስጀምር

"ማነው?" አልኳት

“ማን?" መለሰችልኝ

እንዲህ እንዲሰማሽ ያደረገሽ?" በረዥሙ ተንፍሳ ፀጥ አለች።


💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ሰባት


#በሜሪ_ፈለቀ

"እንዲህ እንዲሰማሽ ያደረገሽ?"በረዥሙ ተንፍሳ ፀጥ አለች።

"ድብቅ ነሽ።" አልኳት።

"ድብቅ እንኳን አይደለሁም::"

መለሰችልኝ፡፡

"እኔ የማልነግርሽ ክስተትም ስሜትም ኖሮኝ አያውቅም፡፡ ስላንቺ
አንዲትም ነገር አውርተሽ አታውቂም።"

"ጠይቀኸኝ አታውቅም፡፡ ለራሴ ቦታ አለኝ፡፡ ዋጋ የሌለኝ ሰው ጋ ራሴን የምጥል ርካሽ አይደለሁም::" ያለችው በትክክል ገብቶኝ እንደሆነ እርግጠኛ አልነበርኩም።

"አቤት? ዋጋ ባልሰጥሽ ኖሮ ስለራሴስ አወራሽ ነበር?"

"ዋጋ ስለሰጠኸኝ ሳይሆን ዋጋ ስለሰጠሁህ ነው ያወራኸኝ፡፡
ከሴቶችህ ብዙዎቹ ስለራሳቸው ነግረውናል፡፡ አንተ ግን ስለራስህ
ለአንዳቸውም ነግረህ አታውቅም። ለምን ይመስልሃል?ልትሰማቸው እንጂ ሊሰሙህ ጊዜያቸውንም ልባቸውንም አልሰጡህም። ወይም እንደዛ አስበሃል።" ከተናገረችው ሁሉ የገባኝ(ቃል በቃል ባትለውም) ልቤን ሰጥቼሃለሁ' ያለችው ነው።

"አሁን ልሰማሽ ዝግጁ ነኝ፡፡ ንገሪኝ! "

"አሁን ሰዓት ሄዷል። ወደ ቢሮ እንመለስ!" አለች በዓይኗ አስተናጋጅ እየፈለገች። ፍቅር የብዙ ነገር ቁልፍ መሆኑ ገባኝ
መሰለኝ፡፡ አስቤ ስለማላውቃቸው ብዙ ነገሮች ማሰብ ጀመርኩ፡፡
ከመለዮዬ ውጪ ምን ስለመልበስ አስቤ የማላውቀው ሰው ራሴን ልብሶች ስሸምት አገኘሁት።ያንተ ተክለ ሰውነት ልብስ ያስጌጣል እንጂ አንተን ልብሱ አያስጌጥህም፡፡ ለምትለብሰው መጠንቀቅ አይጠበቅብህም።"ብላኛለች ስምሪት ከመለዮዬ ሌላ ለብሼ ያየችኝ የመጀመሪያ ቀን፡፡

“ለምን እራቁቴን አታዪኝም?"

"አትባልግ እንግዲህ!"

በሌላ ቀን ለአንዲትም ቀን አስቤው የማላውቀውን ራሴን ቤተክርስቲያን ስፀልይ አገኘሁት፡፡ (በእርግጥ ከፀሎት ይልቅ ለንግግር የቀረበ ነገር ነበር) ፍቅር የሁሉ ነገር ቁልፍ መሆኑ መሰለኝ፡፡ የሁሉንም የህይወት ጥጎች ማጠንጠን ጀመርኩ።እስካሁን አንድ የሆነ ቦታ ላይ የሆነ እድሜዬ ላይ ቆሜ የነበር አይነት ስሜት ነበር የሚሰማኝ፡፡ ገና አሁን በስምሪት ፍቅር መኖርን የጀመርኩ፡፡ በገፋችኝ መጠን ወደርሷ የሚስበኝ ፍቅሯ
ልቤን ከብዶት ይጎትተኝ ጀመረ።ቀናቶች የንስር ክንፍ አውጥተው ይበራሉ እሷ በቻለችው መጠን ትሸሸኛለች እኔ ደግሞ ከምችለው በላይ ወደርሷ እወነጨፋለሁ። የምንገናኝባቸውን እና ልናወራ የምንችልባቸውን አጋጣሚዎች
ትዘጋቸዋለች።

ከነገ ጀምሮ እረፍት ወጣለሁ::" አለችኝ የሆነ ቀን የቀኑ ስራ ማብቂያ ሰዓት ላይ እየወጣን።

"ለምን? ሽሽት ነው?" አልኳት።

የምን ሽሽት? ማረፍ ፈልጌ ነው።" አለችኝ ዓይኖቼን እየሸሸች።ቆምኩኝ ቆመች አየኋት አቀረቀረች የጡቷቿ ጫፎች ደረቴን እስኪነኩት ተጠጋኋት። አልሸሸችኝም።ምንም እንቅስቃሴ አላደረገችም፡፡ ወደ ጆሮዋ ከንፈሮቼን አስጠግቼ “ታውቂያለሽ? ሁሌም አንድ እርምጃ ወደፊት የማያራምደን
የ'ባይሳካስ?” ፍርሃት ነው። እመኚኝ!! እመኚኝና ልብሽን ስጪኝ። አንድ ነገር ቃል እገባልሻለሁ። ልብሽን አልሰብርም
አልኳት። ዓይኗን ገርበብ አድርጋ ነበር የሰማችኝ ከመግለጧ በፊት አየኋት፡፡ ዓይኔ ከንፈሯ ላይ ቀረ። ውጤቱን ማሰብ
አልፈለግኩም።ወይም ምንም ቢሆን ግድ አልነበረኝም።
ከንፈሮቿን ሳምኳቸው። ለምን ያህል ሰከንድ እንደሆነ ባላውቅም
መልሳ ስማኛለች፡፡ እጇ በወገቤ ዙሪያ አልፏል። ይሄን ያሰብኩት ድንገት አቁማ ገፍታኝ ስትቆም እንጂ ስትስመኝ
ከጥፍጥናዋ ውጪ ማወቅ የቻልኩት ነገር አልነበረም።

“ኪሩ? ምንድነው የምታደርገው?" ጮኸችብኝ፡፡ ፈገግ አልኩ። ልቧን ስትሰማው ስማኛለች፡፡ መንገድ ላይ መሆናችን እንኳን አላሳሰባትም ነበር፡፡ አዕምሮዋን ስትሰማው ነው የገፋችኝ።
ባትነግረኝም የማትክደው ስሜት አላት። ፈገግታዬ አበሳጫት። ተናደደች።

"ኪሩ ሁለተኛ እንዲህ ብታደርግ እንጣላለን። የምሬን ነው!!"
አለች ድርጊቴ እንዳናደዳት ለመግለፅ እየጣረች።

"እሺ፡፡ ከዛሬ በኋላ ራስሽ ካልጠየቅሽኝ አላደርገውም::"

"ማለት?"

ኪሩቤል ሳመኝ ብለሽ አፍ አውጥተሽ ካልጠየቅሽኝ አልስምሽም።" አልኳት።

ወገኛ! ኪሩ እኔ አንተ እንደምታውቃቸው አይነት ሴቶች አይደለሁም።" አለች መንገድ እየጀመረች።

"አውቃለሁ!! ከነሱ የሚለይሽ ነገር ባይኖር ከነሱ የተለየ ስሜት
አትሰጪኝም ነበር።" መለስኩላት እርምጃዬን ከርሷ ጋር እያመጣጠንኩ።
'ለምን እኔን? ለምን? ደግሞስ ለምን አሁን? አንተ ማንም ሴት የምትደነግጥልህ ወንድ ነህ!"

"ማንም ሴት ደንግጣልኝ ይሆናል፡፡ ካንቺ ውጪ ያስደነገጠችኝ ሴት የለችም ለውጡ እንዴት አይታይሽም?" አልኳት።

ተለይታኝ ሄደችበልቤ። ተሸክሜያት ወደ ሱሴ ሄድኩ። በቀኖችህ ውስጥ ለምታደርገው ትግል ጥያቄው መሸነፍህ አይደለም።መዋጋትህ እንጂ ምክንያቱም ሳትታገል ሁሌም ውጤቱ የታወቀ ነው። ተሸናፊ ነህ። በትግልህ ውስጥ ውጤቱ ከሁለት አንዱ ነው። ማሸነፍ ወይም መሸነፍ!! ጥያቄው መዋጋትህ ላይሆን ይችላል የተዋጋህለት አላማ እንጂ። እሷ ናት። ምንንም ባልፍላት የሚገባት። እረፍት መውጣቷን ተከትሎ ናፍቆቷን መታገስ ከምችለው በላይ ነበረ። ስልኳ እረፍት ከወጣችበት ቀን ጀምሮ ዝግ ነው።ጭንቅላቴ የሚፈነዳ መሰለኝ፡፡
እቤቷ ላለመሄድ ከቁጥር በላይ ለሆነ ጊዜ አመነታሁኝ።
በስምንተኛው ቀን እሷን ሳላያት ባድር ትንፋሼ ቆሞ የማድር መሰለኝ።ከስራ ወጥቼ እቤቷ ሄድኩ:: በሩን ስትከፍትልኝ ምን እንደምላት፣ምን ለብሳ እንደማገኛት፣ ስታየኝ ምን እንደሚሰማት እያሰብኩ በሩን በስሱ ቆረቆርኩ ደገምኩት።ጨዋታ አቋርጦ እንደከፈተልኝ የሚያስታውቅ ሰው ያላለቀ ሳቁን እየቀጠለ በሩን ከፈተልኝ።

"አቤት?" አለኝ።

ሰምቼዋለሁ ዝም አልኩ፡፡ ደገመልኝ፡፡ ዝምታዬን ደገምኩለት።ስምሪት ከጀርባው ብቅ አለች። ምንም አይነት የፊት ሜክአፕ
ስትጠቀም አይቻት አላውቅም።ተቀባብታ ሌላ ሴት መስላለች፡፡ከከንፈሯ ውጪ ያልደመቀ የለም:: ለፓንትነት የቀረበ ቁምጣ እና ለጡት ማስያዣነት የቀረበ ሹራብ ለብሳለች። ፀጉሯ ቢመሳቀልም ተለቋል።እሱን አየሁት።በሲሊፐር ነው።
እንግድነት አይታይበትም።የከንፈሩ ጠርዝ ላይ አስተዋልኩ። ስምሪት ያስደነገጣት የኔ መምጣት ይሆን ወይም የመጣሁበት ሰዓት አላውቅም ደንግጣለች፡፡

"እንዴ? ኪሩቤል?" እየተንተባተበች ጨበጠችኝ፡፡

ሰውየው ለኔ ማሳወቅ የፈለገው ነገር ያለ መሰለኝ አቅፎ ወደ ራሱ አስጠግቶ ፀጉሯን ሳማት፡፡ እሷ በድርጊቱ ያፈረች መሰለኝ ዓይኔን ሸሸችው።

"ማሬ የስራ ባልደረባዬ ነው።" አለች ለሰውየው።ለኔ ደግሞ "የአርሴማ አባት ነው::" ተጨባበጥን።

“ኦው ፖሊስ ነህ? የሆሊውድ አክተር ነበር የመሰልከኝ፡፡ ሃሃሃ" ሰውየው መቀለዱ ነው።በቡጢ ዱልዱም አፍንጫውን ባጠፋለት ደስ እንደሚለኝ ቢያውቅ፡፡ በዚህ መሃል አርሴማ ዓይኗን እያሻሸች በአባቷና በእናቷ እግር መሃል ብቅ አለች። ስታየኝ ፈገግ ማለቷ ያስታወሰችኝ ስለመሰለኝ ደስ አለኝ። ልስማት
ስጠጋት ግን ሸሸችኝ፡፡

“ይቅርታ በማይሆን ሰዓት መጣሁ መሰለኝ። የስራ ጉዳይ እቤት ድረስ ይዤ መምጣት አልነበረብኝም::" መናገር ስለነበረብኝ አልኩኝ እንጂ እግሬ ከመሬቱ ጋር ያዛመደው ነገር ያለ ይመስል
አልተንቀሳቀስኩም።ሰውየው እንድገባ ጋበዘኝ፡፡ ለአፉ እንዳለው ያስታውቅበታል፡፡ተሰናብቻቸው እግሬን ከተተከለበት አንቀሳቅሼ በመጣሁበት አቅጣጫ መራሁት። አለመታደል ነው #ቀላውጦ_ማስመለስ ትል ነበር እናቴ፡፡ የምፈልገው ስለርሷ አለማስብ ነው። የማደርገው ግን ተቃራኒውን ነው
የጠራችው ሰውየው የስራ ባልደረባዋ መሆኔን እንዲያምናት ብቻ ነው? ድምፅዋ ውስጥ ለምን ፍርሃት ሰማሁ? ለምን ባለቤቴ ነው አላለችኝም የዛን
እለት አርሴማ
👍2
አባቷ እያለ በምን ስሌት እኔጋ ደወለች? የት ሄዶስ ነበር? ደጋግሜ እሷን ማሰቤን ለማቆም እታገላለሁ የሚገባኝ እሷን ማሰብ ስለማቆም እያሰብኩ እንኳን የማስበው እሷን መሆኑን ነው።

አንዳንዴ ራስህን ለማግኘት ራስህን ልትከፍል ትችላለህ።ለመጀመሪያ ጊዜ ስሜቴን በሱስ መበረዝ አላማረኝም። መታመም ፈለግኩ። ወደ ቤቴ ሄጄ ተጋደምኩኝ፡፡ ሁሉም ነገር ፀጥ አለብኝ።
በምድሪቷ ያሉ ፍጡሮች ሁሉ በሆነ መዓት አልቀው እኔና ቤቴ ብቻ አንድ የምድር ጠርዝ ላይ ተርፈን ከሆነ እንቅልፍ የነቃሁ
መሰለኝ፡፡ አመሻሹ ሲገፋ የመጠጣት ፍላጎቴ ታገለኝ፡፡ስልኬ ሲጠራ አላመንኩትም።ስምሪት ናት።

“እንደ ባለጌ ሴት ነው አይደል የምታስበኝ?" አለችኝ ስልኩን
አንስቼ ሄሎ ከማለቴ።በምን ምክንያት?” መለስኩላት።

ምን እንደምታስብ ይገባኛል።" አለችኝ በቀሰስተኛ ድምፅ።

“በፍፁም!! መገመት እንኳን አትችዪም። ስምሪት አጠገብሽ ሆኜ እንባሽን ከጉንጭሽ ላይ መጥረግ ነው ፍላጎቴ” ጥቂት ዝም አለች።

ማልቀሴን በምን አወቅክ?"

“ባለቤትሽስ? ወጥቶ ነው?"

አብሮኝ አይኖርም። አንዳንዴ ነው የሚመጣው፡፡” መለሰችልኝ፡፡መስማት የፈለግኩት ግን ባለቤቴ አይደለም' የሚለውን ነበር፡፡

"ልምጣ? እንዳይሽ ብቻ ነው::"

መምሸቱን እና ልጇ መተኛቷን ምክንያት ደርድራ እንዳልሄድ ከለከለችኝ፡፡ እውነቷን ነው መሽቷል፡፡ ወደርሷ መሄድ ግን
እየተጓዙ ማደር ቢሆን እንኳን ደስ እያለኝ አደርገው ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ የሰቀልከው ተስፋጋ ለመድረስ መንጠራራት ተስፋውን
ከመጨበጥ በላይ ደስታ አለው:: ጉልበት እና የተስፋ ስንቅ ያጅቡታል። ስልኩን ዘግቼው ተጋደምኩ። የማስበው ምን
ከፍቷት እንዳለቀሰች ነው።የሰው ሚስት የመሆኗን ሀቅ ሆነ ብዬ ከሀሳቤ ላለመደመር እታገላለሁ።ላያት የመፈለጌን
እብደትም ችላ ልለው እፍጨረጨራለሁ። ብዙም ሳትቆይ መልሳ ደወለች።ግራ ተጋባሁ፡፡

“ሳልነግርህ ረስቼው የእናትህን አድራሻ ፍንጭ የሚሰጥ መረጃ ተገኝቷል።” በእርግጠኝነት ይሄንን ልትነግረኝ እንዳልደወለች ገብቶኛል፡፡

"እሺ በይኝ ልምጣና ልይሽ? አስር ደቂቃ ብቻ? ስለመረጃውም ትነግሪኛለሽ፡፡" ስላት በጣም ታሽታ ስታበቃ መለሰችልኝ።

"እሺ ግን እኔ ልምጣ! ተመልሶ ሊመጣብኝ ይችላል፡፡" አለችኝ፡፡
ቁጭ ብዬ እሷ እስክትደርስ መጠበቅ የምችል አልመስልህ አለኝ፡፡

“መሽቷል። እራሴ መጥቼ ይዤሽ እመለሳለሁ።ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ።" አልኳት።

የለበስኩትን ቱታ አልቀየርኩትም።እንዴት እንደደረስኩ አላውቀውም።እሷን የማግኘት ጉጉቴ ሰቅዞኝ ለብቻዬ ፈገግ
እያልኩ ነበር፡፡ ታክሲው ውስጥ ምን ያህል እንደተቀመጥኩም አላውቅም በሯ ላይ ስደርስ ደወልኩ፡፡ከመደንገጤ የተነሳ መመለስ ሁሉ ዳድቶኝ ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍2
#ዘሪና_አጫጅ

ስለፋና ስጥር
እድሜዬን በሞላ
እጅ ከምን ብዬ
ያለኝን ሳሰላ
ከረባዳው ኪሴ
ያለኝን አጫጭዳ
ስትከምር አየኋት
ፍቅሬ ከኔ ወስዳ፡፡
#አዕምሮ_ሲበድን

ዲፕሎም ቢቆጠር ዲግሪውም ቢበዛ
ሱፉ ጌጡ በዝቶ ፊትም ቢወረዛ
ህይወት ብትሰምርና ንብረቱ ቢበዛ
ራሱን ካልለካ ካጣ ልጓሙን
የህይወት መስፈርቱን መመዘኛውን
ምንድን ነው የተማረው ?
ምንድን ነው ያወቀው ?
ዲፕሎም ዲግሪ እንደው በድን ህይወት የለው፡፡
#ይድረስ

እኔ የማውቀው፣ መለዮ ለባሽ
የገባሮች እንባ አባሽ
የግፍ ማዕበል ቀልባሽ
የደከመ ሚያበረታ፣ የዘመመ የሚደግፍ
የኑሮን ሸከም እንደ ሾላ፣ ከጫንቃ ላይ የሚያራግፍ።

አንተ ግን
የጀግኖችን ልብስ ለብሰህ
ከኑሯችን ጭነት ብሰህ
ላገርህ እንኳን ባትሞት፣ አገርህን ትገላለህ?
እንዴት እንደ ወረርሺኝ፣ በመደዳ ትጥላለህ
በላቡ ያወዛህ ገባር፣ የቀለበህ ጥሮ ግሮ
ተርቦ ያጎረሰህ፣ በለጋስ ምጣዱ ጋግሮ
አቤት ብሎ ቢጮህልህ፣ መሄጃ አጥቶ
ተቸግሮ
ልጁን ቤቱን ስታሸብር
ደረቱን በጥይት ስትገምስ፣ ጐኑን ቅልጥሙን ስትሰብር
ትንሽ እንኳን አታፍርም?
ህሊና ባይኖርህስ፣ ከሰው አትበደርም?

ያልገነባኸውን ስታፈርስ፣ ያልፈጠርከውን ስትገድል
ለራበው ለተቸገረ፣ ሞትን እንደ ቆሎ ስታድል
ስታወድም ስታከስም፣ ስትፈነከት ስታቆስል
ሁሌም ቃታ ስትስብ፣ ሁሌም ሳንጃህን ስትስል
የሰለባህን ቀሪ እድሜ፣ መውሰድ የምትችል ይመስል
የምትበላው ይስማማሃል፣ ከምትጠጣው ትስማማለህ?
ደም በላሱ ከንፈሮችህ፣ ልጆችህን ትስማለህ??

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ስምንት


#በሜሪ_ፈለቀ

ፊቷ አብጧል። የጣት አሻራ ፊቷን ወርሶታል። የላይኛው ከንፈሯ
በአንድ በኩል አብጧል። ከሰዓታት በፊት ያየኋት ውብ ሴት መሆኗን ያስጠረጥራል።

"እሱ ነው?" አልኳት አገኘው ይመስል እጄን ለጡጫ ጨብጬ።በጭንቅላቷ ንቅናቄ አዎን አለችኝ፡፡ ምን ማለት ወይ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግራ ገባኝ፡፡ አቀፍኳት፡፡ ጣቶቿ ላይ ያለውን ብልዝ አይቼ ከጥፊ የዘለለ እንደደበደባት ገባኝ፡፡ እንዳለችኝ አርሴማ አልተኛችም። ጭራሽም እቤት የለችም፡፡ ይዟት
እንደሄደ ነገረችኝ፡፡ የደበደባት እኔ በመምጣቴ ምክንያት መሆኑን
ስትነግረኝ በቁሜ እግሬ ብርክ ያዘው። ምንም ቃል ሳልተነፍስ በሯን ዘግተን ወዳቆምኩት ታክሲ ይዣት ሄድኩ። ምንም ሳንነጋገር አንገቴ ስር እንደተሸጎጠች እቤት ደረስን።ስለሰውየው ልታስረዳኝ መናገር ጀመረች:: በሁኔታዋ ቁስሏን ማባስ መሰለኝ፡፡

"አሁን ምንም መስማት አልፈልግም። ምንም ለኔ ማስረዳት አይጠበቅብሽም። እረዳሻለሁ::" ብያት ትከሻዋን ነካ ሳደርጋት አመማት።

"እዚህጋም መቶሻል?" አልኳት ከልቤ እየተናደድኩ፡፡

"ሰውነቴ እንዳለ ቁስል ነው:: የተረፈ ቦታ የለኝም::" እየተናገረች እኩል አብጦ ሊጨፈን ከደረሰ ዓይኗ እንባዋ ይወርዳል፡፡

"የተለመደ ነው::" አለች ቀጥላ፡፡

አንዳንዴ ፊቷ ላይ ብልዝ አይቼ እንደማውቅ አስታወስኩ፡፡ሁሌም ሰበቧ ወድቃ እንደነበር ነው። ከመተኛቷ በፊት ሰውነቷን ዘና እንዲያደርግላት የሞቀ ውሃ በርዤ አሰናዳሁላት።

“ውሃ አሙቄልሻለሁ።ገላሽን ልጠብሽና የሚበላ ነገር ትቀምሻለሽ።"

"ምንም አልበላም።" መለሰችልኝ። ገላዋን የማጠቤን ሀሳብ እንዳልሰማ ማለፏ ተቃውሞ እንደሌለበት ወስጄው በቀስታ
የለበሰችውን ሹራብ አወለቅኩት፡፡ የጡት ማስያዣ አላሰረችም።ሰውነቷ በላልዟል። የቀበቶ ግርፋት መሆኑን ብጠረጥርም
እንባዋን እንዳላገረሽባት በመስጋቴ ልጠይቃት አልፈለግኩም።

“አሁን እኔጋ ነሽ!! ነፃ ሁኚ!" አልኳት ስትሳቀቅ ስላስተዋልኩ.ልብሷን በሙሉ ስገፈው ሰውነቷ በሙሉ በሰንበር
ተዥጎርጉሯል፡፡ ተጠንቅቄ ገላዋን አጠብኳት፡፡ ለማንም አዝኜ በማላውቀው ልክ አዘንኩላት። እንደምትሰበር ጌጥ አሳሳችኝ።እርቃኗን የአልጋውን ልብስ ገልጬ እንዳስተኛኋት ክንዴ ላይ
እንቅልፍ ወሰዳት:: ባይነጋ፣ ከእንቅልፏ ባትነቃ፣ እንደ ህፃን ክንዴ ላይ እንደተኛች ብናረጅ ፣ የሚያሳሳ ገላዋን እንዳቀፍኩ
የዓለም ፍፃሜ ቢሆን......

በጀርባዬ ተኝቼ አላውቅም።በደረቴ ካልተኛሁ እንቅልፍ አይወስደኝም። ዛሬ እንቅልፍ ስለመተኛት አይደለም ግዴ ዓይኔን ብከድን ስነቃ አጠገቤ የማጣት ነው የመሰለኝ፡፡ፒጃማ ለብሼ ተኝቼ አላውቅም። ይጨንቀኛል። ዛሬ እሷ ምቾት እንድታጣ አልፈለግኩም። እቤቴ ማንም ሴት መጥታ አታውቅም፡፡ ዛሬ
ስምሪትን አቅፊያት ለወትሮዬ ሰያፍ የምሰመርበት አልጋዬ ላይ አብሪያት ተኝቻለሁ። ይሄንን ሁሉ ብታውቅ? እየጠበቅኳት እንደሆነ ነቅታ ብታይ? አሰብኩት። ወዲያው እንዲህ አሰብኩ የሚሰማኝን ስሜት ነው የማደርገው ወይስ እሷን ለማማለል? ሳስበው አብዛኛዎቻችን እኮ ግብዝ ነን፡፡ ለሚሰማን እውነተኛ ስሜት ሳይሆን ሰዎች ለሚሰጡን የውደሳ ምላሽ ቃርሚያ
እናጎበድዳለን፡፡ ጥሩ ስናደርግ እንኳን ግብዝ ነን። ደግ ለመሆን ከምናደርግ ይልቅ በሌሎች ዘንድ ደግ ለመባል ነው ደግነት የምናሳየው ለቅድስና ደግ ከመሆን ይልቅ ለእውቅና ደግ
እንሆናለን። ሀምሳ ብር ስንቸር ቢያንስ ያደረግንላት ሰው እውቅና እንዲቸረን እንፈልጋለን፡፡ አምስት መቶ ሺህ ብር
ስንሰጥ በሬዲዮ እና በቴሌቭዥን እንዲነገርልን እናደርጋለን፡፡አነሰም በዛም ደግነታችን ዓይንና ልብ እንዲስብ እንፈልጋለን፡፡ያደረግኩት ይሄንን መሰለኝ፡፡ ቢያንስ የሚሰማኝን ስሜት እንድታውቅልኝ መመኘት። ተወራጨች። እየቃዠች እንደሆነ ገብቶኛል፡፡ አጥብቄ አቀፍኳት።

"እሽሽ... ... " አልኳት እንደ ህፃን ልጅ። እያማተበች ተነሳች።

"እኔጋ ነሽ!! አለሁ!" አልኳት አልመለሰችልኝም።ሙቀት
እንደሚፈልግ ህፃን ተጣበቀችብኝ፡፡ በእግሮቿ ጭኖቼን ፈልፍላ እግሮቿን እግሮቼ መሃል አስገባቻቸው፣ ጭንቅላቷን አንገቴ ስር ሸጉጣ ከአልጋው ይልቅ ከግማሽ በላይ ሰውነቷ እኔ ላይ
ተኛች። በሁለቱም እጆቼና በሁለቱም እግሮቼ ወደ ራሴ አስጠግቼ አቀፍኳት፡፡ ደስ አለኝ። ለወትሮው እንዲህ መንሰፍሰፍ
የወንድ ልጅ ስሜት አይመስለኝም ነበር፡፡ ለዛሬ እንዳመነችኝ አይደለም የተሰማኝ፡፡ ለሁሌውም ጠብቀኝ ያለችኝ ነው የመሰለኝ እንዴትና ከምን እንደምጠብቃት አላውቅም፡፡በፍፁም እንድትጎዳ እንደማላደርጋት ግን ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡ ብዙም ሳትቆይ እንደገና እንቅልፍ ወሰዳት።ከሚደበድባት ሰውጋ
ለምንድነው የምትሆነው? በምንም መልኩ ለማስቆም አቅሙ አላት፡፡ ለምን?

"አንዳንድ ሰዎች አብሮነታቸው ከሚጠቅምህ ይልቅ ይጎዳሃል።
እየጎዱህም ግን ልታጣቸው አትፈልግም።" ትል ነበር እናቴ ብዙ
ጊዜ። እሷ ማውራት የፈለገችው ስለ ባሏ መሆኑን አውቃለሁ።ስምሪት ስለእናቴ ያለችውን አሰብኩ። የት ልትሆን ትችላለች? ምናልባት ገዳም ገብታ? ምናልባት ሌላ ባል አግብታ ሌሎች
ልጆች ወልዳ? ማን ያውቃል ምናልባትም አሁንም ሀብታሞች የሚዝናኑበት ሆቴል እየሸረሞጠች? የነበራትን ገንዘብ ሰጥታኝ፣ቤቷን ጥላልኝ የት ልትሄድ ትችላለች? ምናልባት ራሷን አጥፍታ ቢሆንስ? አንዴ ስለእናቴ መልሼ ደግሞ ስለ ስምሪት ስፈትል ስቋጭ ሽልብ እንዳደረገኝ ነጋ፡፡ ያንን ሁሉ ሰዓት
አለማጨስ የኑሮ ያህል ትግል ነበረው። መንቃቷን አውቃለሁ።መንቃቴን አውቃለች፡፡ ጀርባዬጋ ዞሮ ባቀፈኝ እጇ ጣቶች በቀስታ ትነካኛለች።

"በልጅነቴ ነው ያገባሁት::"አለችኝ ሳትንቀሳቀስ። ወዲያው ግን
ከአንገቴ ዝቅ ብሎ እንባዋ ረጠበኝ፡፡

"የማታለቅሺ ከሆነ ብቻ ነው መስማት የምፈልገው:: ካለዚያ አልፈልግም። እንባሽን ማየት አልችልም::" አልኳት ቀና ብዬ እያየኋት፡፡ የፊቷ እብጠት ጠፍቶ ብልዘቱ ብቻ ቀርቷል፡፡በጭንቅላቷ እንደማታለቅስ ነግራኝ ተመልሳ ደረቴ ላይ
ተጋደመች እና ማውራት ጀመረች። ማውራት ከመጀመሯ በፊት የሆነ አስማት ነገር ሰርታለች:: ደረቴን ሳመችኝ። ስታወራልኝ ቅደም ተከተሉን አልጠበቀችም። አልረበሽኳትም። ብስጭት፣ፀፀት፣ አልፎ አልፎ እንባ እየተፈራረቁባት በስሜት ነው
የምታወራኝ። ፀጉሯን በጣቶቼ እያበጠርኩ ስሰማት የገባኝ ይሄ
ነው።

ያገባችው ሰው ቤተሰብና የሷ ቤተሰቦች በገንዘብ የተጣሉ ፀበኞች
ናቸው:: እርሷ የቤተሰቦቿ ብቸኛ ልጅና ተስፋቸው ነበረች።ቤተሰቦቿ ከጠላታቸው ልጅ ጋር ፍቅር መጀመሯን ሲያውቁ
ከፍቅሯና ከቤተሰቧ እንድትመርጥ ምርጫ ሰጧት። ቆይቶ ስታውቀው የእርሱ ቤተሰቦች ፀበኛቸው
ከማጣታቸው ይልቅ ልጃቸውን ማጣታቸው እንደሚጎዳቸው ያውቁ ስለነበር ልጃቸውን ይደግፉት ነበር። ፍቅሯን መርጣ ከቤቷ ስትወጣ ደግሰው ተቀበሏት። አባቷ ምን ያህል ቆራጥ
መሆናቸውን ብታውቅም እስከመጨረሻው ይከፉብኛል ብላ
አላሰበችም ነበርና በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ
የሚገባው የመሰላት መስዋዕትነት ነበር።

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍4
#ካሳ

በለስ ብትነፍግማ
ቅጠሏን ብታርቅ
አዳም ምርጫ አጥቶ
ሃፍረቱን ሊደብቅ
ከእግዜር በተጣላ
ከፊቱ እንዲርቅ፡፡
👍1
#ድምጽ_አልባ_ጩኸት

ባይሆንማ ኖሮ ድምጽ አልባ ጩኸት
ለአዕምሮ ቃል ማውጫ ቢኖር አንደበት
ከምድር የሚሰማው የሰዎች ብሶት
ጫጫታና ረብሻ እግዜር ሆኖበት
መልስ ባልሰጠ ነበር መስማት አቅቶት፡፡
#ፀደይን_በመስኮት

ክረምቱ ሲወጣ
ርጥብ ዳሱን ነቅሎ
አዳሜ
ከተሜ
ጃንጥላውን ሰቅሎ
ካቦርታውን ጥሎ።
አዳም ከሄዋኑ
(ድስት ከነክዳኑ)
ላጤውም ለብቻው
ወንዱ ደረት ሊያሳይ
በባሕር ዳርቻው
ሴቱም እንደልቡ፣ ቂጡን እየጣለ
በሙቅ አሸዋ ላይ
እየተንጋለለ
ቅብጠት ድርያ ሲያምረው
ማጭድ ታጥቆ ገባ
ሁሉን የማይምረው
ፊት ያለውን ሁሉ
በብረት መዳፉ፣ የሚያጠናግረው።
እምቢልታ ተነፋ
ደወል ተደወለ
ያልታደለው ጠፋ
ቀሪው እቤት ዋለ
ሰው ቤቱ መሸገ
መስኮት እንደጋሻ፣ እየወለወለ።
በየአደባባዩ
እዩኝ እዩኝ ባዩ
እንዳልተጀነነ
ሰው ለመኖር ብሎ፣ ከኑሮ መነነ!
እኔም እንዳገሬው፣ ለነፍሴ ብሳሳ
ለብሻት ሰነበትኩ፣ ቤቴን እንደገሳ።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ቀላውጦ_ማስመለስ


#ክፍል_ዘጠኝ


#በሜሪ_ፈለቀ

መሆናቸውን ብታውቅም እስከመጨረሻው ይከፉብኛል ብላ
አላሰበችም ነበርና በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ የሚገባው የመሰላት መስዋዕትነት ነበር። ሁሉም ሰላም እና ውብ ነበር። እየቆየ የባሏ ባህሪ መቀየር ጀመረ:: እሷ መርማሪ ፖሊስ
መሆኗን ተከትሎ ቤቷ ብጥብጥ ወረሰው።ዘግይቶ ሲገባት በብዙ
ህገወጥ ንግዶች ላይ እጁ እንዳለበት ጠረጠረች፡፡ ቢሆንም በቂ መረጃ የላትም
ቢሆንም ታፈቅረዋለች፡፡ቢሆንም ካለ እርሱ አንካሳ ናትና በየእለቱ እንደምትበረታባቸው ወንጀለኞች መረጃ
ለማግኘት አልታተረችም።በዚህ ትርምስ ውስጥ አርሴማ መጣች፡፡በመጀመሪያ የአርሴማ መወለድ ነገሮችን ያበረደ
መሰለ። ውጪ ማደሩን ተወ። መደብደቡን አቆመ።ድጋሚ የምታልመው ጥሩ ትዳር ኖራት። አርሴማ እያደገች ጤነኛ
አለመሆኗን ሲያውቅ ከበፊቱ በባሰ ከፋ፡፡

"እሺ እኔ ምን ማድረግ ነበረብኝ? እኔ እግዚአብሄር ነኝ? ልጄ ጤነኛ ብትሆን እኔስ ደስተኛ አልነበርኩም? ምን ማድረግ እችል ነበር?" አለችኝ ቀና ብላ፡፡
አርሴማ ከፍ ስትል ጭራሽ ከቤቱም ወጣ፡፡ በሁለት ሳምንት አንዴ (ትናንት እንዳደረገው) አርብ ከሰዓት መጥቶ አርሴማን ቤተሰቦቹጋ ይዟት ይሄዳል። ለልጁ የሚያስፈልገውን እሱም ሆነ
ቤተሰቡ ከማድረግ ቦዝነው አያውቁም፡፡ እሷን ከወንድ ጋር ታየሽ፣ ለልጄ መልካም አርአያ እየሆንሽ አይደለም እያለ
መቆጣጠሩን አለፍ ሲልም ትላንት እንዳደረገው መደብደቡን ቀጠለ። ምንም ማድረግ እንዳትችል አርሴማ አበሰረቻት። አርሴማ አባቷን ስታይ ፈንጠዝያ የሚቀሙት አይደለም። እሱ ሄዶ
ከትምህርት ቤት ያመጣት ቀን ስትጫወት ታመሻለች።

ልጄ ጤነኛ ብትሆን እና እንደ ጤነኛ ልጅ በሌላ የምትደሰት ብትሆን እሺ!
እንዴት አንድ የሳቋን ምክንያት
አሁንም ድረስ፡፡ ከእርሱ ጋር የነበራትን ህይወት ከመመለስ ልንጠቃት? ታውቃለህ? ሲደበድበኝ እያየች
አትጠላውም፡፡ አትፈራውም፡፡ እስሩ ገብታ ነው የምትሄደው።አለች ጥልቅ መከፋት ባለው ድምፅ፡፡

ለዓመታት እንዲመለስላት የምትችለውን ስታደርግ ኖራለች።አሁንም ድረስ።ከእርሱ ጋር የነበራትን ህይወት ከመመለስ ውጪ ሌላ አማራጭ አታስብም።

"ዛሬ ወደ ቤት የምትመለሺበት ምክንያት የለሽም።አብረን እንዋል!! ማታ እራት ልጋብዝሽ!" አልኳት ካለችበት ድብርት
እንድትወጣ፡፡ አልመለሰችልኝም፡፡ ቀና ብላ እያየችኝ "የእናትህን ጉዳይ ዛሬ እንድናጣራ አስቤ ነበር፡፡" አለችኝ ድምፅዋ ውስጥ ደስ የማይል ጥርጣሬ አደመጥኩ። አመነታሁ። ለማወቅ ጉጉት
አድሮብኛል። ለዛሬ ግን ከዚህ በላይ አሳዛኝ ነገር ለመስማት ዝግጁ አልነበርኩም።

"ነገ እናድርገው።ነገ ጠዋት። አሁን ምንም መስማት አልፈልግም። አሁን ስትስቂ ማየት ብቻ ነው የምፈልገው::"
አልኳት:: በምንቸገረኝ ትከሻዋን ሰበቀች። የገጠማትን ረስታ ከኔጋር መሆኗን ብቻ እንድታጣጥም ስጣጣር ዋልኩኝ። ቁርስ
ሰርቼ አበላኋት:: ተመልሰን ተኛን። ማታ ስላልተኛሁ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡ ስነቃ አጠገቤ ሳጣት ጮኬ ተጣራሁ።ምሳ እየሰራች ነበር፡፡ ገብቷታል:ፈ። ሆዷን ይዛ ሳቀችብኝ፡፡ መቃም እንደምፈልግ
ስነግራት ቡና እንደምታፈላልኝ ነገረችኝ፡፡ በየመሃሉ ጭልጥ ትልብኛለች።ሊመሻሽ ገደማ ወጥተን ቀሚስ እና ጫማ
ገዛሁላት፡፡ ለእራት ልንወጣ ቀሚሷን ላብሳ ተኳኩላ ብቅ አለች።ዝም አልኳት።

"አላማረብኝም? እ?" አለችኝ፡፡

"ምንም ተጨማሪ ነገር ሳትጠቀሚ እኮ ውብ ነሽ!" መለስኩላት።

እሱ ግን ሳልኳኳል አስጠላዋለሁ።" አለችኝ ከንፈሯን ወደ አንድ ጎን አጣማ (ቁሌታም ሴት ይወዳል ብላኝ ነበር ጠዋት ስታወራኝ። የወሲብ ፊልሞች ላይ እንደሚታዩት ሴቶች እንድትለብስለት እና የእነርሱን እንቅስቃሴ እንድትኮርጅለት
( እንደሚያደርጋት አክላልኝ ነበር፡፡)

"አሁን ለእኔ ብለሽ ነው የተቀባሽው? ለእኔ ብለሽ ከሆነ አጥፊው
ምክንያቱም እንደዛ ቆንጅዬ ነሽ! ለራስሽ ብለሽ ካደረግሽው ተይው::" ስላት አመነታች፡፡ ከዛም አጠፋችው።

እራት እየበላን እሷ ወይን እኔ ቢራ እየጠጣን እንዲህ ከወጣች
ዓመታት መቆጠራቸውን ከእንባዋ እየታገለች ነገረችኝ። ሁለት ብርጭቆ እንደጠጣች ሞቅ አላት።

"ታውቃለህ ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም። ትክክል መሆኑንም እንጃ!" አለችኝ እቤት እንደገባን፡፡

"ምኑ?"

"የሚሰማኝ ስሜት"

"ምንድነው የሚሰማሽ?" ከአፏ የሚወጣው ዓረፍተ ነገር ምንም ቢሆን እኔ ጆሮጋ ሲደርስ “ላንተ ፍቅር የሚል ቢሆን እየተመኘሁ።

“በደለኝነት፣ ኀጢአተኝነት፣ ጥፋተኝነት፣ ከዳተኝነት፣ ክምር ወቀሳ!” ጭንቅላቷን ይዛ ጫማዋን እያንቋቋች ተረማመደች።
ልቤን ሲበርደው ታወቀኝ፡፡

“ለምን? በምን ምክንያት?” የራሴ የማይመስል ድምፅ ነው ያወጣሁት፡፡ እግሬም የዛለብኝ መሰለኝ እና ተቀመጥኩ።

"ታውቃለህ? ድሮ ድሮ የዛሬ ስምንት ዓመት በድብቅ ፍቅር እንደጀመርን አንድ ቀን ከሰፈር አርቆ ይዞኝ ሄደ፡፡ ሁለታችንም
ህይወት እንደምናያቸው የፍቅር ፊልሞች መጨረሻቸው ግጥምጥም ግጥምጥም ብሎ በደስታ ለዘለዓለም ኖሩ የሚሆን
የሚመስለን ወቅት ነበር፡፡ (የወቅቱን ስሜት በትዝታ ልጓም ጎትታ እንደመቦረቅ እያለች) የሆነ ህንድ ፊልም ላይ እንዳየው
የእኔንም የሱንም የግራ እጅ የቀለበት ጣታችንን ጫፍ በምላጭ ቆርጠን አደማነው።ያስቃል አይደል? የሆነ የጅል ቀልድ ነገር ይመስላል? ግን አያስቅም እሺ! የሁለታችንንም የደሙ ጣቶች
አጋጥመን ቃል ገባልኝ፡፡ ቃል ገባሁለት።እሱ የገባልኝን ቃል
የኖረው ሁለት ዓመታት ብቻ ነው:: እኔ እያንዳንዷ ቃሌን ለመጠበቅ ስምንት ዓመታቴ ተቀርጥፈው ተስሉ፡፡ ለሱ ብዬ
ሁሉንም ተውኩ፡፡ ለማንም ወንድ ልቤንም አካሌንም አስደፍሬ
አላውቅም። እስከ ህይወቴ ፍፃሜ በልቤ ከርሱ ሌላ ላይነግስ ምዬለታለኋ? ምን እንደሚሰማኝ ታውቃለህ? ደሙ በደሜ
ውስጥ ያለ (ትኩረቴን ላለማጣቷ እያረጋገጠች) እውነታው
ባይገጣጠምም እኔ ግን እዛው የዛሬ ስምንት ዓመት ላይ ነኝ።"ማውራቷን አቋርጣ ማልቀስ ጀመረች።ሞቅታውም እያገዛት መሆኑ ገብቶኛል።

"ታውቃለህ አይገባህም! እኔን ስትሆን ብቻ ነው የሚገባህ!" አለችኝ፡፡ ፀጥ ብዬ እየሰማኋት ሀሳቤን ከማቡካት ውጪ ምርጫ አልሰጠችኝም።እውነቷን ነው:: አንዳንዴ ከምክንያታዊነት የሚልቅ ስሜት እንዳለ አሰብኩ። በቦታው ስትገኝ ብቻ የሚገባህ! ሲስማህ ብቻ የምታውቀው። እሷ ዓለሟ ትዳሯ ነው። ዓለም ቤቷ ነው። ዓለሟ ልጇ ናት:: ዓለምን እንደማሸነፍ የላቀ ምን ሀሴት አለ? ምንስ ስኬት ይኖራል? ትዳሯን እንደገና ማሸነፍ
እንደገና በሱ ልብ መንገስ፣ ለልጇ የምትወደውን አባቷን መመለስ፣ ዓለሟን የራሷ ማድረግ ነው ምኞትና ልፋቷ!

ሲመስለኝ ያልተረዳችው ነገር አብዛኛው ወንድ ወደድኩሽ ሲል ሊያስመስል ይችላል፡፡ ጠላሁሽ ካለ በቃ ማለቱ እንደሆነ አልገባትም። አርሴማን ሊወስድ ሲመጣ እግረ መንገዱን አብሯት መተኛቱ ከፍቅር ጋር ተዳቅሎባታል። የነሳትን ክብር ጋርዶባታል ፍቅሩን ያልጨረሰ እየመሰላት ልትጨምርለት ትዳክራለች።

“አንዳንዴ እንዲጠላኝ ያደረገው ፖሊስ መሆኔ ነው ብዬ አስብና ራሴን እወቅሳለሁ፡፡ ምናለ እሱ እንደሚፈልገው የቤት እመቤት ብሆን? እላለሁ! ልጄ በየቀኑ የምታየው አባት ይኖራት ነበር::"
ለንፅፅር የምታቀርበው ነገር ሲኖርህ ነው የተሻለ እና የባስ ብለህ ደረጃ የምታወጣው። እሷ ከእርሱ ውጪ የምታውቀው የላትም፡፡በምን ንፅፅር የምትለውጠው ህይወት የተሻለ መሆኑን
ትመዝናለች?

"ታውቃለህ አንዳንዴ እርግፍ አድርጌ ትቼው ቤተሰቦቼን ሄጄ ይቅርታ ልለምናቸው አስቤ አውቃለሁ፡፡ ያሳፍራል አይደል? እሉ ይበልጥብኛል ባልከው ሰው ተክደህ
👍2🥰1😁1
በሚያነክስ ልብ
መመለስ? ለነገሩ አሁን እረፍዷል፡፡ ስምንት ዓመት ዘግይቻለሁ።ግን ምን የሚሉኝ ይመስልሃል? ዘመድ አዝማድ እየተጠቋቆመ ቅስሜን የሚያደቀው አይመስልህም?" እሷ ታወራለች እኔ
የምሰማውን ላጣጥም በሀሳብ እዛቁላለሁ፡፡

ሰው እንኳን ወድቀህ ተመቻችተህለት ክርስቶስ ሰው ሆኖ ቢመጣ በመኮነን የተቀባበለው ፍጡር ነው:: ምንም የሰራኸው ኀጢኣት ባይኖር በእናትህ በደል አንተን ይፈጅሃል፡፡ ለድርጊት
ፈሪ የሆኑ ሰዎች ማድረግ የሚችሉት የሰውን ውድቀትና ጥፋት መንቀስ ብቻ ነዋ፡፡ ስምሪት ሰው የራሱ ጉዳይ የማለት አቅም ያላት ሴት እንዳይደለች አውቃለሁ፡፡ ቤተሰቦቿን በተመለከተ
አንድ ነገር ማድረግ እንዳለብኝ ይሰማኛል፡፡ ጊዜው በትክክል
መቼ መሆኑን ባላውቅም።በሞቅታ ስለምታወራ ከመስማት ውጪ አፌን አላላቀኩም...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
አትሮኖስ pinned «#ቀላውጦ_ማስመለስ ፡ ፡ #ክፍል_ዘጠኝ ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ መሆናቸውን ብታውቅም እስከመጨረሻው ይከፉብኛል ብላ አላሰበችም ነበርና በጊዜው ላፈቀረችው ሰው ቤተሰቧን ማጣቷ የሚገባው የመሰላት መስዋዕትነት ነበር። ሁሉም ሰላም እና ውብ ነበር። እየቆየ የባሏ ባህሪ መቀየር ጀመረ:: እሷ መርማሪ ፖሊስ መሆኗን ተከትሎ ቤቷ ብጥብጥ ወረሰው።ዘግይቶ ሲገባት በብዙ ህገወጥ ንግዶች ላይ እጁ እንዳለበት ጠረጠረች፡፡…»
#የተገላቢጦሽ

እኔ ጎመን ቀቃይ
እቴ ቅቤ አንጣሪ
ምች ምን አግብቶት....
የሆነ አቃጣሪ፣
ወደ'ሷ አደላና....
አጠናግሮ ጣለኝ፣
ላም ባልዋለበት....
ኩበት ሊያስለቅመኝ!!

🔘ሀብታሙ ወዳጅ🔘
😁2
#ድብቁ_እውነታ

ወዳንተ ልንመጣ
ለማግኘት ጽድቅህን
በዱር በገደሉ
ስንዞር ስንመንን
ታርዘን ተጠምተን
ድካም ተሰምቶን .
ከምድር የለም ብለን
መክረን ተስማምተን .
ወዳንተ ልንከንፍ
ርቀትህን ስንለካ
ጎጆህን ቀልሰህ
ድምጽህን አጥፍተህ ውስጣችን ነህ ለካ፡፡

🔘በፋሲል ኀይሉ🔘
አትሮኖስ pinned «#ብቸኝነቴን_መልሺልኝ የተሰኘው ምርጥ የፍቅር ታሪክ #በፍቅር_ቤት እየተለቀቀ #የመጨረሻውን_ክፍል ይዞላችሁ ቀርቧል ያልጀመራችሁት እታች ባለው ማስፈንጠርያ ገብታችሁ አንብቡ የጀመራችሁትም መጨረሻውን ክፍል እንሆ። 👇»
#በእቅፍሽ_ውስጥ_ያለው_ሰላም

በደጃፌ
ያዱኛ ጅረት ይፈስሳል
ሲዘረጋ መዳፌ
አልማዝ አፍሶ ይመለሳል።

ድህነትን አልቀድስም፣ ሀብታም መሆን አልጠላም
ግና ገንዘብ ኪስን እንጂ፣ የልብን ክፍተት አይሞላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።

በጉልምስና ዘመኔ፣ ወደ ልጅነት ተዛውሬ
የወይን ፅዋየን ወርውሬ
እልፍ ጡቶችን ብጠባ
ካንዲት ሽንቁር ተመዝዤ፣ ሌላይቱ ውስጥ ብገባ
ብለዋውጥ ማህደር
ብቀያይር ሰገባ
ምን አገኘሁ? ምን አተረፍሁ? ምን ፈየድኩኝ? ምኔ ረባ?

ሥጋ በሥጋ ቢሞረድ፣ የደነዘ ነፍስ አይሰላም
ከሁሉም ግን የሚልቀው፣ እቅፍሽ ውስጥ ያለው ሰላም።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
👍2