አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#መወድስ

ፊትሽ እንደ ምሥራቅ፣ ብርሃን ያመርታል
ፈገግታሽ ዋስ ሆኖ፣ እስረኛ ያስፈታል
ውይ መዓዛሽ ሲያምር!
የሎሚ የንጆሪ፣ የኮክ ሽታ ድምር።

ከየዛፉ ቅጠል
ንፋስ በክንዶቹ፣ ከሚሰበስበው
ከሳሩ ከሰርዶው፣ መሬት ከሚሳበው
በደብር አፀድ ላይ፣ ከሰፈነው ለምለም
ከየኔክታሩ ጣም፣ ከያበባው ቀለም
አውጣጥቶ ማን ሰጠሽ?
እንዲህ ምን አስጌጠሽ
እንዲህ ምን አሰላሽ?
መች ተጣድሽ? መች ፈላሽ?
ለዛሽ በፊትሽ ላይ መች ተጠነሰሰ
ውበትሽ ምንገድ ላይ፣ ገንፍሎ ፈሰሰ

ገላየ ጭንቅ አይችል፣ ዐይንሽ ስውር መቀስ
ኧረ ቀስ! ኧረ ቀስ!
ከደም ከሥጋ እንጂ፣ አልተሰራም ካለት
በውበትሽ አምላክ፣ ለልቤ እዘኝለት!
#ምንሽን

የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፣ በወጣሁበት እንዳልቀር
አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፣ ግና ምንድር ነው ማፍቀር?
እንዳስመሳይ አዝማሪ፣ ካልሸነገልኩሽ በቀር
ከተወለድሁ እስተዛሬ፣ ከጣትሽ መች ጎርሼ
ወተትሽን መች ቀምሼ
ወለላሽን መች ልሼ?

ሲርበኝ
ጠኔ በቀኝ በግራ፣ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ
የት ነበር የንጀራሽ ሌማት?
ሾላ ስለቅም ተሻምቼ፣ ከሽመላ ከማማት
ኑሮየ ሁዳዴ ጦም፣ ፋሲካ አልባ ሕማማት
እና ከድሎት አገር፣ የሲሳይ ዶፍ ከሚያወርደው
ምን ገፍቶኝ ነው በሞቴ? ወዳንቺ ምሰደደው
ምን ነክቶኝ ነው? ምንሽን ነው የምወደው?

እኔና ብጤዎቼ፣ እኛ ቅብዝብዝ ልጆችሽ
መስኮት በሩ ተዘግቶብን፣ ተበትነን በደጆችሽ
ይሄው ሶስት ሺ ዘመን፣ ወደ ሰማይ አንጋጠን
በንዝርት እግር ተንበርክከን፣ በቀይ ዕንባ ስንማጠን
የለት እንጀራችንን ነፍጎ፣ የለት ገጀራችንን ሰጠን።

አሁንም ለመከራሽ፣ ማን አለና የሚገደው
እሪታሽ እንደዘፈን፣ ያለም ጆሮ ለመደው
እና ምንሽ ነው ሚስበኝ? ምንሽን ነው የምወደው?

ዛሬም ሆነ ያለፈው
በላባ ብእርም ይሁን፣ በኪቦርድሽ የተጻፈው
ታሪክሽን ሳነበው፣ ደምና አመድ ነው የሞላው
መች ተነቅሎ ከወለልሽ፣ የሾህ ጉንጉን አሜኬላው
መች ተጥሶ ያውቃልና፣ የጭቆናሽ ዘመን ኬላው
ሥልጣን ፈልሶ ሲሸጋገር፣ ካንዱ ጭራቅ ወደሌላው።😔🇪🇹
#ዘመም_ይላል_እንጂ

እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት

እንደሰዉ ጭካኔ፣ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ፣ ታምር ነው መኖሬ።

የበጎ ሰው ሀሳብ፣ ሲካድ ዕለት በለት
ጉድጓድ ተምሶለት
ስብእና ሲቀበር፣
በዚህ ምድር መኖር፣ አያስመኝም ነበር።
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፣ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፣ እንዳንቀልባ ቀልቶ

ታረደ
ነደደ

ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፣ አያስመኝም ነበር።

አዎ

ለጊዜውም ቢሆን፣ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፣ ወደ ፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ፣ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፣ ሚስቱን
ያስረግዛል።

ይቅርታና ምሕረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፣ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ፣ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ፣ ተገርስሶ አይወድቅም።

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አስር


#በሜሪ_ፈለቀ

...የእውነታው ኑሯችን ለፍፁምነት የተጠጋጋ እንኳን አይደለም፡፡በመፅሐፌ ውስጥ ፍፅምናን ለምን ይጠብቃሉ? መፅሐፌ የሀሳቤና የኑራችን ግልባጭ እንጂ እነርሱ የሚመኙት የ'ቢሆን ዓለም ሊሆን እንዴት ይችል ነበር?

በአንዱ ቀን እንደተለመደው ኢሜሌን ስከፍት ረዥም ሀተታ ያለው መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ማርቲ ነበረች፡፡ ስለመፅሃፉ ይዘት
ተያያዥ ሀሳቦች ከተነተነች በኋላ ስለተሰማት ስሜት የፃፈችው ጭብጥ መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነበር።

ታሪኬን ነግሬህ የፃፍከው እስኪመስለኝ ያለፍኩትን መንገድ እና የተሰማኝን ስሜት ነው የፃፍከው:: ወንድ ሆነህ እንዲህ የሴትን ጥልቅ ስሜት መፃፍህ እስገርሞኛል፡፡ መፅሐፍህን እያነበብኩኝ
የምታውቀኝ የምታውቀኝ አይነት ነበር የሚሰማኝ። በቅርቡ ከሀገር ቤት የመጣች ጓደኛዬ ገዝታልኝ ከመጣቻቸው አዳዲስ መፅሐፍት ውስጥ አንዱ ምርጫ አልባ ምርጫ ነበር፡፡ ይሄን መልዕክት ስፅፍልህ መፅሐፍህን ለሶስተኛ ጊዜ አንብቤዋለሁ::"የሚል ነበር። ተመሳሳይ አስተያየት አንብቤ ባውቅም አንድም ይሄኛው ጥልቀት ያለው ትንተና የተካተተበት መሆኑ ሁለትም ማብራራት በማልችለው ምክንያት ከሌሎቹ ተመሳሳይ መልስ አልመለስኩም። ይሄ መልዕክት ከፊደላቱና ከሀሳቡ በተጨማሪ መንፈስ ነበረው:: አውስትራሊያ ሆና የፃፈችበትን ስሜት አዲስ መንፈስ አጋብቶብኛል።

"ውድ ማርታ ስለመፅሐፌ ለፃፍሻቸው ውብ ሙገሳዎች ከልቤ አመሰግናለሁ። በፃፍሽልኝ መልዕክት ስለመፅሐፍት ያለሽን ሰፊ ግንዛቤ ማወቅ በመቻሌ ምክንያት ያንቺን አድናቆት ማግኘት
ከፍ ያለ ደስታ አለው። ያንቺ የኑሮ መንገድ ከየትኛው የመፅሐፉ ታሪክ ጋር እንደተመሳሰለ ባላውቅም ከፃፍኩት ታሪክ ውስጥ በአንዱ ተመሳሳይ ጉዳት እንኳን ተጎድተሽ ከነበር ላለፍሽው
ሀዘን አዝናለሁ:: አንዳንዴ የተሰማሽን መተንፈስ ከፈለግሽ እና ይረዳኛል ብለሽ ካሰብሽ ፃፊልኝ፡፡ በድጋሚ አመሰግናለሁ::" ብዬ መለስኩላት:: የእኔና የማርቲ እውቂያ የጀመረው በእነዚህ
የመልዕክት ልውውጦች ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ከተፃፃፍን በኋላ የብዕር ጓደኛሞች ለመሆን ተስማምተን በየቀኑ መፃፃፍ ቀጠልን፡፡ በቀን ሁለቴ... ሶስቴ... አራቴ አምስቴ...መቁጠር አቆምን፡፡ ያወቅኳት መሰለኝ፡፡ ያወቀችኝ መሰላት።በየሰዓቱ ስለምታደርገው ጥቃቅን ነገር ሳይቀር ከፎቶዎቿ ጋር
እያያያዘች ትፅፍልኛለች:: ከሁለት
የዘለለ ልኬላት ባላውቅም ፤ አዋዋሌን በሙሉ ባልፅፍላትም ለፃፈችልኝ ቁጥር
ያህል ጊዜ መልስ እፅፍላታለሁ፡፡ በጠዋት ዓይኖቼን ስገልጥ ማየት የምመኘው የእርሷን መልዕክት ሆነ። በሆነ ምክንያት ሳትፅፍልኝ ካረፈደች ስጋቴ እያንዳንዷን ደቂቃ የመላ ምት ቁልል እየደረመሰ ሊያሳብደኝ ይደርሳል፡፡ ምክንያቱም ለማርቲ ምንም ጥቅምም ሆነ ዕውቀት የማይደምርላት ዝባዝንኬ ሳይቀር ስፅፍላት በዊልቸር እንደምሄድ እና መናገር እንደማልችል ፅፌላት አላውቅም:: አታውቅም! ማርቲ ስልክ ደውላ ድምፄን መስማት ሳትፈልግ ቀርታ ወይም ምስሌን እያየች ልታወራኝ
ሳትጨቀጭቀኝ እረስታ አልነበረም አጋጣሚው ያልተፈጠረው፡፡ለቀናት እስከመኮራረፍ ያደረሰን ምክንያት ሆኖ ያውቃል፡፡በደሌን የምትቆልልብኝ የምሰጣትን ቀሽም ምክንያት ሁሉ
ስታምነኝ ነው። በእርግጥ በሆነኛው ቀን በስካይፒ ካላየሁህ ብላ ከልቧ ስላመረረች የሚከሰተውን ለመቀበል
ራሴን አሳምኜ ኮምፒተሬ ፊት ተቀምጬላትም ነበር፡፡ በሚቆራረጠው ኔትወርክ ምክንያት ከሰከንዶች የዘለለ መተያየት አልቻልንምና በቅን ልቧ ኔትወርኩ ብልሹ ስለነበር ድምፄን መስማት አለመቻሏን እንጂ
ዲዳነቴን አልተጠራጠረችም።

ለእንደኔ ዓይነት ሰው ይሄን እድል ማን ይሰጠው ነበር? ማርቲስ ብትሆን እውነቱን ብታውቅ የሰጠችኝን ፍቅርና ያሳየችኝን ህልም መሰል ቀን ትሰጠኝ ነበር? ምንም መጨረሻው ከህልም
መንቃት ዓይነት ቢሆንም እነዚህን ቃላት ማጣጣም የተለየ ነገር ነበረው፡፡ እና ለምን ብዬ እውነቱን ነግሪያት የደስታ ቀኔን
ላሳጥር? እንኳን ለመፈቀር መብቃት እንደሙሉ ሰው መታየት የሚናፍቀኝ ሰው ነኝ፡፡ በየመንገዱ የሚያየኝ ሰው አንዳች አሳዛኝ ገር እንደተመለከተ ከንፈሩን ሲመጥልኝ ስበግን የኖርኳቸው ዓመታት ጥቂት አይደሉምና በፍቅር መቆለጳጰስ ይቅርብኝ ማለት አልችልም ነበር፡፡ አንዳንዶች አፍ አውጥተው ይሄን
የመሰለ ልጅ... “እግዜር ለራሱ የሰራውን ያሳምራል:: የመሳሰሉ አሳማሚ አባባሎች ሲሉ እየሰማሁ የገፋሁት ቀን ጥቂት
አይደለምና ከማርቲ ፍቅር እውነቱን ነግሪያት የሚመጣውን መቀበል መምረጥ አይቻለኝም።

ቤክዬ ልይህ ስልህ ስትከለክለኝ እኮ አስቀያሚ ነህ ብዬ ደምድሜ ነበር፡፡ የላክልኝን ፎቶዎች እንኳን መጠራጠር ጀምሬ መፅሐፍህ ጀርባ ላይ ካለው ጉርድ ፎቶህ ጋር ስንቴ እንዳመሳሰልኳቸው
ባየህ!" ብላ ፅፋልኝ ነበር በዚያው ዕለት:: የፃፍኩላትን በሙሉ ባላምንበትም ደግማ እንተያይ ወይም ልደውልልህ እያለች
እንዳትጨቃጨቀኝ ፍቅር ከሚታየው ሳይሆን ከልብ መዋሃድ ጋር ብቻ መሆኑን በውብ ቃላትና ገለፃ አንዳንዴም በሚያሳምን ምሳሌ እያጣቀስኩ እፅፍለታለሁ። በእርግጠኝነት ያላመነችኝ
እንኳን ቢሆን ለትክክለኛው ምክንያት የቀረበ ግምት

አይኖራትም ነበር፡፡ ጉረኛ፣ ኩራተኛ፣ ቀብራራ፣ በራሱ የሚተማመን፣ የተረጋጋ...... ልታየኝና ልትሰማኝ አለመፈለጌን የምታመኃኝባቸው ፀባዮቼ ናቸው።

የምትዋሸው ወይ የምትደብቀው ታሪክህ የምታፍርበት ነው::ትላለች የኔዋ ረቂቅ:: ምናልባት ደግሞ የምትወደውን ነገር
የሚያሳጣህ ሊሆንም ይችላል። በእርግጥ እኔ የደበቅኳት ታሪኬን
ሳይሆን ተፈጥሮዬን ነው። እኔ በረከት ነኝ፡፡ መራመድም መናገርም የማልችል በረከት ለመሆን ያበረከትኩት አንዳችም
ጠጠር የለም:: ከአባዬ እና ከእማዬ ለመወለድ የሩካ ወንድም ለመሆን የኔ ፈቃድና ምኞት አይደለም:: የሆንኩትን ሆኜ ለመፈጠሬ የእኔ አስተዋፅኦ
ባዶ ነበር። ግንሳ? ፈቅጄ ባልመረጥኩት አፈጣጠሬ ጉድለት ሳቢያ ቀኖቼ ጎዶሎ ሆነውብኝ ነው ለመደበቅ የተገደድኩት።

ከአሁን ወደ ኋላ ንጄ ካስነበብኳችሁ ጣፋጭ ገፅ ወደ ፊት የጊዜን ካብ ስደረድር የኑሮን ጥፍጥና ለማጎምዘዝ ጊዜው የንስር ክንፍ ተውሶ ይንደረደር ነበር፡፡ እነዚህ ገዖች ጉራማይሌ ስሜት
የታጨቀባቸው ነበሩ።

"አንተ? ማታ እስኪሪብቶህን አገንፍለህ ነው እንዴ ያደርከው?"

"አንቺ ባለጌ ታላቅሽ እኮ ነኝ፡፡ አፍሽን አትክፈቺ!" እላታለሁ በእጆቼ ምልክት የእውነት እያፈርኳት፡፡ ክትክት ብላ በማፈሬ ትስቅብኛለች፡፡ ያሳፈረኝ የእርሷ ንግግር ብቻ አይደለም። ያለችው
እውነት መሆኑም ተደምሮ እንጂ፡፡
ከእንቅልፌ ከባነንኩ በኋላ ለማስታወስ ስሞክር ያልተከሰተልኝ መልክ ያላት ሴት ፈዛዛ የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ስስ ቀሚስ ለብሳ የአልጋዬ ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ስታጫውተኝ ነው ያደረችው:: ቁልጭ ብሎ ቅርፀ ምስሏ ባይታወሰኝም ቆንጆ እንደሆነች ይታሰበኛል።....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍5
Forwarded from አትሮኖስ via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ያልጣዱት_አይበስልም

ፍቅር እንደ ዝናብ፣ ከሰማይ አይወርድም
ያበባ መደብ ነው
በሰው የሚታነፅ፣ በሰው የሚወድም
ተዘርቶብን እንጂ፣ ተሰብከን አንወድም።

“ወዳጄ ወዳጄ”፣ የሚያቀነቅኑ
አገር ያቀኑ ለት፣ መች ልብን አቀኑ

ሳይወጡ ሳይወርዱ
ውብ ሥራን ከውብ ቃል፣ ሳያስተባብሩ
ከድሜ እና ከምቾት፣ ቆርሰው ሳይገብሩ
ፍቅር መች ይፈልቃል?
በስብከት በምልጃ፣ በየዋህ ሰዎች ህልም
ያልጣዱት አይበስልም
ያልዘሩት አይበቅልም።
#ባሕር_ውስጥ_ገብቶ_ይተኛል

ምናልባት አማልክት ካሉ
ካላቸው ህልውና
ሰዎች ሆይ ሰብሰብ በሉ
እንሰዋላቸው ምስጋና!!

አጣድፈው ስለሚጠሩን

ለዘላለም እንድንኖር፣ አድርገውስላልፈጠሩን!
መጭውን ክፋት እንዳናይ፣ ባጭር ስለሚያስቀሩን

እድሉን እንኳን ቢያገኝ፣ ሁሌ መኖር ማን ይመኛል?
ዓባይ እንኳን ባዝኖ ባዝኖ፣ ባሕር ውስጥ ገብቶ ይተኛል።
#ጡቶችሽ_ያምራሉ


#በዘሪሁን ገመቹ

እስኪ ስለመጀመሪያ ፍቅሬ እና ጠቅላላ ታሪኩ ላውራችሁ..ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር የሚባለውን ጣፋጭ መርዝ የተጐነጨውት የአስራ ሶስት ዓመት ልጅ ሳለው ነው፤ያ ማለት ያፈቀርኳትም የ13 ዓመት ልጅ ነበረች እያልኳችሁ አይደለም….እሷ በወቅቱ ቢያንስ 20 ዓመት ይሆናታል፤ልክ ጎረቤታችን ሆና ተከራይታ እንደገባች ነው አይኔም ቀልቤም የተለጠፈባት …. በእኛ እና በእሷ ቤት መካከል አንድ ግቢ ብቻ ነው ያለው፡፡
እንዴት በዛ ዕድሜህ ልታፈቅራት ቻልክ? ብላችሁ እደምትጠይቁኝ እርግጠኛ ነኝ.. ሳላፍርም ሳልኮራም ነው የምመልስላችሁ…እንደነገርኮችሁ ልጅቷ ለሰፈሩ መጤ ነች ..አንድ የመንግስት መስሪያ ቤት በፀሀፊነት ተቀጥራ ነው ወደ እኛ ሰፈር ለመምጣት የተገደደችው፡፡ስሟ ሶስና ክፍሎም ይባላል…በቀይ እና በጠይም መካከል ያለ የሰውነት ቀለም አላት፤ከሶስና ነገሮች በጣም የሚማርከኝ ቄንጣዊ አረማመዷ ነው..መቼስ ሁለት ዓመት እና ከዛ በላይ ካልሰለጠነች እና ካልተለማመደች በስተቀር አንደ እዛ አይነት አረማመድ በተፈጥሮ ታድላ ነው ብሎ ለማመን እስከአሁን ድረስ ይከብደኛል…..፡፡

ብታዩ እርምጃዋ.. የመንቀጥቀጥ..የመንዘርዘር..የመውረግረግ …. የመሾር ድብልቅ ውጤት ያለበት ነው….አንዳንዴም እንዲሁ ለዓመል ያህል ብቻ ይመስለኛል መሬቱን ነካ አድርጋ ወደሚቀጥለው ደረጃ ምትራመደው…
ይገርማችኃል ከትምህት ቤት መጥቼ ደብተሬን ከማስቀመጤ ወይም እቤት ገብቼ መክሰሴን ከመብላቴ በፊት እሷን ለማየት ነው የምፈለገው… ለዛም ብዬ ወይ አጥራችንን ተደግፌ እሷ ለሆነ ጉዳይ እስክትወጣ ጠብቃታለው..ከስራ ካልመጣችም እስክትመጣ ልክ ገበያ የሄደች እናቱን ከረሜላ ገዝታልኝ ትመጣለች ብሎ በጉጉት እና በናፍቆት እንደሚጠብቅ ጨቅላ ልጅ ..
…ስትመጣ ማለፊያ መንገዷ ጋር ቆምና ሰላም እስክትለኝ ጠብቃለው..ካዛ በደስታ እየፈነጠዝኩ ወደ ቤት እገባለው ወይም ይባስ ብዬ እሷኑ ተከትዬ ወይም የሆነ ነገር አሳብቤ ወደ ግቢያቸው ሄዳለው.. ..አንድ ሁለት ቃል ካናገረቺኝ በቃ እየፈነጠዝኩ እየቧረቅኩ መልካም ውሎ መልካም ለሊት አሳልፋለው፡፡
በወቅቱ ባይገባኝም የሶስና አፍቃሪና አድናቂ እኔ ብቻ አልነበርኩም… ከአንድ ደርዘን የበለጡ ከቅርብም ከሩቅ ሰፈርም እየኳተኑ የሚመጡ ጓረምሶች ነበሩ..ታዲያ እዴት እንደሆነ ባላውቅም አንዳንዶቹ እኔን እንደአጋናኝ ድልድይ ይጠቀሙብኝ ጀመር ..ደብዳቤ ይሰጡኛል አደርስላቸዋለው….መልዕክት ይልኩኛል በፍንጠዛ ሄጄ እነግራታለው..እሷ መልስ ከነገረቺኝ በመጣውበት ፍንጠዛ ሄጃ መልሱን አደርሳለው…ይሄ ድልድይነቴ ከሶስና ጋር ያለንን ቀረቤታ በጣም አሻሽለልኝ..ሚስጥረኛዋ ሆንኩ..፡፡እንደውም በተለይ ትምህርት በማይኖርባቸው የቅዳሜ እና እሁድ ቀናቶች ብቻዋን ለመሄድ የማትፈልጋቸው ቦታዎች ሸጐጥ አድርጋኝ ትሄዳለች…አቅፋኝ ትዞራለች..ብስጭቷን ታጋራኛለች..ደስታዋን ትዘምርልኛለች….፡፡
አንድ ቀን ሶስና ያተለመደ ትዕዛዝ ሰጠቺኝ ‹ ከአንድዬ በስተቀር ሌላ ሰው እኔ ጋር መልዕክት ቢልክህ እንዳትሰማቸው .. ..›› ..አለቺኝ..አንድዬ ያለችው እንግዲህ ደርዘን ይሞላሉ ካልኳችሁ ተከታዬቾ መካከል አንድ ነበር….ላካ አጅሪት አስባ አስልታ ይበጀኛል ያለችውን ልቧን የሰለበውን ሰው መምረጧ እና ለእኔም መንገሯ ነበር...እኔ ጅሉ በወቅቱ ምን እየተካሄደ እንደሆነ ስላልገባኝ በደስታ ነበር እሺ ያልኳት፡፡
ቀረቤታችን ግለቱን እንደያዘ ዘለቀ …አብረን ሆነን ላገኘናቸው ሰው ሁሉ ወንድሜ ነው እያለች ታስተዋውቀኝ ነበር..ያ ነገሯ ሲከነክኝ ከረመ እና አንድ ቀን በዚሁ ጉዳይ ላይ ላናግራት እቤቷ ሄድኩ
‹‹ሀይ ዘርሽ…እንኳን መጣህ የሆነ ቦታ አብረን እንሄዳለን›› አለቺኝ በመምጣቴ እየፈነጠዘች፤የደረስኩት ልብሷን እየቀየረች በነበረችበት ቅጽበት ነበር… የለበሰችውን ሱሪ አወልቃ ቀሚስ ልትለብስ ነው እየጣረች የነበረው… ያለምንም መሳቀቅ እዛው ስሯ እንደቆምኩ ሱሪዋን አወለቀች….. ትዝ ይለኛል ሰማዩን የመሰለ ሰማያዊ ፓንት ነበር ያደረገችው..፡፡ አፌን ከፈትኩ ….ከላይ የለበሰችውን ቲሸርትም አወለቀች…..ጡት ማስያዢያ ያላፋናቸው አጐጊ ጡቶቾ አፈጠጡብኝ..ተርበደበድኩ
፤ብትሰጠኝ …ማለቴ ብታጐርሰኝ እና ብጠባቸው ተመኘው….፡፡ልክ ከአስራ አንድ ዓመት በፊት ካለውዲታዬ እንደተነጠቅኩት የእናቴ ጡት …እሷ ቁብም ሳትሰጠኝ ያዘጋጀችውን ቀሚስ አነሳችና ልትለብስ ስትል ‹‹ቆይ ቆይ…….. .!!!››አልኳት ሳላስብ
‹‹ምነው ምንአየህ?..›› ብላ መልበሷን አቁማ ሰውነቷን በጥርጣሬ ማየት ጀመረች
‹‹ ምንም አላየሁም..ጡቶችሽ ግን ያምራሉ..›› አልኳት
አቤት የሳቀችው ሳቅ ‹‹ ኪ..ኪ..ኪ…››ወደ እኔ ቀረበችና ጐትታ አቀፈችኝ…. ስታቅፈኝ ፊቴን ዕርቃን ሰውነቷ ላይ ቀበርኩት …በሁለት ጡቶቾ መካከል ፡፡ ለምን ያህል ደቂቃ እንደሆነ ባላውቅም … ብቻ ሳቋን እየሳቀች እዛው አቆየቺኝ ‹‹አይ ዘርሽ…እየደረሽ ነው ማለት ነው..ጡቶችሽ ያምራሉ ነው ያልከኝ..ግን እስኪ እውነቱን ንገረኝ..ጡቴ ብቻ ነው የሚያምረው..?
‹‹ኸረ አይደለም ..አይንሽ፤ ፀጉርሽ፤ አፍንጫሽ..መቀመጫሽ በወቅቱ(ቂጥሽ ነበር ያልኳት)..በተለይ አረማመድሽ..አነጋገርሽ…ሳቅሽ…በቃ በአጠቃላይ ምንም የማያምር ነገር የለሽም..››ይሄን ሁሉ ስናገር …ቀሚሷን እንኳን ሳትለብስ በቀኝ እጆ እዳንከረፈፈች እርቃኗን እንደቆመች እያዳመጠቺኝ ነበር ‹‹በምን አወቅክ..?››
‹‹ምኑን?››
‹‹እንዲህ ማማሬን ነዋ››
በጥያቄዋ በተራዬ ተገረምኩ‹‹እንዴ በየቀኑ ቤትሽ የምመጣው ያንቺን መልክ ለማየት ነው እኮ..!!!››
‹‹እንዴ … ለምንድነው እኔን የምታየኝ . ?..
‹‹ሳድግ ስለማገባሽ ነዋ››አቋርጣው የነበረውን ያ ተንከትካች ሳቋን መልሳ ለቀቀች… ኪ…ኪ..ኪ..ኪ ….‹‹ቆይ ቆይ እስቲ ቀሚሴን ልልበስ እና እናወራለን ውድ ባለቤቴ›› አለችና ቀሚሷን ለበሰች እና እጄን እየጐተተች ወደ መቀመጫው ይዛኝ ሄደች እና ከጐኗ አስቀመጠቺኝ
‹‹እስኪ ንገረኝ እኔን ማግባት ትፈልጋለህ..?››
መቼስ ልጅነት አንዳንዴ የዋህም ፤ ደፋርም ያደርጋል ‹‹አዎ በጣም ነው የምወድሽ ..አገባሻለውም..››አልኳት
‹‹አግብተኸኝስ?›.
‹‹በቃ እንደእማዬ እና አባያ እቤት ሰርተን አብረን እንኖራለን…ልጆች እንወልዳለን..››በደስታ እየተፍለቀለቅኩ መለስኩላት
‹‹እንዴት አድርገን ነው ልጆች የምንወልደው..?››ብላ ግራ አጋቢ ጥያቄ ጠየቀቺኝ
‹‹በቃ ታረግዢና ትወልጃለሻ››
‹‹እኮ እንዴት አድርጌ ነው የማረግዘው…?››ምን አይነት መልስ እንድመልስላት እንደፈለገች አላውቅም..እኔም በወቅቱ በባልና ሚስቶች መካከል የሚከወኑ ግንኙነቶችን ስለማላውቃቸው ያሰበችውን መልስ ልነግራት አልቻልኩም..
‹‹ በል ተነስ እንሂድ›› አለቺኝ….እንዴት የ13 ዓመት ልጅ ሆኖህ ይሄን ማወቅ ያቅትሀል? እንዳትሉኝ ይህ የምነግራችሁ ታሪክ የተከወነው በ2009 ዓ.ም ሳይሆን በ1987 ዓ.ም አካባቢ ነው…የዛን ጊዜ በእንደዚህ አይነት ጉዳይ ላይ የነበረ ንቃተ ህሊና ከግምት ማስገባት አለባችሁ…..ብቻ እሷም ከጐኔ ተነስታ በዝምታ እየተኳኳለች ሳለ ‹‹እና እንጋባለን አይደል..?››እርግጠኛ ለመሆን ደግሜ ጠየቅኳት
‹‹እንዴ በትክክል እንጋባለን..እቤት እንሰራለን …አስራ ሁለት ልጆችም ወልድልሀለው››አለቺኝ
‹‹አይ ሁለት ልጅ ብቻ ነው የምፈልገው›› ኮስተር ብዬ
‹‹አይ ሁለት እማ ትንሽ ነው …ባይሆን ስድስት ልጆች አንወልዳለን ….ሶስት ሴት ሶስት ወንድ..››በዛ ተስማማን..እኔ በወቅቱ አወራ የነበረው በፍፁም ነፍሴ ከአንጀቴ ነበር..እሷ ለካ
👍4
እየቀለደቺብኝ ነበር……ለማንኛውም ከዛ ቡኃላ ባሪያዋ ሆንኩ እላችኃለው…እቤቴ ምገባው በመከራ ተፈልጌ ነው..ደግነቱ በቤታችን ውስጥ ከሚርመሰመሱ ስምንት ልጆች መካከል እኔ ኖርኩ አልኖርኩ ብዙም ከቁጥር ስለማላጐል ቤተሰቦቼ አስታውሰው ከሚፈልጉኝ ቀናቶች ይልቅ ረስተውኝ የሚተውኝ ቀናቶች በብዙ እጥፍ ይበልጣል…ይሄ ደግሞ ለእኔ ተመችቶኝል..፡፡
የፈለገችው ቦታ ብትልከኝ በደስታ ነው የምበርላት..እቤት ውስጥ ምግቧን ከማብሰል ውጭ ሌላ ስራ ንክች አታደርግም..እቤት አፀዳላታለው…ልብስ አጥብላታለው(ብዙ ግዜ እየተቆጣቺኝ ተውኩት እንጂ ፓንቷንም ጭምር አጥብላት ነበር )የቤቷን ዕቃዎች ብረት ድስት፤ሳህኖች፤ብርጭቆ አንድም ዕቃ አይቀረኝም
ሌላው አሁንም ትዝ የሚለኝ እና ከሶስና ጋር ነበረኝን ግንኙነት በጥሩ ጐኑ የማስታውሰው ትምህርቴን በተመለከተ ያደረገችልኝ ነገር ነው…እሷ እኛ ሰፈር ስትገባ ከአራተኛ ክፍል ወደ አምስተኛ ክፍል እንዳለፍኩ ሰሞን ነበር ….ስንተኛ ወጥቼ አለፍኩ ከ57 ልጆች መካከል 31 ኛ..
ታዲያ አንድ ቀን ሶስና ‹‹ባሌ ወደፊት ዶክተር ወይም ፓይለት ነው ምትሆነው አይደል? ››ብላ ጠየቀቺኝ ‹‹በትክክል አንቺ ከፈለግሽ ሆናለው›› በማለት ቃል ገባውላት… ከዛ በማግስቱ ፓይለት ወይ ዶክተር ለመሆን ምንድነው የሚያስፈልገው? ብዬ ፊቱ የማይፈታውን አባቴን በድፍረት ጠየቅኩት‹‹ጅሎ ጐበዝ ተማሪ መሆን ይጠይቃል..ዝም ብሎ እንደአንተ ሰፈር ለሰፈር ሲያውደለድሉ መዋል ሳይሆን ከደብተር ጋር ጓደኛ መሆን ይጠይቃል›› ብሎ በዘወትራዊው የቁጣ ንግግር መለሰልኝ..ከዛም ደብተሬን እና መጽሀፍቶችን ጓደኛዬ አደረግኳቸው…መቼስ በህይወቴ አጣጥሜ ከተረዳዋቸው ነገሮች አንዱ አንድ ሴት በህይወት ውስጥ ድንገት ዘው ብላ ገብታ የሆነ ያህል ጊዜ ቆይታ ድንገት ተመልሳ ሾልካ ስትሄድ አንድ የሌለህን ነገር በውስጥህ ሰርታ እና ገንብታ..በፊት የነበረህን አንድ ሁለት ነገር ደግሞ አፍርሳ እና ደረማምሳ ነው ምትሰናበትህ ...ከሴቷ ጋር ያሳለፍካቸውን ነገሮች መለስ ብለህ ስትገመግማቸው ትርፍም ይኖርሀል ኪሳራም አታጣም..፡፡
እና በሶስና ምክንያት እሷን ወደፊት አገባለው በሚል የልጅነት ምኞት የጀመርኩት የማንበብ ጅማሬ እንሆ ወደ ዘወትራዊ ልምድ ተሸጋግሮ እስከአሁን እንደተጣባኝ አለ…. ግን ዶክተርም ፓይለትም አልሆንኩም ምክንያም መሆን በምችልበት ጊዜ እሷ አብራኝ ስላልነበረች አስፈላጊ መስሎ አልታየኝ…….ወይም እንደእዛ ለመሆን የሚያስችል ጥረት ለመጣር ወኔው አልነበረኝም ….
እንግዲህ እንዳዛ እንዳዛ እያልን ሰባተኛ ክፍል እስክደረርስ ከሶስና ጋር ተስፈኛ ሆኜ ኖርኩ…የሚገርመኝ በዛን ወቅት አንድ እኩያ ጓደኛ እንኳን የለኝም ነበር….ምን ጊዜ አለኝ እና ሙሉ ጊዜዬን ለትምህርቴ እና ለፍቅሬ አስረክቤያለው….
እንግዲህ እንደነገርኳችሁ ሰባተኛ ክፍል ሆኜ በአንድ የቀን እርጉም በእለተ ቅዳሜ ሶስና እሩቅ ቦታ ቢያንስ ሁለት ሰዓት የሚያቆይ ቦታ ላከቺኝ….እንደአጋጣሚ የላከቺኝ ቦታ ሳልደርስ ዕቃውን ከመንገድ ላይ አገኘውና አንድ ሰዓት ሳይሞላ ተመለስኩ…. ስደርስ ዛሬ ስራ ስለሌለ እቤት ማገኛት መስሎኝ ነበር…ግን በራፍ ዝግ ነው ..ከፋኝ፡፡ እንዲህ እየተንቀዠቀዥኩ የመጣውት ከእሷ ጋር የማሳልፈውን ጊዜ ረዘም ለማድረግ ነበር..ያው ቁልፍ ስላለኝ አወጣውና ከፍቼ ገባው ….የሆነ የመተረማመስ ድምጽ ከመኝታ ቤት ሰማው..የያዝኩትን ዕቃ እዛው ሳሎን ወርውሬ በፍጥነት ወደመኝታ ቤት አመራው….ከፈትኩት…
በወቅቱ ያየውትን ትዕይንት እስከዛሬ ድረስ ልክ እንደልዩ ፊልም ጥርት ብሎ በህልሜ ሳይቀር ደጋግሞ እያመጣ ያሳቅቀኛል..አንድዬ የምትለው ጓረምሳ የእኔን ሶስና ተሸክሞታል..አልጋው ላይ እንዳይመስላችሁ እልጋውማ እኔ ከመሄዴ በፊት እንዳነጠፍኩት እንደዛው ነው…መሀል ወለላ ላይ ነው ያሉት …እንደቆሙ …፡፡ ሙል በሙሉ ሁለቱም እርቃናቸውን ናቸው…እሷ እጆቾን በአንገቱ ዙሪያ ጠምጥማቸዋለች…እሱ ደግሞ በፈርጣማ እጆቹ የግራና ቀኝ እግሮቾን ከራሱ ሰውነት ጋር አጣብቆ ይዟቸዋል..፡፡እሷ እራሷዋን አታውቅም ..ዛር እንደወረደበት ሰው እላዩ ላይ ትጨፍርበታለች ..መኝታውን ስከፍት እንኳን ቀልቧን ሰብስባ ልትሰማኝ አልቻለችም ..እርግጥ የእሷ ጀርባዋ ነው ለእኔ የሚታየኝ ፡፡የእሱ ፊት ወደ እኔ ስለዞረ ወዲያው ነው ያየኝ..ፊቱን አጨማደደብኝ እና በፊቱ እቅስቃሴ ከአካባቢው ዞር እንድል ገሰፀኝ…፡፡ስለደነዘዝኩ የእሱን ፊት ለማንበብ የሚያስችል ማስተዋል አልነበረኝ ..ሶሲን እንደተሸከማት ጭፋራውንም ሳያቆርጡ ቀስ በቀስ እየተራመደ ወደ እኔ ይዞት ቀረበ…..ያ የምወደው ቂጧ በአየር ላይ ተንጠልጥሎ የእሷን እና የእሱን እንቅስቃሴ በመከተል ይንዘፈዘፋል … ፡፡ግማሽ ሜትር እስኪቀረው ቀረበኝ …እኔም ምን ሊያደርግ ነው? በማለት በማሰብ ላይ ሳለው አንድ እግሩን አነሳና የከፈትኩትን በራፍ በላዬ ላይ ደረገመብኝ….በዚህን ጊዜ እደመባነን አልኩ እና ተንቀሳቀስኩ….ከውስጥ ግን ‹‹ምድነው..ማነው በራፉን የከፈተው?›› የሚል የሶስናን ድምጽ ሰማው
‹‹ቆንጆ ምንም አይደል.. አደናቅፎኝ ነው..›› ሚለውን የእሱን የውሸት መልስ ሰማው.. ከዛ አልቆምኩም በዝግታ እቤቱን ለቅቄ ወጣው ..ከዛን ቀን ቡኃላ ሰፈር መዋል አቆምኩ…በምንም አይት አጋጣሚ የሶስናን አይን ላለማየት ጥረት አደርግ ጀመር…እሷ የተከሰተውን ነገር ስለተረዳች ልታስረዳኝም ልታባብለኝ ብትሞክር ልሰማትም.. ላናግራም አልፈለግኩም…፡፡ቡኃላ ሲደክማት መሰለኝ የራስህ ጉዳይ ብላ ተወቺኝ ፡፡ይሄ ድርጊት ከተከወነ ከሶስት ወር ቡኃላ አንድአለምን አግብታ ሰፈሩን ለቃ ሔደችልኝ… ተገላገልኩ….
እንግዲህ በዛ ባልጠና የልጅነት ጊዜዬ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ የመከዳት እጣ የደረሰኝ ፡፡እርግጥ አሁን ሳስበው መጀመሪያውኑ እሷ እኔን የምትቀርበኝ እንዲሁ ስለምትወደኝ ነው እንጂ አንድ ልብሱን አስተካክሎ መልበስ የማይችል ጩጬ ወደፊት አድጐ ያገባኝል ብላ አይደለም.. እርግጥ እኔም በወቅቱ እንደእዛ የመረዳት አቅሙ አልነበረኝም…በዛ ላይ እሷን ያጣውበት ጊዜ በጣም አንገብጋቢ እና መጥፎ ጊዜ ነበር፡፡ ነገሮች ማገናዘብ የጀመርኩበት..ስለሴት እና ወንድ ግንኙነት የሆኑ የሆኑ ነገሮች መረዳት በጀመርኩበት…ከሰው ተሸሽጌ የወሲብ ፊልሞችን ማየት በጀመርኩበት እና አንድ ቀን ለዛውም በቅርብ ከሶሲ ጋር አደርገዋለው ብዬ ምራቄን መዋጥ በጀመርኩበት….ያንንም በተደጋጋሚ በህልሜ ማየት በጀመርኩበት ያንንም ተከትሎ የዘር ፍሬዬን በህልሜ ማዝረክረክ በጀመርኩበት በዛ መጥፎ ጊዜ ላይ ነበር ሶሲ ህልሜ ሳትሆን ቅዠቴ እንደነበረች የተረዳውት፡፡ሶሲ አሁን ከሁለት ባሎች አራት ልጆች ወልዳ አዳማ ከተማ እንደምትኖር አውቃለው…..እኔስ….?እኔማ…

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍1
አትሮኖስ pinned «#ጡቶችሽ_ያምራሉ ፡ ፡ #በዘሪሁን ገመቹ እስኪ ስለመጀመሪያ ፍቅሬ እና ጠቅላላ ታሪኩ ላውራችሁ..ለመጀመሪያ ጊዜ ፍቅር የሚባለውን ጣፋጭ መርዝ የተጐነጨውት የአስራ ሶስት ዓመት ልጅ ሳለው ነው፤ያ ማለት ያፈቀርኳትም የ13 ዓመት ልጅ ነበረች እያልኳችሁ አይደለም….እሷ በወቅቱ ቢያንስ 20 ዓመት ይሆናታል፤ልክ ጎረቤታችን ሆና ተከራይታ እንደገባች ነው አይኔም ቀልቤም የተለጠፈባት …. በእኛ እና በእሷ ቤት…»
#አሏት_ዝሙተኛ

⚡️ተፃፈ በ ሰናይ



ከብዙ ሀሳብ፤ከብዙ ጭንቀት
ወዲያ ወዲህ ስል ፤ስንከራተት
ፍሬኑን ይዤ አቆምኩት
የሆነ ዳርቻ ፤የሆነ ሀሳብ ላይ
የወለደች እናት ፤ያጠባችን ሴት
የሴት አዳሪ ፤ሴተኛ አዳሪ
አሏት ዝሙተኛ
ከሁሉም ጋር የምተኛ
ሲመሽ የምትሳብ
ለክብሯ ማታስብ
ለምን በዚህ ዘመን
ሞያ ባልታጣበት
ጥበብ ባልጠፋበት
ለምን በዚህ ጊዜ
፨፨፨፨፨፨፨
አንዱ መካሪ ነኝ ባይ
አንዱ በሽሙጥ በሀሜት
ይመስላቸዋል ፤የምትኖር በቅንጦት
ሴተኛ አዳሪ፤ የሆነች በድሎት
እሷም አንድ ወቅት ፤እኮ ነበረች
ገላዋን የማታስነካና ፤የተዋበች
ልጅ ወልዳ ፤አባቱ ሲጠፋ
ይመጣል ብላ ስትጠብቅ፤ በተስፋ
ፋና ለማግኘት ስትታገል
ተስፋ ሲሆንባት ገደል
የምታጠባው የጡት ወተት፤ ሲደርቅባት
የልጇ ሆድ ሲጎድል
ከመልአከ ሞት፤ለማምለጥ ሲታገል
በዚች እናት ታድያ ፤እንዴት ይፈረዳል
የትንሹ ልጇን ፤ገላ ልትገነባ
በራሷ ገላ ፤ተደራድራ
ሆና የሚቀልጥ የሻማ ሰመመን፤ ልጇን ብታበራ

@NeNu4
1
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አስራ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል)


#በሜሪ_ፈለቀ

....በቀኝ እጅዋ የሌባ ጣት እንደመዳበስ ትነካካኛለች ምኔጋ እንደነካችኝ እንደነበረም ማስታወስ አልቻልኩም። ከእንቅልፌ ስባንን ጠዋት ሆኖ ሩካ ልትቀሰቅሰኝ በሬን እያንኳኳች ነበር። ከላዬ ተገፎ ከግማሽ በላዩ መሬት በተነጠፈ የልጋ ልብሴ አንሶላዬን እየሸፈንኩ እንድትገባ ነገርኳት
ይሄኔ ገብታ ነው “እስኪሪብቶህን
አገነፈልክ የምትለኝ።

“ተነስ እሺ አሁን ቁርስ እንብላ!"

“ማርቲ ልትመጣ ነው!" አልኳት የሚያስጮኃት አጀንዳ መሆኑን
ባውቅም እንደዚህ የምትዘል አልመሰለኝም ነበር፡፡ ጭንቀቴ
ወዲያው ጨንቋት ፈንጠዝያዋን ትታ ሀሳብ የገባት መሰለች::

"መቼ ነው የምትመጣው?" አለችኝ ማጥኛ ጠረጴዛዬ ጠርዝ ላይ
በግማሽ መቀመጫዋ እየተቀመጠች

“ከስድስት ቀን በኋላ! እና ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም፡፡የማብድ እየመሰለኝ ነው:: የምትመጣው እኔን ብላ ነው።ያንቺንም ሰርግ ለመታደም ነው:: ሳትመጣ እውነቱን ብነግራት
አትመጣም:: ጭራሽ ዓይኗን ላላየው ነው:: መጥታ እውነቱን ስታየው ልትጠላኝ እንደምትችልም አውቃለሁ፡፡ የቱን መምረጥ እንዳለብኝ መወሰን አቃተኝ::” ከገለፅኩት ስሜቴ በላይ በጥልቀት
ምን እንደሚሰማኝ ሩካ እንደሚገባት አውቃለሁ።

“በርዬ በእውነተኛነት ስለመቆም ካንተ የተሻለ ልምዱ የለኝም፡፡የፍቅር ግንኙነትን አስመልክቶ ግን የተሻለ ልምድ ሳይኖረኝ
አይቀርም ነገሮችን ለመረዳትም ሆነ ለማስረዳት በአካል መገናኘትና በርቀት መነጋገር የትየለሌ ልዩነት አለው እስክትመጣ አፍህን ሰብስበህ ስትመጣ ሊፈጠር የሚችለውን ነገር ለመቀየር ወይም ለመቀበል ራስህን ብታዘጋጅ የተሻለ ይመስለኛል።" አለችኝ ጭንቀቴን ልታቀልልኝ እየሞከረች።ያለችውን ቀላል አድርጋ ትበለው እንጂ ሊገጥመኝ የሚችለውን አስባ እንደፈራችልኝ አውቅባታለሁ፡፡ ልቤ እንዳይሰበር
ፈርታልኛለች:: እንዳልጨነቃት ስታስመስል አሁንም አሁንም ግንባሯን ታሻሻለች። አንዱ ከአንዱ የማይያያዝ ወሬ
ትዘላብዳለች፡፡ ቁርሴን ሰርታ አብልታኝ ስለማያገባኝ ሁሉ ነገር ዘባርቃልኝ ከቤት ወጣች፡፡

ማርቲ የረቂቅ ሰርግ መድረሱን ስታውቅ ለመምጣት መወሰኗን ስትነግረኝ ላስቆማት ብችል ደስ ባለኝ፡፡ በየትኛውም ጨዋታዬ ስለሩካ አለመጥቀስ የማልችለው ነገር ነውና ታውቃታለች:: ሩካ
እኔ ሳላውቅ ነበር መጀመሪያ የፃፈችላትና የተዋወቁት፡፡ በስልክም የተወሰኑ ቀናት አውርተዋል። የማውቃት የማውቃት
ይመስለኛል፡፡ ትለኝ ነበር ማርቲ ስለ እህቴ ስትፅፍልኝ። በምን ፍጥነት ተወዳጅተው መቆለጳጰስ እንደጀመሩ ግራ ያጋቡኝ
የሩካን የሙሽራ ቀሚስ በጋራ እንደመረጡ ሩካ የነገረችኝ ጊዜ
ነበር፡፡ በስካይፒ እንደሚያወሩ ያወቅኩት ስለማርቲ ቁንጅና የምትነግረኝ ቀን ነው:: በስምንት ወራት ውስጥ ከማርቲ ጋር
የተቆራኘንበትን ጥብቀት እያሰብኩ ወደ መኝታ ቤቴ ስገባ ሳራ አንሶላዎቼን እየቀየረችልኝ ነበር። ዊልቸሬን ወደ ጠረጴዛዬ አስጠግቼ ኮንፒውተሬን ከፈትኩ፡፡ የማርቲን መልዕክት ፍለጋ።
የሳራ ዓይኖች ትከሻዬን ስለተጫኑኝ ለማራገፍ ቀና አልኩ።አልተሳሳትኩም:: የቀየረቻቸውን የቆሸሹ አንሶላዎች በእጇ ይዛ ቆማ ዓይኗን ጭናብኛለች፡፡ በጥያቄ አየኋት።

"አንሶላዎቹን ላጥባቸው ነው::" አለችኝ በቃሏ። አስተያየቷን ደምሬ ስሰማት ልትነግረኝ የፈለገችው አንሶላዎቹ የረጠቡበትን ምክንያት እንዳወቀች ነው የመሰለኝ፡፡ የማብሸቅ ዓይነት ፈገግታ
እያሳየችኝ ክፍሌን ለቃ ወጣች።

ስድስት ቀን እንዲህ አጭር ነው? በእንዲህ ያለ ውዝግብ ቀናት ውስጥ
ጊዜው የብርሃንን ፍጥነት ይዋሳል ፣ እሷ ልታገኘኝ ስለጓጓች ረዘመብኝ አለችኝ።እኔ ግን መገናኘታችን የሚጎትተው መዘዝ ፍራቻ ስለቆነደደኝ እንዲረዝም ብመኝም አጠረብኝ። እንዲህ የተወዛገበ ቀን ለራሴ እፈጥርለታለሁ ብየ አስቤ አላውቅም።

መምጫዋ ቀን ደረሰ:: እናም ሩካ እና ኤፍሬም አጅበውኝ እየጠበቅኳት ነው።
ከፍርሃቴ የተነሳ ልቤን የምተፋት
እስኪመስለኝ እየደለቀች ነው።እጆቼ እየተንቀጠቀጠ እና እያላባቸው የዊልቸሬን መደገፊያ በወጉ መንተራስ እቅቷቸዋል፡፡የለበስኩትን ስስ ሸሚዝ ማውለቅ እስኪያሰኘኝ እየሞቀኝ ነው፡፡
ሩካና ኤፍሬም ሀሳቤን በጭንቅ ከተሞላው ጥበቃዬ ለማሸሽ
ጨዋታ ይፈጥራሉ። ስለሰርጋቸው ጣጣ
ይነግሩኛል፡፡አልሰማቸውም ወይም ደግሞ ብሰማም አይስበኝም፡፡ በጭንቅላቴ ውስጥ እዚህም እዛም እኳትናለሁ።

“ብቻህን ብትቀበለኝ ነው ደስ የሚለኝ፡፡ እንዳገኘሁህ ሰው አየኝ አላየኝ ሳልል እስክጠግብህ ልስምህ ነው የምፈልገው::"ትናንትና ማታ ከፃፈችልኝ መሃል አሰብኩ፡፡

“የምትጠብቂው ዓይነት ሰው ሆኜ ባታገኚኝስ?" ብዬ መልሼ ፅፌላታለሁ።

'የምጠብቀው ዓይነት የለኝም:: የማውቀው ፍቅረኛ ነው ያለኝ፡፡
ጥቃቅን ልዩነቶች አያሳስቡኝም::" ነበር መልሳ የፃፈችልኝ፡፡

ትንፋሼ ቀጥ ልትል ትንሽ ሲቀራት ሻንጣዋን እየጎተተች ዓይኗን
በፍለጋ እያቅበዘበዘች ብቅ አለች:: ዊልቸሬን ወደኋላ አዙሬ መመለስ ነበር ያሰብኩት።ኤፍሬም ትከሻዬን ጨበጥ ጨበጥ ሲያደርገኝ ለመረጋጋት መጣር ጀመርኩ።በአንድ እይታ አወቅኳት፡፡ አቅራቢያዬ ሆናም ፍለጋዋን አላቆመችም። ሩካን አይታት ለፈገግታ ለማሸሽ የጀመረችውን ከንፈሯን ጨርሳ
ሙሉ ፈገግታ ከማሳየቷ በፊት አየችኝ። ከንፈሯን ሰበሰበችው።እኔ እንዴት ነው
ያልኩት? ፈገግኩ?አፈጠጥኩባት? ዓይኔን አሸሁ? የሆንኩትን እንጃ ብቻ
ድንጋጤዋ አቃዠኝ፡፡ ረቂቅ ብዙ ቅርቢያ እንዳለው ሰው ተጠመጠመችባት:: ማርቲ ደርቃ ቀርታለች፡፡ ዓይኗ ከዊልቸሬ
ላይ አልተነቀለም ነበር፡፡ ልቅረባት ልራቃት እያሰብኩበት ባልነበረበት ደቂቃ ኤፍሬም ዊልቸሬን ገፍቶ እግሯ ስር አደረሰው እና ለሰላምታ እጁን ዘረጋላት፡፡

"ኤፍሬም! የሩካ እጮኛ ነኝ! ስላንቺ ብዙ ሰምቻለሁ። እንኳን ደህና መጣሽ!" ለዘረጋላት እጅ አፀፋ እጁን እየዘረጋች
የተናገረውን የሰማችው አልመሰለኝም:: ፈዝዛ እያየችኝ ነው።ፈገግ አልኩ መሰለኝ። ከዛም እጄን ዘረጋሁላት በዘገምተኛ ሂደት ከኤፍሬም እጅ ያላቀቀችውን እጇን ሰዳ ጨበጠችኝ፡፡

"እንዴ? አትሳሳሙም እንዴ?" አለች ሩካ ምንም ያልተከሰተ እያስመሰለች፡፡ ጉንጬን ልትስመኝ ዝቅ አለች፡፡ አዟዙሬ
አቀበልኳት፡፡ ለተወሰነ ሰከንድ የሚያሳብድ ዓይነት ረጭታ ሆነ።

"እንንቀሳቀስ አይደል? የተቀረውን ናፍቆታችሁን እቤት ትወጡታላችሁ።" አለች አሁንም ሩካ ቶሎ ተሽቀዳድማ
አንደኛውን ሻንጣ ለመግፋት እየተሰናዳች፡፡ ሌላኛውን ሻንጣ
ኤፍሬም ያዘ፡፡ ዊልቸሬን ለመንቀሳቀስ አዞርኩ፡፡ ማርቲ እስከአሁን ዓይኗ ከእኔ ላይ አልተነቀለም።

"አይይ እኔ እንኳን ሆቴል ሄጄ ትንሽ ባርፍ ሳይሻለኝ አይቀርም።" አለች በደከመ ድምፅ:: በእርግጥ እቅዳችን እቤት
ከነሩካ ጋር ምሳ በልተን አብረን ወደ ሆቴሏ መሄድ ነበር። እኔ ማለቷ የጠበቅኩት ስለነበር ብዙም አልገረመኝም፡፡

“ኸረ በጭራሽ! እቤት ላንቺ ተብሎ ምሳ ተዘጋጅቷል፡፡ ሻወር መውሰድ ከፈለግሽም እቤት ትተጣጠቢያለሽ!" አለቻት ሩካ።መልስ ሳትመልስ ወደ መኪናችን ተከተለችን። ከዊልቸሬ ወደ
መኪና ለመግባት ተደግፌ ስነሳና ተንፏቅቄ ስቀመጥ እንደ ተዓምር አፍጥጣ እያየችኝ ነበር፡፡

ይሄ አቃጣሪ ጊዜ ህይወቴን ጣእም አልባ ሊያደርገው እንደሚናድ ድንጋይ ካብ ተንደርድሮ አሁን ላይ ደረሰ። ማርቲ ምሳ አብራን ከታደመች በኋላ ወደ ሆቴሏ ከሄደች ሁለት ቀን አለፈ።ላልቆጠርኩት ያህል ጊዜ ፃፍኩላት። ለአንዱም አልመለሰችልኝም።ሆቴሏንም መልቀቋን አረጋገጥኩ ኢትዬጵያ ውስጥ ልትጠይቀው የምትችለው ዘመድ እንደሌላት አውቃለሁ። ወይ ወደ ሃገሯ ተመልሳለች
👍4
አለዚያም እንዳገኛት ስላልፈለገች ነው ሆቴሉን የቀየረችው።

"ጊዜ ስጣት!" ይሉኛል ሩካና ኤፍሬም። የምሰጣት ጊዜ እኔን እየጨረሰኝ እንደሆነ እያወቁ፡፡ ጥበቃዬ ተስፋ ወደ መቁረጥ
ሲጠጋጋ ኢሜል ላከችልኝ፡፡ በመዓት ወቀሳ የታጀለ የእርሳኝ መልዕክት ነበር። እያነበብኩት አስቀድሜ እውነቱን
ስላልነገርኳት አለመፀፀቴን ተረዳሁ፡፡ ምክንያቱም የጊዜ ጉዳይ እንጂ ውጤቱ ያው ነበር። የትኛዋም ሴት ዊልቸር እየገፋች ዘመኗን ለመኖር ምኞቷ አይሆንም። የአማርኛ ፊልም ተዋናይ
ካልሆነች በቀር፡ አልተማረርኩም። እየጠበቅኩት ያለ ቀን መሆኑን ያወቅኩት እረፍት ሲሰማኝ ነበር።

ነገ ብሩህ ቀን ይሆናል።” አለችኝ ሩካ ሶፋ ላይ ተጋድሜ ሀሳብ እያመነዠኩ።

" ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም። ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም፡፡ ምክንያቱም ነገን መኖር ስንጀምር ዛሬ
ተብሏል። ብዙዎቻችን ግን ሁሌም ብሩህ ነገን ለመኖር ስንናፍቅ ብዙ ዛሬያችን ያልፈናል። እናም ብሩህ የሚባል ቀን ሳይኖረን እናልፋለን። ብሩህ ቀን በእጃችን ያለው ዛሬ ነው::" አልኩት
ራሴን የሚሰማኝ ድብዛዜ ከዚህ የተለየ ቢሆንም ማመን የምፈልገው ያንን ነበር።

"ምን ማድረግ ትፈልጋለህ? የት እንሂድ?" አለችኝ ሩካ ኣጠገቤ እየተቀመጠች፡፡ የሰሞኑን ቀናት የ'ምን ላድርግልህ' ጭቅጭቅ ያስጨንቀኛል። ሳራ እንኳን ያለወትሮዋ በየገባሁበት እየተከታተለች ለምቾቴ ትጣጣራለች፡፡ ሩካን ለሳራ ገላዬን ለመታጠብ የሚያስፈልገኝን እንድታገባባልኝ እንድትነግራት ብቻ
ጠየቅኳት፡፡ መታጠቢያ ቤቱ ውስጥ ስገባ ሳራ ነበረች፡፡እንድትወጣ ብጠብቅም አልወጣችም::

"ልርዳህ?" አለችኝ። ልብስ ማውለቁን መሆኑ ገብቶኛል።የሰሞኑ ሁኔታዋ
ግራ አጋቢ ሆኖብኛል:: ሹራቤን
እንድታወልቅልኝ እጄን አነሳሁላት፡፡

======================
ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም። ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም። ምክንያቱም ነገን ለመኖር ስንጀምር ዛሬ
ተበሏል። ብዙዎቻችን ግን ሁኔም ብሩህ ነገን ለመኖር ስንናፍቅ ብዙ ዛሬያችን ያልፈናል። አናም ብሩህ የሚባል ቀን ሳይኖረን እናልፋለን። ብሩህ ቀን በእጃችን ያለው ዛሬ ነው።

💫ተፈፀመ💫

ድርሰቱን እንዴት አገኛችሁት? አስተያየታችሁን እጠብቃለው #Like #Share እያደረጋችሁ ለወዳጆቻችሁ ጋብዙ በሌላ ድርሰት እስከምንገናኝ መልካም ጊዜ 👍

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ሁሉም_ለምን_ያልፋል?

የጣፈንታ መዳፍ
ደስታና መከራን፣ እያፈሰ ሲናኝ
“ሁሉም ያልፋል” ብሎ፣ ማነው የሚያፅናናኝ?

ግራ በተጋባ፣ በዞረበት አገር
ካንቺ የምጋራው፣ ሠናይ ሠናይ ነገር
ፊቴን የሚያበራው፣ ያይንሽ ላይ ወጋገን
ዛሬ ተለኩሶ፣ የሚያሳየኝ ነገን
ለምን ሲባል ይለፍ፣ ያንን መሳይ ፍቅር
ደስታሽ ይገተር፣ ሣቅሽ ቆሞ ይቅር!!

በብሩህ ቀለማት የተሸላለመ
የተዋበ ህልሜ
በሁለት ጦርነት፣ መካከል የቆመ
አጭሩ ሰላሜ
ያፍላነት ወኔየ፣ የጉርምስና አቅሜ
ነበር ተብሎ እንዳይቀር፣ እንዳገኘው ወትሮ
ባለበት ላይ ይቁም፣ ባስማት ተገትሮ

እና

ከጣፈንታ መዳፍ፣ ሞልቶ ከሚፈሰው
በሰው የሚደርሰው
ለሰው የሚደርሰው
በጊዜ ኬላ ላይ ተዛዝሎ ሲሰለፍ
በጎ በጎው ይቆይ፣ ክፉ ክፉው ይለፍ!!
አትሮኖስ pinned «#ምርጫ_አልባ_ምርጫ ፡ ፡ #ክፍል_አስራ_አንድ (የመጨረሻ ክፍል) ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ ....በቀኝ እጅዋ የሌባ ጣት እንደመዳበስ ትነካካኛለች ምኔጋ እንደነካችኝ እንደነበረም ማስታወስ አልቻልኩም። ከእንቅልፌ ስባንን ጠዋት ሆኖ ሩካ ልትቀሰቅሰኝ በሬን እያንኳኳች ነበር። ከላዬ ተገፎ ከግማሽ በላዩ መሬት በተነጠፈ የልጋ ልብሴ አንሶላዬን እየሸፈንኩ እንድትገባ ነገርኳት ይሄኔ ገብታ ነው “እስኪሪብቶህን…»
#ከተለየሁሽ_ወድያ

ከተለየሁሽ ወድያ
ስንት ቅጥሮች ፈረሱ
ስንት ሕዝቦች ፈለሱ
ስንት ኮከቦች ተተኮሱ
ስንት ፀሐዮች ተለኮሱ
ስንት ዝነኞች ተረሱ
ስንቶች ካመድ ተነሱ፤

ስንት ባሕሮች ደረቁ
ስንት አለቶች ውሀ አፈለቁ
ስንቶች አማልከት ሞቱ
ስንት ደናግል ገለሞቱ፤

ባለት አጥር የከለሉት
የማይጣስ ጥሶ ሾልኮ
በብረት ጣት የጨበጡት
ከመዳፍ ሥር አፈትልኮ
ምንም ነፃ መስሎ ቢታይ
ሁሉም ዮጊዜ ግዳይ
ሁሉም የጊዜ ምርኮ፤

አንቺ ከየት አመጣሽው
የለውጥን ሞገድ መግቻ
ባስቀመጥሁሽ ያገኘሁሽ
አንቺን ብቻ፤ አንቺን ብቻ።
Forwarded from አትሮኖስ via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አገር_እንቁጣጣሽ

አገር እንቁጣጣሽ
የዳ ክንድሽ አቅፎኝ
ያሳር ከንፍሽ አቅፎኝ
ዕንቁሸን ስመኘው፥ ጣጣሽ ብቻ ተርፎኝ
መኖርን ስፈራ፥ መሞትም ስፈራ
ካየር ንብረት በቀር፥ ንብረት ሳላፈራ
ወሩ ተጠራቅሞ፥ አንድ ደርዘን ሞልቶ
እንደባለጌ ልጅ፥ በሩን በግሩ ከፍቶ
አዲስ ዘመን ገባ፤

አዲስ አመት ገባ
ያለ መስቀል ወፎች፥ ያለ ዓደይ አበባ
በግዜርሠራሽ ማማ
ቁራ ብቻ ሰፍሯል
የመስቀል ወፍማ
ወይ አገር ለውጧል
ወይ ልብሱን ቀይሯል

አዲስ አመት ገባ
በቄጤማ ምትክ፥ ብሎኬት ጎዝጉዞ
በቅፍ ዓደይ ምትክ፡ ጉንጉን ሽቦ ይዞ
በሉባንጃ ምትክ፥ አቧራ ኢያጤሰ
በፈንድሻ ምትከ፥ ጠጠር አያፈሰ፤

አዲሰ አመት ገባ
አዲስ እንዲህ ዋዛ
ተፈጥሮ በውበት፥ መንፈሴን ሳይገዛ
መእዛው ሳይዋጅ
መስከረም መግባቱን በሬድዮ ልስማው?
አንደ መንግሥት አዋጅ።
#ያንቺው_ጉረኛ

አነጋገሬ የሰለጠነ
እረማመዴ የተመጠነ

ስደሰት ፊቴ፣ የግዚሀር ባውዛ
ስስም ከንፈሬ፣ ያበባ ጤዛ
ካለት ያወጋሁ፣ ከንብ የተጋሁ

እንደ ዘንገና፣ ውሃ የረጋሁ
ከጎህ ቀድሜ፣ ባይንሽ የነጋሁ።

ባስብ በመላ፣ ብናገር እውነት
ባቅፍሽ ክንዶቼ፣ የሐር መቀነት።

ጣትሽ ደባብሶኝ፣ ጥፍርሽ ቢበጣኝ
ዘቢብ ነው እንጂ፣ መች ደም ሊወጣኝ

ለምድር ቢቀርብ፣ ቁመቴ ቢያጥር
በጎልያድ ግንባር፣ የማነጣጥር
ልቤ በጣቱ፣ ሰማይ ሚነካ
ከነራስ ደጀን፣ ከንጦጦ የካ
ቁመት በኩራት፣ የሚለካካ

ብትደገፊኝ፣ የላባ ፍራሽ
ብትመገቢኝ፣ የመና ቁራሽ።

እንኳን በጃኖ፣ እንኳን በሱፉ
እንደ ቁጥቋጦው፣ ልክ እንደዛፉ
ቅጠል ለብሼ፣ የምሽቀረቀር
የተለጋ ልብ፣ ቀልቤ ማስቀር

ያንቺው በረኛ
ያንቺው ቁንን ነኝ፣ ያንቺው ጉረኛ።
#ንቀን_ያለፍነው_ቃል

ከለታት አንድ ቀን፣ ወደ ቤቷ ሄድኩኝ
ጥቅል ጎመን አርዳ፣ እንጉዳዩን ጠብሳ
ጋበዘችኝ ምሳ
ሙያዋን አደነቅሁ
ገበታው ሲነሳ
ካያቷ ተዋወቅሁ።

አረጋዊት ናቸው፣ እድሜያቸው የገፋ
ድሮ ልጅ እያሉ፣ አይናቸው የጠፋ
በድሜያቸው በረካ፣ በፅዋቸው ጭላጭ
አምሯቸው ብሩህ፣ ልሳናቸው ምላጭ
ወግ ማውጋት ጀመሩ
ቃል እያለዘቡ
ቃል እየጠረቡ፣ ቃል እያሳመሩ
ሀረግ አለዝበው፣ ዘይቤ እየነቀሱ
በጸጥታ ሞቶ፣ ያላጀብ ተቀብሮ
የተረሳ ታሪክ እየቀሰቀሱ
እንደ መቅረፀ ድምፅ፣ ጆሮየን ጠመድሁት
አጥብቆ ገረመኝ
ያረጋዊቷ ወግ፣ ቅድም ከበላሁት
ከንጉዳዩ ዝልዝል፣ የበለጠ ጣመኝ።

ጸሐፌ ትዛዛት ቸል ብለው ያለፉት
ዜና ነጋሪዎች፣ አይተው የገደፉት
ያገሬን ሰው ገድል፣ መከራ ፍስሐ
ሳልታክት ቀዳሁት፣ ልክ እንዳርብ ውሃ።

ከጥሞናየ ላይ ላፍታ ተፋትቼ
ጋባዤን ፈለግኋት
ፊትለፊቴ አየኋት
ያቻት ያቻትና
ከሶፋው ላይ ሆና
እግሮቿን ዝርግትግት፣ ሰውነቷን ዘና
እንደፊት መስተዋት
ዘመናይ ሞባይሏን፣ ፊቷ ስር ደቅና
ከስልኳ ሰሌዳ፣ ፊደል ትነካለች
ፎቶ ታምሳለች፣ ኢሜል ትልካለች
ያያቷ ጣፋጭ ወግ፣ ላፍታ እንኳ መች ደንቋት
ሜሴንጀር ዋትሳፕ፣ ኢሞ ቴሌግራም
ሁሉን የወሬ ቋት
ትበረብራለች፣

ካሥር አመት በፊት
ለረፍት ከከተማ፣ ወደ ገጠር ሄጄ
ደጅ ላይ ማለዳ፣ ፀሐይ ስር ተጥጄ
አያቴ ብቅ ብሎ
ከተቀመጥሁበት የወይራ ግንድ ላይ፣ ራሱን አዳብሎ
“ያኔ ጎበዝ ሳለሁ” ብሎ ወግ ሲወጥን
አልባሌ ወሬ፣ እኔን የማይመጥን
የሰማሁ ይመስል፣ በኀይል አዛግቼ
ከካፖርቴ ኪስ ውስጥ፣ መጽሐፍ አውጥቼ
(የማርክስ፣ የፍሮይድ ምናልባት የኒቼ?)
ገለብ ገለጥ ሳደርግ፣ እሱ ይህን አይቶ
የጀመረውን ቃል፣ አንጠልጥሎ ትቶ

ለጥናት ነው መሰል፣ እዚህ መቀመጥህ፣
ወግድልኝ በለኝ፣ እንዳልበጠብጥህ”

ብሎ ይወገዳል
አድማጭ ካጣጭ ጋራ ወደሚገኝበት፣ ጠላ ቤት ይሄዳል።

አያቴ ከሞተ፣ አመታት አለፉ
ፀፀት ጭንቅላቴን፣ በብረት መዳፉ
እየኮረኮመኝ
ሀፍረት በሸኮናው፣ እየረመረመኝ
በራሴ ስበግን
ምን ሆኘ ነበር ግን
ምን ነክቶኝ ነበር ግን?
በማለት አጥብቄ ራሴን ስረግም
ይሄውና ዛሬ
ጋባዤን አየኋት፣ ታሪኬን ስትደግም።
አንድም በመሰልቸት፣ አንድም በቸልታ
ወይ ባወቅሁሽ ናቅሁሽ፣ አለያም በወረት
የያዝነውን ዳቦ፣ ቆጥረነው ከኮረት
ጠላ ከሚጠጣ፣ ቆሎ ከሚበላ
እድፍ ከሚለብሰው
ለዐይን ከማይሞላ
ካንድ ስም አልባ ሰው
ምን ጥበብ ይገኛል? በሚል ተዘናግተን
በቻይና ቅፅር ጡብ፣ ጆሯችንን ዘግተን
ልቦና ቆልፈን
ንቀን ያለፍነው ቃል፣ ንቆ ነው ያለፈን።

#ክብር_ለአያቶቻችን_ለተንቀሳቃሽ #ላይብሬራችን
#የባከነ_ሌሊት

ወይ ሮንድ አላደርኩ
ወይ ኰከብ አልቆጠርኩ
ወይ ደልቶኝ አልጨፈርሁ
ወይ ውስኪ አልተዳፈርሁ
ወይ ሰአታት ቆሜ
ቤተስኪያን ስሜ
ሰይጣን አላሳፈርሁ።

ሌቦች ደብድበውት
አንዱን ምስኪን ላሥር
ባምቢስ ድልድዩ ስር
ቆስሎ የወደቀ
ገላው በላዩ ላይ፣ እንደጨርቅ ያለቀ
ፊቱ ተሸፍኖ በደምና አቧራ
“በዑራኤል ርዱኝ” ብሎ የሚጣራ
ምስኪን አባወራ
ብብት ስር ገብቼ
አፋፍሼ አንስቼ
ተሸክሜ አድኜ
ስፈልግ አምቡላንስ፣ ሲሻኝ ዶክተር ሆኜ
ወይ ምግባር አልሰራሁ
ወይ ጀብድ አልፈጸምኩኝ፣ ወይ ጽድቅ አላፈራሁ።
አንድ በትረ ሙሴ
ሁለት ስስ አሎሎ
ከጭኔ መሀከል ሲያመሽ ተንጠልጥሎ
ሊባከን ዝም ብሎ
እሸኝ የኔ ጀግና እንደሰነፍ ቆሎ”
የምትል መለሎ
ልቤን ሳትሰውረው
አልጋዬን ሳትሰብረው።

ወግ ቢጤ ምንጭሬ፣ ፈስቡክ ላይ ሳልለጥፍ
እናትዋን ጨረቃ” የሚል ግጥም ሳልጽፍ።
አንዲት ሴት አዳሪ፣ ቺቺንያ መንገድ ላይ
ዕድሏ.ሰባራ ሰውነቷ አማላይ
ካፍያውና እንባዋ ተጋግዘው የሚያረጥባት
ደምበኛ ስትጠብቅ ደመኛ ጥሎባት
አምስት ደፋሪዎች ከበው ሲያዋክቧት
ሲገፉ ሲስቧት
ኧረ በናታችሁ በወላድ ማሕፀን
እህት የላችሁም?” ብላ ስትማፀን
ልመናዋ ስቦኝ
እንዳበጀ በለው፣ በደሏ አንገብግቦኝ
ከኋላ ደርሼ
ነበልባል ለብሼ፣ ነበልባል ጎርሼ
እንደብሩስሊ፣ እንዳየሩ ጋኔን
እግሬን ወንጨፍ ወንጨፍ
ወዝወዝ ወዝወዝ ጎኔን
በማረግ ቃኝቼ
ከኋላ ነው ሲሉኝ ከፊት ተገኝቼ
ካምስቱ መካከል አራቱን ነጥየ
ከቻልኩ በካራቴ ካልቻልኩ በሣቅ ጥየ።
ድል ሳላስመዘግብ
ውጥረት ሳላረግብ
ወይ ታሪክ ሳልሰራ ወይ ታሪክ ሳልዘግብ
ያለ ምንም ጣጣ ያለምንም ጸጋ
አለሰበብ መሽቶ አለሰበብ ነጋ።