#ያሳደግኩት_ቀጋ
ባልንጀራዬ ብዬ ምስጢሬን ነግሬው
ውስጠ ገመናዬን ሀቄን አካፍዬው
ያቺን ጫፏን ይዞ አጥንቶ ኋላዬን
ከመቅፅበት መጥቶ ሲወጋው ጀርባዬን
ኮትኩቼ ኮትኩቼ ያሳደግኩት ቀጋ
ኮተት ኮተት አለ እኔኑ ሊወጋ....
አልኩኝ.......
ባልንጀራዬ ብዬ ምስጢሬን ነግሬው
ውስጠ ገመናዬን ሀቄን አካፍዬው
ያቺን ጫፏን ይዞ አጥንቶ ኋላዬን
ከመቅፅበት መጥቶ ሲወጋው ጀርባዬን
ኮትኩቼ ኮትኩቼ ያሳደግኩት ቀጋ
ኮተት ኮተት አለ እኔኑ ሊወጋ....
አልኩኝ.......
#ማዶ_ለማዶ
ድንገት ዘወር ብየ፣ ያለፈውን ስቃኝ
የመስክ ውሃ ነበርሁ፣ ሜዳ የማይበቃኝ
አሁን ግን ታሰርኩኝ፣ ባንድ ትልቅ ቀፎ።
ያንችም ነፃ ገላ
በትንሽ ሰቀላ
ቀረ ተቆልፎ
ለሌሎች የመጣው፣ ለኔና'ቺ ተርፎ።
ይሄ ግዙፍ መአት
ጠልፎ ሳያስቀረን
ማታ፣ ሁለት ሰኣት
ቀጠሮ ነበረን
ትመጫለሽ ማታ?
ቀፎየን ልበርግድ፣ ሰንሰለቴን ልፍታ?
ይነጠፍ ወይ አልጋው
ለኔ - ላንቺ - ለሞት
ሶስትዮሽ ምኝታ
ሶስትዮሽ ጨዋታ?
ይሰረዝ ቀጠሮው?
ወደ ፊት ይዛወር
ወደ ማናውቀው ቀን፣ ወደ ማናውቀው ወር?
አሁን እዚህ ሆነን፣ ቅንጦት ነው መገመት
እናስተላልፈው ወይ፣
ከለታት ላንዱ ቀን፣ ካመቶች ላንዱ ዓመት?
እንዳማረኝ ይቅር?
ያ ሙቀት! ያ ፍቅር!
ያ መስህብ፣ ያ ለዛ
ያ ተረከዝ! ያ ባት!
ናፍቆትም ደዌ ነው፣ የሌለው ክትባት።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
ድንገት ዘወር ብየ፣ ያለፈውን ስቃኝ
የመስክ ውሃ ነበርሁ፣ ሜዳ የማይበቃኝ
አሁን ግን ታሰርኩኝ፣ ባንድ ትልቅ ቀፎ።
ያንችም ነፃ ገላ
በትንሽ ሰቀላ
ቀረ ተቆልፎ
ለሌሎች የመጣው፣ ለኔና'ቺ ተርፎ።
ይሄ ግዙፍ መአት
ጠልፎ ሳያስቀረን
ማታ፣ ሁለት ሰኣት
ቀጠሮ ነበረን
ትመጫለሽ ማታ?
ቀፎየን ልበርግድ፣ ሰንሰለቴን ልፍታ?
ይነጠፍ ወይ አልጋው
ለኔ - ላንቺ - ለሞት
ሶስትዮሽ ምኝታ
ሶስትዮሽ ጨዋታ?
ይሰረዝ ቀጠሮው?
ወደ ፊት ይዛወር
ወደ ማናውቀው ቀን፣ ወደ ማናውቀው ወር?
አሁን እዚህ ሆነን፣ ቅንጦት ነው መገመት
እናስተላልፈው ወይ፣
ከለታት ላንዱ ቀን፣ ካመቶች ላንዱ ዓመት?
እንዳማረኝ ይቅር?
ያ ሙቀት! ያ ፍቅር!
ያ መስህብ፣ ያ ለዛ
ያ ተረከዝ! ያ ባት!
ናፍቆትም ደዌ ነው፣ የሌለው ክትባት።
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#እንደምትወዳት_ንገራት
ሕይወት - የብድር በሬ፣ መቼ ሁሌ ይጠመዳል?
ለጊዜው ብቻ የመጣ፤ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፣ ደሞ ካንተ ይወሰዳል።
ቀለበት፣ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ፣ ሁል ጊዜ የሉም
ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት
ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ፣ እንደምትወዳት ንገራት።
አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምዑዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያፀድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፣ ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት - የላምባ መብራት
አሁኑኑ ዛሬውኑ፣ እንደምትወዳት ንገራት።
ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደ ጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደ እማትቀባው አመድ
ወደ እማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንተም አንደበት ሳለህ፣ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት!!
🔘ልጠይቅ አልጠይቅ ላይ ላላቹ ይሁንልኝ ተብላችኋል😄🔘
ሕይወት - የብድር በሬ፣ መቼ ሁሌ ይጠመዳል?
ለጊዜው ብቻ የመጣ፤ ጊዜው ሲደርስ ይሄዳል
የተሰጠህ ጸጋ ሁሉ፣ ደሞ ካንተ ይወሰዳል።
ቀለበት፣ አምባር አይደሉም
እጅህ ላይ፣ ሁል ጊዜ የሉም
ቀናት፣ ሳምንታት፣ ወራት
ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ፣ እንደምትወዳት ንገራት።
አበቦች ሁሉ ሳይረግፉ
ምዑዝ ሽታዎች ሳይጠፉ
ያፀድ በሮች ሳይቆለፉ
በንቦች ጎዳና ላይ፣ ተርቦች ሳይሰለፉ
በንፋስ ክንፍ ሳይመታ
ሕይወት - የላምባ መብራት
አሁኑኑ ዛሬውኑ፣ እንደምትወዳት ንገራት።
ርቃ ሳትገሰግስ
ገና ስንቋን ስትደግስ
እንዲሁ እንዳማረባት
ቀልብህ እንደቀረባት
መቃብር በመዳፉ
እንደ ጠጠር ሳይቀልባት
አፈሩን ሳትዛመድ
ወደ እማትቀባው አመድ
ወደ እማትስበው አየር
ሳትቀየር
አንተም አንደበት ሳለህ፣ እሷም ጆሮ ሳያጥራት
ዛሬውኑ! አሁኑኑ! እንደምትወዳት ንገራት!!
🔘ልጠይቅ አልጠይቅ ላይ ላላቹ ይሁንልኝ ተብላችኋል😄🔘
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ
፡
፡
#ክፍል_ስምንት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
ጥቁርና ነጭ አይደሉ? ቢሆንም የከዳሁት ልቡ አንደኛውን ሲሄድ ህመሜን ደምሬ ልታመም ወስኜ ዛሬ አብሬው ጠፋሁ። እኔ የጊዜ ዑደትን ማስላት ምን ሊረባኝ ያልኖርኩባትን ነገ ትቶኝ ይሄዳል ብዬ ዛሬዬን ልብከንከን? ኤፍሬምን በተመለከተ ከነገ እውነት የዛሬ ስሜቴ ልክ ነው። ከእርሱ ጋር አንድ ቀን ዘልአለም ነው አንድ አይደለም። ከእርሱ ጋር አንድ ቀን ዘለዓለም ነው። ዘለዓለም
ደግሞ ውሱን አይደለም፡፡ ዛሬ ዘለዓለም ናት! ስለዚህ ከርሱ ጋር ዘለዓለም መኖር ምርጫዬ ሆነ፡፡
"ደህና እደሪ" ሲለኝ ፀጉሩን እንደዳበሱት ህፃን አንቀላፋሁ።
"እወድሻለሁ" ያለኝ ቃል በጆሮዬ ለብዙ ዘለዓለም ቀናት ተንቆረቆረ።
ዘለዓለም ጥግ ኣልባ ነውና ዛሬ ለኔ ያለው ስሜት ጥግ አልባ ነው። ያንን ብቻ አምናለሁ። ነገ ስለመለያየቴ መርሳት ፈለግኩ፡፡ዘለዓለም ከእርሱ ጋር አለሁና! እስከሁሌው እቅፍ ውስጥ ብኖር
ብዬ ሳሳሁ። ጠዋት ተመልሰን ስለየው የመጨረሻዬ እንደሆነ እያወቅኩ ነበር በስስት የሳምኩት።እናም "ደህና ዋይልኝ" ሲለኝ ቀጥሎ ሊፈጠር ስለሚችለው ክስተት ሳላስብ ከደህና በላይ ሆንኩ፡፡ ከእርሱ ተለይቼ ብዙም ሳልቆይ አያሌው ደወለልኝ። እመኑኝ ኤፍሬምን ላለማጣት እናትና ወንድሜን አያስከፍለኝ
እንጂ ምንም አደርግ ነበር፡፡ አሁን ግን
ተመሳቅሏል፡፡እውነቱን ብነግረውም አብሮኝ ስለመዝለቁ ዋስትና
የለኝም፡፡
“ምን ብታቀምሺው ነው? ንግስቴን አመስግናት ሲለኝ እንኳን ያላፈረኝ?" አለኝ፡፡ ዝም አልኩት፡፡
“ከሰላሳ ደቂቃ በኋላ ላግኝሽ?" ብሎ ቀጠረኝ:: በድኔን እየጎተትኩ
ደረስኩ። ብሩን በቦርሳ በካሽ ሰጠኝ:: የማይሆን ነገር ባስብ በበርዬ ያስፈራራኝን ደገመልኝ።ከአንድ ሰዓት በኋላ እንደሚፈርምለት እየፈነጠዘ ነግሮኝ ተለያየን።ታክሲ ይዤ እየሄድኩ በመስኮቱ
አሻግሬ አያለሁ።ታክሲው ጎን የቤት መኪና አየሁ ውስጡ የነበሩት ሰዎች ትኩረቴን ሳቡት።አያሌውን የኤፍሬም እናት።አልተሳሳትኩም፡፡ ከንፈር ለከንፈር እየተሳሳሙ ነው ያየሁት።በደስታ
የሰከሩ ይመስላሉ፡፡ እናትየው የፋብሪካው ድርሻ እንዲሽጥ መወትወታቸው የተለየ ምክንያት ሊኖረው
እንደሚችል እንዴት አልጠረጠርኩም? የማደርገው ጠፋኝ፡፡
ቢሮው እያለከለኩ ስደርስ ብዙም አልዘገየሁም። የማደርገው ነገር የሚያመጣውን ቀውስ ማሰብ አልፈለግኩም፡፡ ሊፈርም
ያዘጋጃቸውን ሰነዶች እንደያዘ ኤፍሬም ፈዞ ያየኛል። የሆነውን አንድ በአንድ ነገርኩት። ገንዘቡን ለአያሌው ጠረጴዛው ላይ አስቀመጥኩለት።
"እኔጋ የሚቀርህን ገንዘብ እመልስልሃለሁ፡፡" ብዬው ስወጣ
ለመጨረሻ ጊዜ የኤፍሬምን ፊት አየሁት:: ደንዝዟል።ለመጨረሻ ጊዜ ይህን አለ፡፡
"ያ ሁሉ ለክፍያ ነበር?"
ኤፍሬም ድጋሚ ሊያየኝ እንደማይፈልግ የስንብት በሚመስል የመጨረሻ መልዕክቱ በስልክ አሳውቆኛል: ህይወት አስጠላኝ፣ እማዬና በርዬ እኔን ማባበል ስለቻቸው።በርዬ መፅሀፉን
የሚያሳትምለት አሳታሚ ድርጅት አጊንቶ ከስድስት ወር በኋላ ታተመለት:: ርዕሱ 'ምርጫ አልባ ምርጫ መሆኑን ያወቅኩት
ልናስመርቅ ስንሰናዳ ነው:: ሁሉ ነገር ቢያስጠላኝም የበርዬ ህልም መሳካቱ በተወሰነ መልኩ የደስታ ምንጭ ሆኖልኛል።መደበቂያዬ መፅሀፍ ማንበብ ሆኗል፡፡ ከማይገፋ የብቸኝነት ወራት በኋላ በርዬ ሱፍ ለብሶ፣ እኔ የሀበሻ ቀሚስ ለብሼ የመፅሀፉ ምረቃ ዝግጅት ላይ ከመታደማችን በፊት እማዬጋ
ሄድን፡፡ በደስታ አነባች:: መገኘት ባትችልም በልጆቿ ደስታ በማያባራ እንባ ታጠበች። ይህቺን ቀን እውን ለማድረግ ብዙ አልፌያለሁ እና አብሪያት አለቀስኩ፡፡
አዳራሽ ውስጥ ስንገባ ሰዓት ገና ቢሆንም ወዲህ ወዲያ የሚሉ
ሰዎች ነበሩ፡፡
"ሩካ?" የሰማሁትን ድምፅ ማመን አቅቶኝ ዞርኩ፡፡ ኤፍሬም የበርዬ መፅሀፍ ምረቃ ላይ ምን ይሰራል? አላችሁ? እኔም
ራሴን እንዲያ ከጠየቅኩ በኋላ ወዲያው
እስካሁን ያላስተዋልኩትን ነገር አስታወስኩ፡፡ የመፅሀፉ ሽፋን ላይ
አሳታሚና አከፋፋይ ተብሎ የተፃፈው የኤፍሬም ድርጅት ስም ነው።
"ወይዬ” አልኩት የምለው ጠፍቶኝ፡፡ በርዬ ዊልቸሩን እየገፋ አጠገቤ ሲደርስ ፍፁም በወዳጅነት መንፈስ ተቀላልደው አልፎን ሄደ፡፡ እንደትንግርት የሚሆነውን ከማየት ውጪ ምርጫ አልሰጡኝም:: በርዬ አልፎኝ ከሄደ በኋላ በአይኑ ጠቀሰኝ፡፡ እንዴትና የት ተግባቡ
“ይሄን መፅሀፍ ካነበብኩ በኋላ እንደገና ላውቅሽ እንደሚገባ ወሰንኩ።ኤፍሬም!!" አለኝ እጁን እየዘረጋልኝ፡፡
"ረቂቅ" አልኩት እጄ ሳላዘው ሊጨብጠው እየተዘረጋ።
።።።።።።።።
እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው።ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው 'ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል።እንደኔ አቋቋም ደግሞ የኔ ትክክል ይሆናል። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ።የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራው ስዳኝህ እቀሽማለው።
።።።
#በረከት
እሷ ዋሸኸኝ ነው የምትለኝ፡፡ እኔ ደግሞ አልነገርኳትም እንጂ ዋሸኋት ብዬ አላሰብኩም ወይም እንደዛ ማመን አልፈልግም።በእርግጥ ያልነገርኳት አለመነገር የሚችል አልያም ባይነገርም
በእኔ እና በሷ ግንኙነት ሂደት ለውጥ የማይፈጥር ዝባዝንኬ ሆኖ አልነበረም
እሷን እስከማጣት የሚስቀጣኝ ሊሆን
እንደሚችል አውቅ ነበር።ግን ማወቅ ከባድ አይደለም መኖር እንጂ! ያወቁትን ሁሉ መኖር የሚቻል ቢሆን ኖሮ ይህች ዓለም ከብዙ ስህተቶችና ጥፋቶች በተረፈች ነበር። ምክንያቱም የማይረቡ የምንላቸውን ጭምር አብዛኛዎቹ ጥፋቶች ባለማወቅ የሚደረጉ አይደሉም።
"ይቅርታ ውዴ! አንቺን ለመጉዳት ብዬ ያደረግኩት ምንም ነገር የለም። እመኚኝ፡፡" ብዬ የስልኬ መልዕክት መፃፊያ ሳጥን ውስጥ ካሰፈርኩ በኋላ ስልኩን አቀበልኳት::
“ታዲያ ለምን ዋሽኸኝ? ያን ሁላ ጊዜ ስንፃፃፍ ላንተ ጨዋታ ነበረ? እያሾፍክብኝ ነበር?" እኔ ከፃፍኩላት ስር ይሄን ፅፋ
ስልኩን መለሰችልኝ፡፡ በኖርኩባቸው የሃያ ሰባት ዓመት የዕድሜዬ ቁጥር ልክ ብዙዎች በተለያየ ምክንያት ሲያዝኑ እና ሲሰበሩ አይቼ አውቃለሁ። እሷ ላይ በማነበው ልክ ፊት ላይ የተገለጠ መሰበር አስተውዬ ማወቄን እጠራጠራለሁ፡፡ ምክንያቱ እኔ መሆኔ ደግሞ በሰባት ዓመቴ ወድቄ የተሰበረ እጄ ሲታከም ከተሰማኝ ህመም በላይ ያማል።
“በፍፁም አልነበረም:: የፃፍኩልሽን እያንዳንዷን ቃል እና ስሜት
ከልቤ ነው ያልኩሽ! የፃፍሽልኝ እያንዳንዱ ቃል ደግሞ በዘመኔ ሁሉ እየመነዘርኩት ደስታን የምሸምትበት ሀብቴ ነው ።
ስለሚቀጥለው ግንኙነታችን ልብሽ የሚልሽን አድርጊ ስላለፈው
ግን እመኚኝ የተሰማሽም የተሰማኝም እውነት ነበር። በዛሬው ጥርጣሬሽ ትናንትናችንን አታርክሺው ይሄን ፅፌ አቀበልኳት።አንብባ ስትጨርስ መልስ መፃፍ ጀመረች፡፡ ስልኩን መልሳ
ስታቀብለኝ ግን ምንም የተፃፈ መልዕክት የለዉም፡፡ ልቧን በቃላት ማስፈር የተሰማትን ስሜት ማቅለል ሆነባት የተወችው መሰለኝ።
ሩካ እና ኤፍሬም በእኔና በማርቲ መሃከል የተከወነውን የስልክ መቀባበል እንዳላስተዋለ ለማስመሰል ለቡና ቁርስነት የቀረበው ፈንድሻ ላይ ራሳቸውን ጠምደዋል፡፡ሁላችንም በፀጥታ
ሀሳቦቻችንን እያላመጥን መሰለኝ ሩካ ቡናውን ፉት ስትል
ፉፉፉፉፉፉትታዋ እንኳን አንድ ጠረጴዛ ለከበብነው አራት ሰዎች ከጊቢ ውጪ ለሚያልፍ ሂያጅ የ'ቡና ጠጡልኝ መልዕክት ይነግራል፡፡
"አቦል ልድገማችሁ?" የሚለው የሳራ ድምፅ (ሩካ ከሶስት ወር በፊት የቀጠረቻት በእድሜ ገፋ ያለች የቤት ሰራተኛችን ናት፡፡

👍2❤1😁1
በገነነው ፀጥታ መሃል በድምፅ ማጉያ የጮኸች ያህል ለጆሮ
ደማቅ ነበረ።
“እኔ በቃኝ:: አሁን ብሄድ ሳይሻል አይቀርም:: ለምሳውም ለቡናውም አመሰግናለሁ። እግዜር ያክብርልኝ!" አለች ማርቲ ከመቀመጫዋ እየተነሳች።
እኔ አደርስሻለሁ ቆይኝ መታጠቢያ ቤት ደርሼ ልምጣ::” ብሎ ኤፍሬም ከሳሎኑ ሲወጣ ሩካ ተከተለችው:: በእርግጠኝነት ሩካ የሆነ ምልክት አሳይታት ይመስለኛል ሳራም ወደ ጎዳ ተከተተች፡፡
💫ይቀጥላል💫
#Like #Share ማድረግ እንዳይረሳ በጣም እየቀነሳቹ ነው።
ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

#ላንዲት_ድንጋይ_ፈላጭ_አረጋዊት
አንዲት አረጋዊት
ጥቁር ኢትዮጵያዊት
ትመካበት የላት
ባለጸጋ ዘመድ
ፊቷ የለበሰ፣ ፅናት ላብና አመድ
እሷ አለቃ ሆና፣ ክንዶቿን ቀጣሪ
እሷ ድሃ ሆና፣ የሀብታሞች ጧሪ።
እየተጋች አድራ፣ እየለፋች ስትውል
እድሜና ተስፋዋን፣ ያስተሳሰረው ውል
ቢቀጥን ቢሳሳ
ከሸረሪት ፈትል
መሐረብ ዘርግታ
ተዘከሩኝ ሳትል
እንባ ሳታስቀድም
ምሬት ሳታስከትል
ፍላጎት ባይኖራት፣ ለውዳሴ ከንቱ
የሰራችው ገድል፣ ዜናው ባይሰማ
ይህ ሁሉ ከተማ
ህንጻው ሰገነቱ
የሷን ላብ ጠብቶ ነው፣ የፋፋው ደረቱ።
አንዲት አረጋዊት
ጥቁር ኢትዮጵያዊት
በዝምታ ዜማ፣ ፅናት የምትዘምር
ይፈልቃል ከጆቿ፣ እፁብ ድንቅ ተአምር!
መዶሻው ተነሳ
እቧራው በነነ
በመዳፎቿ ስር፣ ድንጋይ ዳቦ ሆነ!
አንዲት አረጋዊት
ጥቁር ኢትዮጵያዊት
ትመካበት የላት
ባለጸጋ ዘመድ
ፊቷ የለበሰ፣ ፅናት ላብና አመድ
እሷ አለቃ ሆና፣ ክንዶቿን ቀጣሪ
እሷ ድሃ ሆና፣ የሀብታሞች ጧሪ።
እየተጋች አድራ፣ እየለፋች ስትውል
እድሜና ተስፋዋን፣ ያስተሳሰረው ውል
ቢቀጥን ቢሳሳ
ከሸረሪት ፈትል
መሐረብ ዘርግታ
ተዘከሩኝ ሳትል
እንባ ሳታስቀድም
ምሬት ሳታስከትል
ፍላጎት ባይኖራት፣ ለውዳሴ ከንቱ
የሰራችው ገድል፣ ዜናው ባይሰማ
ይህ ሁሉ ከተማ
ህንጻው ሰገነቱ
የሷን ላብ ጠብቶ ነው፣ የፋፋው ደረቱ።
አንዲት አረጋዊት
ጥቁር ኢትዮጵያዊት
በዝምታ ዜማ፣ ፅናት የምትዘምር
ይፈልቃል ከጆቿ፣ እፁብ ድንቅ ተአምር!
መዶሻው ተነሳ
እቧራው በነነ
በመዳፎቿ ስር፣ ድንጋይ ዳቦ ሆነ!
#በሀገሬ_ሰማይ_ስር
🇪🇹 🇪🇹
ገመቹ ጎንደርላይ ፣ አይተ ሓጎስ ባሌ
አንዳርጌ ወለጋ፣ ኦባንግ መቀሌ፤
በፍቅርተሹመው ፣
ሰው በሰውነቱ ፣ ሚዛን እስኪገመት
አይገርመኝም ሽረት ፣ አይደንቀኝም ሹመት።
🔘ኢዛና መስፍን🔘
🇪🇹 🇪🇹
ገመቹ ጎንደርላይ ፣ አይተ ሓጎስ ባሌ
አንዳርጌ ወለጋ፣ ኦባንግ መቀሌ፤
በፍቅርተሹመው ፣
ሰው በሰውነቱ ፣ ሚዛን እስኪገመት
አይገርመኝም ሽረት ፣ አይደንቀኝም ሹመት።
🔘ኢዛና መስፍን🔘
#መኖር_ነው_የምመኝ
በማይ በምሰማው
አንዳንዴ ስገረም
ሕይወት ከናላማው
ስሕተት ይሆን እንዴ? በሞት የሚታረም
ማለት ይቃጣኛል
የዚህ ዓለም ኑሮ
ጥያቄ ወርውሮ
ምላሽ ያሳጣኛል።
ደሞ አንዳንዴ ሳስብ
ስለሰው ልጅ ሥራ
የሰናፍጭ ቅንጣት፣ በምታክል ጥበብ
የሚንድ ተራራ
በጨለመ ምድር፣ ብርሃን ሚዘራ .
በሰማይ ጎዳና፣ ወፍ የሚያሰማራ
ባሕርን የሚያጠምድ፣ መብረቅ የሚገራ
ከቀለሞች መሃል፣ ምስል የሚያነቃ
ከዝምታ መሃል፣ የሚያፈልቅ ሙዚቃ
በቃሉ በጣቱ
በቅመም ቅንጣቱ
ዘልቆ የሚያከመኝ
እንደሳንዱቅ ከፍቶ፣ መልሶ ሚገጥመኝ
ይህንን ሁሉ ሳይ ሕይወት እየጣመኝ
መኖር! መኖር! መኖር! መኖር ነው የምመኝ።
በማይ በምሰማው
አንዳንዴ ስገረም
ሕይወት ከናላማው
ስሕተት ይሆን እንዴ? በሞት የሚታረም
ማለት ይቃጣኛል
የዚህ ዓለም ኑሮ
ጥያቄ ወርውሮ
ምላሽ ያሳጣኛል።
ደሞ አንዳንዴ ሳስብ
ስለሰው ልጅ ሥራ
የሰናፍጭ ቅንጣት፣ በምታክል ጥበብ
የሚንድ ተራራ
በጨለመ ምድር፣ ብርሃን ሚዘራ .
በሰማይ ጎዳና፣ ወፍ የሚያሰማራ
ባሕርን የሚያጠምድ፣ መብረቅ የሚገራ
ከቀለሞች መሃል፣ ምስል የሚያነቃ
ከዝምታ መሃል፣ የሚያፈልቅ ሙዚቃ
በቃሉ በጣቱ
በቅመም ቅንጣቱ
ዘልቆ የሚያከመኝ
እንደሳንዱቅ ከፍቶ፣ መልሶ ሚገጥመኝ
ይህንን ሁሉ ሳይ ሕይወት እየጣመኝ
መኖር! መኖር! መኖር! መኖር ነው የምመኝ።
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ
፡
፡
#ክፍል_ዘጠኝ
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
"ከዛሬ በፊት ነግሬሽ ቢሆን ኖሮ ምንድን ነበር የሚፈጠረው?ከነጉድለቴ ትወጂኝስ ነበር?" አስቀድሜ ስልኬ ላይ ፅፌው ልሰጣት ሳመነታ የነበረውን አቀበልኳት
አቀበልኳት: አንብባው ቀና ስትል ያፈጠጠባት ዓይኔን ቀለበችው:: በዝቅተኛ ግን በቁጣ ድምፅ "ማድረግ የነበረብህ ያን ነበር፡፡ ግድ ሊልህ የሚገባው ነገር የእኔ ስሜት ለውጥ ወይም ውሳኔዬ ሳይሆን ያንተ ሀቀኝነት ነበር። ታውቃለህ? በእውነተኛ
ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልብ-ወለድ መፃፍ ትክክለኛ ተስዕጦህ ነው:: በእኔና ባንተ መሃከል የነበረው ነገር ላንተ እንደዛ ነበር::
አንዷን ገፀ-ባህሪህን እንደምታዋራት እና እንደምታስወራት ያህል የምትዝናናበት ልብ-ወለድ!!" ብላኝ ስልኬን ከጠረጴዛው
አጋጭታ አስቀምጣ ወደ ውጪ ወጣች:: እየሆነ የነበረውን እየተከታተሉ እንደነበር በሚያሳብቅባቸው አኳኋን ሩካ እና
ኤፍሬም ተከታትለው ወደ ሳሎን ብቅ አሉ፡፡ ኤፍሬም በ'አይዞህ!'
ባይነት ትከሻዬን ጨበጥ አድርጎ ማርቲን ያረፈችበት ሆቴል ሊያደርሳት ተከትሏት ወደ ውጪ ወጣ፡፡
"ያልጠበቅከው ነገር አልነበረም የተፈጠረው:: ለእርሷም ዱብ-ዕዳ ነው የሆነባት፡፡ ጊዜ ስጣትና የሚሆነውን እንጠብቅ፡፡" አለችኝ ሩካ የከፋኝ ሲመስላት ሁሌ እንደምታደርገው በሁለቱ
እጆቿ ጉልበቴን ተደግፋ እግሬ ስር ቁጢጥ ብላ የተሰማኝን ለመረዳት ዓይን ዓይኔን እያየች፡፡ ላስረዳት ከምፍጨረጨረው በላይ ቀድማ የእኔን ህመም በራሴው
እንደምትታመምልኝ ስለማውቅ መልስ ልሰጣት አልደከምኩም።ፀጉሮቿ መካከል ጣቶቼን ሰድጄ የራስ ቅሏን ቆዳ እየነካካሁ
ደቂቃዎች አለፉ። ጉልበቴ ላይ ግንባሯን ደፍታ ሳላወራ ሰማችኝ፡፡ ሳላስረዳት ገባኋት፡፡ እንባዬ በዓይኔ ባይገነፍልም
ማልቀሴን አየችው። ሩካ ናታ! ግነት የለውም፡፡ እንደውም አልገለፅኳትም። ሩካ የሌላ ሰው ስሜት የራሱን ያህል በተጠጋጋ ቅርበት የሚሰማት ለነፍስ የቀረበች ፍጡር ናት!
በረከትን ሆኜ በምተውነው ራሴን ካወቅኩበት ጊዜ ጀምሮ እስከአሁን ባለ መደበኛ የየዕለት የኑሮ ተውኔት ውስጥ በጉልህ የደመቁ ሶስት ሴቶች የሀሳቤን አቅጣጫ ፈቃዴን እያዛቡ ያንዥዋዥውታል። እማዬ ሩካ እና ማርቲ።
እማዬ ያው እማዬ ናት።ለእኔ ለልጇ ብላ አስር የዘመኗ ቁጥር በእስር ቤት እየተቆረጠመባት ያለች እናቴ! በየቱም ድርጊቴ የከፈለችልኝን መስዋዕትነት ጥቂት ሽራፊ እንኳን ላካክስላት
እንደማልችል ሳስብ ከንቱነቴ ይገንብኛል፡፡ ማድረግ የምችለው ብቸኛ ነገር የእማዬ ፊት ላይ ለሚታይ የፈገግታ ፍንጣቂ
ምክንያት ለመሆን ቢያቅተኝ እንኳን ቢያንስ በጉንጫ ላይ ለሚወርድ አንዲት የእንባ ዘለላዋ ምክንያት ላለመሆን
መፍጨርጨር ነው።
ረቂቅ ታናሽ እህቴ ናት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፍቅረኛዋ በሚጠራት ቁልምጫ ሩካ እያልኩ ነው የምጠራት:: ብቸኛዋ
እህቴ! ስለሩካ ማብራራት ቀላልም ከባድም የሚሆንበት ምክንያት ብዙ ነው። ልክ ለመሰላት ነገር የማታመነታ ቆራጥ መሆኗን ባመንኩ ልቤ በየደማቅ አበባው ተዟዙራ መዓዛውን ቀስማ
የማትረካ ቀልቃላ ቀለማም ቢራቢሮ ትመስለኛለች፡፡ ብዙም ሳይቆይ ውስብስብ የሆነች ጭምት ትሆንብኛለች
በጭምትነቷ ሳልረጋ ስስና ተሰባሪ ትሆንብኛለች።ሩካ የህይወቴም የመፅሐፌም ዋና ገፀ ባህሪ ናት! መፅሐፍ መፃፌን ነገርኳችሁ? ከወራት በፊት አንድ መፅሐፍ ፅፌ ለንባብ
አብቅቻለሁ። ለስነ ጥበባዊ ውበቱ መጠነኛ ቅብ ከመጨመሬ ውጪ ሙሉ ለሙሉ የሩካ ታሪክ ነው:: ርዕሱ "ምርጫ አልባምርጫ!!! የተሰኘ ነው:: የመጨረሻዋ ሴት ማርቲ የተከሰተችው በዚህ መፅሐፍ ሰበብ ነው፡፡
ስለእነርሱ ማንነት ከምፅፍላችሁ ቀድሞ የተውኔቱን ያልሰነበተ ትዕይንት የማርቲ
ልብ የተሰበረበትን ገፅ እንደምትፈልጉ አውቃለሁ። ምን አስቸኮላችሁ? ልክ ነበርክ ወይም ተሳስተሃል ብሎ ለመፍረድ ምን ከዳኝነታችሁ በፊት እኔን ማወቁ ለፍርዱ አይረዳችሁም ብላችሁ
ነው? ይመስለኛል። ለነገሩ እኔም ብሆን ያደረግኩትን ያደረገው ሌላ ሰው ቢሆን የፍርድ ወንበሬ ላይ ለመሰየም እጣደፍ ነበር::የፍርድ አንቀፅን በመዶሻ ድለቃ አጅቦ ማንበብ ከባድ የሚሆነው
የተፈራጅ እግርን ተውሶ በቆመበት ማጥ መቆም ሲቻል ነው።ነገር ግን የእኔ የልክነት ጥግ' ነው ብዬ ያመንኩበት የግሌ እውነት ለእናንተም የልክነት ጣሪያ መሆን አለበት ብዬ እናንተን በተሳሳች ሂሳብ መዳኘት ከቂልነቴ ባሻግር የጠበበ
የሀሳብ ምህዳሬን ገልቦ አደባባይ ማስጣት ይመስለኛል።
እኔ የቆምኩበትን ጫማስ “ስህተት ብላችሁ ለመዳኘት ለመሆኑ
የእናንተ ልክ በየትኛው ሚዛንና በማን ዳኝነት ተሰፍሮ ነው ልክነቱ የተረጋገጠው?
አይደለም ለሌላ ሰው ለራሳችን እንኳን “ልክ ነው ያልነውን እምነታችንን ጊዜ አላንጓለለብንም? የዛሬ ምናምን ዓመት በፊት የልክነት ጫፍ የመሰለን በጠበበም ወይ በሰፋ አስተሳሰባችን ሳቢያ ዛሬ አልተቀየረም? እንዴት ነው በጊዜ፣ በመረዳታችን መጠን፣ በቦታና በበሽቃጣ የህይወት ክስተቶች እንደማይቀየር
ዋስትና በሌለን ልክነት ሌላውን በስህተት የምንዳኘው?
የኔ ስህተት ውስጥ ተዘፍቆ ላገኘሁት ሰው ከመዳኘቴ በፊት የዝፍቀቱን ሰበብ መረዳቱ ይቀል አልነበር? ምክንያቱ ደግሞ
የእኔ ልክ የልክ ጣሪያ ሊሆን አይችልም፡፡ የሆነ ቦታ.... የሆነ ጊዜ.....ለሆነ ሰው ስህተቱ ሊሆን ይችላል፡፡
እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ያንተ ግራ ነው። ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው። ቀኝ ይሄ ነው ወይም ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ፡፡
እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል። እንደ እኔ አቋቋም ደግሞ የእኔ እውነት ይሆናል። ባንተ እውነት ለማመን ያንተን
ጫማ መዋስ አለብኝ፡፡ የቆምኩበት ሆኜ ለስህተትህ ሒሳብ እየሰራሁ ስዳኝህ እቀሽማለሁ፡፡
እግሬን አውሻችሁ የዳከርኩበትን ስትዳክሩት አሁን ካለሁበት
የጊዜ ካብ ወራትን ወደኋላ ንጄ አፍ ውስጥ እየጣፈጠ የሚሟሟ
ግን እንዳያልቅ እንደሚሳሱለት፤ ያልቃል ብለው ማጣጣሙን እንዳይተውት ጥፍጥናው እንደሚያባብል ጣፋጭ ከረሜላ የሚጣፍጠውን የኑሮ ተውኔቴን ገፅ ላስነብባችሁ። እዚህ የጊዜ
ካብ ላይ ለማማረር ምክንያቶቼ የሚዘቅጡብኝ፤ የመጀመሪያ መፅሐፌን ለንባብ ያበቃሁ፤ የከበቡኝ ሰዎች የተደላደለ ቀን የሚያልፉበት፤ እማዬ በደስታ ያነባችበት እና የመፅሐፌን
አንባቢ አስተያየት በኢሜሌ እያነበብኩ ተስፋዬን የምስቅል በረከት ነበርኩ። በኤፍሬም ማተሚያ ቤት አማካኝነት
ማስታወቂያ ተሰርቶለት ስለነበር መፅሐፌ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደራሽነቱ ሰፊ ሆኖ ነበር፡፡ በመፅሐፌ ቀደምት ገፆች አንዱ ገፅ ላይ በተፃፈው የኢሜል አድራሻዬ የሚደርሱኝን የአንባቢያን
አስተያየት ማንበብ የሚደፍነው የስሜት ሽንቁር አለው፡፡
አንዳንዶቹ እንደዚህኛው ቦታ ላይ ታሪኩ እንደዚህ ባይሆን:መጨረሻው እንደዚህ ቢሆን የሚሉ ናቸው:: እንዲህና እንዲያ
ቢሆን የተባሉትን መልዕክቶች ስጨምቃቸው እኔ ከፃፍኩት በአንድ መስመር የማይገናኝ ሌላ ታሪክ እንደሚሆን እያሰብኩ ፈገግ እላለሁ። አብዛኛዎቻችን ስናነብ ደራሲው
ያሰበውን ሳይሆን እኛ የምናስበውን ቢፅፍልን እንፈልጋለን፡፡በተዘዋዋሪ የመፅሃፉ ደራሲ ራሳችን መሆን ነው የምንሻው::ለፃፈልኝ በሙሉ በምስጋና ብመልስም ጥያቄዎቹን ከራሴ ህይወት እውነታ ጋር እያዛመድኩ ለራሴ እመልሳለሁ::
'የምንትስ ገፀ ባህሪ ታሪክ መጨረሻው አልታወቀም:: ሲሉኝ
በእውነተኛው ዓለም መጨረሻቸው ያልተቋጨ ወይ ያልታወቀ
ታሪክ ባለቤቶች ብዙ አይደሉ? እላለሁ አባቴና ሰራተኛችን ሙሉ የነበራቸው ድብቅ ፍቅር መጨረሻው ምን
ነበር? እማዬ ወደ ስራ ሩካ

👍4❤1
ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ጠብቆ አባዬ ወደ ቤት ይመለሳል፡፡ የማውቅ አይመስላቸውም፤ የምሰማ አይመስላቸውም ፤ ባውቅም ብሰማም ለእነርሱ ፍጡር አይደለሁም።አባዬ ቀን ሙሉን ሲላት የሰማሁትን የፍቅር ልምምጥ በሙሉ ለእማ ዬ ማታ ሲደግመው ስሰማው ለየትኛዋ የተናገረው እውነት መሆኑን ማገናዘብ ያቅተኛል፡፡ከእኔ በቀር ስለእነርሱ ታሪክ ማን ያውቃል? ፍቅራቸው መቋጫ ሳይኖረው በማይታወቅ ምክንያት ሙሉ ከቤታችን ጠፋች፡፡ አባዬ ደግሞ ራሱን አጠፋ፡፡ የሙሉ መጥፋት የፍቅራቸው መጨረሻ ነበር? ወይስ የአባዬ ሞት? የተፈጠረው ሁሉ የግንኙነታቸው መጨረሻ እንጂ የፍቅራቸው መጨረሻ ነበር?
“እንትና የተባለው ገፀባህሪ ለምን እንደዛ
እንዳደረገ አልተጠቀሰም።የሚሉትን ሳነብ የሁሉም የ'ለምን?' ጥያቄዎች መልስ አላቸው እንዴ? እያልኩ አስባለሁ፡፡ ሁሉም ጥያቄ መልሱ የታወቀ አይደለም። ወይ መልስ የለውም አለዚያም
መልሱን የምናውቅበት የእውቀት ደረጃ ላይ አልደረስንም።እስኪ መልሱልኝ እኔ በተወለድኩበት ቀን ከተወለዱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት መካከል እኔ መናገር የማልችል ዲዳ እና መራመድ የማይችል ሽባ ለምን ሆንኩ? መልስ አትስጡኝም ብትሰጡኝም ማድረግ በማልችላቸው ነገሮች ምክንያት እኔ
ለማልፈው መከራ አጥጋቢ መልሶች ሊሆኑ አይችሉም።የገዛ አባቴ የዘሩን ክፋይ ሊገድለኝ መሞከሩ የትኛው ምክንያት መልስ ይሆነዋል? በእኔ ምክንያት ሚስቱ በየፀበሉ እና በየጠንቋይ ቤት መክረሟ አሳዝኖት? በህይወት ብቆይም እንደ እህቴ ባለመናገሬ እና ባለመራመዴ ሸክሙ እንደምሆን ተሰምቶት? (በነገራችሁ ላይ ይሄን ታሪክ ከእኔ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ በትራስ አፍኖኝ እስትንፋሴ ልትወጣ ከስጋዬ ስትታገል የእማዬን ድምፅ ሲሰማ ነበር የተወኝ። ከዛን ቀን በኋላ አባዬ እስኪሞት ድረስ እፈራው
እንደነበር ማንም አያውቅም። ራሱን ያጠፋ ቀን እማዬ እኔን እንዲጠብቅላት አሳስባው ስትወጣ እኔ በፍርሃት ስጠብቀው እንደነበር አብራኝ የነበረችው ሩካ የምትረዳበት እድሜ ላይ
ስላልነበረች ከአባቴ ጋር ብቻዬን እንዳትተወኝ መጨነቄ አልገባትም ነበር፡፡ ከአባዬ ጋር በሶፋው ትራስ ከመጫወታቸው ከብዶ ትራሱ ነበር ፍርሃቴን ያናረው:: በደረቴ እየተሳብኩ
የምደበቅበት ፍለጋ ወደ ጓዳ መሄዴን ያወቁት የተለኮሰው ሲሊንደር ተገልብጦ አቃጥሎኝ ስጮህ ነበር፡፡) ለምን ራሱን
አጠፋ? ሊገድለኝ ስላሰበ ተፀፅቶ? ወይስ አባቷን በስጋ ልቡ ብቻ የምታውቀው ሩካ እንደምታምነው አባትነቱን ባለመወጣቱ
ተፀፅቶ? አያችሁ ሁሉም 'ለምን?' መልስ የለውም። ቢኖረውም አልደረስንበትም፡፡
እዚህኛው ቦታ ላይ ታሪኩ አልተሟላም:: የሚሉትን ሳነብ የተሟላ ታሪክ ባለቤት የሆነ ግለሰብ ለማስታወስ እሞክራለሁ፡፡
ትምህርት ቤት እየሄዱ የተሟላ አፈጣጠር ካላቸው እኩዮቼጋ መማር የሚፈጥርብኝን ጎዶሎነት ስሜት እና የእናቴን መታሰር ስሰማ ትቼው በመጣሁት ትምህርት ሳቢያ መሆን የምፈልገውን ባለመሆኔ የተፈጠረውን ትልቅ ክፍተት የትኛው የታሪክ ምርጊያ
ሊሞላው እንደሚችል እስቲ ንገሩኝ?
መናገር ካለመቻል ፤መራመድ ካለመቻል፤ ራሴን ችዬ ገላዬን ለመታጠብ ባለመቻሌ
በጉርምስናዬ ከማፈሬ፤ራሴን በመንከባከብ ለመቻል ከመፍጨርጨሬ ፤
ጉድለቶቼን ጥሼ ሙሉ ሰው መሆኔን
ለማስመስከር ከመዳከር ፤ ......... ከዚህ ሁሉ ልቆ ታናሽ እህቴ እኔን ለማስተማር እና ለማኖር ስትል ወጣትነቷን በፍቅር ታቅፋ ልትኖር ሲገባ ከተለያዩ_ሀብታም ወንዶች ጋር እየወጣች የምታመጣውን ገንዘብ ዊልቸር ላይ ተቀምጦ ማመንዠክ እና ከመመልከት የዘለለ ምንም ማድረግ አለመቻል የሚፈጥረውን የማንነት ሽንቁር የትኛው የታሪክ ልስን ሙሉ ያደርገዋል?
“እንትና የተባለችው ገፀ-ባህሪ እንዲያና እንዲህ ባታደርግ ጥሩ ነበር:: የሚሉትን ሳነብ ባናደርጋቸው ወይ ብናደርጋቸው ጥሩ የነበሩ የትዬለሌ ክስተቶች ግን ተቃራኒውን የሆኑበት አጋጣሚ
ትንሽ አልነበረም::እያልኩ አስባለሁ፡፡ እማዬ ራሷን ምስቅልቅል ውስጥ ነክራ ለህክምና አሜሪካን ሀገር ያለች እህቷ ጋር
ስትልከኝ ታክሜ ድኜ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር። እማዬ ለእኔ ህክምና ከመስሪያ ቦታዋ በድብቅ ገንዘብ ባትወስድ ጥሩ ነበር፡፡ መውሰዷ ባይታወቅም የበዛ ጥሩ ነበር። በዚሁ ጦስ ተፈርዶባት ስትታሰር በስሜታዊነት ተገፍቼ የጀመርኩትን ትምህርት አቁሜ ከአሜሪካ ባልመለስ ጥሩ ነበር። መጥቼ ስራ ለመስራት
የጠየቅኳቸው ቦታዎች ሁሉ በዊልቸሬና ባለመናገሬ ብቻ ማሰብም እንደማልችል እየቆጠሩ ስራ ባይከለክሉኝም እጅግ
በጣም ጥሩ ነበር። ግን ጥሩ መሆኑ ብቻ ነገሩን እውን አያደርገውም።የክስተቱ ጥሩ መሆን ለተፈፃሚነቱ ዋስትና
አይሆንም።
“እንትና የተባለችው ገፀባህሪ የእጇን ያለማግኘቷ ልክ አይደለም።ኸረ? ማን የእጁን እንዳገኘው? ክፉዎች የእጃቸውን
ሳይሆን የጥሮዎቹን እጅ ዋጋ እየዛቁ ያለጉድለት በሞላ ጎተራቸው ጠግበው ውለው ሲያድሩ ደጋጎች የዘሩትን የደግነት ሰብል በእንክርዳድ ተወሮ በጠኔ በሚያልቁበት እውነት ውስጥ እየዳከርን አይደለም?......
💫ይቀጥላል💫
Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

👍1🥰1
#መወድስ
ፊትሽ እንደ ምሥራቅ፣ ብርሃን ያመርታል
ፈገግታሽ ዋስ ሆኖ፣ እስረኛ ያስፈታል
ውይ መዓዛሽ ሲያምር!
የሎሚ የንጆሪ፣ የኮክ ሽታ ድምር።
ከየዛፉ ቅጠል
ንፋስ በክንዶቹ፣ ከሚሰበስበው
ከሳሩ ከሰርዶው፣ መሬት ከሚሳበው
በደብር አፀድ ላይ፣ ከሰፈነው ለምለም
ከየኔክታሩ ጣም፣ ከያበባው ቀለም
አውጣጥቶ ማን ሰጠሽ?
እንዲህ ምን አስጌጠሽ
እንዲህ ምን አሰላሽ?
መች ተጣድሽ? መች ፈላሽ?
ለዛሽ በፊትሽ ላይ መች ተጠነሰሰ
ውበትሽ ምንገድ ላይ፣ ገንፍሎ ፈሰሰ
ገላየ ጭንቅ አይችል፣ ዐይንሽ ስውር መቀስ
ኧረ ቀስ! ኧረ ቀስ!
ከደም ከሥጋ እንጂ፣ አልተሰራም ካለት
በውበትሽ አምላክ፣ ለልቤ እዘኝለት!
ፊትሽ እንደ ምሥራቅ፣ ብርሃን ያመርታል
ፈገግታሽ ዋስ ሆኖ፣ እስረኛ ያስፈታል
ውይ መዓዛሽ ሲያምር!
የሎሚ የንጆሪ፣ የኮክ ሽታ ድምር።
ከየዛፉ ቅጠል
ንፋስ በክንዶቹ፣ ከሚሰበስበው
ከሳሩ ከሰርዶው፣ መሬት ከሚሳበው
በደብር አፀድ ላይ፣ ከሰፈነው ለምለም
ከየኔክታሩ ጣም፣ ከያበባው ቀለም
አውጣጥቶ ማን ሰጠሽ?
እንዲህ ምን አስጌጠሽ
እንዲህ ምን አሰላሽ?
መች ተጣድሽ? መች ፈላሽ?
ለዛሽ በፊትሽ ላይ መች ተጠነሰሰ
ውበትሽ ምንገድ ላይ፣ ገንፍሎ ፈሰሰ
ገላየ ጭንቅ አይችል፣ ዐይንሽ ስውር መቀስ
ኧረ ቀስ! ኧረ ቀስ!
ከደም ከሥጋ እንጂ፣ አልተሰራም ካለት
በውበትሽ አምላክ፣ ለልቤ እዘኝለት!
#ምንሽን
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፣ በወጣሁበት እንዳልቀር
አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፣ ግና ምንድር ነው ማፍቀር?
እንዳስመሳይ አዝማሪ፣ ካልሸነገልኩሽ በቀር
ከተወለድሁ እስተዛሬ፣ ከጣትሽ መች ጎርሼ
ወተትሽን መች ቀምሼ
ወለላሽን መች ልሼ?
ሲርበኝ
ጠኔ በቀኝ በግራ፣ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ
የት ነበር የንጀራሽ ሌማት?
ሾላ ስለቅም ተሻምቼ፣ ከሽመላ ከማማት
ኑሮየ ሁዳዴ ጦም፣ ፋሲካ አልባ ሕማማት
እና ከድሎት አገር፣ የሲሳይ ዶፍ ከሚያወርደው
ምን ገፍቶኝ ነው በሞቴ? ወዳንቺ ምሰደደው
ምን ነክቶኝ ነው? ምንሽን ነው የምወደው?
እኔና ብጤዎቼ፣ እኛ ቅብዝብዝ ልጆችሽ
መስኮት በሩ ተዘግቶብን፣ ተበትነን በደጆችሽ
ይሄው ሶስት ሺ ዘመን፣ ወደ ሰማይ አንጋጠን
በንዝርት እግር ተንበርክከን፣ በቀይ ዕንባ ስንማጠን
የለት እንጀራችንን ነፍጎ፣ የለት ገጀራችንን ሰጠን።
አሁንም ለመከራሽ፣ ማን አለና የሚገደው
እሪታሽ እንደዘፈን፣ ያለም ጆሮ ለመደው
እና ምንሽ ነው ሚስበኝ? ምንሽን ነው የምወደው?
ዛሬም ሆነ ያለፈው
በላባ ብእርም ይሁን፣ በኪቦርድሽ የተጻፈው
ታሪክሽን ሳነበው፣ ደምና አመድ ነው የሞላው
መች ተነቅሎ ከወለልሽ፣ የሾህ ጉንጉን አሜኬላው
መች ተጥሶ ያውቃልና፣ የጭቆናሽ ዘመን ኬላው
ሥልጣን ፈልሶ ሲሸጋገር፣ ካንዱ ጭራቅ ወደሌላው።😔🇪🇹
የሰው አገር ሙጥኝ ብየ፣ በወጣሁበት እንዳልቀር
አገሬ ፍቅርሽ ሳበኝ፣ ግና ምንድር ነው ማፍቀር?
እንዳስመሳይ አዝማሪ፣ ካልሸነገልኩሽ በቀር
ከተወለድሁ እስተዛሬ፣ ከጣትሽ መች ጎርሼ
ወተትሽን መች ቀምሼ
ወለላሽን መች ልሼ?
ሲርበኝ
ጠኔ በቀኝ በግራ፣ እንደ ጭፍራ ሲከበኝ
የት ነበር የንጀራሽ ሌማት?
ሾላ ስለቅም ተሻምቼ፣ ከሽመላ ከማማት
ኑሮየ ሁዳዴ ጦም፣ ፋሲካ አልባ ሕማማት
እና ከድሎት አገር፣ የሲሳይ ዶፍ ከሚያወርደው
ምን ገፍቶኝ ነው በሞቴ? ወዳንቺ ምሰደደው
ምን ነክቶኝ ነው? ምንሽን ነው የምወደው?
እኔና ብጤዎቼ፣ እኛ ቅብዝብዝ ልጆችሽ
መስኮት በሩ ተዘግቶብን፣ ተበትነን በደጆችሽ
ይሄው ሶስት ሺ ዘመን፣ ወደ ሰማይ አንጋጠን
በንዝርት እግር ተንበርክከን፣ በቀይ ዕንባ ስንማጠን
የለት እንጀራችንን ነፍጎ፣ የለት ገጀራችንን ሰጠን።
አሁንም ለመከራሽ፣ ማን አለና የሚገደው
እሪታሽ እንደዘፈን፣ ያለም ጆሮ ለመደው
እና ምንሽ ነው ሚስበኝ? ምንሽን ነው የምወደው?
ዛሬም ሆነ ያለፈው
በላባ ብእርም ይሁን፣ በኪቦርድሽ የተጻፈው
ታሪክሽን ሳነበው፣ ደምና አመድ ነው የሞላው
መች ተነቅሎ ከወለልሽ፣ የሾህ ጉንጉን አሜኬላው
መች ተጥሶ ያውቃልና፣ የጭቆናሽ ዘመን ኬላው
ሥልጣን ፈልሶ ሲሸጋገር፣ ካንዱ ጭራቅ ወደሌላው።😔🇪🇹
#ዘመም_ይላል_እንጂ
እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰዉ ጭካኔ፣ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ፣ ታምር ነው መኖሬ።
የበጎ ሰው ሀሳብ፣ ሲካድ ዕለት በለት
ጉድጓድ ተምሶለት
ስብእና ሲቀበር፣
በዚህ ምድር መኖር፣ አያስመኝም ነበር።
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፣ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፣ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፣ አያስመኝም ነበር።
አዎ
ለጊዜውም ቢሆን፣ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፣ ወደ ፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ፣ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፣ ሚስቱን
ያስረግዛል።
ይቅርታና ምሕረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፣ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ፣ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ፣ ተገርስሶ አይወድቅም።
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰዉ ጭካኔ፣ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ፣ ታምር ነው መኖሬ።
የበጎ ሰው ሀሳብ፣ ሲካድ ዕለት በለት
ጉድጓድ ተምሶለት
ስብእና ሲቀበር፣
በዚህ ምድር መኖር፣ አያስመኝም ነበር።
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፣ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፣ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር፣ አያስመኝም ነበር።
አዎ
ለጊዜውም ቢሆን፣ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፣ ወደ ፊት ይጓዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ፣ ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፣ ሚስቱን
ያስረግዛል።
ይቅርታና ምሕረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው፣ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ፣ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ፣ ተገርስሶ አይወድቅም።
🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ
፡
፡
#ክፍል_አስር
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
...የእውነታው ኑሯችን ለፍፁምነት የተጠጋጋ እንኳን አይደለም፡፡በመፅሐፌ ውስጥ ፍፅምናን ለምን ይጠብቃሉ? መፅሐፌ የሀሳቤና የኑራችን ግልባጭ እንጂ እነርሱ የሚመኙት የ'ቢሆን ዓለም ሊሆን እንዴት ይችል ነበር?
በአንዱ ቀን እንደተለመደው ኢሜሌን ስከፍት ረዥም ሀተታ ያለው መልዕክት ደረሰኝ፡፡ ማርቲ ነበረች፡፡ ስለመፅሃፉ ይዘት
ተያያዥ ሀሳቦች ከተነተነች በኋላ ስለተሰማት ስሜት የፃፈችው ጭብጥ መልዕክቱ እንዲህ የሚል ነበር።
ታሪኬን ነግሬህ የፃፍከው እስኪመስለኝ ያለፍኩትን መንገድ እና የተሰማኝን ስሜት ነው የፃፍከው:: ወንድ ሆነህ እንዲህ የሴትን ጥልቅ ስሜት መፃፍህ እስገርሞኛል፡፡ መፅሐፍህን እያነበብኩኝ
የምታውቀኝ የምታውቀኝ አይነት ነበር የሚሰማኝ። በቅርቡ ከሀገር ቤት የመጣች ጓደኛዬ ገዝታልኝ ከመጣቻቸው አዳዲስ መፅሐፍት ውስጥ አንዱ ምርጫ አልባ ምርጫ ነበር፡፡ ይሄን መልዕክት ስፅፍልህ መፅሐፍህን ለሶስተኛ ጊዜ አንብቤዋለሁ::"የሚል ነበር። ተመሳሳይ አስተያየት አንብቤ ባውቅም አንድም ይሄኛው ጥልቀት ያለው ትንተና የተካተተበት መሆኑ ሁለትም ማብራራት በማልችለው ምክንያት ከሌሎቹ ተመሳሳይ መልስ አልመለስኩም። ይሄ መልዕክት ከፊደላቱና ከሀሳቡ በተጨማሪ መንፈስ ነበረው:: አውስትራሊያ ሆና የፃፈችበትን ስሜት አዲስ መንፈስ አጋብቶብኛል።
"ውድ ማርታ ስለመፅሐፌ ለፃፍሻቸው ውብ ሙገሳዎች ከልቤ አመሰግናለሁ። በፃፍሽልኝ መልዕክት ስለመፅሐፍት ያለሽን ሰፊ ግንዛቤ ማወቅ በመቻሌ ምክንያት ያንቺን አድናቆት ማግኘት
ከፍ ያለ ደስታ አለው። ያንቺ የኑሮ መንገድ ከየትኛው የመፅሐፉ ታሪክ ጋር እንደተመሳሰለ ባላውቅም ከፃፍኩት ታሪክ ውስጥ በአንዱ ተመሳሳይ ጉዳት እንኳን ተጎድተሽ ከነበር ላለፍሽው
ሀዘን አዝናለሁ:: አንዳንዴ የተሰማሽን መተንፈስ ከፈለግሽ እና ይረዳኛል ብለሽ ካሰብሽ ፃፊልኝ፡፡ በድጋሚ አመሰግናለሁ::" ብዬ መለስኩላት:: የእኔና የማርቲ እውቂያ የጀመረው በእነዚህ
የመልዕክት ልውውጦች ነበር፡፡ በተደጋጋሚ ከተፃፃፍን በኋላ የብዕር ጓደኛሞች ለመሆን ተስማምተን በየቀኑ መፃፃፍ ቀጠልን፡፡ በቀን ሁለቴ... ሶስቴ... አራቴ አምስቴ...መቁጠር አቆምን፡፡ ያወቅኳት መሰለኝ፡፡ ያወቀችኝ መሰላት።በየሰዓቱ ስለምታደርገው ጥቃቅን ነገር ሳይቀር ከፎቶዎቿ ጋር
እያያያዘች ትፅፍልኛለች:: ከሁለት
የዘለለ ልኬላት ባላውቅም ፤ አዋዋሌን በሙሉ ባልፅፍላትም ለፃፈችልኝ ቁጥር
ያህል ጊዜ መልስ እፅፍላታለሁ፡፡ በጠዋት ዓይኖቼን ስገልጥ ማየት የምመኘው የእርሷን መልዕክት ሆነ። በሆነ ምክንያት ሳትፅፍልኝ ካረፈደች ስጋቴ እያንዳንዷን ደቂቃ የመላ ምት ቁልል እየደረመሰ ሊያሳብደኝ ይደርሳል፡፡ ምክንያቱም ለማርቲ ምንም ጥቅምም ሆነ ዕውቀት የማይደምርላት ዝባዝንኬ ሳይቀር ስፅፍላት በዊልቸር እንደምሄድ እና መናገር እንደማልችል ፅፌላት አላውቅም:: አታውቅም! ማርቲ ስልክ ደውላ ድምፄን መስማት ሳትፈልግ ቀርታ ወይም ምስሌን እያየች ልታወራኝ
ሳትጨቀጭቀኝ እረስታ አልነበረም አጋጣሚው ያልተፈጠረው፡፡ለቀናት እስከመኮራረፍ ያደረሰን ምክንያት ሆኖ ያውቃል፡፡በደሌን የምትቆልልብኝ የምሰጣትን ቀሽም ምክንያት ሁሉ
ስታምነኝ ነው። በእርግጥ በሆነኛው ቀን በስካይፒ ካላየሁህ ብላ ከልቧ ስላመረረች የሚከሰተውን ለመቀበል
ራሴን አሳምኜ ኮምፒተሬ ፊት ተቀምጬላትም ነበር፡፡ በሚቆራረጠው ኔትወርክ ምክንያት ከሰከንዶች የዘለለ መተያየት አልቻልንምና በቅን ልቧ ኔትወርኩ ብልሹ ስለነበር ድምፄን መስማት አለመቻሏን እንጂ
ዲዳነቴን አልተጠራጠረችም።
ለእንደኔ ዓይነት ሰው ይሄን እድል ማን ይሰጠው ነበር? ማርቲስ ብትሆን እውነቱን ብታውቅ የሰጠችኝን ፍቅርና ያሳየችኝን ህልም መሰል ቀን ትሰጠኝ ነበር? ምንም መጨረሻው ከህልም
መንቃት ዓይነት ቢሆንም እነዚህን ቃላት ማጣጣም የተለየ ነገር ነበረው፡፡ እና ለምን ብዬ እውነቱን ነግሪያት የደስታ ቀኔን
ላሳጥር? እንኳን ለመፈቀር መብቃት እንደሙሉ ሰው መታየት የሚናፍቀኝ ሰው ነኝ፡፡ በየመንገዱ የሚያየኝ ሰው አንዳች አሳዛኝ ገር እንደተመለከተ ከንፈሩን ሲመጥልኝ ስበግን የኖርኳቸው ዓመታት ጥቂት አይደሉምና በፍቅር መቆለጳጰስ ይቅርብኝ ማለት አልችልም ነበር፡፡ አንዳንዶች አፍ አውጥተው ይሄን
የመሰለ ልጅ... “እግዜር ለራሱ የሰራውን ያሳምራል:: የመሳሰሉ አሳማሚ አባባሎች ሲሉ እየሰማሁ የገፋሁት ቀን ጥቂት
አይደለምና ከማርቲ ፍቅር እውነቱን ነግሪያት የሚመጣውን መቀበል መምረጥ አይቻለኝም።
ቤክዬ ልይህ ስልህ ስትከለክለኝ እኮ አስቀያሚ ነህ ብዬ ደምድሜ ነበር፡፡ የላክልኝን ፎቶዎች እንኳን መጠራጠር ጀምሬ መፅሐፍህ ጀርባ ላይ ካለው ጉርድ ፎቶህ ጋር ስንቴ እንዳመሳሰልኳቸው
ባየህ!" ብላ ፅፋልኝ ነበር በዚያው ዕለት:: የፃፍኩላትን በሙሉ ባላምንበትም ደግማ እንተያይ ወይም ልደውልልህ እያለች
እንዳትጨቃጨቀኝ ፍቅር ከሚታየው ሳይሆን ከልብ መዋሃድ ጋር ብቻ መሆኑን በውብ ቃላትና ገለፃ አንዳንዴም በሚያሳምን ምሳሌ እያጣቀስኩ እፅፍለታለሁ። በእርግጠኝነት ያላመነችኝ
እንኳን ቢሆን ለትክክለኛው ምክንያት የቀረበ ግምት
አይኖራትም ነበር፡፡ ጉረኛ፣ ኩራተኛ፣ ቀብራራ፣ በራሱ የሚተማመን፣ የተረጋጋ...... ልታየኝና ልትሰማኝ አለመፈለጌን የምታመኃኝባቸው ፀባዮቼ ናቸው።
የምትዋሸው ወይ የምትደብቀው ታሪክህ የምታፍርበት ነው::ትላለች የኔዋ ረቂቅ:: ምናልባት ደግሞ የምትወደውን ነገር
የሚያሳጣህ ሊሆንም ይችላል። በእርግጥ እኔ የደበቅኳት ታሪኬን
ሳይሆን ተፈጥሮዬን ነው። እኔ በረከት ነኝ፡፡ መራመድም መናገርም የማልችል በረከት ለመሆን ያበረከትኩት አንዳችም
ጠጠር የለም:: ከአባዬ እና ከእማዬ ለመወለድ የሩካ ወንድም ለመሆን የኔ ፈቃድና ምኞት አይደለም:: የሆንኩትን ሆኜ ለመፈጠሬ የእኔ አስተዋፅኦ
ባዶ ነበር። ግንሳ? ፈቅጄ ባልመረጥኩት አፈጣጠሬ ጉድለት ሳቢያ ቀኖቼ ጎዶሎ ሆነውብኝ ነው ለመደበቅ የተገደድኩት።
ከአሁን ወደ ኋላ ንጄ ካስነበብኳችሁ ጣፋጭ ገፅ ወደ ፊት የጊዜን ካብ ስደረድር የኑሮን ጥፍጥና ለማጎምዘዝ ጊዜው የንስር ክንፍ ተውሶ ይንደረደር ነበር፡፡ እነዚህ ገዖች ጉራማይሌ ስሜት
የታጨቀባቸው ነበሩ።
"አንተ? ማታ እስኪሪብቶህን አገንፍለህ ነው እንዴ ያደርከው?"
"አንቺ ባለጌ ታላቅሽ እኮ ነኝ፡፡ አፍሽን አትክፈቺ!" እላታለሁ በእጆቼ ምልክት የእውነት እያፈርኳት፡፡ ክትክት ብላ በማፈሬ ትስቅብኛለች፡፡ ያሳፈረኝ የእርሷ ንግግር ብቻ አይደለም። ያለችው
እውነት መሆኑም ተደምሮ እንጂ፡፡
ከእንቅልፌ ከባነንኩ በኋላ ለማስታወስ ስሞክር ያልተከሰተልኝ መልክ ያላት ሴት ፈዛዛ የወይን ጠጅ ቀለም ያለው ስስ ቀሚስ ለብሳ የአልጋዬ ጠርዝ ላይ ተቀምጣ ስታጫውተኝ ነው ያደረችው:: ቁልጭ ብሎ ቅርፀ ምስሏ ባይታወሰኝም ቆንጆ እንደሆነች ይታሰበኛል።....

👍5