አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
572 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
አንብቧቸዋል፡፡ እርሱ ነው የነገረኝ፡፡" አልኩት ስለእርሷ አውርቶ
አለመድከሙ እየደነቀኝ፡፡

'ስለእርሷ የሚያወራ ሰው ሳገኝ ያገኘኋት ያህል ነው የምደሰተው።"አለኝ ቀዝቀዝ ብሎ።

ስለእርሷ ብዙ ላወራልህ ባልችልም እስካልደከመህ ልሰማህ ግን እችላለው ጥሩ ጓደኛ መሆን የምንችል ይመስለኛል።" አልኩት።

እሱን እንኳን እጠራጠራለሁ" መለሰልኝ፡፡

አትቸኩል፡፡ በሂደት የምናየው ይሆናል" ስለው ተቆጣ፡፡

ከዚህ በኋላ ከምንገናኝ መፅሀፉን ብመልስልሽ ይቀለኛል::”

አሁን መፅሀፉን አልያዝከውም አይደል?”

በፈለግሽው ቀን ግን አመጣልሻለሁ።”

"ስለዚህ ቢያንስ አንድ ጊዜ ወይ ቢሮህ እመጣለው ወይ ቁርስ እንበላለን".....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ትዝታን_ባጎበር

በንጹሕ ክፍል ውስጥ፥ በላባ ፍራሽ ላይ
እንኳን ሲተኙበት፥ ግልገል ሱሪ አውልቀው
ገና ሲያዩት ብቻ፥ በንቅልፍ የሚያጠምቀው
እዚያ ላይ ተኝቼ፥ ምቾቴን አጣለሁ
እንደ ጠላ ብቅል፥ እገላበጣለሁ፤

ባጭር ቁመትና፥ በጠባብ ደረት ውስጥ
ማደር እየጠላሁ
እንደ ሉባንጃ ጢስ፥ ክፍሉን እየሞላሁ
ብለጠጥ ብሰፋ
ምቾት ዳናው ጠፋ
ረፍት ደብዛው ጠፋ፤

ይብላኝ እንጂ ለኔ
ይብላኝ ለክንዶቼ
ይብላኝ እንጂ ለኛ
ሌቱ ምን አለበት፥ ኮከብ አቅፎ ተኛ፤

ልረሳሽ ፈልጌ፥ ላወጣሽ ክደሜ
ፎቶሽን አውድሜ
ጽኑ ሐውልትሽን፥ ዶግ አመድ አድርጌ
ላወጣው ከደሜ፥ ደምሽን ጠርጌ
ልረሳሽ ፈልጌ፤

ፀረ-ቢምቢ አጎሰር፥ ካልጋው በስተራስጌ
የተንጠለጠለው
ከቀሚስሽ ጋራ፥ ምን አመሳሰለው
ተዘግቶበት መስኮት፥ ተከርችሞበት በር
ተጠምዶ ጠበቀኝ፥ ትዝታሽ ባጎበር
ምቾቴን ያጣሁት፥ ለካ ለዚህ ነበር።
👍1
#ሙግት

ጊዜ በሰው ሕይወት፥ ዘበት አይታከተው
እኔም ምላሽ ባጣም፥ መጠየቄን አልተው
ኩታ ገጠም ናቸው፥ እልፋና ኦሜጋ
እንዴት ቀን ይመሻል፥ በቅጡ ሳይነጋ?

ማን ዘረፈው ጠጉሬን?
ማን አሰረው እግሬን?
ጉልበቴን ምን በላው? አቅሜን ማን ወረሰው?
ተወልዶ ሳይጨርስ
እንዴት ያረጃል ሰው?
#ላንዲት_ተመጽዋች_ብላቴና

በቱሪስት ዓይን ውስጥ፥ ጠውልጋ እንዳትታይ
ከገጽታ ገንቢው፥ ግብዝ አደባባይ
የጠገበ ፖሊስ፥ የመንገድ አስከልካይ
ገፍቶ ያባረራት
ጥግ ይዛ የቆመች። እንደመንገድ መብራት
ትግሏ ጎደሎ ቀን፥ ግቧ የማታ ራት
ኩራቴን ላካፍላት፥ እፍረቷን ልጋራት፤

ድሪቶ ሳይለብስ፥ ባካል ባይመነምን
ሁሉም ተመጽዋች ነው
አዱኛ ተሰጥቶት፥ ጤና የሚለምን
ጉልበት ስልጣን ተርፎት፥ ፍቅር የሚለምን
በጸጋ ተራቁቶ፥ ህልሙን የሚሸምን።
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_ሶስት


#በሜሪ_ፈለቀ

"ስለዚህ ቢያንስ አንድ ጊዜ ወይ ቢሮህ እመጣለሁ ወይ ቁርስ እንበላለና"

በእርግጥ ለምን እንደሆነ በማይገባኝ ምክንያት ወንድ ልጅ ሲናደድ እና እልህ ሲይዘው ደስ ይለኛል። ኤፍሬምን ግን
ማናደድ ፈልጌ አልነበረም።ምርጫ ስላልሰጠኝ እንጂ፡፡ ይኸው ነወ። በሚቀጥለው ቀን የማላውቀውን ስልክ ጥሪ አስተናገድኩ፡፡አያሌው! ኤፍሬም ሚስቱ በሞተች በሶስት ዓመት
ውስጥ ቁጭ ብሎ አብሯት ምሳ እራት የበላ፣ ፈገግ ሲልላት የታየ ብቸኛዋ ሴት መሆኔን ነገረኝ፡፡

አሁን በአንድ ብቻ ሳይሆን በተጨማሪ የተለየ ምክንያት ኤፍሬምን ለመጥበስ ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አድርጌ መሞከር
ስላለብኝ አጭር ጅንስ ቁምጣ ወደ አንድ ጎኑ ባዘነበለ ሰፊ አላባሽ፣ በሸራ ጫማ አድርጌ ኤፍሬም ቢሮ በድጋሚ መጣሁላችሁ።
ሃሃሃ እንኳን ኤፍሬም እናንተ እንኳን ኤጭ! አላችሁ አይደል?
ቅዳሜ ስለነበር ማንም ይኖራል ብዬ አልገመትኩም ነበር።ፀሀፊው የሆነ ነገር እየተወራጨች ብላኛለች “ኢር ፎን
ሰክቻለሁ። አልፌያት ገባሁ። ኤፍሬም
ስብስባ ላይ ነው:: ከአያሌው ጋር ተያየን፡፡

"ይቅርታ!! ስትጨርስ እጠብቅሃለሁ::” ብዬው ወጣሁ።

ምናልባትም ከግማሽ ሰዓት በኋላ ስብሰባቸው አልቆ ሲወጡ ፀሃፊውን ጨምሮ እዛ ከነበሩት ሰራተኞቹ ጋር ከዚህ በፊት በግልምጫ እንዳልሸኙኝ ሁሉ እንደሚተዋወቅ ሰው እየቀደድን
ስለነበር መውጣታቸውን ያወቅኩት ሰራተኞቹ እየተወለካከፉ ወደየስራቸው ሲዞሩ ነበር፡

“ምን እያደረግሽ ነው? ይሄ ለእኔ ከስራ ቦታዬ በላይ ነው።ልረበሽበት አልፈልግም::” አለኝ ኤፍሬም ቢሮው እንደገባን እየተበሳጨ።

በቅዳሜ ምድር ያንተ ቢሮ መግባት ሲገርመኝ ሰራቸኞቹን ሁሉ ትጠገርራቸዋለህ?"

"ረቂቅ ቁርስ እንብላ ልትዪኝ አይደለም አይደል የመጣሽው?"

ኸረ አይደለም፡፡ ቅዳሜህን አውሰኝ ልልህ አስቤ ነው አመጣጤስ፡፡ ቁርስ ካልበላህ ግን እሱንም ያካትታል::"

'ምን እያሰብሽ ነው?"

'ምን እንደምናደርግበት? እርግጠኛ አይደለሁም ግን ውለህ
እንደማታውቀው አይነት አዋዋል አስውልሃለሁ:: እና ትወደዋለህ አታስብ፡፡” መለስኩለት:: አውቄ ስጠም እንጂ ምን
እንደጠየቀኝ ገብቶኛል:: እየተበሰጫጨ ኮቱን አንስቶ እየደረበ ለመሄድ ተሰናዳ፡፡

ረቂቅ ከዚህ በላይ መታገስ አልችልም። ነይ መፅሀፉን እሰጥሻለሁ።" አለኝ፡፡

ሆ! በአንድ መፅሀፍ ጦስ አሳሬን ልጨልጥ?" መኪናውን እየነዳ
ብቻውን ያወራል፡፡ ሳቄ መጥቷል። መበሳጨቱ ደግሞ ሲያምር፡፡

'ሀያ አራት ሰዓትህን ብቻ ስጠኝ፡፡ ሙሉ ቅዳሜን" ደጋግሜ እጠይቀዋለሁ። አይመልስልኝም።ብቻውን ያወራል። ሆ! ይላል እየደጋገመ።

ቁርስ መብላት እፈልጋለሁ።" አልኩት ለሶስተኛ ጊዜ፡፡

"ቢሮ ሰዎች ይጠብቁኛል፡፡ መፅሀፉን ይዘሽ ስንለያይ ትበያለሽ አለኝ በመጨረሻ።

"ሂሳብ ማን ሊከፍል? ታካብዳለህ እንዴ ልትፋታኝ አይደል?"

ከፈለግከሽ የቁርስሽን ሂሳብ እሰጥሻለሁ።" ንዴት ድምፁን እያጎረነነው።

"ያለአጃቢ? ደስ አይልም! አንተ ግን አንድ ቀን ብዙ መሆኑ ነው? እንኳን ለሰው ለእንቅልፍ ይሰጥ የለ? ብቻዬን
እለፈልፋለሁ። አይመልስልኝም። የመኪናውን በር ከፈትኩት እና አንድ እግሬን አስወጣሁ ቀጥዬ "ልወርድ ነው።" አልኩት።
መኪናውን ሲጢጢጥ አድርጎ አቆመው።

"አነቅከኝ::" አልኩት እኔ ዱለቴን እየበላሁ እሱ እያየኝ፡፡ ግራ ገብቶት አየኝ፡፡ የምሬን ነው ከመጠቅለሌ ጀምሮ እስከምጎርስ
በዓይኑ ምግቡን ይሸኘዋል፡፡

ከምግቡ ጋር እኮ አብረህ ገባህ!"

"አስቤው አልነበረም::" አለኝ ንዴቱ በረድ እያለለት።

"የቁርስ ምርጫህ ምንድነው?"

"የምግብ ምርጫ የለኝም::

"የቀለም ምርጫ ግን ይኖርሃል።"

"የለኝም::"


"እሺ ኮከብህ ምንድነው?"

"አላውቀውም::"

"ቆይ እሺ ጎደኛ ምናምን እንኳን የለህም?"

"ከሊዲያ ሌላ ጓደኛ ኖሮኝ አያውቅም። ጓደኝነት ላይ እንኳን ጥሩ ነኝ ብዬ አላስብም::" አለኝ በቁርጥሽን እወቂ አይነት፡፡

"እሱን እኔ ላረጋግጥልህ እችላለሁ:: አስቀያሚ ጓደኛ ነህ!"

ውጪ እንድጠብቀው ቢነግረኝም እስከመኝታ ቤቱ ተከተልኩት::
መፅሀፉን ከሰጠኝ በኋላም ምንም እንዳልነካ ቢያስጠነቅቀኝም ወደ ሳሎን ገባሁ።ሶፋው ላይ ከተደረደሩት አሻንጉሊቶች መሀል አንዱን ከማንሳቴ ኤፍሬም ከየት መጣ ሳልለው መነጨቀኝ እና ቦታው መለሰው።አስደንግጦኛል።

ይቅርታ!" አለኝ መልሶ።

የእርሷ እጅ፣ የእርሷ ጠረን፣ የእርሷ ምስል...... ሁሉም ነገር እሷ ራሱ ህያው ሆና ያለችው እዚህ ቤት ነው።እዚህ
ቤት ፍቅሬ አልሞተችም።የሳቅነው፣ ያለቀስነው፣ የተላፋነው፣የተጣላነው. እዚህ ቤት ነው።ሁሉም ነገር እንደ ዛሬ ትኩስ ህልውና አለው።እሷ ከሞተች በኋላ የቤቱቀለም አልተቀየረም።
የቤቱ እቃ አልተቀየረም።ሁሉም እሷ እንዳስቀመጠችው ነው።ማንም እዚህ ቤት ሲገባ ጠረኗን የተሻማኝ፣ ትዝታዋን የተጋራኝ ስለሚመስለኝ ለማንም ሰው እንዲገባ ፈቅጄ አላውቅም።" አለኝ
በተሰበረ ልብ፡፡

በቋሚነት የሚኖረው እናቱ ቤት መሆኑን ሚስቱ ስትናፍቀውና ሲከፋው እዚህ ቤት እንደሚመጣ ነገረኝ፡፡ ከልቤ አዘንኩለት ብቻ አደለም ሀዘኑን አጋባብኝ።

ቢሮ ሰዎች ቀጥሪያለሁ። እንሂድ" አለኝ የእኔን ተረጋግቶ የመሬቱ ምንጣፍ ላይ መቀመጥ ሲያይ እንድወጣለት ፈልጎ፡፡

"ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለህ:: ትናንት ወይም ነገ፤ ትዝታ ወይም ተስፋ!” አልኩት፡፡ አንዳንዴ እንደ አዋቂ ያደርገኝ የለ? የበርዬ እህት አይደለሁ?

"ከሊዲያ ጋር የኖርኳቸው አምስት ዓመታት ትዝታ ብቻ አይደሉም።ነፍስ ያላቸው ስንቆች ናቸው።"መለሰልኝ።

"የሚወዱትን ማጣት ምን ያህል እንደሚከብድ አውቃለሁ::"

"የእኔን ያህል አይገባሽም::"

ሁላችንም የራሳችን ስቃይ ሌላውን ያልጎበኘ ህመም እንዳለው ነው የሚገባን፡፡" እያወራሁት ከሱ በባሰ እኔ ታመምኩ። እንባዬ መጣ፡፡

"ገና በዘጠኝ ዓመቴ አባቴ አንገቱን በገመድ አንጠልጥሎ ሲሞት
በዓይኔ አይቼዋለሁ::" ይሄን ከተናገርኩ በኋላ ከኤፍሬም መለየት አማረኝ፡፡ተነስቼ መኪናው ውስጥ ገባሁ፡፡ ምንም
ሳንነጋገር ብዙ ተጓዝን: የረቀቀችው ረቂቅ ይህቺ ነኝ፡፡እንደጎርፍ የሚግተለተል ሳቅና ልፍለፋዬ በአንዴ የሚደፈርስ ትንሽ ቢራቢሮ፡፡

"እዚህጋ አውርደኝ።" አልኩ ድንገት ማጨስ ስላማረኝ።አቆመልኝ፡፡ መረበሼ ረብሾታል፡፡ዝምታዬ ጨንቆታል።
ያስቀመጥኩትን መፅሀፍ አቀበለኝ፡፡

"ያንተ ይሁን። በመፅሀፍ አሳብቤም ቢሮ አልመጣብህም።"ያልኩት እውነቴን ነው:: ፊትለፊት ያገኘሁት ሱቅ ገብቼ
ሲጋራዬን እዛው መማግ ጀመርኩ።

የማስታውሳቸው የልጅነት ቀኖቼ ላይ ሁሉም ልክ ነበር፡፡ እማዬ ደከመኝ ሳትል በምቾት የምታኖረን ልጆቿ እኔና በርዬ

አባታችን ልጆቹን እና ሚስቱን የሚወድ ጎበዝ ሰካራም፧ በርዬ ከውልደቱ ጀምሮ መራመድም መናገርም የማይችል ታላቅ
ወንድሜ፤ እማዬ ሁሉንም ምንም ጉድለት እንደሌለ፣ በርዬም ጤነኛ፣ ባሏም በየእለቱ የማይሰክር እና ሁሉ እንደሞላለት ታስመስለው ነበር፡፡ ልጅነቴ እንዳላስተውል አድርጎኝ ይሆን
የጎደለ ስንጥር የኑሮ ክፍተት አይታየኝም ነበር፡፡ በእርግጥ ማገናዘብ የምችልበት እድሜዬ ላይም ቢሆን ቅንጡ ኑሮ
ባይባልም የተደላደለ ነበር ኑሯችን፡፡ አንድ ቀን ግን ልክነት አበቃ:: እማዬ አንድ ቅዳሜ በርዬንና እኔን እንዲጠብቅ ለአባዬ
ጥላለት ሸመታ ወደ ገበያ ሄደች፡፡ በምን አጋጣሚ ዘወር እንዳለ በርዬ እየተሳበ የተለኮሰ ሲሊንደር አጠገብ ደርሶ እሳት እግሩን አቃጠለው፡፡ በርዬ በአባዬ ቸልተኝነት እንዳልተቃጠለ እኔ ምስክሩ ነበርኩ፡፡ እኔና አባዬ የምናደርገው
👍2🔥21
ጠፍቶን ስንጯጯህ እማዬ ደረሰች።

"ልጄን ልጄን" ብላ ስትጮህ በርዬ እግሩ የተቃጠለ ሳይሆን የሞተ ነው የመሰለኝ። በተሰበሰበው ሰው መሃል አባዬ ሲወጣ
አየሁት።አወጣጡና እንባ ያቀረሩ አይኖቹ ስዕል ዛሬም ድረስ ትዝ ይለኛል:: የመሸነፍ ስሜት፣ አቅም የማጣት ህመም፣
እንደ አባት ሀላፊነትን ያለመወጣት ፀፀት.. ... አድጌ ያንን ገፅታውን ስተረጉመው ብዙ ስሜት ነበረው፡፡ ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ ለምን ልቤ ወደ አባዬ እንደጎተተኝ ሳይገባኝ እሱ በወጣበት መንገድ ወደጎሮ ወጣሁ፡፡ አባዬ ጓሮ ተንጠልጥሎ ነፍሱ ልትወጣ
እየተንፈራፈረ ነበር፡፡ ደነዘዝኩ፡፡ ሰዎች ጩኸቴን ሰምተው ሲደርሱ ዘግይተው ነበር፡፡ ከአባዬ ሞት ብዙም ሳይቆይ በርዬ
ለህክምና ከሀገር ወጥቶ ውጪ ከምትኖር የእማዬ እህት ጋር መኖር ሲጀምር እኔና እማዬ ጥቂት የማይባሉ ዓመታትን እና ችግሮችን ብቻችንን ገፋን።
ብሩን መክፈል ስላልቻለች ቤታችን በሀራጅ ተሽጦ ትንሽዬ ቤት ተከራይተን መኖር ስንጀምር ነው እማዬ የተወሰነውን ለበርዬ መታከምያ ገንዘብ ቤታችንን አስይዛ ከባንክ እንደተበደረች ያወኩት።በርዬንም ከብዙ ገንዘብ ግፍገፋ በኋላ ምንም ሊረዱት ባይችሉም የማሰብ ክህሎቱ ከጤነኛ ሰው በብዙ የላቀ በመሆኑ መማሩ መጨረሻውን እንዲቀይርለት አክስቴና ባሏ እዛው ትምህርት አስጀመሩት።

የተፈጠረውን ሁሉ ተቀብለን መኖር በጀመርንበት ሰዓት ግን የባሰ ምስቅልቅል ተተካ።...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
#ካልዳሰስኩ_አላምንም

ሊነጋ ነው ሲሉኝ፣ ለኮስኩት ፋኖሴን
ሊወብቅ ነው ሲሉኝ፣ ደረብኩት በርኖሴን
ሰላም ወርዷል ሲሉኝ፣ ጋሻዬን አራገፍኩ
ሰው አልሰማ ብል ነው፣ ከፉ ቀኔን ያለፍኩ።

ቃል ገብቶ ቃል ማፍረስ
ያገር ልማድ ሁኗል
እንጀራ እንደ መብላት፣ በበሬ እንደማረስ።
ፍቅር ሥጋ ለብሶ፣ በጁ ካላቀፈኝ
ተስፋም ብብቴ ስር፣ ገብቶ ካልደገፈኝ
ኢምንት ነው ምንም
ካልዳሰስኩ አላምንም።
#የሌት_ማህሌት

ትንሽ ቆየት ብሎ
ኮረንቲው ይጠፋል
እሱን ተከትሎ
ደምኖ ያካፋል
ከናፍቆትሽ በቀር፣ ሁሉ ነገር ያልፋል።

አሁን መብራት ጠፋ፣ ተረኛ ነን አይደል
ቁና ይዤ ቀረብሁ፣ ጨለማ ሲታደል።

እያገላበጠ ብቻነት አመሰኝ
“ዝናቡ እየጣለ ጋራ ጋራውን
ጎርፍ ያመጣሽ እንደሁ ልጠብቅ ወንዙን”
የሚል እንጉርጉሮ በድንገት ታወሰኝ
ግን ይሄ ትውስታ
አራራይ ትዝታ
ለቆሰለው ልቤ፣ መዳኒት አልሆነም
ያባቶቼ ዘፈን፣ ለኔ አልተዘፈነም።

ማዶ ዝናብ ዘንቧል
ዶፉን ተከናንቧል
እንጦጦ ዲልዲላ
በገፈጅ ይመስል፣ ቀበናም ቢሞላ
ምንም አያመጣ፣ ከእድፍ ውሃ ሌላ።

እሳት ነው ፍጥረትሽ፣ ከውሃ ጋ አትኖሪም
አንቺ መብረቅ እንጂ፣ ጎርፍ አትሳፈሪም።
#ከልጅነት_ፍቅር_አንዲት_ጠብታ

በሰላላው መንገድ
የትየለሌ አግር፥ እንደሊጥ ባቦካው
ጸአዳ ጣትሽን፥ ጉድፍ እንዳይነካው
ማጡን እየዘለልሽ፥ ዳጥ ዳጡን እያለፍሽ
ጤዛ የወረረው፥ ዛፍ እየተደገፍሽ
ትንሽ ስትመጭ፥ ብዙ ሰታዘግሚ
ሁለቴ ተራምደሽ፥ አስሬ ሰትቆሚ
ለተደናገረው፥ መንገድ ሰትጠቁሚ
የተላከ ሕፃን፥ አሰቁመሽ ስትስሚ

እኔ ሰናፍቅሽ
እኔ ስጠብቅሽ
እንደጉድ ተውቤ
ላማልልሽ ጥሬ
በጆንትራ ዘይቤ
ጠጉሬን አበጥሬ
ጅማት እያጠበቅሁ፥ ጅማት እያላላሁ
የገዛ ከንፈሬን፥ ቀርጥፌ እየበላሁ
ሰጠብቅሽ በጣም
ምሰልሽ ነው እንጂ፥ አካልሽ አልመጣም፤

ባይኖቼ ስፈልግ
መስኮት እከፍትና
ሌላ ነው የሚያልፈው፥ በሰፊው ጎዳና
ያው ገጣባ አህያ፥ ያቻት ድኩም በቅሎ
በግ እየጎተተ፥ አለፈ ቆለኛ
ቅርጫት ያጎበጣት፥ ሚስቱን አሰከትሎ
ያውና ድሀ እደግ፥ መንገድ ዳር የተኛ

የተጎነጎነ፥ የሣር አምባር መስሎ፤
ባይኖቼ ሳማትር፥ መስኮት እከፍትና
ሌላ ነው የሚያልፈው፥ በሰፊው ጎዳና፤

ሁሉም ተለውጦ
ያ ገጣባ አህያ፥ ጸጉር አቆጥቁጦ
ያች ድኩም በቅሎ፥ ስጋር ፈረስ ቀድማ
ቆለኛው ሰውየ፥ ሙከት በጉን ሽጦ
ለሚሰቱ ነጭ ሻሽ፥ ለሱ ሸራ ጫማ
በትርፉ ሸምቶ
ሁሉም ከሄደበት፥ ቀንቶት ተመልሶ
ሁሉም ከድቀቱ፥ በወግ ተፈውሶ፤

እኔ ብቻ ቀረሁ
መንገድሽ ረዝሞ፥ ባሳብ እያሳጠርሁ
አንቺን እየናፈቅሁ
አንቺን እየጠቅሁ
ጅማት እያላላሁ፥ ጅማት እያጠበቅሁ።

🔘 በውቀቱ ስዩም🔘
#ስንቱን_አፀደ_አክስመነው

ያገራችን ቦለቲካ በሁለት ቃል ሲደመደም
ምኒልክ ይቅደም!
ምኒልክ ይውደም!

መቸም ያዳም ልጅ መሆን፣የማይፈታ ጣጣ
ሁለመናው ሲዞርብን፣የመኖር ሰበብ ስናጣ
ጉልበትና ስልጣን ኖሮን፣ንብረት መሬት ባንደለድል
እንዳባቶች፣እንደናቶች፣ዘምተን ታጥቀን ባንገድል
ለሱስ ያህል ያምረናል ጦር፣ላመል ያህል ያምረናል ድል።

አልፎ ሂያጆች ሆነን ሳለ፣ደማቅ ድንበር አስምረን
በመናኛ ድንኳን ዙርያ፣የኮረንቲ ቅፅር አጥረን
ያብሮ መኖር መላ ጠፍቶን፣ያብሮ መሞት ዘዴ ፈጥረን
ከቤታችን ጠብ ቢጠፋ፣ከጎረቤት ተበድረን

በየሱስ ስም በማርያም ስም
በነ ሌኒን በማርክስም
ዛሬ ደሞ በምኒሊክ
ባገኘው ወዳጅ መጠን፣ባፈራነው የጠላት ልክ
ዋጋችንን ስንተምነው
ስንቱን ቀትር፣አጨለምነው
ስንቱን አፅድ፣አከሰምነው?!

ከአዳምኤል መፅሀፍ የተወሰደ

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አራት


#በሜሪ_ፈለቀ

እማዬ የተወሰነውን ለበርዬ መታከሚያ ገንዘብ ቤታችንን አስይዛ ከባንክ እንደተበደረች ያወቅኩት። በርዩንም ከብዙ ገንዘብ ግፍገፋ በኋላ ምንም ሊረዱት ባይችሉም የማሰብ ክህሎቱ ከጤነኛ ሰው በብዙ የላቀ በመሆኑ መማሩ መጨረሻውን እንዲቀይርለት
አክስቴና ባሏ እዛው ትምህርት አስጀመሩት፡፡

የተፈጠረውን ሁሉ ተቀብለን መኖር በጀመርንበት ሰዓት ግን የባሰ ምስቅልቅል ተተካ፡፡ አስረኛ ክፍል ማትሪክ ተፈትኜ
ውጤት መጣብኝ (ለመፈተን ያህል
እንጂ አልሰራሁም፡፡) እማዬ ብቻ በምታውቀው ዓመታት ያስቆጠረ
ታሪክ በርዬን ውጪ ሀገር ልካ ለማሳከሚያ ብር አንሷት ከምትሰራበት መስሪያ ቤት ባነሳችው ገንዘብ ጦስ የተነሳ ከዓመታት በኋላ ተረጋግጦ የመስሪያ ቤቱን ገንዘብ በመመዝበር
የአስር ዓመት እስራት ተፈርዶባት ዘብጥያ ወረደች፡፡ ይሄኔን የተፈጠረውን ሲያውቅ በርዬ ከውጪ ሀገር ትምህርቱን ትቶ
መጣ። እንዳንዴ እሱ ባይመለስ ኖሮ ብቻዬን ምን ዓይነት ቀንኀሊኖረኝ እንደሚችል ሳስብ ደስታ የራቀው ኑሮ የሚኖረኝ የነበረ ይመስለኛል፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ በተለይ መኖር ቋጥኝ መግፋት
የሚሆንብኝ ሰዓት ላይ እሱ ባይኖር አንድ ሀሳብ ይቀልልኝ እንደነበር አስባለሁ፡፡ ወዲያው ግን ይሄን ማሰቤንም እንዲህ
በማሰቤ ራሴንም እጠላዋለሁ፡፡

የአስራ ሰባት ዓመት ሴት፣ ወጣት፤ በአምስት ዓመት የሚበልጣት በዊልቸር የሚገፋ ወንድም ያላት፣አባቷ የሞተባት፣ እናቷ የታሰረችባት ረቂቅ ሆንኩ፡፡

“ቅዳሜ የቀረውን አስራ ስድስት ሰዓት ምን በመስራት እንደምንጀምረው ምሳ እየበላን እንደራደር?" አለኝ ኤፍሬም
አጠገቤ ደርሶ:: አላመንኩትም፡፡ ደስ ያለኝ በየትኛው ምክንያት እንደሆነ ሳይገባኝ ተጠመጠምኩበት፡፡ የለበሰውን ሙሉ
ልብስ ቡቲክ ገብተን አስቀይሬው ነበር ቀኑን የጀመርነው::
እነዚህ ለቅዳሜ ያፀደቅናቸው ህጎች ናቸው። ስልክ መዝጋት፣
ስለሊዲያ አለማውራት፣ ስለአባቴ አለመጠየቅ፣ ከዛሬዋ ቅዳሜ
ውጪ ሌላ ቀን የለም ብሎ ማመን፡ ትናንትንም ነገንም ረስቶ ደስ መሰኘት፡፡ ከላይ የዘረዘርኩላችሁ ለሁለት ያፀደቅነውን ነው።ለብቻዬ ግን ሊረሳው የማይችለው ቀን ልሰጠው ምያለሁ።

“ማጨስ እንዴት ጀመርሽ? በጓደኛ ተፅኖ?"

"አይደለም። ምነው? ሴት ልጅ ስታጨስ ውበቷ ይቀንስብኛል ከሚሉት ጎራ ነህ?"

ላይ ተቀምጦ እስክነቃ እየጠበቀኝ ነበር፡፡

"እኔ እንኳን ከማንነት ጋር አላያይዘውም፡፡ ከጤና አንፃር ግን ባታደርጊው እመርጣለሁ::" አለኝ እና በድርድር ቅዳሜ
እስኪያልቅ ሶስት ሲጋራ ብቻ ላጨስ
ተስማማን፡፡ እኔ የማውቃቸው አብዛኛው ባለገንዘብ ወንዶች ገበጣ ሲጫወቱ እንዳላደጉ ሆቢህ ምንድነው?” ሲባሉ ጎልፍ፣ የበረዶ ሸርተቴ፣ራግቢ ምናምን ማለት ይዳዳቸዋል።ኤፍሬም ከጠረጴዛ ቴኒስ እና ከሊዲያ ውጪ የሚወደውን ነገር እንኳን አያውቀውም፡፡ቅዳሜን አሰከርናት። ቅዳሜን አሳበድናት፡፡ ቅዳሜ ምትሀት ነገር ነበረች።

እሁድ ጠዋት ሆቴል አልጋ ላይ ስነቃ ኤፍሬም ተነስቶ ወንበር ላይ ተቀምጦ እስክነቃ እየጠበቀኝ ነበር።መፀፀቱ እንዲገባኝ ብዙ ሊነግረኝ አልተገባውም።
ፀጥታው ብዙ እሪታ ነበረው።ወትሮም ፀጥታ እጠላለሁ።በጆሮዬ የምሰማው ድምፅ ሲጠፋ የምትጮህ ነፍሴን መስማት እፈራለሁ እስካልተኛሁ መለፍለፍ እመርጣለሁ።ዛሬ ግን ዝም አልኩ። ለምንድነው የምከተለው?ያለምንም ቃል ልውውጥ የሚያደርገውን የማደርገው ለምንድነው?

ለምንድነው? ምንም ቃል ሳይተነፍስ ተጣጥቤ ለባበስኩ።ቁርስ
ቀርቦ እየበላን ፀጥታው ጮኸብኝ።

"ብሎን እንደጠፋበት ሰዓት ሰሪ አደፈጥን እኮ!" አልኩት።ሁለታችንም ምግቡ ላይ አቀረቀርን እንጂ በተገቢው እየተመገብን አልነበረም።

"አንቺ ግን ምንም አይመስልሽም አይደል?" አለኝ በትዝብት አይነት።

"የምልህ ግራ ገብቶኝ እንጂ ፀፀት ላይ እንደጣድኩህ ገብቶኛል።በሆነ ነገር ማለቃቀስ መፍትሄ ያመጣል ብዬ ስለማላስብ አላላዝንም::" ያልኩት ከልቤ እንጂ እየኮነንኩት አልነበረም።
አልመለሰልኝም ፀጥ አለኝ።

"መጥፎ እንዲሰማህ ስላደረግኩህ ይቅርታ በጣም!" አልኩት።አሁንም አልመለሰልኝም። ልሂድ?' አላልኩትም:: ምንድነው ሀሳብሽ?” አላለኝም:: መኪናውን ነድቶ መቃብር ስፍራ ደረስን፡፡
ቃል ወጣው፡፡

"መጣሁ!"

ከተወሰነ ደቂቃ በኋላ መታገስ አቃተኝ። ተከተልኩት።አላየኝም:: ያየሁት ነገር የምቋቋመው አይነት አልነበረም፡፡
እንደምትሰማው ሁሉ፣ እንደምታየው ሁሉ፤ እንደምታባብለው ሁሉ መቃብሯ ላይ አቅሉን እየሳተ ያወራል፤ ያለቅሳል፤
ይጠይቃል፤ ይመልሳል። ብዙም እርምጃ ባልራቀ ርቀት በእንባዬ አጅበዋለሁ። የሷ የነበረውን ገላ ለሌላ ሰው ስላጋራባት ይቅርታ ይለምናታል፣ተነስታ እንድትወቅሰውና የፀፀት ወላፈኑ
እንዲበርድ ይማፀናታል፡፡ እግሬን አላዘዝኩትም:: በደመ ነፍስ
እየተጓዝኩ ታክሲ ይዤ እቤቴ ደረስኩ፡፡ ማጨስ አይደለም ያማረኝ ማልቀስ!! በርዬ እንዳየኝ ገብቶታል። እቅፉን ዘረጋልኝ።እንደ ህፃን ድምፅ አውጥቼ አለቀስኩ። ለበርዬ የሆነውን ሁሉ ነገርኩት።ቀጥዬ ያደረኩት አያሌውን ማግኘት ነበር።

ኤፍሬምን ካሁን በኋላ ላገኘው አልፈልግም።" አልኩት ለአያሌው ደውዬ እንዳገኘሁት።

ማንም በሱ ቦታ ቢሆን በመጀመርያ ቀን ሊሰማው የሚችለው እንደዚህ ነው።"

"አይደለም።" መለስኩለት።

"እየገፋሽ ያለሽው ገንዘብ ይታይሻል ረቂቅ? እንደ ' ቦሊ ቦል' ከአንዱ ወንድ እጅ ወደሌላው መንጠር አልሰለቸሽም? " እውነቱን ነው ሰልችቶኛል።ነገር ግን ኤፍሬም የሚስቱ መቃብር ላይ የሆነው መሆን በገንዘብ ለመደራደር ይከብዳል። በተቀመጠበት ትቼው ወደቤቴ ተመለስኩ።

ለቀናት እቤት አርፌ ተቀመጥኩ።እንኳን ለእማዬ የማስረው ስንቅ እቤት ውስጥ እንኳን የሚበስል ነገር እያለቀብኝ ነው።ባንክ ያለችኝን አራት መቶ ብር አውጥቼ ምን ምን እንደማደረግ አቀድኩ። አስማማው ጋር ወይም አንዱ በፊት የማውቀው ሰው ጋር ልደውል ባስብም ሳስበው ገና ሰለቸኝ። ሁሌ ችግር ማውራት እንኳን የሚሰሙኝን ወንዶች እኔን እንዴት ወንድ እና ገንዘብ ዘውድና ጎፈር እንደሆኑብኝ ልንገራችሁ።የምነግራችሁ ጅማሬዬን እንጂ ሰበቤን አይደለም። ምክንያቱም ወንድን ለገንዘቡ ብላ የምትተኛ ከንቱ ለመሆን የትኛውም ሰበብ እና ምክንያት ሚዛን የሚደፋ አይደለም።

#ያኔ

አባቷ የሞተባት፣ እናቷ ስንቅ የሚያስፈልጋት እስረኛ፣ ወንድሟ
መፅሀፍ ማሳተም የሚመኝ በዊልቸር ሂያጅ ዲዳ የሆነባት ረቂቅን የሆንኩ ጊዜ፤ አንድ ሆቴል አስተናጋጅ ሆኜ በማገኛት
ገንዘብ ልንኖር ስዳክር በርዬ ሲያለቅስ ያየሁት ጊዜ፤ በርዬ ስራ ፍለጋ በፀሀይ እጁ እስኪርድ ዊልቸሩን እየገፋ ውሎ እጁ ተልጦ ያየሁት ጊዜ ፤ በርዬ መፅሀፉን ሊያሳትም አሳታሚ ፍለጋ ሲዞር ዉሎ አፍንጫውን ነስሮት የገባ ጊዜ እንደምንም አጠራቅሜ የበርዬን መፅሀፍ ላሳትምለት ቃል የገባሁ ጊዜ እማዬ ልንጠይቃት ስንሄድ እያለቀስኩ ልጆቼን አላይም ብላ አልወጣም ያለችን ጊዜ ፤ እማዬ ሲጋራ እንዳስገባላት የጠየቀችኝ
ጊዜ ፤ የወደደኝ የመሰለኝ ፍቅረኛዬን
ከሌላ ሴት ጋር ያየሁት ጊዜ ከእነዚህ በአንዱ ጊዜ ወይም በሁሉም ጊዜ ምንም ለማድረግ ተዘጋጅቼ ነበር፡፡ ከአንድ ሀብታም ባለሚስት ጋር ሆቴል ሲመጣ ተቀራረብን። ባለትዳር መሆኑን ሳይደብቀኝ ቁንጅናዬ እንዳማለለው ነገረኝ፡ ስለሰማሁት የታክሲ አምስት መቶ ብር (የመስተንግዶ ደሞዜን) ሰጠኝ፡፡ ስለተሳምኩለት የወር አስቤዛ
አደረገልኝ፡፡ ስለወጣሁለት የቸገረኝን እንድነግረው ሊያሟላልኝ ማለልኝ። የጠገበኝ ሲመስለው ሄደ:: ሌላ ተመሳሳይ ሰው ለመድኩ። በርዬ መማር የሚፈልገውን ኮምፒውተር ሳይንስ
መማር ጀመረ።
👍7🔥1
ለእማዬ ስንቅ ለማሰር መጨነቅ ተውኩኝ፡፡ ተርፎን የማስቀምጠው ገንዘብ ባይኖረኝም ቢያንስ መሰረታዊ ነገሮች አይጎልብንም::

በርዬ ሰሞኑን አድፍጦ መፃፍ ጀምሯል፡፡ ለወትሮው በተጨማደዱ ወረቀቶች የሚሞላው የቆሻሻ ቅርጫት ባዶ ሆኗል፡፡ የሚፅፈው ታሪክ የሰመረለት ይመስላል። ስለምን እንደሆነ ብጠይቀውም
ሳያልቅ እንደማይነግረኝ ስለደረቀ ትቼዋለሁ። ብቻዬን ካርታ እየተጫወትኩ ስልኬ ጮኸ፡፡ አነሳሁት።

"ኤፍሬም ነኝ፡፡ ዝም ብለሽ ስትጠፊ አሳስበሽኝ ነው::"

'አሳስበሽኝ? ናፍቀሽኝ?" አልኩት እንደመጣልኝ፡፡

ስልኬን ከአስማማው እንዳገኘው ሲነግረኝ የመጀመሪያው እለት
ከአስማማው ጋር እራት መታደሜን እንደነገርኩት አስታወስኩ፡፡

ላግኝሽ?" አባባሉ ከእሺ ውጪ ሌላ መልስ አይሰጠውም፡፡

እራት እየበላን አቶ አያሌው የነገረኝን በድጋሚ ስለራሱ ማወቅ አለባት ብሎ ያሰበውን በመጠኑ ነገረኝ፡፡ እራሱን ካወቀበት ጊዜ ጀምሮ የሚያውቃት አብሮ አድግ ጓደኛው እና የልጅነት ሚስቱ
በሞተች በስድስት ወር ልዩነት አባቱ ተከትለዋት እስከሞቱበት ቀን ድረስ ኤፍሬም ከቤተሰቡ ድርጅት ጋር የሚያያዝ ስራ የማይሰራ መሆኑንና ከአባቱ ቀጥሎ የድርጅቱን ምክትል
አስተዳደርነት ለሚስቱ ትቶላት
የሚወደውን የዩንቨርስቲ መምህርነት
ይሰራ እንደነበር ነገረኝ። አባቱ ከመሞታቸው አስቀድመው በሚስቱ ሞት ተስፋ ለቆረጠ ልጃቸው ሁሉንም
ሀላፊነቶች ያስረከቡት አንድም ከርሱ የተሻለ ሊያምኑት የሚችሉት ሰው ስላልነበራቸው ሁለትም በሊዲያ ሞት ራሱን ጥሎ ስለነበር በስራ ራሱን እንዲወጠር አስበው ነበር።

ኤፍሬም ማስተዳደር ከጀመረ ጀምሮ ሁሉም ሴክተሮች በየዓመቱ የትርፍ መቀነስ ማሳየታቸውን እና አባቱ እና ሚስቱ በሚያስተዳድሩበት ጊዜ እንደነበረው የድርጅቱን ህልውና ከጥያቄ
ማውጣት ለሚስቱ ሲል እያለፋ ቢሆንም እንዳቃተው አክሎ ሲያወራኝ የተሸነፈ ይመስል ነበር።ቤተሰቡ (እናትና ወንድሙ) የፋብሪካውን ሼር ለአያሌው ሽጦ በሚያገኘው ጠቀም ያለ ገንዘብ የተቀሩትን በድርጅቱ የሚጠለሉ ንግዶች እንዲያሳድግበት እረፍት እየነሱት ሳለ በዚህ ቀውስ ውስጥ እኔ ወደ ህይወቱ ብቅ ማለቴን አክሎ ነገረኝ....

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 እና #Share ማድረግ እንዳይረሳ ስለድርሰቱ ያላችሁንም አስተያየት ስጡን።

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ምርጫ_አልባ_ምርጫ ፡ ፡ #ክፍል_አራት ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ እማዬ የተወሰነውን ለበርዬ መታከሚያ ገንዘብ ቤታችንን አስይዛ ከባንክ እንደተበደረች ያወቅኩት። በርዩንም ከብዙ ገንዘብ ግፍገፋ በኋላ ምንም ሊረዱት ባይችሉም የማሰብ ክህሎቱ ከጤነኛ ሰው በብዙ የላቀ በመሆኑ መማሩ መጨረሻውን እንዲቀይርለት አክስቴና ባሏ እዛው ትምህርት አስጀመሩት፡፡ የተፈጠረውን ሁሉ ተቀብለን መኖር በጀመርንበት ሰዓት…»
#ካንቺ_ጋራ

ካንቺ ጋራ ሆኜ፤ የኖርኳቸው ጊዜያት
ያሳለፍኩት እድሜ
ጣፋጭ እንደኃጥያት
አጭር እንደ ጳጉሜ፤

አንቺ በላባ እግር፥ ደመና ላይ ቆመሽ
ሺ ሌሊት ከፊቴ፥ ሺ ሌት ከኋላዬ
ኮከቡን በሞላ በወረንጦ ለቅመሽ
ነዛሽው በላየ፤

ምንም እንኳ ሕዋው፥ ብርሃን ባያንሰው
ግርዶሽ ሆኖት ቆሟል፥ ይሄ ሰው ለዚያ ሰው
ግርዶሽ ቢነባበር፥ ኀይል የለው ባንች ፊት
መጋረጃው ሆነ፥ የብርሃን ወንፊት።
#ይድረስ

በገዛ ጆሮና በገዛ ዓይኖችሽ ላይ
ሙሉ ስልጣን ያሰሽ
ከቶ እንደምን አለሽ፤

አለሁ እንደሾላው
እንደወፍ መነሻው
እንደወፍ መሸሻው
ፀሐይ እየሞቀ ከመተንፈስ በቀር፥ ሌላ እንደማይሻው፤

መኖር ብቻ ሲሆን፥ የሰው ልጅ እቅዱ
በሲኦል ቢኖርም፥ አይቀርም መልመዱ
እኔም ከመበላት፥ መብላት ይሻል ብየ
ፍሪደም ሲርቀኝ፥ ፍሪዳን ጥየ
ነፃነት ቢርበኝ፥ እየበላሁ እህል
አለሁ ይህን ያህል
አለሁ ይህን ያህል።
#ስብርባሪሽ_ወጋኝ

ሁሌ እምጎመጅሽ
ሁልዜ እማልምሽ
የንጉሥ ብርሌ
የግርማዊ ከንፈር
ወትሮ የሚቀስምሽ
የምታረኪለት፣ የድለኛውን ጥም
እኔ ግን ምስኪኑ
ሲሳይሽ ባይደርሰኝ፣ ከእዳሽ አላመልጥም
ያንፀባረቅሽ ዕለት፣ ግርማሽ ያላስጠጋኝ
ዛሬ ብትወድቂ፣ ስብርባሪሽ ወጋኝ!!
#ቅን_መሆን

ገንዘብ አታወጣ
ፍለጋ አትዞረው
ፊትህ አይገረጣ
በመዳፍህ ያለው
ፈጣሪ ጀምሮት
መርቶ ትሩፋቱን
ለልጁ የቸረው
የማለዳ ዘርህ
ነገ መከሊትህ ነው
የቅፅበት ቅንነት
የእርጅና ፍትፍት ነው
ምነው ወዳጅህን
ቅንቅን ሆነህበት
ጀርባውን ባትዞረው።
#ምርጫ_አልባ_ምርጫ


#ክፍል_አምስት


#በሜሪ_ፈለቀ

እኔ ወደ ህይወቱ ብቅ ማለቴን አክሎ ነገረኝ።

እናቱ በግልፅ “ስራህን ከቁስልህ መደበቂያ አድርገኸዋል። ያንተን
ድርቅናና የሟች ሚስትህን ትዝታ ማስታመም እየሰለቸኝ ነው::"
ብለውት ልቡ መድቀቁን ሲነግረኝ ግን ያቺ ከቀናት በፊት ሊያያት እንደማይፈልግ ሲሆንባት ለነበረችው ረቂቅ እየተናገረ አይመስልም።

"በዚህ ከቀጠልኩ እነርሱ እንደሚፈሩት ከዓመታት በኋላ የድርጅቱንም ሆነ የቤተሰባችንን ህልውና አደጋ ላይ ልጥለው እንደምችል ማሰቤ ይባስ ውጥንቅጥ ውስጥ ይከተኛል::" ሲለኝ
ይሄን ሀሳብ ለጥዝጠዛ ለማመቻቸት ወሳኙ ጊዜ መሆኑን አሳሰበኝ።

"ጥቅሙ የሚያመዝን ከሆነ ለምን በቤተሰቦችህ ሀሳብ አትስማማም?"

"አንደኛ አሳማኝ አይደለም፡፡ በግሌ ከማስተዳድራቸው ዘርፎች
በላይ ፋብሪካው ትርፋማ እየሆነ በመጣበት ወቅት በተለይ የእማዬ እንዲሸጥ መወትወት አልዋጥልህ ነው ያለኝ፡፡ ሁለተኛኀአባዬ ያስረከበኝን ምንም
ነገር ማብዛት እንጂ ማጉደል አልፈልግም።

መቃብሩ ጋር ጥዬው የሄድኩ ዕለት ራሱን ስቶ ሀኪም ቤት ገብቶ ነበር፡፡ ማረፍ እንዳለበት በሀኪም ስለታዘዘ ለወንድሙ
ውክልና ፈርሞለት እረፍት መሆኑን እና ላይደውልልኝ ከራሱ ጋር ብዙ ቢሟገትም ቀኖቹ አላልቅ ብለውት አማራጭ ሲያጣ
እነደደወለልኝ ሳይደብቅ ነገረኝ።

አሁን ጓደኝነቴን አምነህ ብትቀበል ነው የሚያዋጣህ።"

"ምን ያህል “ኮስት ያደርገኛል?"

እንነጋገርበታለን::" አልኩት:: ፈገግ አለ፡፡ መስማማቱ ነው።

"ስለሴት ልጅ የምትወደውን ሶስት ነገሯን ንገረኝ እስቲ?" አልኩት እራት መብላት ጨርሰን ወደ ቤት እየሸኘኝ፡፡ ጠዋት
ወደ ላንጋኖ ልንሄድ ተቀጣጥረናል።

"እናትነቷን"

ሶስት ነው ያልኩህ::"

"እኔ ስለሴት ልጅ ይሄ የምለው የተለየ ነገር አልወድም። ራሷን ስትሆን፣ የራሷ እምነት ፣ የራሷ ፋሽን፣ የራሷ ኩራት! በቃ
የራሷ ነገር ሲኖራት ራሷን ስትሆን ደስ ትለኛለች:: የሰው ልጅ ምርጥ እየሆነ የሚመስለኝ ራሱን ወደ መሆን ሲያድግ ነው።"

“ለምሳሌ?"

“ለምሳሌ እንዳንቺ!! እራት ቀጥሬሽ ቁምጣ በቲሸርት ለብሰሽ
ትመጫለሽ" አለኝ ቁምጣዬን እያየ::" ቤዚካሊይ የራስሽ የሆነውን ነገር ሰው ለማስደሰት ብለሽ አትቀይሪውም::"

"በቻይንኛ ወድጄሻለሁ እንደማለት”

ባህሪሽ ደስ ይለኛል ማለት በቻይንኛ ወድጄሻለሁ እንደማለት መሆኑን አላውቅም ነበር።" ፈገግ አለ።"አንቺስ?"

"እኔ ምን?"

"አባትነቱን"

"ሶስት ነው ያልኩሽ?" አለ እየተንፈቀፈቀ::

"ባክህ የወንድ ሁሉ ተምሳሌቴ ወንድሜ ነው፡፡ ዓይንህን ብቻ አይቶ ጥልቅ ስሜትህ የሚገባው አይነት ነው። የወንድ መለኪያዬ እሱ ነው።

ወዲያው ስልኬ ጠራ። አያሌው ነው። ኤፍሬምን ቀና ብዬ አየሁት። አንሺው፣ ችግር የለውም::” እንደማለት ምልክት
አሳየኝ፡፡ ለኔ ግን የገባኝ፡፡ 'አምንሻለሁ እንዳለኝ ነበር:: አነሳሁት።

"እድል ካንቺ ጋር የሆነች ይመስላል፡፡ ተጠቀሚባት:: እንደሌሎቹ
ወንዶች አጣጥሞሽ ሲበቃው ከነድህነትሽ ጥሎሽ እንዲሄድ
አትፍቀጂለት" አለኝ፡

፡መልስ ሳልሰጠው ዘጋሁት።

"ምን እያሰብክ ነው?" አልኩት ላንጋኖ ሀይቁ ዳር አሸዋው ላይ እንደተቀመጥን፡፡ እኩለ ለሊት ሆኗል፡፡ ከመጣን ሶስተኛ ቀናችን ነው።

"አንቺን" አለኝ፡፡ በኤፍሬም ድምፅ ይሄን መስማት ብዙ ነገር ነበር፡፡

"እቀፈኝ!"

ግን እንደዛ አላደረገም:: ከአጠገቤ ተነስቶ ከጀርባዬ በኩል እግሮቹ
መሃል አድርጎኝ ተቀመጠ። በግዙፍ ሰውነቱ ሙሉ ውስጡ ደበቀኝ። ከብዙ ክፋቶች የተጠበቅኩ መሰለኝ፡፡ አንገቴ ስር የሚሰማኝ ሞቅታ ትንፋሹ እጠብቅሻለሁ፣ አለሁልሽ' ያለኝ
መሰለኝ፡፡ የማንም ወንድ ገላ በዚህ መጠን ናፍቆኝ ማወቁን እጠራጠራለሁ
"እንግባ?" ከማለቱ እኔ ተነስቻለሁ። ገብቶታል።እንደህፃን ልጅ ብድግ አድርጎ ከመሬት አንስቶ እንደታቀፈኝ አልጋው ጋረሸ አደረሰኝ።

መች ነው እንዲህ ለሱ የተሰማኝ? ከዛሬ በፊት በነበሩት ቀናት?፣ከአዲስ አበባ ስንመጣ እግሮቹ ላይ እንቅልፌን ተኝቼ መኪና ሲነዳ?፣ ሀይቁ ውስጥ ስንዋኝ?፣ የጠረጴዛ ቴኒስ ስንጫወት?፣
ቼዝ ሲያለማምደኝ?፣ ካንፋየር አጠገብ እራት እየበላን ውስኪ ስንጠጣ? ክፍላችን ውስጥ በድሮ ሙዚቃ የድሮ ዳንስ ስንደንስ?እግሩ ስር አስቀምጦኝ ፀጉሬን ሲያበጥርልኝ ካርታ ተጫውተን አሸንፌው በውርርዱ አዝሎኝ ጊቢውን ዞር በአንዱ ወይም በሁሉም ሰዓት የተለየ ስሜት ተሰምቶኛል።

ቁርስ መብላት ደስ የሚለኝ ፍርፍር በሻይ ነው::" አለኝ ጠዋት እቅፉ ውስጥ እንዳለሁ።

"ፍርፍር? ፍርፍር? ስጋ ሳይኖረው?"

ቢኖረው ጥሩ! ባይኖረውም ከሌላ ምግብ ፍርፍር ምርጫዬ ነው:" አለኝ ከአልጋው ለመነሳት ያቀፈኝን እጁን በቀስታ እያነሳ።

"እንቆይ? እንደዚህ ትንሽ እንቆይ? አቅፈኸኝ ትንሽ እንተኛ?" አልኩት:: ተመልሶ አጥብቆ አቅፎኝ ተኛ።

መታቀፍ የተለየ ትርጉም እና ስሜት የሚሰጠኝ ነገር ነው። ለአቃፊው የምሰጠው ዋጋ የትርጉሙን ልኬት የሚያወጣና የሚያወርደው ቢሆንም ያቀፈኝ ሰው ስሜቴን ብነግረው ባልነግረውም ያጋባሁበት እነደሆነ ነው የሚሰማኝ።ባቀፈኝ ቅፅበት ሸክሜን የተጋራልኝ፣ ካለሁበት ትርምስ የደበቀኝ ነው የሚመስለኝ፡፡ ይሄን ትርጉም በትክክል የሚያሟላልኝ የእማዬና
የበርዬ እቅፍ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ተሰምቶኝ በማያውቅ ልክ የኤፍሬም።


ከሶስት ቀናት በኋላ ከራሴ እውነት ጋር መላተም ጀመርኩ::አያሌው እቤት ድረስ መጥቶ አስር ሺህ ብር አስቀምጦልኝ
መሄዱን በርዬ ነገረኝ፡፡

"እሺ ልመልስለት:: ከዛስ? ከዛ ምን እንብላ? ከዛ ለእማዬ ምን
እንሰርላት? ከዛ ገንዘብ ፍለጋ የማልወደው ገላ ላይ ልጣድ?
ንገረኛ?" ብሩን መልሺለት ስላለኝ ነው በርዬ ላይ የምጮኸው።ለኤፍሬም እውነቱን እንድነግረው ሲወተውተኝ፡፡
በርዬ አቀረቀረ:: አድርጌው እንደማላውቅ
ሁሉ ለገንዘባቸው ከምተኛላቸው ወንዶች ጋር መሆን ቀፋፊ ነገር ሆነብኝ፡፡

ከኤፍሬም ጋር የስራሁትን ፍቅር ማርከስ መሰለኝ፡፡ የሆነ ልክ ከኤፍሬም ጋር ከተኛሁ በኋላ ገላዬ የተቀደሰ ነገር መሰለኝ፡፡ ያንን ማርከስ መሰለኝ፡፡ በእርግጥ ኤፍሬምን ገንዘብ ብጠይቀው
ይከለክለኝ ነበር? አይከለክለኝም ይሆናል፡፡ በግልፅ ምክንያት
የአያሌውን ገንዘብ ብመልስለት ለኤፍሬም እውነቱን እንደሚነግረው አስፈራርቶኛል፡፡ በድብቅ ምክንያቴ ግን ኤፍሬም ጋር ያለኝ ነገር ከዚህ በፊት ከማውቃቸው ወንዶች ጋር እንደነበረኝ ስራ እንደሆነ እንዲሰማኝና እንዲቀልብኝ
አልፈለግኩም:: ሌላው አማራጭ ግን እንደገሃነም አስፈሪ ነው፡፡እውነቱን መናገር! ለኤፍሬም የቀረብኩህ ተከፍሎኝ ነውኀልበለው? ከዛስ? ጥሎኝ ሲሄድ ትርፌ ምንድነው? ፊልም ላይ
ብቻ ነው ይሄ የሚሰራው:: አባዬ ራሱን ያጠፋው የቤተሰቡን ምስቅልቅል መሸከም ስለከበደው ነበር:: ያንን የተሸናፊ ፊቱን ልረሳው አልችልም፡፡ እኔ እማዬንና በርዬን የራሳቸው ጉዳይ ብዬ
ህሊናን መምረጥ አልችልም።የኔ ህሊና
ንፅህና የቤት ኪራያችንን አይከፍልም ወይም የበርዬን ትምህርት ቤት ክፍያ
አያጠናቅቅም አልያም ለእማዬ ስንቅ አይሆንም።ህሊና በአገልግል አይቆጠርም።

ከኤፍሬም ጋር ሳንገናኝ የዋልንበት ቀን ጠፋ። እቤት ከማድርበት ከኤፍሬም ጋር የማድርበት ቀን በለጠ፡፡ ሀኪም ያዘዘለትን ሀያ የእረፍት ቀን አረፍንበት። አብሬው አሳለፍኩ፡ እሱ በትክክል ምን እንደሚሰማው ግን አሁንም ማወቅ አልቻልኩም:: ከነዚህ ቀናት በኋላ አሁን ጥያቄዬ ህሊና ብቻ አይደለም ኤፍሬምን ማጣት ማሰብ ያስፈራኝ ጀምሯል። ኤፍሬም ሊዲያ የሞተችበት
ረቡዕ ዕለት ሁሌም መቃብሯጋ እንደሚሄድ ስለማውቅ
👍61🔥1
አበባ ገዝቼ ሄድኩኝ፡፡ በጉልበቱ ተንበርክኮ እያዋራት አገኘሁት::ተመሳሳዩን አደረግኩኝ። ስሞኝ እንደማያውቀው ሳመኝ:: ስላየኝ ደስ ብሎታል። ሊዲያ በሀኪም ልጅ ማርገዝ አደጋ እንዳለውተነግሯት ነበር፡፡ ያ እንዳይፈጠር ሲጠነቀቁ ዓመታትን ከቆዩ
በኋላ አረገዘች:: መውለድ እንደማትችል ዶክተር ቢነግራትም ጥፋቱን ለመጋፈጥ ወሰነች። እርሱን አባት ለማድረግ ብላ
ማርገዟን እንኳን ሳትነግረው አራት ወር ቆየች:: በሰቀቀን የጠበቁት የተፈራው ቀን ሲመጣ እርሷም ልጇም ሳይተርፉ ቀሩ፡፡ ይሄን ሲነግረኝ አቀፍኩት።

ኤፍዬ አንተን ለማስደሰት ለነፍሷ ያልራራች ሴት፣ ኖራ ልትሰጥህ የማትችለውን ደስታ ከሌላ ሴት አገኘኸው ብላ የምታዝን ይመስልሃል?" ፀፀቱ እንዳለቀቀው ስለማውቅ ነው ይሄን ያልኩት በእርግጥ ሙሉ እንዲሆን ለሚፈልግ ልቤም እያደላሁ ነበር፡፡ ካሰብኩት በላይ ተቆራኘኝ ፍላጎቴ ምን እንደሆነ ግራ ገባኝ።ኤፍሬምን ገንዘቡን? አላውቅም:: ለራሴ ኤፍሬምን ለበርዬና ለእማዬ ስል ደግሞ።የትኛው ጋር መቆም እንዳለብኝ ግራ ገባኝ።ስራ የሚጀምርበት ቀን ሲደርስ "ያስብኩትን ያህል ስራ አልናፈቀኝም ።" አለኝ ምሳ እየበላን።...

💫ይቀጥላል💫

Like 👍 #Share ማድረግ እንዳይረሳ

ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን
👍1
አትሮኖስ pinned «#ምርጫ_አልባ_ምርጫ ፡ ፡ #ክፍል_አምስት ፡ ፡ #በሜሪ_ፈለቀ እኔ ወደ ህይወቱ ብቅ ማለቴን አክሎ ነገረኝ። እናቱ በግልፅ “ስራህን ከቁስልህ መደበቂያ አድርገኸዋል። ያንተን ድርቅናና የሟች ሚስትህን ትዝታ ማስታመም እየሰለቸኝ ነው::" ብለውት ልቡ መድቀቁን ሲነግረኝ ግን ያቺ ከቀናት በፊት ሊያያት እንደማይፈልግ ሲሆንባት ለነበረችው ረቂቅ እየተናገረ አይመስልም። "በዚህ ከቀጠልኩ እነርሱ እንደሚፈሩት…»
#የመጻተኛው_እንጉርጉሮ

ያኔ ዋዛ ሳለ፣ ግድግዳ ጣራ በር
“ዞሮ ዞሮ ከቤት” ይሉት ብሂል ነበር።
ለንስር ጎጆ አለው፣ ለከብት አለው በረት
የኔናንቺ ድርሻ
ቤት ጎምዥቶ መቅረት
አገር ናፍቆ መቅረት
መንገድ አቅፎ መቅረት
ዞሮ ዞሮ ዞሮ እንደገና ዙረት።