#መአዛሽ_ፈወሰኝ
ጎራዳ አፍንጫየን
ጎራዴ እፍንጫየን
ከሰገባው ስቤ
ስምግሽ ቀርቤ
አንገትሽ ሽነት ዛፍ
ጡትሽ ደብረ-ከርቤ
እፎይ!!!
እንዲያው ሲፈርድብኝ፥ ቤቴ አዲስ አበባ
ሰማዩ ጥንብ ነው፥ መሬቱም አዛባ
ዓይን ጆሮ ምላስ፥ ለኑሮ ሳያንሰኝ
ምን በድየው ጌታ፥ አፍንጫ ለገስኝ
እያልሁኝ ሳማርር፥ አንቺን ልኮ ካስኝ
መዳኒት ሆነና፥ መእዛሽ ።ፈወሰኝ
ጎራዳ አፍንጫየን
ጎራዴ እፍንጫየን
ከሰገባው ስቤ
ስምግሽ ቀርቤ
አንገትሽ ሽነት ዛፍ
ጡትሽ ደብረ-ከርቤ
እፎይ!!!
እንዲያው ሲፈርድብኝ፥ ቤቴ አዲስ አበባ
ሰማዩ ጥንብ ነው፥ መሬቱም አዛባ
ዓይን ጆሮ ምላስ፥ ለኑሮ ሳያንሰኝ
ምን በድየው ጌታ፥ አፍንጫ ለገስኝ
እያልሁኝ ሳማርር፥ አንቺን ልኮ ካስኝ
መዳኒት ሆነና፥ መእዛሽ ።ፈወሰኝ
#ላንድ_መስቲካ_ሻጭ_ብላቴና
በደብተርሽ ምትካ፥ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎ ሂያጅ እግር ሥር፥ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፥ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቼ፥ ምታደርጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፥ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመሰል፥ መረረኝ መስቲካው፧
አፈር ጠጠር ለብሶ፥ በዶዘር ተድጦ
መለኩ ከነጎርፉ
ሰማይ ከነዶፉ
ለጌቶች ተሸጦ
አተር ነው አያሉ፥ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው አያሉ፥ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፥ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጥቶሽ
ገና በልጅነት፥ ልጅነት አምልጦሽ፤
በምቢልታ በዋሽንት፥ በከበሮ ታጥሮ
ሰክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው፥ ለሰው አይሰማ፤
ጠዋት የፎከረ፥ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ፥ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸከም ያላንቀልባ ሲያዝል
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፥ ትከሻሽ የማይዝል።
በደብተርሽ ምትካ፥ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎ ሂያጅ እግር ሥር፥ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፥ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቼ፥ ምታደርጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፥ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመሰል፥ መረረኝ መስቲካው፧
አፈር ጠጠር ለብሶ፥ በዶዘር ተድጦ
መለኩ ከነጎርፉ
ሰማይ ከነዶፉ
ለጌቶች ተሸጦ
አተር ነው አያሉ፥ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው አያሉ፥ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፥ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጥቶሽ
ገና በልጅነት፥ ልጅነት አምልጦሽ፤
በምቢልታ በዋሽንት፥ በከበሮ ታጥሮ
ሰክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው፥ ለሰው አይሰማ፤
ጠዋት የፎከረ፥ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ፥ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸከም ያላንቀልባ ሲያዝል
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፥ ትከሻሽ የማይዝል።
❤1
#ቅድስትና_ትዕግስት
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
ቅድስት ልክ ስምንት ሰዐት ከሩብ ሲል ትዕግስት ቤት ደረሰች፡፡
“ውይ ቅድስትዬ....! ምነው እንዲህ ጠቋቆርሽ....? ፀሐይ እንኳን የለ ዛሬ....” አለች፣ትዕግስት አራት ጊዜ ጉንጭዋን ስማት....
“ኧረ ተይኝ ባክሽ... ለእንደኔ ያለ ሰው ከነዚያ ሴቶች ጋር ሦስት ሰዐት ሙሉ ስለ ልብስና ጫማ ማውራት ራሱ፣ ከሰባት ፀሐይ በላይ አያከስልም?" አለች ቅድስት፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብላ እየተቀመጠች....
እናም፣ በተገናኙ ቁጥር የሚያደሩት ተመሳሳይ ወሬያቸው በእንዲህ
ሁኔታ ተጀመረ፡፡
“አይ ለእኔ ነው ስለነሱ የምትነግሪኝ ቅድስትዬ? እኔስ ምናቸው አስመርሮኝ ብረንች(ይቺ ቃል ግር እንዳትላቹ በእንግሊዘኛ ብሬክ ፋስትን ከ ላንች ጋር አዳቅሎ የተፈጠረ ነው በኛ ደሞ ቁምሳ ማለት ነው) መምጣት ተውኩና!”
“ደግ አደረግሽ... እኔ የምለው? ማስተርስ ድረስ የተማሩ ሴቶች ከልብስንና ከወንድ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አለማቻላቸው አያሳዝንም? በጣም ያሳፍራል እኮ!"
“በጣም እንጂ....! ዐሥር ሴት ሚኒስትር ቢሾም ታች ያለነው ሴቶች ትላንት ስለገዛነው ነገ ስለምንገዛው ልንገዛ ፈልገን ስላጣናው ብቻ ምናወራ ከሆነ፣ ይህች ሀገር እንዴት ብላ ቀና ትላለች...? ሲንፏቀቁ መኖር እኮ ነው!"
"ጎሽ...እኔ እኮ አንቺ ጋር መምጣት የምወደው ለዚህ ነው....ተንፈስ ስለምታደርጊኝ... ቁም ነገር ስለምታዋሪኝ እኮ ነው አንቺ ጋር መምጣት ደስ የሚለኝ ቲጂዬ!”
“እኔስ ብትይ....! እሺ..... ዛሬስ ምን ተፈጠረ ታዲያ?”
“ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል... ያው ሴሞ ሴሞ ነው...ሃሜት ሃሜት... ወሬ... ሰው ቡጨቃ... እይው የገዛሁትን ልብስ.... ይሄ ሽቶ ደስ አይልም...? እገሊት ጂም ጀመረች... እንትና ዮጋ ጀመረች
ይሄው ነው ቲጂዬ!”
“አይገርምም...ዘለዓለም ያው ናቸው... ዘለዓለም..ማፈሪያዎች!”
“እህስ!...ዛሬ ደግሞ ያቺ ሶሎሜ መጥታ ጭራሽ ስትጠብሰኝ አረፈደች.. ደህና ተገላግለናት ነበር፡፡”
“መጣች እንዴ? ዱባይ ቫኬሽን ላይ ነኝ ምናምን ብላ ስታናፋ አልነበረም እንዴ?”
“እንግዲህ ያ የግፍ ዶላር ቶሎ አልቆ ይሆናላ! ወር ሳይሞላት ተመለሰች!”
“አዬ! ለዚህችው ነው ያ ሁሉ ጉራ! ...ግን አንቺን ምን አርጋ አናደደችሽ ቅድስትዬ?”
“ኧረ... ተይኝ! ገና በሥርዓት እንኳን ሳልቀመጥ እየሮጠች መጥታ ... 'ቶፕሽ ያምራል... እኔ የዛሬ ሁለት ዓመት በአራት መቶ ብር ገዝቼው ነበር... በቢጫው አለኝ... አሁን ግን ፋሽን ስላለፈበት ለሠራተኛዬ ሰጠኋት አትለኝም?”
“አታደርገውም!”
“አደረገችው እንጂ ትግስትዬ!አደረገችው”
“እና አንቺስ ዝም አልሻት?”
“ማ? እኔ ቅድስት እንዲህ ባደባባይ ሰድባኝ ዝም የምላት ይመስልሻል?”
“እና... እና ምናልሻት?”
“የኔ እናት... ተማስሉብሽ ይሆናል... ይሄ ሌተስት ፋሽን ነው... የጣሊያን እቃ ነው! የገዛሁት ደግሞ አንድ ሺህ ስምንት
መቶ ብር ነው አልኳታ!”
“ወይኔ አንቺ.. አንጀት አርስ እኮ ነሽ!”
“ታዲያስ...የሆነች ባላገር..ትላንት ብረንች ማለት አቅቷት፣ብራንች የምትል ሴትዮ፤ አንዴ ዱባይ ሄጄ መጣሁ ብላ
ትላጥብኛለች እንዴ?”
“ሃሃ... አይ ቅድስት!”
“ይልቅ እነሱን ተያቸውና ቲጂዬ የሚበላ ነገር አለሽ? ሁሉም ሰው ዳይት ላይ ነኝ ምናምን ብሎ ደህና ነገር አልበላሁም፡፡”
“ተይ እንጂ...! ዛሬም ዳይት ላይ ናቸው?”
“ታዲያስ! ለተቆራረጠ ሙዝ ሰማንያ ብር ይከፍላሉ. ዳይት ላይ ነኝ... መቀነስ አለብኝ ቅብጥርሶ ይላሉ፡፡ ምናለ ስለአንጎላቸው እንዲህ ቢጨነቁ......?”
“እኮ...! እና ታዲያ ምን ላምጣልሽ?”
“ሥጋ...ቅባት ያለው ነገር ምናምን... አታምጪብኝ! ትንሽ ጨምሬያለሁ ሰሞኑን ደግሞ...”
“ኧረ ተይ! ምንም አልጨመርሽም ቅድስትዬ! እንደውም ሳትከሺ አትቀሪም...”
“አይ ቲጂዬ...ቦዲ ሼፐር አርጌ ነው... ቦርጩን ጥፍንግ አድርጎ ስለያዘልኝ ነው...”
“ፓ! አሪፍ ነገር ነው ባክሽ... የት አገኘሽው? እኔ ፈልጌ ፈልጌ
የሚሆነኝ አጣሁ...” "መድኀኔ ዓለም ሞል ግራውንድ ፍሎር ላይ የሆነ ቤት አለ....
መዓት አላቸው... ዘጠኝ መቶ ብር ነው የገዛሁት... ብዙ አይመችም
ግን ቢያንስ ይሰበስብሻል... አብረን ሄደን ትገዣለሽ ሰሞኑን....”
“እሺ... አስታውሺኝ በቃ...ያስፈልገኛል.... በይ በቃ ሽሮ ላምጣልሽ እንግዲህ....”
"እሺ. ..ቲጂዬ..."
ቅድሰት የቀረበውን ሽሮ መብላት ጀመረች፡፡
“ውይ ቲጂዬ! ሲጣፍጥ ግን ቅቤ ሞጀርሽበት!”
“ሃሃ ... ለዚያ እኮ ነው ሚጣፍጠው...”
“ልቀንስ እያልኩሽ ቅቤ ትግችኛለሽ አይደል... አንቺ ምን አለብሽ?”
“ብዪ ባክሽ... ከልኩ አያልፍም...”
“ምን? ቦርጭ?”
“አዎ...."
“ሃሃሃ!”
“ኧረ ቅድሰትዬ ሳልነግርሽ... ዮጋ እኮ ጀመርኩ ቀጥ አላልኩብሽም ትንሽ?”
“ዮጋ?”
“አዎ...”
“ጎበዝ ነሽ ልጄ... እኔ አንዴ ከሰኒ ጋር ጀምሬ እናቴ... ሁለመናዬ ተላቀቀ፡፡ እሱን ለመጠገን አጥሚት እና መረቅ ስበላልሽ ነው ይሄን ቦርጭ እዚህ ያደረስኩት ቲጂዬ!”
“ሃሃሃ... ቀልድሽ እኮ ደስ ሲለኝ ቅድስትዬ!”
“አሹፊ አንቺ... ይልቅ ማን በጣም እንደከሳ ገምቺ...”
“ማ?
“እሌኒ!”
“እሌኒ እሌኒ? እሌኒ መርሻ?”
“እህ!”
“እንዴ? እንዴት አርጋ ከሳች በናትሽ?”
“ሙግግ ብላ መጣች ዛሬ... በሳምንት ሁለት ኪሎ እየቀነስኩ አሁን ዐሥራ ሁለት ኪሎ ቀንሻለሁ አለችን...”
“ተይ ባክሽ....! ያን ሁሉ ሰውነት እንዴት አድርጋ ናደችው በናትሽ?”
“የሆነ ቲቪ ላይ የሚታይ የዳይት ሾው አለ አሉ... እሱን አይቼ ሄጄ ነው አለችኝ...”
“ምን ቲቪ ላይ? እዚህ አገር?”
“አዎ....”
“እና ሄዳ ምን አደረጉላት?”
“ምግብ መጥነው ይሠሩልሻል አሉ... “በወር አራት ሺህ ብር እከፍልና ምግቤን ይሠሩልኛል... አሽገው ቤቴ ድረስ አምጥተው ይሰጡኛል' አለችኝ...”
“ተይ እንጂ... ምን ቲቪ ነው ልጄ?”
“
ፋና መሰለኝ...”
“ለነገሩ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ብዙም አይመቸኝ... ግን መቼ መቼ
ነው የሚታየው አለችሽ?”
“እንጃ... እሁድ መሰለኝ... ብቻ ምሳ እና እራት ዐሥራ ሁለት መኮረኒ ተቆጥሮ ነው የሚሰጠኝ ብላ አሳቀችኝ!”
“ሃሃሃ... አትይኝም?”
“ሙች!”
“እና ግን አከሳት?”
“በጣም... ምግቡ እህል ቅጠል አይልም፤ ግን ካከሳኝ ምን ቸገረኝ
ምናምን አለችኝ...”
“ይገርማል... አምሮባታል በይኛ!”
“ያው መቼስ... ትንሽ ሙግግ ብላለች፣ ረኀብተኛ ነው የምትመስለው ፤ ግን ቦርጭዋ ጠፍቶላታል፡፡ ለነገሩ ዛሬ ዕድሜ
ለብራዚል “ሂውማን ሄር የማታምር ሴት አለች?”
“ልክ ነሽ እሱስ... ሂውማን ሄር ሴቱን ሁሉ እኩል አደረገው እኮ... ምን ዋጋ አለው... ጸጉር ጭንቅላት አይሆን!”
“እኮ!”
“የሚገርመኝ ግን ብር ኖሯቸው እንኳን ደህናውን አይገዙም እኮ...የኔን ዕይው አሁን ከጣልያን ነው ያስመጣሁት... ይኸው ሁለት ዓመቱ ንቅንቅ አላለም... ከገዛሽ ደህና ነገር ነው... የሚልከሰከስ
ሰው አልወድም እኔ...”.....
✨ማታ እንጨርሰው ✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም። 🙏

👍2
#ቅድስትና_ትዕግስት (መጨረሻው ነው)
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
፡
፡
“እሺ... ሌላስ ምን አዲስ አለ ታዲያ!”
“ዝናሽም በስንት ጊዜዋ ዛሬ መጥታ ነበር!”
“ተይ እንጂ! እንዴት ናት?”
“አረጀችብኝ.... ጉስቁልቁል ብላለች... ያው እሷን ታውቂያታለሽ.በሜካፕ ኀይል ነው እንጂ እኮ ዕድሜዋ ሄዷል..."
“አዎ እሱስ... ምን ሜካፕ ብትለቀለቅ አንገቷ አሳልፎ ይሰጣት የለ...
ያ.. የአውራ ዶሮ ኩልኩልት የመሰለ አንገት..."
“አንቺ ተይ በስማም... ሃሃሃ!”
“ምን ላርግ ብለሽ ነው....? ደግሞ እኮ ሰው መልክ ባይኖረው ፀባይ
አይኖረውም?
ያ...ባሏ እንዴት ችሏት እንደሚኖር ነው የሚገርመኝ
እኔ...”
“ውይ! አልሰማሽም እንዴ?”
“ምኑን?”
“አልጋ ለይተዋል አሉ እኮ...”
“ተይ ተይ!”
“ሙች! ቆዩ እኮ... ለንብረት ብለው ነው የማይፋቱት ሲሉ ነበር..."
“ወይ ጉድ... የተጎሳቆለችው ለዚህ ነው በይኛ...."
“ይሆናል እንግዲህ...”
የሚገርመው ፌስ ቡክ ላይ ይሄን ሰልፊ ስትለጥፍ እኮ ነው የምትውለው....
ደህና ፊት እንዳለው ሰው... ለነገሩ ስልኳ
ሌተስት' ስለሆነ አሪፍ አርጎ ያነሳታል... በዐይን እስክታያት ቆንጆ ትመስላለች
ሃሃሃሃ...ስልክ ብትይ...አንቺ ግን እስካሁን አልቀየርሽም እንዴ
ይሄንን ስልክ? ዓመት አለፈው እኮ!”
“አዝዣለሁ ሆድዬ... ሰሞኑን ከካናዳ ይመጣልኛል."
“አይ ደግ አደረግሽ....!”
ቅድስት ሸሮውን ጥረግ አድርጋ በልታ ጨረሰችና እጆቿን ታጥባ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡
“ሽቶሽ ደስ ይላል ቅድስትዬ...” አለች ትዕግስት፣ እቃውን ቦታ ቦታ
አሲዛ ወደ ሳሎን ተመለሰችና አጠገቧ እየተቀመጠች፡፡
“ውይ... ሽቶሽ ብትይ ሳልነግርሽ... ያቺ ሕሊና ያረገችውን ዛሬ...”
“የእነዚህ ሴቶች ጉድ አያልቅ! እሷ ደግሞ ምናረገች በናትሽ....?”
ዋው... ሽቶሽ ደስ ይላል... ምንድነው ስሙ አትለኝም?”
እና ነገርሻት...?”
ደህና ዴኦዶራንት ተቀብታ የማታውቅ ዝተታም የአራት ሺህ ስድስት መቶ ብር ሽቶ ስትመኝ አይገርምሽም? እኔማ ምን አለብኝ
ከነዋጋው ነገርኳት.... ያ አመዳም ፊቷ የበለጠ አመድ መሰለ ...
ሃሃሃ”
“ሃሂ... በጣም ያሳዝናል ብቻ የእነሱ ነገር... ስንት የሚያስጨንቅ ነገር እያለ.. ሃገር እየታመሰች ወሬያቸው ሽቶ..ቅባት.ልብስ ሃሜት... ወንድ... ያሳዝናል በጣም.... መማር ምን ጥቅም አለው
ግን?”
“ምንም!”
ጥቂት ቆይቶ ቅድስት መሄድ እንዳለባት ተናገረችና ተነሳች፡፡
“በቃ ልሂድ ቲጂዬ! የማታው እራት ላይ አለሽ አይደል?” አለቻት እንደቆመች፡፡
“አለሁ ቅድስትዬ...”
“ዋ እንዳትቀሪ... አንቺ ስለምትመጪ ነው የምመጣው ... ከነዚያ ሴቶች ጋር ትርኪምርኪ ማውራት አልችልም... አደራሽን እንዳትቀሪ”
“አልቀርም ቅድስትዬ...”
“ጎሽ... በይ ልሂድና ልበጃጅ...”
“ምን ልትለብሺ አሰብሽ ዛሬ?”
“የሆነ ጥቁር ሌስ ቀሚስ ገዝቻለሁ... አንቺስ?”
“እኔ እንኳን አልወሰንኩም፡፡”
“ጸጉርሽንስ? አትሠሪም?”
“አይ ፍሪዝ ላረገው ነው ባክሽ...”
ለነገሩ ያንቺ ጸጉር በፍሪዝ ያምራል..."
“ታንኪው ሆዴ... በይ ልሂድ...”
“ቻው የኔ ቆንጆ...
እሙጳ.. እሙጿ፡፡ እሙጳ....
እኔ የምልሽ ቲጂዬ...?”
“ወዬ ቅድስትዬ...."
“አንቺ ጋር ስመጣ እኮ ነው አንጎል ያለኝ አንጎል የሚመስለኝ...”
“እኔስ ብትዩ!
💫አለቀ💫
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏

#ገንዳው
እዚህ አሜሪካ በሀገረ ማርያም
በጊዜያዊ ቤቴ ጊዜያዊ በረንዳ
ቆሜ ሳነጣጥር
አየሁኝ መንገድ ዳር፥ ተገትሮ ያለ የቆሻሻ ገንዳ
ዳቦው እንደ ጉድፍ
ወተቱም እንደ እድፍ
ልብሱም እንደ ቅጠል
በገንዳው ከርስ ውስጥ፥ ይረግፋል እንደ ጠል፤
ያሜሪካ መልኳ
አይደለም ሕንጻዋ፥ ሰማይ የሚነድለው
አይደለም መንገዷ እንደቆለኛ ቅል የተወለወለው
አይደለም ፖሊስዋ፥ ዝሆን የሚያህለው
ያሜሪካ መልኳ፥ ጎልቶ የተሳለው
በገንዳዋ ላይ ነው፥ እመንገድ ዳር ባለው፤
ባገሬ ሰማይ ሥር
ሰው ጠኔ ገፍትሮት፥ ሲወድቅ በመደዳ
ያሜሪካ ንስር
ላንዲት ስኒ ሆዱ፥ በጋን እያለቀዳ
እዚያ ማጣት እዳ
እዚህ ማትረፍ እዳ
እዚያ ባዶ ሞሰብ
እዚህ ሙሉ ገንዳ
ከዕለታት አንድ ቀን
በሰማያት እና በምድሪቱ ድንበር
ከእኛ ጎታ አጠገብ፥ የቆሻሻ ገንዳ ተቀምጦ ነበር
የሰማይ አማልክት፥ አላጋጭ ቀልደኛ
“ራበን መግቡን”፥ ለንላቸው እኛ
ብዙ መና ጋግረው፥ ሲያዘንሙ ከሰማይ
የእኛን ጎታ ስተው፥ ከተቱት ገንዳው ላይ፤
ከቶ ለምን ይሆን
ያፍሪቃ ሕፃናት፥ በደቦ ሚያለቅሱ
የወተቶች አዋሽ፥ የርጎ ሚሲሲፒ፥ በበዛበት ዓለም ጤዛ የሚልሱ
የሹራብ ተራራ
የቡልኮ ጋራ
በበዛበት ዓለም፥ ጭጋግ የሚለብሱ
የምድር ጠቢባን
ለዚህ ግዙፍ ምስጢር፥ መልስ አገኝ ብላችሁ፥ጠፈር አታስሱ
ኣሜሪካ ያለው፥ የቆሻሻ ገንዳ፥ ግጣሙ ሲክፈት ወለል ይላል መልሱ።

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አልሞትም
ስሚ!
እኔ በዚህ አለም፣ብዙ ብሰቃይም
አንድ ሃሙስ የቀረው፣መስዬ ብታይም
አምሮቴን ሳላገኝ፣ሱሴን ሳላከትም
በመሬት ከርስ ውስጥ፣ገላየን አልከትም
#አልሞትም!
ማንም ባልደፈረው፣መንገድ ሳልገሰግስ
እንደ ንጉስ አይዙር፣ግማሽ ቀን ሳልነግስ
በጠገበው ሳልስቅ፣ለራበው ሳልደግስ
#አልሞትም!
ዝማሜን ሳላውቅ፣ያንደበቴን ግድብ
ዙፋን ላይ ሳልሸና፣ጌቶችን ሳልሰድብ
ከድሃ ሳላብር፣ካገሬው ሳልወግን
ከምድር በረከት፣ ድርሻዬን ሳልዘግን
#አልሞትም!
ስሚ!
ልቤ እንደምኞቱ፣ቢያገኝ እንደምርጫው
ያላማዬ ማብቂያ፣አንቺ ነሽ መቋጫው
እና
አገሬን ለቅቄ፣ልብሽ ላይ ሳልከትም
በውብ ከፈርሽ ላይ፣ከንፈሬን ሳላትም
#አልሞትም!
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
ስሚ!
እኔ በዚህ አለም፣ብዙ ብሰቃይም
አንድ ሃሙስ የቀረው፣መስዬ ብታይም
አምሮቴን ሳላገኝ፣ሱሴን ሳላከትም
በመሬት ከርስ ውስጥ፣ገላየን አልከትም
#አልሞትም!
ማንም ባልደፈረው፣መንገድ ሳልገሰግስ
እንደ ንጉስ አይዙር፣ግማሽ ቀን ሳልነግስ
በጠገበው ሳልስቅ፣ለራበው ሳልደግስ
#አልሞትም!
ዝማሜን ሳላውቅ፣ያንደበቴን ግድብ
ዙፋን ላይ ሳልሸና፣ጌቶችን ሳልሰድብ
ከድሃ ሳላብር፣ካገሬው ሳልወግን
ከምድር በረከት፣ ድርሻዬን ሳልዘግን
#አልሞትም!
ስሚ!
ልቤ እንደምኞቱ፣ቢያገኝ እንደምርጫው
ያላማዬ ማብቂያ፣አንቺ ነሽ መቋጫው
እና
አገሬን ለቅቄ፣ልብሽ ላይ ሳልከትም
በውብ ከፈርሽ ላይ፣ከንፈሬን ሳላትም
#አልሞትም!
🔘በውቀቱ ስዩም🔘
❤1
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ግጥሎት (ግጥምና ፀሎት)
አቤቱ ውሃን አየር ላይ ያረጋህ
ምድሪቱን በጠረባ የዘረጋህ
በጃርት ወስፌ ጠንቁለህ፣ ያሞራን ዐይን ያፈሰስህ
ካላጣኸው እጄ ጠባብ፣ ኤሊን ድንጊያ ያለበስህ
ካልቸገረህ ወጣትነት፣ አዳምን ባርባ አመት ያስረጀህ
በኅዳር በሽታ ዘመዶቼን የፈጀህ።
እንደምን ዝም ትላለህ፣ በቫይረስ ሲቀቀል ዓለም
በሰማይ ቤት እፍረት የለም?
ደሞ ተከታዮችህ ሁሉ
ከየጎሬው እየፈሉ
ቁጣው ነው መቅሠፍት ያመጣ እያሉ
ጆሯችንን በመጽሐፈ ባልቴት፣ ኪሳቸውን በመባ ይሞላሉ።
ግን ምንድ ነው የሚያስቆጣህ
ጸሎት አልጎደለብህ፣ ምስጋና ውዳሴ አላጣህ
ደሞ እንኳን ኮሚኒስት ቻይና፣ መላው ዓለም በሞላ
እንኳንስ የሌሊት ወፍ፤ ሌቱን ጠቅልሎ ቢበላ
ለምን ይደብርሃል፣ አፒታይት ከሰጠኸው በኋላ
ያወላገድከው ቢጠለፍ፣ ያጣመምከው ቢሰበር
ውሉን ስቶ ቢመናቀር
ማነው ተጠያቂው ባክህ፣ ካንተና ካንተ በቀር።
እና ዛሬ ላይ አልጋየ ላይ፣ ተዳክሜ ተኝቼ
እንደ ኢዮብ እከክ ለብሼ፣ ተመስጌን እያልኩ እንድቀኝ
ፈገግ ብለህ ስትጠብቀኝ
እስኪበቃኝ ረግሜህ
እስክጠግብ አማርሬህ
እንደ ኢዮብ ሚስት፣ ልክ ልክህን ነግሬህ
ወደ ሌለህበት ዞሬ፣ ለዘላለም እተኛለሁ
ሥጋየን አራግፌ፣ እረፍቴን አገኛለሁ።
🔘በውቀቱ ከፈጣሪ ሊያጣለን እንደፃፈው🔘😁
አቤቱ ውሃን አየር ላይ ያረጋህ
ምድሪቱን በጠረባ የዘረጋህ
በጃርት ወስፌ ጠንቁለህ፣ ያሞራን ዐይን ያፈሰስህ
ካላጣኸው እጄ ጠባብ፣ ኤሊን ድንጊያ ያለበስህ
ካልቸገረህ ወጣትነት፣ አዳምን ባርባ አመት ያስረጀህ
በኅዳር በሽታ ዘመዶቼን የፈጀህ።
እንደምን ዝም ትላለህ፣ በቫይረስ ሲቀቀል ዓለም
በሰማይ ቤት እፍረት የለም?
ደሞ ተከታዮችህ ሁሉ
ከየጎሬው እየፈሉ
ቁጣው ነው መቅሠፍት ያመጣ እያሉ
ጆሯችንን በመጽሐፈ ባልቴት፣ ኪሳቸውን በመባ ይሞላሉ።
ግን ምንድ ነው የሚያስቆጣህ
ጸሎት አልጎደለብህ፣ ምስጋና ውዳሴ አላጣህ
ደሞ እንኳን ኮሚኒስት ቻይና፣ መላው ዓለም በሞላ
እንኳንስ የሌሊት ወፍ፤ ሌቱን ጠቅልሎ ቢበላ
ለምን ይደብርሃል፣ አፒታይት ከሰጠኸው በኋላ
ያወላገድከው ቢጠለፍ፣ ያጣመምከው ቢሰበር
ውሉን ስቶ ቢመናቀር
ማነው ተጠያቂው ባክህ፣ ካንተና ካንተ በቀር።
እና ዛሬ ላይ አልጋየ ላይ፣ ተዳክሜ ተኝቼ
እንደ ኢዮብ እከክ ለብሼ፣ ተመስጌን እያልኩ እንድቀኝ
ፈገግ ብለህ ስትጠብቀኝ
እስኪበቃኝ ረግሜህ
እስክጠግብ አማርሬህ
እንደ ኢዮብ ሚስት፣ ልክ ልክህን ነግሬህ
ወደ ሌለህበት ዞሬ፣ ለዘላለም እተኛለሁ
ሥጋየን አራግፌ፣ እረፍቴን አገኛለሁ።
🔘በውቀቱ ከፈጣሪ ሊያጣለን እንደፃፈው🔘😁
👍2
#ዛሬ_ቀኑ_ምንድነው?
፡
፡
#በሕይወት_እምሻው
ተንበርክኬ ነበር፡፡
በዚያ የጥቅምት ውርጭ፣ ከምሽቱ አራት ሰዐት ተኩል ላይ ከሰማይ በላይ እሪታዬን እያቀለጥኩ፣ቀዝቃዛው አስፋልት ላይ ተንበርክኬ ነበር፡፡ በብርድ በሚንገጫገጨ ጥርሶቼ መሃከል እጮኻለሁ፡፡ ጉሮሮዬ የተሰነጠቀ፣ ደረቴ የተተረተረ እስኪመስለኝ ድረስ እጮኻለሁ፡፡
በኋላ ሲነግሩኝ አደጋው ቦታ አምቡላንስ ደርሶ ልጄን አፋፍሶ እስኪወስደው ድረስ እንዲሁ ስጮኽ ነበር፡፡
ሆስፒታል ስንደርስ በጥድፊያ ልጄን በባለጎማ አልጋ እየገፉ ሌላ
ክፍል ወስደውት አላስገባም አሉኝ፡፡
አትገቢም አሉኝ፡፡
መድኀኒት፣ መድኀኒት የሚለው ኮሪደር ላይ ቆሜ ቀረሁ፡፡ በነጭ ካፖርት ውስጥ ወዲህ ወዲያ የሚራራጡ ሐኪሞች፡፡ ሰማያዊ ለብሰው እዚህም እዚያም የሚሉ ነርሶች፡፡ በየወንበሩ ላይ
አንገታቸውን ደፍተው፣ ጥርሳቸውን እያኘኩ የተቀመጡ ሰዎች፡፡
በአንቅልፍ የናወዙ አስታማሚዎች፡፡ አዲስ አደጋ ይዘው እየጮኹና እያለቀሱ ወደ “ ኢመርጀንሲ” ክፍል የሚበርሩ
አትገቡም እያሉ የሚከላከሉ ነርሶች፡፡ ሐኪሞች፡፡
በቆምኩበት የሆነውን ለማሰብ ሞከርኩ፡፡
እየሣቀ ነበር፡፡ እንቅልፌ መጣ ምናምን ብሎኝ፣ “አንተ እኮ ከእንግዲህ ትንሽ ልጅ አይደለህም... እስከ አምስት ሰዐት መቆየት አትችልም እንዴ...? ዳይፐር እንደገና መግዛት ልጀመር እንዴ?”
ስለው እየሣቀ ነበር፡፡ ያቺ ከአባቱ የወረሳት ዲምፕሉ ፣ ያቺ ፍቅፍቅ እያለ የሚስቃት ሣቁ፣ የግራ መጠምዘዣውን ይዤ ብቅ ከማለቴ በልጄ በኩል ጠርምሶት የገባው መኪና ላንድክሩዘር ነበር። ደማቅና የሚያጥበረብረው መብራቱ ፂርርርርርርር... ጩኸቴ፡፡ ግውውውውውው! ጭለማ፤ የልጄ የሲቃ ጩኸት፤ ጨለማ፡፡ በስሱ የሚሰማኝ የሰዎች ኡኡታ፤ ከአጥንቴ የተለየ
የመሰለኝ ሥጋዬ፤ ድንጋጤዬ፤ ጩኸቴ፤ ጨለማ፡፡ ደማቅ የሰዎች ጩኸት፣ በስመ አብዎች፡፡ አንገቴ ሲዞር፣ ከሶኬቱ ወጥቶ እንደ ጨርቅ የተንጠለጠለው የልጄ እጅ ከጆሮው የሚጎርፈው የደም ጅረት፤ ጩኸቴ፡፡ ተርፈዋል ብለህ ነው? በስመአብ! በስመአብ... ኧረ ለፖሊስ ደውሉ፡፡ ኧረ አምቡላንስ ጥሩ፡፡ በስመ አብ.... የሚሉ ድርብርብ ጩኸቶች፡፡ የሚያለቅሱ ሰዎች፡፡
ከዚያ እንደ ጨርቅ ጎትተው ሲያወጡኝ።
እኔን አወጡኝ፡፡ ደህና ናት፡፡ ተአምር ነው፡፡ ልጁ ግን ተጎድቷል፡፡
ምንም ሳትሆን ወጣች ምናምን ሲሉ ይሰማኛል፡፡
ልጄስ...? ልጄስ...? ልጄን...! ብዬ ስጮኽ ትዝ ይለኛል፡፡
የተከደነ ዐይኖቹ፡፡ ደም የለበሰው ግማሽ ፊቱ፡፡ ደም የተነገከረው
ደረቱ፡፡ ለብቻው የተንጠለጠለው ቀኝ እጁ፡፡ ልጄ!
አትግቢ ወዳሉኝ ዝግ ክፍል ስሮጥ ከወንድ የሚጠነክሩ ሁለት
ነርሶች ጠፍንገው ያዙኝ፡፡
“ልጄን...! ልጄን ልየው?” እያልኩ ሳለቅስ ከለከሉኝ፡፡
“እዚህ መጠበቅ አለብሽ. ሰርጀሪ ገብቷል፡፡ እዚህ ጠብቂ...”
አሉኝ፡፡ በብዙ ሰዎች የተሞላው መስኮት አልባ ስፊ ኮሪደር ውስጥ ተዉኝ፡፡ አብዛኛዎቹ ሰዎች ከብረት የተሠሩ የማይመቹ ወንበሮች ላይ ቁጭ ብለዋል፡፡ ግማሾቹ አቧራ፣ በአቧራ በሆነው ነጭ ወለል ላይ በግዴለሽነት ተዘርፍጠዋል፡፡ የመድኀኒትና የሰዉ ሽታ ተቀላቅሎ፣ የልጄ ምስል ተደምሮ ወደ ላይ አለኝ፡፡
እንደምንም መለስኩት፡፡
አንዲት ሴት ሁኔታዬን ዐይታ ይሁን መቀመጥ ሰልችቷት፣ በ “ነይ
እዚህ ተቀመጪ” እጆቿን ስታንቀሳቅስ፣ በድን አካሌን ይዤ
ከብረት ወንበሩ ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ፡፡ ከዚህ ቦታ፣ ከዚህ ሁኔታ ራሴን ብነጥል፤ ይሄን አስቀያሚ ቦታና ሁኔታ፣ ደመና ሆኜ ትንን ብዬ ብለየው ፤ ከጥቅምት ውርጭ
ጋር ተቀላቅዬ በረዶ ሠርቼ
ብተወው ምናለ? ከዚህ ሌላ የትም ቦታ ብሆን፣ ከዚህ ውጪ ምንም ነገር ቢደርስብኝ ምን ነበር?
“ልጄ..!”
እንደገና መጮኽ ጀመርኩ፡፡
ወንበሯን የለቀቀችልኝ ሴት ትከሻዬን ያዝ አድርጋ፣ “አታልቅሺ..ጸልዪ... ጸልዪ....” አለችኝ፡፡
ደመና ሆኖ መትነን የለም፡፡ በረዶ ሆኖ ከአየር መቀላቀል ፤ ሌላ ቦታ፣ ሌላ ሁኔታ ላይ መሆን እንደማልችል ዐውቃ መሰለኝ፡፡
“ጸልዩ....”
ለቅሶዬን ወደ ቀስታ እህህታ አውርጄ አካባቢዬን ቃኘሁ፡፡ እንደኔ በዝምታ የሚያለቅሱ፣ ንፍጥ የሚናፈጡ፣ እንባ የሚጠርጉ፣ እርስ በእርስ የሚጽናኑና የሚጸልዩ ብዙ ሰዎችን ዐየሁ፡፡
በእንባ የራሱ ዐይኖቼን ጨፈንኩ፡፡ ወዲያው ደግሞ ገለጥኳቸው፡፡
በሩ ጋር አንዷ ነርስ ከፖሊሶች ጋር ስታወራ ተመለከትኩ፡፡ በረጅሙ
ተነፈስኩ፡፡ በአየር ፈንታ እሳት ያስገባሁ ያህል ውስጤ ተቃጠለ፡፡ ውስጤ ነደደ፡፡
“ጸልዪ..” አለችኝ፡፡ አሁንም አጠገቤ የቆመችው ሴት፡፡
ከወንበሬ ተንሸራትቼ ወለሉ ላይ ተንበረከኩ፡፡
አንገቴን አቀረቀርኩ፡፡
ዐይኖቼን ጨፈንኩ፡፡
እጆቼን በእንባ የበሰበሰ ፊቴ ላይ አደረግኩ።
ከጸለይኩ ዕሥራ አምስት ዓመታት አልፈዋል፡፡ ለቀብር ካልሆነ፣
ለዝክር ወይ ለበዓል ቤተ ክርስትያን ከረገጥኩ ብዙ ዓመታት ሄደው
መጥተዋል፡፡ ከእናቴ ሞት በኋላ፤ የቱ ቀን ሚካኤል፣ የቱ ቀን ተክልዬ እንደሆነ አስቤ አላውቅም።
እና ምን ተብሎ ነው የሚፀለየው? አባታችን ሆይ ግማሹ ከጠፋብኝ ሰንብቷል ምንድነው የምለው? አባቴ
ሆይ... በሰማይ የምትኖር...? ዐይኖቼን ገልጬ ሴቲቱን ዐየኋት፡፡ እርጂኝ ዓይነት ዓየኋት
“ዝም ብለሸ ጸልዪ....” አለችኝ፡፡
እጸልያለሁ፡፡ መጀመሪያ ይሄን ሁሉ ጊዜ ስላልጸለይኩ፣ እግዜርን ስለተውኩ ይቅርታ እላለሁ ስለሃጥያቴ ሁሉ ይቅርታ እጠይቀዋለሁ፡፡ ከዚያ ግን... ከዚያ ግን፣ ልጄን ተውልኝ... ልጄን
አትውሰድብኝ እለዋለሁ.....
እንደሚባለው ምሕረቱ የበዛ ሩህሩህ ከሆነ፣ ልጄን እንዲያድንልኝ እማጸነዋለሁ፡፡
እያለቀስኩ መሬቱን መሳም ጀመርኩ፡፡
እየጮኹ... እያጉረመረምኩ መጸለይ ጀመርኩ፡፡
“አምላኬ ሆይ.... ልጄን ተውልኝ... ልጁን አድንልኝ.... እጾማለሁ፡፡አስቀድሳለሁ፡፡ እጸልያለሁ፡፡ብቻ ልጄን ተውልኝ አድንልኝ.... ዐርብ እሮብ እጾማለሁ፡፡ ዐብይ ጾምን እጾማለሁ። ደሃ በስምህ አበላለሁ፡፡ አስቀድሳለሁ... አንተ ግን ልጄን ተውልኝ...አምላኬ እባክህ ልጄን አድንልኝ....
እግዚአብሄር ሆይ.... ልጄን ካዳንክ ባሪያህ እሆናለሁ፡፡እንደፈቃድክ እሆናለሁ፡፡ ያልከኝን አደርጋለሁ......”
አልኩና ቀና ብዬ በእንባማ ዐይኖቼ አሁንም ቆማ የምታየኝን ሴት ዐየኋት፡፡
ዛሬ ምንድነው?” አልኩ በጎርናና ድምፅ፡፡
“እ?” አለችኝ፣ ደንገጥ ብላ፡፡
“ዛሬ...ቀኑ ምንድነው?”
"አስራ ዘጠኝ ገብሬል ነው"
እንደገና መሬት ላይ ተደፋሁ፡፡ ከንፈሮቼ በእንባዬ ታጥበው ጨው ጨው ይሉኛል፡፡
“ገብርኤልዬ... የኔ ገብርኤል... ልጄን አድንልኝና በዓመት ቁልቢ አልቀርም፡፡ በየወሩ ሱቄን ዘግቼ አከብርሃለሁ፡፡ እዘክርሃለሁ፡፡መልአኩ ገብርኤል ልጄን አድንልኝ...አድንልኝ...”ሴቲቱ ጎትታ አነሳችኝ፡፡ ቆምን፡፡
“ይበቃል... በቃ በቃ...” ከእምባዋ እንደምትታገል፣ በእንባ
በተሸፈኑትና እንደ እሳት በሚያቃጥሉኝ ዐይኖቼ ዐየሁ፡፡ ልክ እንደ ቅርብ ዘመዴ አቅፌያት አለቀስኩ፡፡
“በቃ... በቃ.... አይዞሽ...” አለችኝ፡፡
ብዙ ደቂቃዎች አለፉ፡፡
ነርሶቹ ምነው ጠፉ? ዶክተሩስ ለምን ዝም አለኝ? አዲስ ለቅሶ ጀመርኩ።
ሴቲቱ ታባብለኛለች፡፡
የስለት ቃሌን ለገብርኤል እደግማለሁ፣ መሬት እንበረከካለሁ፤
እቆማለሁ፤ ወደ በሩ እሄዳለሁ፤ ነርሶቹን ስለልጄ እጠይቃለሁ፤ጠብቂ እባላለሁ፤ አለቅሳለሁ፤ እቀመጣለሁ፤ እነሳለሁ፤ ተምበርክኬ ለገብርኤል እሳላለሁ፡፡ነፋስ ያስፈልገኛል፡፡ነፋስ.ነፋስ ያስፈልገኛል፡፡ ወጥቼም እንዳልወጣ ሐኪሞቹ መጥተው ቢያጡኝስ? እዚያ ኮሪደር ላይ
ተቀምጩ ትንፋሽ አጥሮኝ የልጄን

መጨረሻ ሳልሰማ እንዳልሞት
በመስጋት ትልቁ በር ሥር ሄጄ ኩምትር ብዬ ተቀመጥኩ፡፡
የሚያንዘረዝር ብርድ ተቀበለኝ፡፡ የድግስ ግልጥልጥ ቀሚሴ አላዳነኝም፡፡ ግን ዝርፍጥ ባልኩበት ቀረሁ፡፡ አየና የተቀመጥኩበት ቀዝቃዛ ሴራሚክ ወለል የሰውነቴ አካል እስኪመስለኝ ተቀመጥኩ፡፡
ለምን ያህል ሰዐት እንደቆየሁ ሳላውቅ ስታጽናናኝ የነበረችው ሴት መጥታ በብርድ የገነተረ ክንዴን ስትነካ ነቃ አልኩ፡፡
“ሐኪሙ እየፈለገሽ ነው... ነይ...” አለችኝ፡፡
ብርክ ያዘኝ፡፡
ሐኪሙን ሲጠብቅ እንዳልቆየ፣ ሰው ሐኪሙ መጣ ስባል ብርክ ያዘኝ፡፡ ለሰዐታት የጠጣሁት ብርድ ሰውነቴን ያንዘፈዝፈው ያዘ፡፡
“አይዞሽ ነይ...” ብላ፣ ጎትታ ስታስገባኝ ትዝ ይለኛል፡፡
ከዚያ የማስታውሰው የሐኪም ነጭ ጋወን የለበሰ ጢማም ሰውዬ፤ ጉንጮቼን በጥፊ ዓይነት ሲመታቸው ነው፡፡ እጆቼን ሲያነቃንቅ፣
“ትሰሚኛለሽ... የኔ እመቤት? ትሰሚኛለሽ?” ሲለኝ፡፡
በጢም የተከበሰ አፉን ፈራሁት፡፡ከአፉ የሚወጡትን ቃላት ክፉኛ ፈራሁ፡፡ ልሽሸው፣ ሊነግረኝ ያሰበውን መርዶ ላመልጥ ፈለግኩ፡፡ግን እሱም ነርሶቹም ከበውኛል፡፡ ብረት አልጋ ላይ ተኝቻለሁ፡፡
ራሴን ስቼ ነበር?
ማውራት ጀመረ፡፡ አቅመ ቢስ ሆኜ መስማት ጀመርኩ፡፡
“ልጅሽ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል፡፡”(መልአኩ ገብርኤል፣ ቁልቢ እስክሞት ድረስ ከነልጄ አልቀርም)
"ብዙ ደም ፈሶታል።"(ተአምሩን ላገኘሁት ሰው ሁሉ መንገር አላቆምም)
“በቀኝ በኩል የደረሰበት ጉዳት አስከፊ ነው፡፡” (አምላኬ ሆይ፣ ካለ
መጽሐፍ ቅዱስ አላነብም፡፡ ላንተ ውዳሴ ከተዘመሩ መዝሙሮች
ውጪ ጆሮዬን ሙዚቃ አላሰማም፡፡)
“ግን ተአምር ነው ....እግዜር በተአምሩ አትርፎታል፡፡ አይዞሽ...
ይድናል... ለተወሰኑ ቀናት ለጥንቃቄ አይ ሲ ዩ ይቆያል... ግን የሚያሰጋ ነገር የለም፡፡”
ልጄ አልሞተም፡፡
ልጄ አልሞተም፡፡
ልጄ አልሞተም፡፡
ዶክተሩ ፈገግ ብሉ ያየኛል፡፡ ያለኝን ለመረዳት እየታገልኩ መሆኑ ገብቶታል፡፡
በስምንተኛው ቀን ልጄ ከአይ ሲ ዩ ወጥቶ መደበኛ ክፍል ተኝቷል፡፡
እኔ ትንንሽ እግሮቹን እየነካካሁ አልጋው ላይ ተቀምጫለሁ፡፡
የምታምር የጠዋት ፀሐይ በመዳን ላይ ያለ ፊቱ ላይ ታበራለች፡፡
እንባ ባቀረረ ወይኔ ጉንጮቹን ዐያለሁ፡፡
እማዬ...” አለኝ ቀስ ብሉ፡፡
“ወይ ልጄ...”
ዛሬ ቀኑ ምንድን ነው?”
ፈገግ አልኩ፡፡
“ምነው እማዬ?” አለ እሱም ፈገግ ብሎ፡፡ ያቺ ከአባቱ የወረሳት
ውብ ዲምፕሉ በትንሹ ፊቱ ላይ....
“መድኀኔዓለም ነው ልጄ... ዛሬ የዓመቱ መድኀኔዓለም ነው....”
አልኩ፣ በአልጋው በስተግርጌ ካለው ኮመዲኖ ላይ፣ ከጠዋት ጀምሮ
የሚበራውን ሻማ በእንባ በተሞሉት ዐይኖቼ እያየሁ፡፡
✨ጨረስን✨

#ላጣሽ_አቅም_አጣሁ
ዓለማዊ ልቤ፥ለበሰልሽ ዳባ፥ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ፥ የጠፋብኝ እንባ፥ ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣሽ አቅም አጣሁ፤
የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን ገድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብየ ነበር፥ ቄስ አንዳስተማረኝ
አንቺን አጣሁ ብየ፥ ማመኑ ቸገረህ
ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤
ልረሳሽ አልቻልኩም፥ ልረሳሽ እልና
ፊትሽን አትመሽ፥ በየብስ በደመና
ከንፈርሽ ያውና
ፈገግታሽ ያውና
ውብ ዓይንሽ ያውና።
ዓለማዊ ልቤ፥ለበሰልሽ ዳባ፥ምናኔ ተመኘ
በናቴ ቀብር ላይ፥ የጠፋብኝ እንባ፥ ፊቴ ላይ ተገኘ
ላጣሽ አቅም አጣሁ፤
የሳምሶንን ገድል
ያላዛርን ገድል
ያቡየን ተአምር
ተቀብየ ነበር፥ ቄስ አንዳስተማረኝ
አንቺን አጣሁ ብየ፥ ማመኑ ቸገረህ
ክረምቱ ጨከነ
ጨላለመ ጋራው
በረዶና ጭፍራው
ከዋሻቸው ወጡ
ዛፎች ተመለጡ
ከምልአት ጎደሉ
ላባቸውን ያጡ
አሞሮች መሰሉ፤
ልረሳሽ አልቻልኩም፥ ልረሳሽ እልና
ፊትሽን አትመሽ፥ በየብስ በደመና
ከንፈርሽ ያውና
ፈገግታሽ ያውና
ውብ ዓይንሽ ያውና።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM