አትሮኖስ
286K subscribers
120 photos
3 videos
41 files
571 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ታዲያስ_ምን_አዲስ_ነገር_አለ?

ታዲያስ ምን አዲስ ነገር አለ?

ጀንበር በምራብ ወጣች
ሮብ ሰኞን ተከተለ
ኦጋዴን ላይ በረድ ፈላ
ስሃራ ላይ ዝናብ ጣለ?

ታዲያስ ምን እዲሰ ነገር አለ?

ኑሮ ታምና ተሻለ
ሸክሙ ከትናንት ቀለለ
አገር ጣጣውን ፈታ፥ ወይስ ጣጣውን አከለ
ዜጋው ራሱን ቻለ፥ ወይስ ራሱን ደለለ
“የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን” እያለ?

ታዲያስ ምን አዲስ ነገር አለ?

ማን ነበሩ እትየ እንትና
መቸም የድሀ ስሙ፥ ለትውስታ አይበቃምና
ምነው እኒያ እንኳ
በቁጥር ለማይሰፈር አመት
የሚጎበኝ እንጂ የማይሸመት
የቲማቲም ጉልት ዘርግተው
እንደብቅል ቀኑን ሙሉ፥ ከጸሐይ ሥር የሚስጡ
ሙያቸውን ለወጡ
በሙያቸው ተለወጡ
ከችግራቸው ወጡ
ወይስ በችግራቸው ተዋጡ
ከብረው መኪና ገዙ፥ ወይስ ሰመኪና ተዳጡ?
#ማንም_ግድ_አይሰጠው

ቂጡን ዙፋን ላይ፥ ስለዘፈዘፈ
በጭቦ በኖረ፥ ድሀ እየዘረፈ
ንጉሥ የተባለ፥ የተቀባ ሌባ
ወትሮ ይወደሳል
ሚያመልከው አያጣም፥ ያውም በግዜር አምሳል፤

ግና ለንባሩ
ከላይ በትረ መንግሥት፥ ለሚቀጠቅጠው
ከታች የማጣት ፊት፥ ለሚገላምጠው
ማንም ግድ አይሰጠው፤

መቸም በዚች ዓለም፥ ታሪክ የሚያደላው
ቅልጥም ለሚሰብረው
እንገት ለሚቀላው
መንገድ ሲሰራለት፥ እግር ለሚቆርጠው
ሐውልት ሲሰራለት፥ ሐውልት ለሚያፈርሰው
ከማውደም በስተቀር፥ ተሰጥኦ ለሌለው
ስጦታ የለሽ ሰው፤
ሕይወት ለሚመልሰ፥ ሕይወት ላመለጠው
ለወጌሻው ግና
ማንም ግድ አይሰጠው፤

ለሰላም ዝምታ፥ ላምባጓሮ መገን
ባዝማሪ ልሳን ላይ፥ ነፍሰ ገዳይ ሲገን
ባቆላማጭ ምላስ፥ ፋኖ ሲመሰገን፤

ከሴት ማሕፀን አፍ
ከህላዌ ደጃፍ
ጨቅላ ተቀብላ
እትብት ለምትቆርጠው
ለዚያች አዋላጅ ሴት
ማንም ግድ አይሰጠው።
#ሙሾ_ላመለጠ_ወጣትነት

ሳይደምን ይዘንባል
ይዶፋል
ከደጃፌ ግርጌ፥ የሕይወት ጎርፍ ያልፋል፤

የከንፌ ርጋፊ
አንድ የላባ ነዶ
ያካሌ ቅራፊ
የቀረ ተጎርዶ
ተጠርጎ ሲወሰድ፥ በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ፤

ሲጋልብ በፊቴ፥ ይህ የውሀ ሰጋር
ጀምበሬን አየኋት
ተጠርጋ ሰትሄድ፥ ከሰርዲን ጣሳ ጋር

የልጅነት ቅርሴ
ድዴ ያባረራት፥ ያች የወተት ጥርሴ
ካሮጌ ቆርኪ ጋር፥ አብራ ተቀላቅላ
ባረፋ ተከባ፥ በጎርፍ ጀርባ ታዝላ
ሰትሄድ እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ፤

የመጀመርያዋ፥ የጉንጨ ላይ ቡግር
የመጨረሻዋ፥ የራሴ ላይ ጠጉር
ከሳር ከትቢያው ጋር፥ እንደተቃቀፉ
በጎርፉ ጀርባ ላይ፥ እየተንሳፈፉ
እንደዋዛ ሲያልፉ
በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ።
#የመኖር_ትርጉሙ

የመኖር ትርጉሙ
የንባ ቅብብል ነው፥ በትውልዶች ማህል
አባትህ ያነባው፥ ላንተም ይደርስሃል፤
ስው የሆንሁ ለታ፥ ደርሶኛል ይህ እጣ
አልቅሼ አንደገባሁ
አስለቅሼ ልውጣ።
#አስታራቂ_የለም

ጠብ ምድርን ባይሞላት
አቤል ባይፈጠር
አቤል ያቤል ጠላት
አቤል የራሱ ጠር
አንድ ሰው ከሁለት፥ ተከፍሎ ሲፋለም
ሸምጋይ
ወይ ገላጋይ
አስታራቂ የለም።
Forwarded from አትሮኖስ (...) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንደምነሽ_ሸገር

እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የቤት አከራየ፥ የጋሽ ጣሰው አገር
እንዱ የሚተከልሽ
ሌላው የሚነቅልሽ
የዘመቻ ድንኳን፤

ቡግርና ችግር፥ ካባቴ ወርሼ
ብኖርብሽ እንኳን
የማልቀየምሽ
ሁሌ የማልምሽ፣

Oh, my God ይመስገን
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤

ከፊል ሩዝና፥ ከፊል ጤፍ እቡክቼ
እንጀራ ሚመሰል፥ ሰጋጃ በልቼ
አዋጅና ዜና፥ ባይፎኔ ሰምቼ
ሐሜት ሲናፍቀኝ፥ በፓልቶክ አምቼ
ጥቃት ሲበዛብኝቱ ፌስቡከ ላይ ሸፍቼ
በኮመንት ሩምታ፥ ጠላቴን ደፍቼ
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤
እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የማይበገረው
ወር እየጠበቀ፥ የሚያንገራግረው
የቤት አከራየ፥ የጋሽ ጣሰው አገር፤
የከሰመው ወንዝሽ
የነጠፈው ወዝሽ
የሚታየው ነጥፎ
እንደምነው ጣፎ
እንዴት ነው ቀበና
እስቲ ድንጋይ ላጥምድ፥ መረብ ልጣልና፤

ልከ እንደነ ፓሪሰ
እንደ ለንደን ሁላ
ፏፏቴም ባይኖርሽ፥ ሽቅብ የሚፈላ
ምንጭሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ቱቦ፥ የወጣ ሰገራ፥ ሰንጥቆሽ ይፈሳል፤

እንደምነሽ ሸገር
የቅጠላቅጠል፥ የፍራፍሬ አገር
አንድ ዘለላ ሙዝ፥ ልጠሽ ባታበይኝ
በሙዝ ልጣጭ ጠልፈሽ፥ ምታንከባልይኝ
አሳድገሽኛል፥ በማርና ወተት
የተሞላ ተረት
እየተረከሽልኝ
ጥማቴን በጥማት እያረካሽልኝ፤

እንደምነሽ ሸገር
Oh my God ይመስገን
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤

ሰርቼ ቀፍየ
ሲነጋም ከፍየ
ሲመሽም ከፍየ
ሥጋ ምታወፍር፥ ነፍሶ የምታሳሳ
ዘናጭ አልጋ ሰጥታ፥ እንቅልፍ የምትነሳ
አገር ላይ ተጥየ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ማንባት_ነው_ያሰኘኝ

ማንባት ነው ያሰኘኝ
ማልቀስ ነው ያማረኝ
ከቁጭቴ ጋራ፥ ወትሮ ከመታገል
የንባ ማድጋየን፥ ሰብሮ መገ
ላገል
ማልቀስ ነው ያማረኝ፤

ያደራ ሳንዱቄ፥ ሲሰበር ከዳኑ
የባልንጀርነት፥ ሲጣስ ቃልኪዳኑ
መጋኛ ሲመታው
ዝምድና ሲከፋ
ፍቅር መሬት ከድታው
ባፍጢሙ ሲደፋ
የዳመነ ፊቴን፥ መዳፌ ውስጥ ልቅበር
የንባ ጋኔን ልስበር፤

እኔ
እንደ በሬ ያረስሁ
እህል የጎመጀሁ፥ ዝማምን የጎረስሁ
እዝመራ ያደረሰው
ፍሬውን ያልቀመስሁ፤

እኔ
መከራን በበርሚል፥ መጥናናትን በፍኝ፥
ከዘመን ያተረፍሁ
እንቧይና ሙጃ፥ የወረሰው ሳሎን፥
ሳልፈልግ የታቀፍሁ
ቀስተ ደመናዬ፥ ምድጃ ሥር ወድቆ
እፍኝ አመድ ዝቆ፥ እፍኝ ትቢያ ቅሞ
ጥላሸቱን ጠግቦ፥ እድፍ ተሸከሞ
ኖህ ከነታሪኩ
ከነታይታኒኩ
እባሕር ውስጥ ሰጥሞ፥ ለማየት የበቃሁ
ፊቴን እየፈጀሁ፥ ደረት እየደቃሁ
ማልቀስ ነው ያማረኝ።
👍1
#ጠብ_አና_ጥሰብ

“ተዋጋ ብሎ ሲሰጠው ጋሻ
ለናቱ ሰጣት፥ የእበት ማፈሻ”
( አገርኛ ቀረርቶ)
የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ
ጠብን መፍራት
ጦርን መግራት
ከጋሻ፥ የእበት ማፈሻ መሥራት።
#ካንቺ_ጋራ

ካንቺ ጋራ ሆኜ፤ የኖርኳቸው ጊዜያት
ያሳለፍኩት እድሜ
ጣፋጭ እንደኃጥያት
አጭር እንደጳጉሜ፤

አንቺ በላባ እግር፥ ደመና ላይ ቆመሽ
ሺ ሌሊት ከፊቴ፥ ሺ ሌት ከኋላየ
ኮከቡን በሞላኝ በወረንጦ ለቅመሽ
ነዛሽው ስላየ፤

ምንም እንኳ ሕዋው፥ ብርሃን ባያንሰው
ግርዶሽ ሆኖት ቆሟል፥ ይሄ ሰው ለዚያ ሰው
ግርዶሽ ሲነባበር፥ ኀይል የለው ባንች ፊት
መጋረጃው ሆነ፥ የብርሃን ወንፊት።
👍1
#ይድረስ_ለጥም_ሚኒስትር

ይድረስ ለጥም ሚኒስትር
ላልጠጣነው ለሚያስከፍሉ
ጥም በቧንቧ ለሚያከፋፍሉ
እንዴት አሉ
አንዴት ዋሉ፤
አለሁ በከፍተኛ ጥም
ባገሬ ተስፋ ብቆርጥም
በጅቡቲ አየተጽናናሁ
አቧራየን እየጠጣሁ
ጠጠሮቼን አየሸናሁ፤
ዘለቅሁት ይህን አመት
የተሸመነ እድፍ ለብሼ
እንደ ማለዳ ድመት፥ ፊቴን በምራቄ አብሼ
ሺህ ጀሪካን ከፊቴ
ሺህ ጀሪካን ከኋላየ፥ አግተልትየ አሰልፌ
ምድረ በዳውን በመስኖ፥ ቤቴ ድረሰ ጠልፌ።
#ለጤዛ_ተዋድቀን!

እድሜያችን ሰባ ነው፤ ቢበዛም ሰማንያ
ይህም ኑሮ ሆኖ፤ ጠዋት ማታ ፍልሚያ
አንዱ ካንዱ ጥዋ፣ ጥቃት የቀመሰ
በየደጃፉ ላይ፣ ምሽግ እየማሰ
ጦር እንደ ቄጤማ፣ እየነሰነሰ
መንደሩን ሸንሽኖ፣ ባጋም እሾህ ቅጥር
ወገን እያስለየ፣ ባሰለፈን ቁጥር
ጤናችን ሲሸረፍ
ቀናችን ሲዘረፍ
የት ሸሽተን እንትረፍ
የት ገብተን እንረፍ?
በዶፍ ዝናብ አገር፣ ለጤዛ ተዋድቀን
ሰላም እንደራበን፣ ደስታ እንደናፈቀን
ትግላችን ሰልፋችን፣ ያከትማል አንድቀን!

🔘በእውቀቱ ስዩም🔘
#መአዛሽ_ፈወሰኝ

ጎራዳ አፍንጫየን
ጎራዴ እፍንጫየን
ከሰገባው ስቤ
ስምግሽ ቀርቤ
አንገትሽ ሽነት ዛፍ
ጡትሽ ደብረ-ከርቤ

እፎይ!!!

እንዲያው ሲፈርድብኝ፥ ቤቴ አዲስ አበባ
ሰማዩ ጥንብ ነው፥ መሬቱም አዛባ
ዓይን ጆሮ ምላስ፥ ለኑሮ ሳያንሰኝ
ምን በድየው ጌታ፥ አፍንጫ ለገስኝ
እያልሁኝ ሳማርር፥ አንቺን ልኮ ካስኝ
መዳኒት ሆነና፥ መእዛሽ ።ፈወሰኝ
#ላንድ_መስቲካ_ሻጭ_ብላቴና

በደብተርሽ ምትካ፥ ትንሽ ሱቅ ታቅፈሽ
ካልፎ ሂያጅ እግር ሥር፥ እንደ ድንቢጥ ከንፈሽ
ጋሼ ግዙኝ ስትይ፥ አንጋጠሽ ወደ ላይ
ለጉድ ተጎልቼ፥ ምታደርጊውን ሳይ
ራሴስ ይታመም፥ ምላሴን ምን ነካው
ግራዋ ይመሰል፥ መረረኝ መስቲካው፧

አፈር ጠጠር ለብሶ፥ በዶዘር ተድጦ
መለኩ ከነጎርፉ
ሰማይ ከነዶፉ
ለጌቶች ተሸጦ
አተር ነው አያሉ፥ አፈር ዘግኖ መፍጨት
ገነት ነው አያሉ፥ መስክ ላይ መፈንጨት
ጠበል ነው እያሉ፥ ተጎርፉ መራጨት
ይህንን ማን ሰጥቶሽ
ገና በልጅነት፥ ልጅነት አምልጦሽ፤

በምቢልታ በዋሽንት፥ በከበሮ ታጥሮ
ሰክራር ተማግሮ
በቆመ ከተማ
እምባሽ ቅኝት የለው፥ ለሰው አይሰማ፤
ጠዋት የፎከረ፥ ቀትር ላይ ሲረታ
ዛሬ ዝሎ ሲወድቅ፥ ትናንት የበረታ
ኑሮን ያህል ሸከም ያላንቀልባ ሲያዝል
ምን ጸጋ ለብሶ ነው፥ ትከሻሽ የማይዝል።
1
#ቅድስትና_ትዕግስት


#በሕይወት_እምሻው


ቅድስት ልክ ስምንት ሰዐት ከሩብ ሲል ትዕግስት ቤት ደረሰች፡፡
“ውይ ቅድስትዬ....! ምነው እንዲህ ጠቋቆርሽ....? ፀሐይ እንኳን የለ ዛሬ....” አለች፣ትዕግስት አራት ጊዜ ጉንጭዋን ስማት....

“ኧረ ተይኝ ባክሽ... ለእንደኔ ያለ ሰው ከነዚያ ሴቶች ጋር ሦስት ሰዐት ሙሉ ስለ ልብስና ጫማ ማውራት ራሱ፣ ከሰባት ፀሐይ በላይ አያከስልም?" አለች ቅድስት፣ ሶፋው ላይ ዝርፍጥ ብላ እየተቀመጠች....

እናም፣ በተገናኙ ቁጥር የሚያደሩት ተመሳሳይ ወሬያቸው በእንዲህ
ሁኔታ ተጀመረ፡፡

“አይ ለእኔ ነው ስለነሱ የምትነግሪኝ ቅድስትዬ? እኔስ ምናቸው አስመርሮኝ ብረንች(ይቺ ቃል ግር እንዳትላቹ በእንግሊዘኛ ብሬክ ፋስትን ከ ላንች ጋር አዳቅሎ የተፈጠረ ነው በኛ ደሞ ቁምሳ ማለት ነው) መምጣት ተውኩና!”

“ደግ አደረግሽ... እኔ የምለው? ማስተርስ ድረስ የተማሩ ሴቶች ከልብስንና ከወንድ ውጪ ሌላ ነገር ማውራት አለማቻላቸው አያሳዝንም? በጣም ያሳፍራል እኮ!"

“በጣም እንጂ....! ዐሥር ሴት ሚኒስትር ቢሾም ታች ያለነው ሴቶች ትላንት ስለገዛነው ነገ ስለምንገዛው ልንገዛ ፈልገን ስላጣናው ብቻ ምናወራ ከሆነ፣ ይህች ሀገር እንዴት ብላ ቀና ትላለች...? ሲንፏቀቁ መኖር እኮ ነው!"

"ጎሽ...እኔ እኮ አንቺ ጋር መምጣት የምወደው ለዚህ ነው....ተንፈስ ስለምታደርጊኝ... ቁም ነገር ስለምታዋሪኝ እኮ ነው አንቺ ጋር መምጣት ደስ የሚለኝ ቲጂዬ!”

“እኔስ ብትይ....! እሺ..... ዛሬስ ምን ተፈጠረ ታዲያ?”

“ምን አዲስ ነገር ይፈጠራል... ያው ሴሞ ሴሞ ነው...ሃሜት ሃሜት... ወሬ... ሰው ቡጨቃ... እይው የገዛሁትን ልብስ.... ይሄ ሽቶ ደስ አይልም...? እገሊት ጂም ጀመረች... እንትና ዮጋ ጀመረች
ይሄው ነው ቲጂዬ!”

“አይገርምም...ዘለዓለም ያው ናቸው... ዘለዓለም..ማፈሪያዎች!”

“እህስ!...ዛሬ ደግሞ ያቺ ሶሎሜ መጥታ ጭራሽ ስትጠብሰኝ አረፈደች.. ደህና ተገላግለናት ነበር፡፡”

“መጣች እንዴ? ዱባይ ቫኬሽን ላይ ነኝ ምናምን ብላ ስታናፋ አልነበረም እንዴ?”

“እንግዲህ ያ የግፍ ዶላር ቶሎ አልቆ ይሆናላ! ወር ሳይሞላት ተመለሰች!”

“አዬ! ለዚህችው ነው ያ ሁሉ ጉራ! ...ግን አንቺን ምን አርጋ አናደደችሽ ቅድስትዬ?”
“ኧረ... ተይኝ! ገና በሥርዓት እንኳን ሳልቀመጥ እየሮጠች መጥታ ... 'ቶፕሽ ያምራል... እኔ የዛሬ ሁለት ዓመት በአራት መቶ ብር ገዝቼው ነበር... በቢጫው አለኝ... አሁን ግን ፋሽን ስላለፈበት ለሠራተኛዬ ሰጠኋት አትለኝም?”

“አታደርገውም!”

“አደረገችው እንጂ ትግስትዬ!አደረገችው”

“እና አንቺስ ዝም አልሻት?”

“ማ? እኔ ቅድስት እንዲህ ባደባባይ ሰድባኝ ዝም የምላት ይመስልሻል?”

“እና... እና ምናልሻት?”

“የኔ እናት... ተማስሉብሽ ይሆናል... ይሄ ሌተስት ፋሽን ነው... የጣሊያን እቃ ነው! የገዛሁት ደግሞ አንድ ሺህ ስምንት
መቶ ብር ነው አልኳታ!”

“ወይኔ አንቺ.. አንጀት አርስ እኮ ነሽ!”

“ታዲያስ...የሆነች ባላገር..ትላንት ብረንች ማለት አቅቷት፣ብራንች የምትል ሴትዮ፤ አንዴ ዱባይ ሄጄ መጣሁ ብላ
ትላጥብኛለች እንዴ?”

“ሃሃ... አይ ቅድስት!”

“ይልቅ እነሱን ተያቸውና ቲጂዬ የሚበላ ነገር አለሽ? ሁሉም ሰው ዳይት ላይ ነኝ ምናምን ብሎ ደህና ነገር አልበላሁም፡፡”

“ተይ እንጂ...! ዛሬም ዳይት ላይ ናቸው?”

“ታዲያስ! ለተቆራረጠ ሙዝ ሰማንያ ብር ይከፍላሉ. ዳይት ላይ ነኝ... መቀነስ አለብኝ ቅብጥርሶ ይላሉ፡፡ ምናለ ስለአንጎላቸው እንዲህ ቢጨነቁ......?”

“እኮ...! እና ታዲያ ምን ላምጣልሽ?”

“ሥጋ...ቅባት ያለው ነገር ምናምን... አታምጪብኝ! ትንሽ ጨምሬያለሁ ሰሞኑን ደግሞ...”

“ኧረ ተይ! ምንም አልጨመርሽም ቅድስትዬ! እንደውም ሳትከሺ አትቀሪም...”

“አይ ቲጂዬ...ቦዲ ሼፐር አርጌ ነው... ቦርጩን ጥፍንግ አድርጎ ስለያዘልኝ ነው...”

“ፓ! አሪፍ ነገር ነው ባክሽ... የት አገኘሽው? እኔ ፈልጌ ፈልጌ
የሚሆነኝ አጣሁ...” "መድኀኔ ዓለም ሞል ግራውንድ ፍሎር ላይ የሆነ ቤት አለ....
መዓት አላቸው... ዘጠኝ መቶ ብር ነው የገዛሁት... ብዙ አይመችም
ግን ቢያንስ ይሰበስብሻል... አብረን ሄደን ትገዣለሽ ሰሞኑን....”

“እሺ... አስታውሺኝ በቃ...ያስፈልገኛል.... በይ በቃ ሽሮ ላምጣልሽ እንግዲህ....”

"እሺ. ..ቲጂዬ..."

ቅድሰት የቀረበውን ሽሮ መብላት ጀመረች፡፡

“ውይ ቲጂዬ! ሲጣፍጥ ግን ቅቤ ሞጀርሽበት!”

“ሃሃ ... ለዚያ እኮ ነው ሚጣፍጠው...”
“ልቀንስ እያልኩሽ ቅቤ ትግችኛለሽ አይደል... አንቺ ምን አለብሽ?”

“ብዪ ባክሽ... ከልኩ አያልፍም...”

“ምን? ቦርጭ?”

“አዎ...."

“ሃሃሃ!”

“ኧረ ቅድሰትዬ ሳልነግርሽ... ዮጋ እኮ ጀመርኩ ቀጥ አላልኩብሽም ትንሽ?”

“ዮጋ?”

“አዎ...”

“ጎበዝ ነሽ ልጄ... እኔ አንዴ ከሰኒ ጋር ጀምሬ እናቴ... ሁለመናዬ ተላቀቀ፡፡ እሱን ለመጠገን አጥሚት እና መረቅ ስበላልሽ ነው ይሄን ቦርጭ እዚህ ያደረስኩት ቲጂዬ!”

“ሃሃሃ... ቀልድሽ እኮ ደስ ሲለኝ ቅድስትዬ!”

“አሹፊ አንቺ... ይልቅ ማን በጣም እንደከሳ ገምቺ...”

“ማ?

“እሌኒ!”

“እሌኒ እሌኒ? እሌኒ መርሻ?”

“እህ!”

“እንዴ? እንዴት አርጋ ከሳች በናትሽ?”

“ሙግግ ብላ መጣች ዛሬ... በሳምንት ሁለት ኪሎ እየቀነስኩ አሁን ዐሥራ ሁለት ኪሎ ቀንሻለሁ አለችን...”

“ተይ ባክሽ....! ያን ሁሉ ሰውነት እንዴት አድርጋ ናደችው በናትሽ?”

“የሆነ ቲቪ ላይ የሚታይ የዳይት ሾው አለ አሉ... እሱን አይቼ ሄጄ ነው አለችኝ...”

“ምን ቲቪ ላይ? እዚህ አገር?”

“አዎ....”

“እና ሄዳ ምን አደረጉላት?”

“ምግብ መጥነው ይሠሩልሻል አሉ... “በወር አራት ሺህ ብር እከፍልና ምግቤን ይሠሩልኛል... አሽገው ቤቴ ድረስ አምጥተው ይሰጡኛል' አለችኝ...”
“ተይ እንጂ... ምን ቲቪ ነው ልጄ?”

ፋና መሰለኝ...”

“ለነገሩ እኔ እንዲህ ያለ ነገር ብዙም አይመቸኝ... ግን መቼ መቼ
ነው የሚታየው አለችሽ?”

“እንጃ... እሁድ መሰለኝ... ብቻ ምሳ እና እራት ዐሥራ ሁለት መኮረኒ ተቆጥሮ ነው የሚሰጠኝ ብላ አሳቀችኝ!”

“ሃሃሃ... አትይኝም?”

“ሙች!”

“እና ግን አከሳት?”

“በጣም... ምግቡ እህል ቅጠል አይልም፤ ግን ካከሳኝ ምን ቸገረኝ
ምናምን አለችኝ...”

“ይገርማል... አምሮባታል በይኛ!”

“ያው መቼስ... ትንሽ ሙግግ ብላለች፣ ረኀብተኛ ነው የምትመስለው ፤ ግን ቦርጭዋ ጠፍቶላታል፡፡ ለነገሩ ዛሬ ዕድሜ
ለብራዚል “ሂውማን ሄር የማታምር ሴት አለች?”

“ልክ ነሽ እሱስ... ሂውማን ሄር ሴቱን ሁሉ እኩል አደረገው እኮ... ምን ዋጋ አለው... ጸጉር ጭንቅላት አይሆን!”

“እኮ!”

“የሚገርመኝ ግን ብር ኖሯቸው እንኳን ደህናውን አይገዙም እኮ...የኔን ዕይው አሁን ከጣልያን ነው ያስመጣሁት... ይኸው ሁለት ዓመቱ ንቅንቅ አላለም... ከገዛሽ ደህና ነገር ነው... የሚልከሰከስ
ሰው አልወድም እኔ...”.....

ማታ እንጨርሰው

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም። 🙏
👍2
#ቅድስትና_ትዕግስት (መጨረሻው ነው)


#በሕይወት_እምሻው


“እሺ... ሌላስ ምን አዲስ አለ ታዲያ!”

“ዝናሽም በስንት ጊዜዋ ዛሬ መጥታ ነበር!”

“ተይ እንጂ! እንዴት ናት?”

“አረጀችብኝ.... ጉስቁልቁል ብላለች... ያው እሷን ታውቂያታለሽ.በሜካፕ ኀይል ነው እንጂ እኮ ዕድሜዋ ሄዷል..."

“አዎ እሱስ... ምን ሜካፕ ብትለቀለቅ አንገቷ አሳልፎ ይሰጣት የለ...
ያ.. የአውራ ዶሮ ኩልኩልት የመሰለ አንገት..."

“አንቺ ተይ በስማም... ሃሃሃ!”

“ምን ላርግ ብለሽ ነው....? ደግሞ እኮ ሰው መልክ ባይኖረው ፀባይ
አይኖረውም?

ያ...ባሏ እንዴት ችሏት እንደሚኖር ነው የሚገርመኝ

እኔ...”

“ውይ! አልሰማሽም እንዴ?”

“ምኑን?”

“አልጋ ለይተዋል አሉ እኮ...”

“ተይ ተይ!”

“ሙች! ቆዩ እኮ... ለንብረት ብለው ነው የማይፋቱት ሲሉ ነበር..."

“ወይ ጉድ... የተጎሳቆለችው ለዚህ ነው በይኛ...."

“ይሆናል እንግዲህ...”

የሚገርመው ፌስ ቡክ ላይ ይሄን ሰልፊ ስትለጥፍ እኮ ነው የምትውለው....
ደህና ፊት እንዳለው ሰው... ለነገሩ ስልኳ
ሌተስት' ስለሆነ አሪፍ አርጎ ያነሳታል... በዐይን እስክታያት ቆንጆ ትመስላለች

ሃሃሃሃ...ስልክ ብትይ...አንቺ ግን እስካሁን አልቀየርሽም እንዴ
ይሄንን ስልክ? ዓመት አለፈው እኮ!”

“አዝዣለሁ ሆድዬ... ሰሞኑን ከካናዳ ይመጣልኛል."

“አይ ደግ አደረግሽ....!”

ቅድስት ሸሮውን ጥረግ አድርጋ በልታ ጨረሰችና እጆቿን ታጥባ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡

“ሽቶሽ ደስ ይላል ቅድስትዬ...” አለች ትዕግስት፣ እቃውን ቦታ ቦታ
አሲዛ ወደ ሳሎን ተመለሰችና አጠገቧ እየተቀመጠች፡፡

“ውይ... ሽቶሽ ብትይ ሳልነግርሽ... ያቺ ሕሊና ያረገችውን ዛሬ...”

“የእነዚህ ሴቶች ጉድ አያልቅ! እሷ ደግሞ ምናረገች በናትሽ....?”

ዋው... ሽቶሽ ደስ ይላል... ምንድነው ስሙ አትለኝም?”

እና ነገርሻት...?”

ደህና ዴኦዶራንት ተቀብታ የማታውቅ ዝተታም የአራት ሺህ ስድስት መቶ ብር ሽቶ ስትመኝ አይገርምሽም? እኔማ ምን አለብኝ

ከነዋጋው ነገርኳት.... ያ አመዳም ፊቷ የበለጠ አመድ መሰለ ...

ሃሃሃ”

“ሃሂ... በጣም ያሳዝናል ብቻ የእነሱ ነገር... ስንት የሚያስጨንቅ ነገር እያለ.. ሃገር እየታመሰች ወሬያቸው ሽቶ..ቅባት.ልብስ ሃሜት... ወንድ... ያሳዝናል በጣም.... መማር ምን ጥቅም አለው

ግን?”

“ምንም!”

ጥቂት ቆይቶ ቅድስት መሄድ እንዳለባት ተናገረችና ተነሳች፡፡

“በቃ ልሂድ ቲጂዬ! የማታው እራት ላይ አለሽ አይደል?” አለቻት እንደቆመች፡፡

“አለሁ ቅድስትዬ...”

“ዋ እንዳትቀሪ... አንቺ ስለምትመጪ ነው የምመጣው ... ከነዚያ ሴቶች ጋር ትርኪምርኪ ማውራት አልችልም... አደራሽን እንዳትቀሪ”

“አልቀርም ቅድስትዬ...”

“ጎሽ... በይ ልሂድና ልበጃጅ...”

“ምን ልትለብሺ አሰብሽ ዛሬ?”

“የሆነ ጥቁር ሌስ ቀሚስ ገዝቻለሁ... አንቺስ?”

“እኔ እንኳን አልወሰንኩም፡፡”

“ጸጉርሽንስ? አትሠሪም?”

“አይ ፍሪዝ ላረገው ነው ባክሽ...”

ለነገሩ ያንቺ ጸጉር በፍሪዝ ያምራል..."

“ታንኪው ሆዴ... በይ ልሂድ...”

“ቻው የኔ ቆንጆ...

እሙጳ.. እሙጿ፡፡ እሙጳ....

እኔ የምልሽ ቲጂዬ...?”

“ወዬ ቅድስትዬ...."

“አንቺ ጋር ስመጣ እኮ ነው አንጎል ያለኝ አንጎል የሚመስለኝ...”

“እኔስ ብትዩ!

💫አለቀ💫

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ገንዳው

እዚህ አሜሪካ በሀገረ ማርያም
በጊዜያዊ ቤቴ ጊዜያዊ በረንዳ
ቆሜ ሳነጣጥር
አየሁኝ መንገድ ዳር፥ ተገትሮ ያለ የቆሻሻ ገንዳ
ዳቦው እንደ ጉድፍ
ወተቱም እንደ እድፍ
ልብሱም እንደ ቅጠል
በገንዳው ከርስ ውስጥ፥ ይረግፋል እንደ ጠል፤

ያሜሪካ መልኳ
አይደለም ሕንጻዋ፥ ሰማይ የሚነድለው
አይደለም መንገዷ እንደቆለኛ ቅል የተወለወለው
አይደለም ፖሊስዋ፥ ዝሆን የሚያህለው
ያሜሪካ መልኳ፥ ጎልቶ የተሳለው
በገንዳዋ ላይ ነው፥ እመንገድ ዳር ባለው፤

ባገሬ ሰማይ ሥር
ሰው ጠኔ ገፍትሮት፥ ሲወድቅ በመደዳ
ያሜሪካ ንስር
ላንዲት ስኒ ሆዱ፥ በጋን እያለቀዳ
እዚያ ማጣት እዳ
እዚህ ማትረፍ እዳ
እዚያ ባዶ ሞሰብ
እዚህ ሙሉ ገንዳ
ከዕለታት አንድ ቀን
በሰማያት እና በምድሪቱ ድንበር
ከእኛ ጎታ አጠገብ፥ የቆሻሻ ገንዳ ተቀምጦ ነበር
የሰማይ አማልክት፥ አላጋጭ ቀልደኛ
“ራበን መግቡን”፥ ለንላቸው እኛ
ብዙ መና ጋግረው፥ ሲያዘንሙ ከሰማይ
የእኛን ጎታ ስተው፥ ከተቱት ገንዳው ላይ፤

ከቶ ለምን ይሆን
ያፍሪቃ ሕፃናት፥ በደቦ ሚያለቅሱ
የወተቶች አዋሽ፥ የርጎ ሚሲሲፒ፥ በበዛበት ዓለም ጤዛ የሚልሱ

የሹራብ ተራራ
የቡልኮ ጋራ
በበዛበት ዓለም፥ ጭጋግ የሚለብሱ
የምድር ጠቢባን
ለዚህ ግዙፍ ምስጢር፥ መልስ አገኝ ብላችሁ፥ጠፈር አታስሱ
ኣሜሪካ ያለው፥ የቆሻሻ ገንዳ፥ ግጣሙ ሲክፈት ወለል ይላል መልሱ።
#ከዚህ_ወድያ_አልወድሽም

ከዚህ ወድያ እልወድሽም
የለም እወድሻለሁ ገና
ማፍቀር አጭር ቢሆንም
መርሳት ረጅም ነውና።
#በዝግ_በር

እንደ ድሮ ቀሚስ፥ መሬት እየጠረግሁ
የእግርሽን አሻራ፥ ተግቼ እየፈለግሁ
እንደጉም
ሳዘግም
እንደሠርዶ ስሳብ
ባካል ብታመልጭኝ፥ ደረስኩብሽ ባሳብ፤

ልብ አይገታም በሩ፥ ልብ አይገታም መስኮት
በዝግ ቤትሽ ገባሁ፥ ልከ እንደ መለኮት።
#አዳምኤል

ካፈርና እስትንፋስ እንደተፈጠረ
ሰው መላክ ነበረ!
ከእግዜር ተጣላና፣ ምድር ላይ ወደቀ
ክንፉን ተነጠቀ።

ግን እግዜር ደግ ነው፣ አልጨከነም በሰው
ክንፎቹን ቢቀማው፣ እንቅልፍ ሰጥቶ ካሰው።

ታድያ ከዚያ ወዲህ
ሰውም ሳያስበው
መላእክትነቱ ከልጓም ሲስበው
ላባ ባያበቅል
በላባ ፍራሽ ላይ፣ ሲገላበጥ ያድራል
ህልሙን ተፈናጦ፣ እንዳሻው ይበርራል።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
Forwarded from አትሮኖስ (...) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM