አትሮኖስ
286K subscribers
119 photos
3 videos
41 files
573 links
╔╦╦╦═╦╗╔═╦═╦══╦═╗
║║║║╩╣╚╣═╣║║║║║╩╣
╚══╩═╩═╩═╩═╩╩╩
ግጥሞች አዳዲስና ቆየት ያሉ የታዋቂ ደራሲያን መፅሐፍቶችን በ PDF እንዲሁንም
ያልተነበቡ ድርሰቶችን ግጥሞችን ታሪኮችን ያገኙበታል።


Contact. @atronosebot
please dont touch the leave button.😔😳😳
Download Telegram
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_አስራ_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ

በአንደኛው እጁ አንገቴን አነቀኝ፡፡ እየሳመኝ አንገቴ ላይ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ሲጠብቅ በእጄ ላስለቅቀው
ዲጉ?" አልኩት ከንፈሬን ከከንፈሩ በቀስታ አላቅቄ፡፡ ቀስ ብሎ እጁን እየሰበሰበ ደጋግሞ ወደውጪ እየተነፈሰ ንዴቱን ለማብረድ ሞከረ በቆምኩበት ትቶኝ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀመጠ። ከቆምኩበት ሳልንቀሳቀስ ቆየሁ፡፡

“ስናደድ የማደርገው እንደዚህ ነው::” አለኝ መሬት መሬቱን እያየ።

“ባር ነበር ልትሄድ የነበረው?" አልኩት መገረሜን መደበቅ እያቃተኝ፡፡
በማንበብ እና በመስማት ደረጃ ሲበሳጩ ወሲብ ማድረግ የሚመርጡ ሰዎች እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ እንደ ዲጉ አይነት የረጉ ሰዎች ባህሪ ይሆናል ብሎ
ማሰብ ግን ከበደኝ።በጭንቅላቱ ንቅናቄ ግምቴ ልክ መሆኑን ነገረኝ፡፡አልፈራሁትም፡፡ አልጠላሁትም፡፡ አልኮነንኩትም። ምን እያሰብኩ እንደሆነ ራሴን የምጠይቅበት ሽራፊ ደቂቃ ሳላባክን አጠገቡ ደረስኩ። ገብቶታል። የእርሱ በማይመስል ፍጥነትና ጉልበት
አጠገቡ ከመድረሴ ቀለበኝ፡፡

"ይቅርታ" አለኝ ጠዋት የበለዘ ክንዴን እያሻሸ በፀፀት በታጀለ ስሜት ውስጥ ሆኜ።

"አልጠላሁትም!! ተቃራኒው ነው የተሰማኝ፡፡" አልኩት ከልቤ።
የዚህን እለት ማታ ልባችን ያገነፈለው ሀሴት ፊታችን ላይ እየጮኸ እራት ሊጋብዘኝ ይዞኝ ወጣ፡፡እንዲህ ያልተቀዣበረ ፍስሃ ተሰምቶት አያውቅም በወንድማማቾች መሃል የተፈጠረው መቃረን ሀሳቤን ሊከፍለው ቢታገልም በሚሰማኝ ፌሽታ ይዋጣል፡፡ የመጀመሪያው ከወንድ ጋር የኖረኝ የተለየ
ስሜት የነበረው እራት ነበር። ለቹቹ የተፈጠረውን ስነግራት ጆሮዬ እስኪደነቁር በስልኩ ሞገድ ጮኸች። እውነቴን መሆኑን ለማረጋገጥ ደጋግማ አስማለችኝ።እንደበፊቱ ሳይሰለቸኝ ደጋግሜ ማልኩላት። ቤን ለስራ ጉዳይ ከከተማ እንደሚወጣ ለእነእታባ ነግሯቸው በነጋታው ሄደ፡፡ እኔና ዲጉ ግን ከኛ መራቅ ፈልጎ መሆኑ ገብቶናል።

ብትችዪና ተጨማሪ ቀናትን እዚህ ብትሆኚ ስወድሽ" አለኝ ዲጉ ቀጥረነው የነበረው የቀን ገደብ የሚያልቅ
ቀን፡ ልጠይቀው የነበረው ከዛስ?” የሚለውን ነበር፡፡ ስለነገ አብሮነታችን ያሰበውን ነበር ማወቅ የምፈልገው:: ምናልባት መልሱን ፈርቼ ወይም ይሄን ለመጠየቅ የፈጠንኩ ስለመሰለኝ
ዲጉ ያለምንም ማቅማማት የዓመት ፈቃዴን ወጣሁ። ለቤተሰቡ የተሻለ የመሰለው በድጋሚ መዋሸት ነበር እናም ቀን ለመጨመር ማሰባችንን ብቻ ነገራቸው:: ደስታቸው ስለአየለባቸው ለምን? እንዴት? ያለ ምንም።

“ዲጉ እየፈራሁ ነው::" አልኩት ከእርሱ ጋር ሆኜ የሚያልፉት እያንዳንዱ ቀናት ልቤ እስኪጨነቅ በመውደዱ እየተጣበበ
እንደሆነ በተሰማኝ ሰዓት

"ለምን? ምንድን ነው የሚያስፈራሽ?"

| "ከዚህ ቀደም እንዲህ ዓይነት ስሜት ተሰምቶኝ አያውቅም፡፡ ዲጉ
በጣም እየወደድኩህ ነው።ተመልስህ መሄድህን ሳስበው ምናለ ቢቀርብኝ እላለሁ።" አልኩት። መልሱ የነገ ህይወቱ ውጥን ውስጥ እኔ መደመሬን እንዲያረጋግጥልኝ እየፈለግኩ፡፡

“ከወደድሽኝ ለምን ልቅርብሽ? በቻልሽው ልክ ውደጂኝ” አለኝ።እርሱም እኔም ነገን መፍራቴን እናውቃለን፡፡ ነገር ግን ስለነገ
ከሚያረጋግጥልኝ ይልቅ “ለነገ ሀዘን የዛሬ ደስታሽን ቀብድ ታስዬዣለሽ?" አለኝ

ነገም እኮ ዛሬ ይሆናል፡፡ ዛሬ ትላንት ሲባል ነገ ዛሬ ሊሆን ትላንት ላይ የነበረኝ ፍካት የዛሬ መክሰም ሊሆን ይችላል፡” ብዬ መለስኩለት።

"ስለነገ ዋስትና የለንም።ዛሬን እንኑር አለኝ።

ይሄ የቃላት ልውውጣችን እየፈራ ለነበረ ልቤ ተጨማሪ ፍርሃት ደረበበት ዲጉ ሁሌም ስለነገ ህይወታችን ልጠይቀው በሞከርኩ ቁጥር ስለአሁን ብቻ እንድንኖር ስለነገ እየወጠንን ዛሬያችንን እንዳናባክን ነው የሚመልስልኝ፡ ባልፈልግም አለማሰብ አቃተኝ።እርሱ ወደ ህይወቴ እስከመጣበት ጊዜ ድረስ ሁሉ ሰላም ነበር በምርጥ ፀሃፊ እንደተተየበ 'ቧልት' ተውኔት
የትዕይንቱን ቅደም ተከተል እየጠበቀ የሚያልፍ ሳቅና ደስታ የሞላበት ፍፁም ነበር፡፡ እኔም ስለዛሬ እንጂ ሰለነገ የማልኖር ነበርኩ፡፡በነጎዱ ትናንቶቼ ውስጥ ለተከሰቱ ስዎችም ክስተቶችም
ቁብ ያልነበረኝ ቅርብ አላሚ ነበርኩ፡፡

አመንኩት። ወይም ካለማመን ውጪ ምርጫ አልሰጠኝም ነበር እና ዛሬን አብሬው ኖርኩ፡፡ የዛሬ ደስታዬን ሸመትኩ፡፡ በደስታዬ ውስጥ ምሉዕነቱ የእርሱ ፍቅር ነበረ።በሳቄ ውስጥ እርሱ ነበረ። የህይወቴ ፀሃይ ሆኖ ያደመቀኝም ያሞቀኝም እርሱ ሆነ፡፡ ልዩነታችን ለእኔ በእርሱ ውስጥ ዛሬ ነበረ። ነገም በእርሱ ውስጥ ይኖራል፡፡ በትናንተናዬ ውስጥ ብዙዎች ኖረዋል፡፡ የቱም ቀኔ በነሱ ውስጥ ኖሮ አያውቅም፡፡ቀኖች እንጂ በእርሱ ውስጥ ያሉት
እርሱ አልነበረም በቀኖቼ ውስጥ ያለው::
ዘግይቶ ሲገባኝ ለእርሱ እንደዛ አልነበረም፡፡በዛሬው ውስጥ እኔ አለሁ።በነገው ውስጥ የትኛዋም ሴት ልትሆን እንደምትችል፡፡በትናንትናው
ውስጥ አንዷ እንደኖረችው፡፡ እኔ የቀኖቹ ክስተት ብቻ ነበርኩ!! ያን ያወቅኩት በብዙ ዛሬዎች ከጠፋሁ በኋላ ማርገዜን የነገርኩት ቀን ነበር፡፡ ልጅህን በሆዴ ተሸክሜያለሁ ያልኩት ሳይሆን የሚሳሳላትን የባተሰቡን አካል ገደልኩኝ
ያልኩት ነበር የሚመስለው፡፡ የማላውቀው አብሬው የከረምኩት ያልሆነ ሌላ ሰው ሆነ።

"ምን አስበሽ ነው?" አለኝ ከብዙ ድንፋታ በኋላ፡ ደንግጬ ስለነበር ዝም ብዬ ነበር ስሰማው የነበረው። የተረጋጋሁ
ስለመሰለኝ የሚያነክስ ልቤን ደግፌ መለስኩለት።

“ምንም! ምንም አስቤ አልነበረም:: ጭራሹኑም አስቤው የተከሰተ
ነገር አልነበረም። ማርገዜን ሳውቅ ግን ደስ ነበር ያለኝ፡፡ አንተም ደስ የሚልህ ነበር የመሰለኝ፡፡"

“በፍፁም! በፍፁም ካንቺ ጋር ራሴን ለማሰር ዝግጁ አይደለሁም::" ያለኝ ብዙ ህመም ነበረው:: ብዙ መስበር፡፡ የበዛ
ውድቀት።

“አልገባኝም:: ከኔ ጋር ራስህን ማሰር? እስከአሁን የነበረን ነገር ምንድን ነበር?"

“ምንም! አብረን የምናሳልፈውን ጊዜ
እወደዋለሁ፡፡ እወድሽማለሁ። ለየትኛውም ሀላፊነት ግን ዝግጁ አይደለሁም::" መኝታ ቤታችን ውስጥ እየጮኸ ነው የሚናገረው:: ቤተሰቦቹ
ቢሰሙት እንኳን ግድ የነበረው አይመስልም። ኢምንት ያህል የፍቅር ቃና የለውም። ለምንድነበር እንደወደደኝ ሲሰማኝ የነበረው

"በቃ? በመሃከላችን የነበረው ነገር ላንተ ትርጉሙ ይህቺን ታህል ነው? ምንም?" ይሄን ስጠይቀው እኔም እየጮህኩና እየተቆጣው ነበር።

“በህይወትሽ አዲስ ነገር አልተከሰተም፡፡ ከሆነ ሰው ጋር መሆንም መለያየትም አዲስ የተከሰተብሽ አታስመስዪ፡፡ የበደልኩሽ አድርገሽ አትውቀሺኝ።” ላለው መልስ አልነበረኝም፡፡ መመለስ
ፈልጌም ቢሆን የትኛውም ቃል ስሜቴን አይገልፀውም ነበር። እየተጎተትኩ ከመኝታ ቤቱ ለመውጣት ስጀምር በተናገረው ይሁን እኔጋር በፈጠረው ስሜት ተቀዣበረ።

“ቤች በእናቴ ይሁንብሽ ይቅርታ! እንደሱ ማለቴ አልነበረም አንቺ ጥሩ ሴት ነሽ! ነገር ግን...አለ ያዘነበት ወይም የተፀፀተበት ልክ በነዛ ቃላት ያጠቆረውን ልቤን ትንሽዬ እንኳን ማከም አይችልም። በእርሱና በወንድሙ መሃከል የተፈጠረው
ፀብ ምክኒያቷ እኔ መሆኔንና ቤን ከቤት የወጣው እኔን ስለሚወደኝ መሆኑን ዘበዘበ። ለቤተሰቡ ቅድሚያ እንደሚሰጥ
ነገረኝ፡፡

"ማለት የፈለግከውን ብለሃል ዲጉዬ::" ብዬው የእጅ ቦርሳዬን ይዤ ወጣሁ። ቢከተለኝ ተመኝቼ ነበር። እሱ ግን አላደረገውም።ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።

የፈራሁት ነገ ዛሬ ሲሆን የህይወቴ ብቻ ሳይሆን የዓለም ፀሃይ እርሱ የሆነ እስኪመስለኝ ዓለም ጨለመችብኝ አይወደኝም። በህይወቴ ፍቅርን ያወቅኩበት ሰው የሳምንታት አጣባቂው እና የአልጋ ፈንጠዝያው አጋር ከመሆን ያለፈ
👍6😁1
ምኑም አይደለሁም።

ካንቺ ጋር የማሳልፈው ጊዜ እወደዋለሁ። እወድምሻለው ግን....ብዙ "ግኖች" አውቃለሁ። የእርሱን “ግን” እስከሰማሁበት ደቂቃ ድረስ አንዳቸውም ያስከተሉት ምክንያት ቁብ ሰጥቶኝ አያውቅም፡፡ ምክንያት ሰጪዎቹም
ምክንያታቸውም እንደሚያልፈው
ቀኔ ስለሚያልፉ።የሚደሰቱበት ግን አብረውት መኖር የማይሹት ገላ
መሸከም አያስጠላም ታዲያ? አብረውት ብቸኝነት ለመግፋት የሚያስደስት ለቁምነገር ግን የማይበቃ ማንነት ማንጋተት አይቀፍም ታዲያ?

አዲስ አበባ በአካል ብገኝም ነፍሴ ማረፊያ አጥታ እየተንቀዋለለች አይነት ነው የሚሰማኝ፡፡ ስራ ባልገባም ከቹቹ
ማምለጥ አልቻልኩም:: እቤት ድረስ መጥታ በጥያቄ ጠመደችኝ፡፡የማብራራት ፍላጎቱም አቅሙም ስላልነበረኝ ማለት
የቻልኩት "ከዲጉ ጋር ተጣላን!" ብቻ ነበር፡፡

ልታፅናናኝ ሞከረች። ወንድሟን ደጋግማ ረገመችው። የእኔ በወንድ ፍቅር እንዲህ መበታተን ደግሞ አስገረማት:: በእርግጥ
እኔም ገርሞኛል፡፡ አሁን እንኳን እንዲህ በሚያነክስ ልቤ የምሻው ብቸኛ ነገር ዲጉን አጠገቤ ማግኘት ነው:: ልቤን
ያነከተው ንግግሩ ህመም እሱን ከማጣት ጋር ሲነፃፀር ገለባ ነው:: አልቻልኩም:: እሱን ማጣት አልቻልኩም፡፡ በምንም
መርሳት አልቻልኩም:: እንባዬን ማስቆምም እንደዛው። ያማል
እጅግ! ያፈቀሩትን ሰው የራስ አለማድረግ ያማል! ብቻዬን የምኖርበት ቤቴ ውሰጥ እንባዬን ስበላ መሽቶ ይነጋል። እንቅልፍ
ባይወስደኝም ጎኔ እስኪቀላ አልጋዬ ላይ እገላበጣለሁ። የመብላት ፍላጎት ባይኖረኝም የግዴን አላምጣለሁ። ምንም የመሆን ፍላጎት የለኝም። ምንም
ባደርግ ዲጉን ከሀሳቤ ማራቅ
አልችልም፡፡ ከእርሱ የገዘፈ ሀሳብ አጣሁ፡፡ ቤተሰቡ ተራ በተራ ስልኬ ላይ በመደወል እረፍት ነሱኝ። ምክንያቱን
ባይነግራቸውም መጣላታችንን ነግሯቸዋል፡፡ በህይወቴ በምሬት ያለቀስኩበት ቀን ማስታወስ አቃተኝ...

ይቀጥላል

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ምሽት። 🙏
👍2
#ቅበሪኝ_አገሬ

ይሄን የአረብ ሩዝ
በትኩሱ ልፌ፣
ዳውን ዳውን ያልኩሽ
አምልጦኝ ነው ከአፌ።
ልሸጥሽ ብሞክር
በጥቅም አሳልፌ፣
አንድ ቀን ሳላድር
መጣሁ ተሸክፌ።
ለካስ በአንቺ ነበር
መኖር መከበሬ፣
ዳግመኛ አይለምደኝም
ቅበሪኝ አገሬ። አሉ ከዛ የመጡት😄
ከአስመሳዮች ፊት ከሸንጎዎች ሰፈር
በሳቅ ተበልቅጦ የከንፈሩ መስመር
በውስጡ ክፋትን ነገርን አሲሮ
እየሳቀ ጎዳኝ
ጥርሱን እያሳየኝ ወቸጉድ ዘንድሮ

 
👍2
Forwarded from አትሮኖስ (...) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ቅዳሴና_ቀረርቶ


#ክፍል_አስራ_ሁለት(የመጨረሻ ክፍል)


#በሜሪ_ፈለቀ

...በራሴ መንገድ በውድቀቴ እንኳን ተሳልቄ የማልፍ ጠንካራ እንደነበርኩ ነው የማስበው።አሁን ግን ተሸነፍኩ።ቹቹ በየቀኑ ከስራ በኋላ እኔጋ ትመጣለች። ስለዲጉ ላወራት የምችል ብቸኛ ሰው እርሷ ናት።እለፈልፍላታለው።ከእኔ እኩል እያወራች ይሆን ትሰማኛለች.በእግሬ ለመጓዝ ሞክሪያለሁ። ዓይኔን ሲያለቅስ አገኘዋለሁ ክለብ ሄጄ ለመጨፈር ሞክሪያለሁ። አድርጌው የማላውቅ
ይመስል ቀፈፈኝ።አስር ደቂቃ ሳልቆይ ወደ ቤቴ ተመለስኩ።ለዲጉ ልደውልለት ስልኬን እያነሳሁ ከራሴ ተሟግቻለሁ፡፡ ራሴን የበለጠ ማዋረድ መሰለኝ፡፡ ራሴን ከማዋረድና አሁን ከሚሰማኝ ስቃይ የቱ እንደሚበልጥ ማበላለጥ እያቃተኝ የመደወሉን ሀሳብ እተወዋለሁ።

አዲስ አበባ በተመለስኩ በአራተኛ ቀኔ የተንኳኳ በሬን ስከፍት ቤን መሆኑ አስደነገጠኝ፡፡ እቤት ገብቶ እንደተቀመጠ "ተጎሳቆልሽ እኮ አሞሻል እንዴ?" አለኝ ከላይ እስከ ታች እያየኝ።

"አዎን ታምሜያለሁ:: ልትጠይቀኝ መስሎኝ የመጣኸው? ደስ
አለህ? ከዲጉ ጋር ስለተጣላሁ ደስ አለህ? እንኳን ያሰብከው ሆነልህ!" ንዴቴን ማብረጃ ስላገኘሁ ተወጣሁበት እንጂ የቤን ቤቱን ለቆ መውጣት ለእኔና ለዲጉ መለያየት ያበረከተው ነገር
ምንም መሆኑን በልቤ አውቃለሁ።
ይወድሻል።" አለኝ ቀለል አድርጎ፡፡

"ቤች ደስ አላለኝም! ደስ ሊለኝም አይችልም:: ዲጉ የምወደው ወንድሜ ነው።አንቺ የእርሱ ሚስት ነሽ! ምንም ቢሰማኝ ካንቺ ጋር ልክ አይሆንም:: እንደወደድሽው አውቃለሁ።እሱም
ለጊዜው የቱን ማስቀደም እንዳለበት ግራ
ገብቶት እንጂ ይወድሻል።አለኝ ቀለል አድርጎ።

እመነኝ አንተ የማታውቀው ነገር አለ ቤን!" አልኩት በቀሰስተኛ ድምፅ።

"ሁሉንም አውቃለሁ።ዲጉ ነግሮኛል። ቁምነገሩ እንዴት ጀመራችሁ አይደለም አሁን በመሃከላችሁ ያለው ትስስር ነው።" አለኝ።

"ትስስር? የውሸት ነው። የወደደኝ በመስለኝ ጊዜ ሁሉ እሱጋ ያ ስሜት አልነበረም።"አልኩት ከልቤ።

“ማረጋገጥ ትፈልጊያለሽ?"

“ምኑን?"

"እንደሚወደሽ?"

"አዎን"

"እመኚኝ! ወደ ቤት እንመለስ! እኔ የምልሽን አድርጊ!” ሲለኝ
ስላመንኩት ሳይሆን ዲጉ አጠገብ ከመሆን የተሻለ የምሆንበት
ቦታ ስላልነበረኝ ለመስማማት አስቤ ነበር፡፡ በቤኒ ታጅቦ ወደ ቤት መመለሱ ጥሩ ሀሳብ ስላልመሰለኝ ቤኒ ብቻውን ተመለሰ።

በሚቀጥለው ቀን ግን እታባ ራሳቸው ቹቹን አስከትለው ሲመጡ እንቢ የማልልበት በቂ ሰበብ በመሆኑ አብሬያቸው ተመለስኩ፡፡
እታባ ሲያዩኝ ነበር የተቆጡኝ።

እናትሽ አይደለሁም? ቢያስከፋሽ ለኔ አትነግሪኝም? እንዴት እኔ እያለሁ ዘመዶች ሽጋ ትሄጃለሽ?" ሲሉኝ የተዋሹት ውሽት
መኖሩ ገባኝ።እቤት ከተመለስን በኋላ ከቤን ጋር በረንዳ ላይ ተቀምጬ ዲጉና ኪዱ ከውጪ መጡ። ኪዱ ተጠመጠመችብኝ፡፡ዲጉ ጨበጠኝ እና መሸሽ በሚመስል ሁኔታ ወደ ቤት ገባ፡፡እታባ ቤተሰቡ በተሰበሰበበት ዲጉ ይቅርታ እንዲጠይቀኝ አደረጉ
እኔ ከሄድኩ ጀምሮ በራሱ ሲበሽቅ መቆየቱን ኪዱ ነገረችኝ ።እኔ ግን መስማት የምፈልገው ከእርሱ አፍ ነው።
ይቅርታ የጠየቀኝ ለቤተሰቡ ብሎ ይሁን ከልቡ ማረጋገጥ ነው ፍላጎቴ።እስኪመሽ ድረስ አንድ ነገር ይለኛል ብዬ ብጠብቀው እየደጋገመ “ስለተመለስሽ ደስ ብሎኛል።" ከማለት የዘለለ ለእኔ
ስላለው ስሜት መተንፈስ አልፈለገም፡፡
ሲመሽ መኝታ ቤት ገብቼ ልብስ ስቀይር ዲጉ ወደ ውስጥ ዘለቀ።

"የት ልትሄጂ ነው?" አለኝ፡፡

"ከቤን ጋር ልንጨፍር!” መለስኩለት ቤን እንዳለኝ።

አደረጉ። እኔ ከሄድኩ ጀምሮ በራሱ ሲስሽቅ መቆየቱን
ነገረችኝ። እኔ ግን መስማት የምፈልገው ከእርሱ አፍ ነው::

“ምን ማለት ነው? ተመልሰሽ የመጣሽው ከእርሱ ጋር ለመሆን ነው?" ድምፁን ከፍ አድርጎ በንዴት ጠየቀኝ።

“ምን ግድ አለህ? ከሆነ ሰው ጋር መሆን ከዛ መሄድ አዲስ በህይወቴ የተፈጠረ ነገር ነው እንዴ? ከኔ ጋር መሆኑ ከበቃህ
ከማን ጋር መሆን እንደሌለብኝ ልትነግረኝ ምኔ ነህ?" አልኩት ከእሱ የባሰ ተቆጥቼ

ሌላው ቢቀር ልጄን ነው በሆድሽ የያዝሽው?" አለኝ አስቦ
ሲያበቃ፡፡

“ኸረ? እኔጋ ልጅ የለህም፡፡ ዝግጁ እኮ አይደለህም: የእኔ እንጂ ያንተ ልጅ አይደለም::"

“በቤተሰቤ ውስጥ እንዲህ እንዲሆን አልፈቅድም::" ከማለቱ ቤን ገባ።

"ጨረስሽ?" አለኝ ምንም እንዳልተፈጠረ አስመስሎ፡፡ ጫማዬን እያጠለቅኩ ነበር። ዲጉ እኔን ትቶ ወንድሙ ላይ መደንፋት ጀመረ።እየሰራ ያለው ነገር ጋጠወጥነት መሆኑን ደጋግሞ ነገረው ከመናደዱ የተነሳ ድምፁ እየተዘጋ መጣ፡፡

የቱ ነው የምር ያናደደህ? ከኔ ጋር መሆኗ ነው ካንተ ጋር አለመሆኗ?” አለው ቤን በእርጋታ። ዲጉ መልስ አልመለሰም።ቤን ቀጥሎ "ቶሎ ውጪ" ብሎኝ ሁለታችንን ለብቻችን ጥሎን ሄደ።

"አሁኑኑ እንደማትሄጂ ንገሪው።" አለኝ በሩን ተደግፎ እንዳልወጣ እየተከላከላ፡፡

ለምን ብዬ? እስኪ ያን የማላደርግበት አንድ በቂ ምክንያት አቅርብልኝ።" አልኩት ፊቱ ቆሜ።

"ዛሬ አብረሽው ከወጣሽ ትጣዪኛለሽ፡፡" ሲለኝ ሳቅኩኝ፡፡

“ዲጉዬ ተጣልተኸኛል እኮ! ልቤን እንክት አድርገኸው ተጣልተኸኛል።” አልኩት፡፡ አልመለሰልኝም:: ዓይኖቹን አሸሻቸው፡፡

“እሺ አሁን አሳልፈኝ፡፡" አልኩት።

መጀመርያውኑም ውሸትሽን ነበር ማለት ነው።አልወደድሽኝም ውሸታም ነሽ።ወደሽኝ ቢሆን በዚህ አጭር ቀን ከቤን ጋር አትሆኚም ።እንዳልሽው መጣላታችን ጎድቶሽ ቢሆን እነደዚህ አታደርጊም።ውሸትሽን ነበር እየተወራጨ ይለፈልፋል።የግንባሩ ደም ስር ተገታትሮ ያፈጥብኛል።መልስ ሳልሰጠው በሩን ከፍቼ ልወጣ ስል በሃይል አስቆመኝ፡፡ ባስቆመኝ ጉልበት ያለማቋረጥ ሳመኝ፡፡

"እሺ ቤች ይቅርታ! ይቅርታ በቃ ክፉ ሆኜብሻለሁ፡፡ ለተናገርኩሽ ልብሽን ለሰበረ ንግግሬ ሁሉ በፈለግሽው ቅጭኝ፡፡ እከፍላለሁ።”አለኝ መሳሙን አቁሞ፡፡ ከዚህኛው ንግግር በኋላ እኔ ካቆመበት ቀጠልኩ።

እንድ ነገር ልጠይቅህ?" አልኩት። አልጋው ላይ እንደተዘረርን

“ምን ልመልስልሽ?"

“ስለተበሳጨህ ብቻ ነው? ወይስ?" ምን ብዬ መጠየቅ እንዳለብኝ ጠፋኝ፡፡ ማወቅ የፈለግኩት ግን እሱጋ የነበረኝን ዋጋ ነበር።

እመኚኝ እንዳየሁሽ!! በዛው ቅፅበት የልቤን አጥር ንደሽው ነበር። መቀበል ያቃተኝ ለፍቅርሽ መንበርከኬን ነበር፡፡ ፈራሁ። አለኝ።ላወራ አፌን ስከፍት ዝም አድል ጣቱን ከንፈሬ ላይ አድርጎ ነገረኝ።

“የዛን እለት ማታ በዛ አውሬነት ውስጥ ሆኜ ራስሽን ልትሰጪኝ ስታምኚኝ ፍቅርሽ ብትነግሪኝ ከምረዳው በላይ ገብቶኛል።" ሲለኝ ደስታዬ ጥጉን አጣ፡፡ ከቤን ጋር ሆነ ብለን ያደረግነው ድራማ እንደነበር ስነግረው አልጋው ላይ ተንጋሎ ሳቀ። ደስ ብሉን ስለወደፊታችን ስናቅድ አመሸን፡፡ለመጋባት ወሰንን፡፡ እንቅልፍ ሳይወስደን ብዙ ቆየን። የዚህን ደስታ ልክ አጣጥሜው ማወቄን እንጃ

አንድ ነገር ገባኝ።ህይወት የሂሳብ ቀመር ይመስል የሁለት ተመሳሳይ ነገር ድምር ወይም ብዜት ሁሌ መልሱ አንድ ዓይነት አይመጣባትም:: ውጤቱን የሚወስኑት ሰዎች ናቸው፡፡

በሚቀጥለው ቀን ማታ እኔና ዲጉ ወጣን፡፡ ወደ ቤት ስንመለስ የማርገዜን ዜና ለቤተሰቡ ልናበስር አቅደናል። ሆቴል መግቢያ በርጋ ስንደርስ የምስራቹን ሊነግረው እና የወደፊት እቅዳችንን
ሊያማክረው ፈልጎ አብሮን እራት እንዲበላ የቀጠረው ጓደኛው አጄ እኩል አብሮን ደረስ።ለሰላምታ እጄን ስዘረጋ የፍንዳታ ድምፅ ሲሰማ፤ ዲጉ በቁሙ ሲወድቅ እና ሰቅጣጭ የመኪና ጎማ
ድምፅ ተሰምቶ መኪናው ሲፈተለክ የምንም ሰከንድ ክፍተት ያለ የማይመስል ፈጣን ትዕይንት ነበር

ከአጠገቤ በንፋ
👍7
ስ ፍጥነት ሮጦ ላዳ ውስጥ የገባውን አጄን እና እግሬ ስር የተዘረረውን ዲጉን ተራ በተራ ከማየት የዘለለ ምንም ማድረግ የማልችልበት ድንዛዜ ላይ ነበርኩ። ሰዎች ከበውኝ
ሲጯጯሁ፣ አጄ በላዳው ዲጉ ላይ የተኮሰበት መኪና በሄደበት አቅጣጫ ተከትሎ ሲሄድ ሁሉም ቅዠት የሚመስል ክስተት ነበር፡፡እግሬ ብርክ ይዞት መሬቱ ላይ ተቀመጥኩ፡፡ በደመ ነፍስ የማደርገው ሳይገባኝ ማን እንደጠራው የማላውቀው
አምቡላንስ ውስጥ ገብቼ ሆስፒታል
የዲጉን አካል ተከተልኩት፡፡ከስንት ደቂቃ ወይ ሰዓት ወይ ቀን በኋላ እንደነበር አላስታውስም። ዲጉን ማትረፍ አለመቻላቸው ታወቀ። እታባ
ራሳቸውን ስተው ለቀብሩ እንኳን መገኘት ሳይችሉ ሆስፒታል ከረሙ:: ፖሊሶች የዲጉ ገዳይ ዲጉ ከዓመታት በፊት የገደላቸው
የአባቱ ጓደኛ ልጅ መሆኑን ደረሱበት። ቤተዘመድ ተላቀሰ፡፡ .

ይሄ ሁሉ ስንት ቀን መፍጀቱን እኔንጃ እኔ ግን እዛው ሆቴሉ ደጃፍ ቀርቻለሁ።ከዛ በኋላ የሚንቀሳቀሰው አዕምሮዬ የሚያዘው አካሌ አይደለም።እዛው ዲጉ የተወኝ ቦታ ባንቺ ቀርታለች። የት እንደሄድኩ እንኳን ሳልነግራቸው ወደ አዲስ አበባ ስመለስም ያደረግኩት ነገር ልክ ይሁን ስህተት ሚዛን አልነበረኝም፡፡ ባንቺ ዲጉ የቆሰለበት ቦታ ሞታለች።ሌላ ራሴ የማላውቃትን ድንዙዝ ሴት ነው ተሸክሜ እየዞርኩ ያለሁት፡፡ ለብዙ የዕድሜዬ ቁጥር ያላወቅኩትን ጣፋጭ ፍቅር በዲጉ አወቅኩት፡፡ ጣዕሙ ሰውነቴን ገና ሳይዋሃደው ፈጣሪን ለማመስገን ወደ ሰማይ የቀና አንገቴ ከመቀልበሱ ሬሳውን እግሬ ስር አገኘሁት። በቅጡ ፀልዬ እንኳን ወደ ማላውቀው አምላክ ለማማረርም ለማወደስም የቸገረ ነገር ሆኖብኝ፡፡ ምነው ቀድሞውኑ ይኼን ድንጋይ ልቤን ለዲጉ ሲሆን
ስጋ ባታደርገው? ምነውስ ደስታዬን መሪር ሀዘን ቸለስክበት?
ካላጣኸው ነፍስ የእኔን ፍቅር የምትጠራው ምን በድዬህ ነው?
ለምንስ ሰጠኸኝ ደግሞስ ለምን ትነሳኛለህ? እላለሁ የዳመነው
ሰማይ ላይ አንጋጥጬ:: ወዲያው ግን ከሰማያዊው ህይወት ጋር
ለማማረር የሚያበቃኝ ጥብቅ ትስስር እንደሌለኝ ሲገባኝ ወደ
ራሴ ተመልሼ ራሴን ለማፅናናት እባትታለሁ። የህይወት ስሌት
የተመጠነ ባይሆንም፤ ልክ ነበርኩ አንድ የማይቀየር ቀመር ግን
አለው።ስህተት በስህተት ሲባዛም ቢደመር ውጤቱ የትዬለሌ ጥፋት ነው።ይሄን ለመቀበል እፍጨረጨራለሁ።

“ቅዳሴው ሲያልቅበት ቀረርቶ ሞላበት።” አለ የሀገሬ ሰው!! ..

ካልቆጠርኳቸው ቀናት በኋላ ስራ ገባሁ፡፡ “ቹችዬ አርግዣለሁ።" ብዬ ስነግራት ቢሮ ውስጥ እሪ ብላ
እያለቀሰች ሳቅና እንባዋን እያዳቀለች "ወንድሜ አልሞተም።አምላኬ ተመስገን!" ብላ ስታቅፈኝ ማልቀስ ይሁን መሳቅ ያለብኝ አላወቅኩም

ተ..ፈ..ፀ..መ

ባቀረብነው ድርሰት ላይ ያሎትን አስተያየት ለመስጠት @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍1
Forwarded from አትሮኖስ (...) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ህልሜን አደራ

ባይመረመሬ ፥ ጥበብ ተሽቀርቅሮ
ከወርቃማ ብርሃን፥ ከብርማ ጸዳል
የተሠራ ሸማ፥ ማግኘት ብችል ኖሮ
ከውብ እግሮችሽ ሥር፥ እዘረጋው ነበር
ግና ምንም የለኝ፥ ከህልሞቼ በቀር፤
የኔ ውድ እንግዲህ
ህልሜን እግሮችሽ ሥር፥ ከዘረጋሁ ወዲህ
ዝግ ብለሽ እርገጪ፥ ዝግ ብለሽ ሂጂ
ህልሜ ላይ ነውና፥ ።የምትራመጂ

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#እመ_መከራ

ኢትዮጵያ እመ መከራ
የግዜር መመራመሪያው
የስቃይ ቤተ-ሙከራ
መውደቅማ ነበር ያባት
እንደ ያሬድ እስከ ሰባት
እንደ በላ ብላቴና
የእንክርዳድ ሙልሙል እንጎቻ
የትውልዴ እጣ ፋንታ
መውድቅ፥ መውድቅ፥ መውድቅ ብቻ! 😔
#እናቴን_ተመኘኋት


#ክፍል_አንድ


#በሜሪ_ፈለቀ

በተለያየ መኝታ በተለያየ እንቅልፍ ውስጥ አንድ አይነት ህልም እንዴት ይታለማል?
የሆነ ሰው ያለፈበት መንገድ እና የደረሰበት ስኬት እንዴት የሌሎች ብዙዎች መንገድና መድረሻ ይሆናል? የሌሎች ብዞዎች ደስታ በአንድ ሰው መዳረሻ እንዴት ይፈጠራል
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
“ለግለቱ የሚተኛኝ ወንድ አስጠላኝ፣ ለፍቅር የሚተኛኝ ናፈቀኝ፡፡” ያለችኝ......

ያኔ በአስራ ሁለት ዓመቴ ከርዳዳ ፀጉሬን እየደባበሰች፣ አረቄዋን እየተጎነጨች፣ ከትልልቅ ዓይኖቿ እንባ እየደፋች፣ ተሰባብሮ ሩብ ታክሉ በቀረ ሙሉውን የፊቷን ገፅታ ማሳየት በተሳነው መስታወቷ ተራ በተራ እያንዳንዱን የፊቷን አካላት እያየች ነበር።

“እንደእነ ጥሩዬ በወግ አግብቼ በማግስቱ ሞቴ ቢሆን ግድ
የለኝም::" ብላኝ ነበር በዓይኖቿ እሩቅ እያየች።

"እኔ ሳድግ አገባሻለሁ!!" አልኳት የዛን ዕለት፡፡

ደንገጥ ብላ እጇን ከፀጉሬ ላይ እያነሳች "ኪዳነ ምህረት! አንተ ልጅ ምን ስል ሰማኸኝ?" ብላኝ ከተቀመጥንበት የበረንዳው ደፍ ላይ ዘላ ተነሳች።

"አንተ? እናትህ እኮ ነኝ። በማን ሀገር ነው ልጅ አድጎ እናቱን የሚያገባው? በል ግባና ምሳህን ብላ!!" ብላኝ ወደቤቷ ገባች። ተከትያት ገባሁ። እንደሁልጊዜው ምሳዬን ሰጠችኝ፡፡እንደሁል ጊዜው ለራሷ ጎርሳ ሰሀኑን ገፋ አደረገችልኝ፡፡ እኔ ግን
እንደሁልጊዜው የሰጠችኝን እንጀራ በሽሮ ተስገብግቤ መብላት አቃተኝ።

የማስበው ሁሉ የጥሩዬን ባል አክዬ ወይንሸትን ማግባት ነበር፡
የጥሩዬን ባል መንገድ ሳገኘው ቁመት እለካካዋለሁ።ባል ለመባል ልደርስላት፣ በትልልቅ ዓይኖቿ ማልቀሷን ላስቆማት
የፊቷን አካላት ሁሉ በአንዴ የምታይበት መስታወት ገዝቼ ልሰጣት፣ ህፃን አይጠጣም እያለች የምትከለክለኝን አረቄዋን የበረንዳዋ ደፍ ላይ አብሪያት ተቀምጨ ልጠጣ፣..... የጥሩዬ ባል
ለጥሩዬ እንደሚያደርግላት በእንጨት ማበጠርያ የወይንሽትን ረዥም ፀጉር ላበጥርላት፡፡

#ያኔ......

በገጠራማዋ መንደራችን የተፈራ የታፈረ አባወራ ሳይቀር ጠላ ከምትሽጥባት ትንሽዬ ቤቷ ውስጥ መደቧን አጣቦ ጠላውን እየኮመኮመ ዓይን ዓይኗን ሲያይ የሚያመሽላት ቆንጅዬ ነበረች።

#ያኔ.....

ባለትዳር የሆኑት የመንደሯ ሴቶች ባሎቻቸው ወይንሸትጋ ሲገቡ አይቼ የማላውቃቸም ጭምር ባሎቻችንን አባለገች ብለው የሚኮንኗት፣ በውበቷ እንደማይቀኑ እና የሷን የአለባበስ እና
የሹሩባ አሰራር በየቤታቸው እየኮረጁ እንደማይመስሏት ፊት የሚነሷት ውብ ነበረች።

#ያኔ.....

የመንደሯ ወንዶች ጠላዋን እየጠጡ በጡትና በመቀመጫዋ ለሀጫቸውን እንዳላዝረከረኩ፣ መደቧ ላይ ይዘዋት ወድቀው ከጠላዋ በላይ በስሜት እንዳልሰከሩ 'ዘማዊት'፣ “ኮማሪት' እና
ሌሎችም ፀያፍ ስያሜዎች የሚሰጧት ግን ከደጂ የሚጎትታቸው ስበት ያለ ይመስል የሚመላለሱላት ነበረች።

#ያኔ.....

በየጠዋቱ እያለቀሰች ሳላያት በፊት እንደሌሎቹ የሰፈራችን ህፃናት እናቴ የምትመስለኝ፣ አያቴ የሚበላ ነገር እቤት የሌለ ቀን 'ወይንሸትጋ ሄደህ ቀማምስ' ሲለኝ በጥቂት እርምጃ ከኛ ቤት የሚርቅ ቤቷ ሄጄ የምቅለስለስ፣ መብቴ እንደሆነ ሁላ ከተለያዩ ወንዶች ከወለደቻቸው ሁለት ልጆቿ ጋር ተቃምቼ ቤቷ የምበላ፣ የልጅነት ባሏ ሞቶባት አዲስ አበባ ከርማ ስትመጣ ጠላ ቤት መክፈቷን የሚያወሩላት በልጅነቴ የሞተች እናቴን የምትመስለኝ 'እናቴ' ነበረች።

#ያኔ......

ባል መሆን ምን እንደሚጠይቅ ባይገባኝም “እናቴ በየቀኑ የሚያስለቅሳትን የባል እጦት መሙላት ሆነ ሀሳቤ፡፡ጠላ ሸጣ የምታጠራቅመውን ሳንቲሟን ተማክረው የሚሰርቁባትን ልጆቿን ምንም እንኳን በእድሜም በጉልበትም ቢበልጡኝም አድጌና ጉልበት አውጥቼ እነርሱን ስርዓት ላስይዝላት ሆነ ምኞቴ፡፡

“ቆይ እኔ ልጆቼን አስሬ አላስቀምጣቸው? ምን አድርጊ ነው የሚሉኝ? ያለችኝ......

ያኔ በአስራ ዘጠኝ ዓመቴ የገጠር ከተማ ከሚሏት ከመንደራችን ራቅ ካለ ገበያ የአያቴን ድንች ሸጬ ስመለስ መንገድ ላይ አግኝታኝ፣ የእኔ ማደግ ከሚታየው በላይ የሷን ማርጀት በሚያሳብቅ ሽፋሽፍት የተከበበ ዓይኗን እያፈጠጠች፣ በባዶ እግሯ ውሃ ያቆረውን መሬት እየደለቀች ከሚፈናጠረው ጭቃማ
ውሃ ጋር እየተጫወተች ነበር፡፡

"ንገሪኝ እስኪ ፈልጌ ነው ልጆቼ ሌባና ቀማኛ የሆኑት? ምናለ እንደ ጥሩዬ አንድ ልጅ በማዕረግ አስመርቄ ሞቴ በበነጋው
ቢሆን?" ብላኝ ነበር፡፡ የተናገረችው ነገር ያላሳዘናት ይመስል ፈገግ እያለች፡፡

“ማን ምን አገባው? ቢጣን ያስተማርሻት አንቺ አይደለሽ? አዲስንስ ቢሆን? ......" እቤቷ እያስገባች የምታበላቸውን፣
ከእናቶቻቸው በላይ የምትንከባከባቸውን እና ያስተማረቻቸውን የስፈሩን ማቲዎች
ስም ደረደርኩላት።የመኖሯ ዋጋው
የሚንረው የምትበላውን ቆርሳ እያጎረሰች ላሳደገቻቸው፣ ጠላ ሸጣ ደብተርና እስኪሪብቶ ለምትገዛላቸው የደሀ መንደራችን ህፃናት ነው።

"አንተ? አንተስ አልማር ብለህ እንጂ ላስተምርህ አላልኩም?"
ብላኝ ዓይኗ ካፊያ እንዳዘለ ሰማይ እየዳመነ በመጣችበት መንገድ
ተመለሰች። ወደቤቷ ተከትያት ገባሁ። እንደቅርብ ጊዜ ልምዴ ከገበያ ይዤላት የመጣሁትን የገብስ ዳቦና የምትወደውን ነጭ ማር ሰጠኋት። እንደ ቅርብ ጊዜ ልምዷ እየተከዘች ስትበላ ረዥም መንገድ ሌጣውን የተጓዘ እግሬን በውሃ እያረጠብኩ አያታለሁ።

የመንደራችን ስኬት መለኪያ የሆነው እና እንደ ሁሉም የመንደራችን ቤተሰብ አያቴ እንደሱ እንድሆን ምሳሌ እንደሚያጣቅስልኝ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ገብቶ እንደተመረቀው
የጋሼ ሰላምነህ ልጅ እንድሆን ቢዘገይም ፊደል መቁጠሪያ ቤት ገብቼ ነበር፡፡ አንድ ቀን የጋሼ ሰላምነህን ልጅ አገኘሁት፡፡
ስለትምህርት ጥቅም እሱ ለዓመታት የተማረውን ምራቅ መዋጫ ፋታ ሳይወስድ መከረኝ፡፡

"ከዛስ?" አልኩት።

“ከዛ ስራ ይኖርሃል። ደመወዝ ይከፈልሃል፡፡ ከዛ ሚስት ታገባለህ፡፡ ከዛ ልጆች ትወልዳለህ።" አለኝ፡፡

“ከዛስ?" አልኩት መልሼ።

“ከዛማ በቃ ደስ ብሎህ ትኖራለሃ!"

“ከዛሳ?” አልኩት ደጋግሜ።

"ቂል ነው እንዴ? ደስ ብሎህ ኖረህ ታልፋለሃ:ፈ።"

"በቃ? መጨረሻው በደስታ መሞት ነው?" አልኩት ግራ እየገባው ያየኛል።

“ከመሞት በፊት ብዙ ደስታ አለው።ብዙ ስኬት አለው።ብዙ......" ጠፋበት መሰለኝ ዝም አለ፡፡

“ያው ነው። የሁሉም ጥቅል ደስታ ማግኘት አይደል? ደስ ባይሰኙም ወደማይቀር ሞት በደስታ መሄድ?" ስለው ይብስ ግራ እየተጋባ "እሺ ቆይ ህልምህ ምንድነው?" አለኝ፡፡

“የምን ህልም?" አልኩት፡፡

ስለ ህልም በትክክል እንደገባኝ እርግጠኛ ያልሆንኩትን ነገር ካስረዳኝ በኋላ "ወደፊት እንዲሆንልህ ወይም እንድትሆነው ወይም እንዲኖርህ የምትፈልገው ምንድነው?" አለኝ፡፡

"ወይንሸት። የወይንሸት ባል መሆን፡፡"
ስለው የነገርኳቸው ሰዎች ሁሉ እንደሚደነግጡት ደንግጦ ሀሳቤ የቂል መሆኑን በምሁር አንደበት ደጋግሞ መከረኝ

የጋሽ ሰላምነህ ልጅ ሌሎች ከተማ የሚኖሩ ዘመዶቹ እንዳለሙት
አለመ። የዚህ መንደር ነዋሪዎችም የጋሼ ሰላምነህን ልጅ ህልም እንድናልም ልጆቻቸውን ያስገድዱናል
በተለያየ በተለያየ እንቅልፍ ውስጥ አንድ አይነት ህልም እንዴት ይታለማል? የሆነ ሰው ያለፈበት መንገድ እና የደረሰበት ስኬት እንዴት የሌሎች ብዙዎች መንገድና መድረሻ ይሆናል? የሌሎች
ብዙዎች ደስታ በአንድ ሰው መዳረሻ እንዴት ይጠፈራል?
ሰው ሲይዘው ለማይረካው ደስታ፣ ነገ ለሚለጥጠው ፍላጎቱ፣ ጨብጦ ለማይበቃው በሽቃጣ ስኬት፤ ህልሜ ነው ብሎ እንዴት ይሄዳል? መማር ህልሙ የነበረ ሰው ስራ ይሆናል
👍3
የሚቀጥለው
ህልሙ ቀጥሎ ማግባት፣ ቀጥሎ መውለድ......ቅጥልጥል ህልም!

እኔ ግን ህልሜ አንድ ነው፡፡ ወይንሸት!! የሷ ባል መሆን፡፡ በቃ ቅጥልጥል የለውም፡፡ የደስታዬ ጥግ የሷ ባል መሆን ነው፡፡ በደስታ የምሞተው የሷ ባል ስሆን ነው።

የአያቴን ድንች እየሸጥኩ ብር የማመጣው ለሷ ነው።የምኖረው
ለሷ ነው:: መማር ህልሜ ስላልሆነ ተውኩት፣ መነገድም፣ሀብታም መሆንም፣
ሁሉም ህልሞቼ አይደሉም።ተውኳቸው::

#ያኔ......

ጠላ በምትሸጥባት ትንሿ ቤቷ ውስጥ ይጎርፉ የነበረ ወንድ ቁጥር እንደ ደበዘዘ መልኳ ተመናመነ፡፡

#ያኔ.......

ከተሜ ቀመስ ፋሽኗን ይከተሉ የነበሩ ጎረቤት ሴቶች ወልደው ከብደው በጎጆአቸው ውስጥ ጠፉ። ከነመኖሯም እረሷት፡፡

#ያኔ......

አንደኛው ልጇ ያላትን ዘርፏት አዲስ አበባ ገብቶ ሌላኛውም መንደሪቷን የበጠበጠ ቀማኛ ሆኖባት ብሶቷን የደመሩባት የወላድ መሀን ነበረች።

የመጨረሻው ክፍል ነገ ይጠብቁ

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍1
#እናቴን_ተመኘኋት


#ክፍል_ሁለት (የመጨረሻ ክፍል)

:
#በሜሪ_ፈለቀ

#ያኔ.......

በህፃን ልቤ ከተሸከምኳት፣ ባደገች ልቤ ካገዘፍኳት ከኔ በቀር መንደርተኛው ሁሉ ጤንነቷን የማይቀበል ብዙ ጊዜ ብቻዋን
የምታወራ ነበረች።

"ዞር በልልኝ ከዚህ! አንተም እንደመንደሩ ሰው እብድ መሰልኩህ? ዞር በል ብዬሃለሁ።ምን በሀጢያት ተወልጄ?
ሀጢያትን ሳቦካ ብኖር ልጄን የምተኛ ሸርሙጣ ታደርገኛለህ?" ያለችኝ......

ያኔ በሀያ አምስት ዓመቴ በረንዳዋ ላይ እሷ ተቀምጣ በገዛሁላት መስታወት የፊቷ ገፅታ ላይ ይሁን የፊቷ ማድያት ላይ የተሳለ ያለፈ ህይወቷ ላይ አፍጥጣ፣ በእንጨት ማበጠሪያ ረዥሙን እና ሽበት ጣል ጣል የጀመረውን ፀጉሯን እያበጠርኩላት 'ላግባሽ?' ስላት ነበር፡፡

"አንተ ባለጌ!! እናትህ መሆኔ ጠፋህና ለብልግናህ ተመኘኸኝ?"
ብላኝ ነበር እንደልጅነቴ ባለማወቄ ያለመሆኑን ስታውቅ፡፡እየተወራጨች ቢሆንም የምታወራኝ ለዓመታት አመሻሽ ላይ የማበጥርላትን ፀጉሯን ማበጠር እንዳቆም የፈለገች አትመስልም።

"ድንች ሸጩ ባጠራቀምኩት ብር ሰርግ እደግስልሻለሁ፡፡ በወግ ማዕረግ አገባሻለሁ። ባልሽ እሆናለሁ::" አልኳት የዛን ዕለት።

የመቀየም ይሁን የማዘን ያልገባኝን መተራመስ ፊቷ ላይ አሳይታኝ በቀስታ እጄን ከፀጉሮቿ ላይ አንስታ ተነሳች።
አንዳንድ ጊዜ እናቴ የሚያስመስላትን ፊቷን አመጣችው አንዳንዴ እንደሚሆነው የሌላ ሰው ከባድ ሰውነት የተሸከመ
ይመስል እግሯ እየተጎተተ ወደ ቤቷ ገባች። እንደነዚህ አይነት
አንዳንድ ቀኖቿ ላይ እንደማደርገው ተከተልኳት፡፡ ኩርምት ብላ መደቧ ላይ ተኛች፡፡ ትዩዩ ያለው ጠባብ መደብ ላይ ተቀምጬ አያታለሁ። ዓይኖቿ እንባ አቀረሩ።

#ያኔ.......

እቤት ስጠፋ ብቅ ይል የነበረው ያሳደገኝ ብቸኛው ዘመዴ አያቴም ስለሞተ እቤቷ ከኔ ውጪ ማንም አይገባም፡፡ የቀረው
ልጇም ሊዘርፋት የሚችለው ገንዘብ ስላልነበራት መኖሪያውን ከሷ አርቋል፡፡

#ያኔ.......

ነፍስ ያለው ሳቋ ብቸኛ ምንጭ የሆኑት ጤንነቷን በሚጠራጠሩ የመንደራችን ቤተሰቦች በተደጋጋሚ የሚቀጡት ህፃናት እንኳን ሲርባቸው እንዳልበሉ፣ ሲታረዙ በኪሮሿ ሹራብ ሰርታ እንዳላለበሰቻቸው፣ እናታቸው እንዳልነበረች ሁሉ ከቤቷ ቀሩ።

#ያኔ.......

“መካሪ ስለሌለው'፣ “እሱም እንደሷ እብድ ነው'፣ “አሳዳጊ የበደለው ሌላ ብዙ የምባለው እኔ ብቻ በጎጆዋ ነበርኩ፡፡

“የሙሽራ ልብሴን አልብሰኝ፡፡ ቀለበቱን እሰርልኝ፡፡ ወግ ማዕረግ አይታ ሞተች ልባል።" ያለችኝ

#አሁን.....

በጉልምስናዬ በበሽታ እና በሃዘን የደቀቀ ሰውነቷን መደቧ ላይ አሳርፋ፣ በመስታወቷ ልታየው የማትፈልገውን የፊቷን ገፅታ በእጆቿ ሸፍና፣ ከሚቆራረጥ ትንፋሿ እየታገለ በሚወጣ ቀሰስተኛ ድምፅዋ ነበር።

“ልጇን ያገባች ባለጌ ናት እንዲሉኝ አልፈልግም፡፡ ወግ ማዕረግ
ሳታይ ሞተች እንዲሉኝም አልፈልግም። ሊቀብሩኝ ሲመጡ ሙሽራ ሆኜ ያግኙኝ፡፡" አለችኝ፡፡ ግድግዳው ላይ በላስቲክ
ተሸፍኖ የተሰቀለውን ከአዲስ አበባ የገዛሁላትን የሙሽራ ቀሚስ ለመገለጥ በደከማቸው ዓይኖቿ እያየች።

በዚህ ቅፅበት የምላት ስላልነበረኝ ምንም አላልኳትም፡፡ ለገላዋ የወዘፍኩትን ውሃ በርዤ ገላዋን አጠብኳት። የታመመች ሰሞን ታደርግ እንደነበረው ሰውነቷን እንዳላይ አቅሙ ኖሯት አትከለክለኝም።

በአበባነት ዘመኗ እንደምታደርገው ሰውነቷን ውብ ጠረን ባለው ቅባት አሸሁላት፡፡ የሙሽራ ቀሚሷን አለበስኳት፣ ነጩን ጫማ አጠለቅኩላት፣ በሽበት የተወረረ ተነቃቅሎ ያለቀ ፀጉሯን አበጥሬ
በልጅነቴ ስታደርግ እንዳየኋት ጠቅልዬ በክር አስያዝኩላት፣ስታደርግ እንዳየኋት ዓይኗን በኩል ከንፈሯን በቀለም
አሳመርኩላት፣ ጣቷ ላይ ቀለበት አጠለቅኩላት። እንደቆነጀች
መደቧ ላይ አስተኝቻት በልጅነቴ የማውቀውን አሁን እያማጠች
የምትፈግገውን ነፍስ ያለው ፈገግታ አያለሁ፡፡ ከልጅነት እስከ ጉርምስና፣ ከወጣትነት እስከ ጉልምስና
የኖርኩለት ህልሜ እሷ ነበረች።ህልሜ በበሽታ ደቃ ልትሞት እጄ ላይ እያጣጣረች ነው። ከዚህ ወዲያ የምኖረው ለምን ይሆን? ለማንስ ይሆን?

#አሁን......

ላግባሽ ብዬ ስማፀናት “አሻፈረኝ ልጄ ነህ' ያለችኝ ወይንሽት በሞቷ አፋፍ ላይ ቀለበት እንዳደርግላት ጠየቀችኝ፡፡

#አሁን.....

ህልምና ዓለሜ የሷ ባል መሆን ብቻ የነበረው እኔ ህልሜ አብሯት ሊሞት እጄ ላይ ነው። ዓለሜም ሊጨልም እየተንደረደረ ነው።

#አሁን...

ባሏ ልሆን ማደጌን፣ ምኞቷን ልሞላላት መጎርመሴን፣ ማዕረጓን እንድታገኝ መጎልመሴን እንጂ እሷ ሚስቴ እንድትሆን ይሁን እናቴ እንድትሆን የምፈልግ የተዘባረቀብኝ እኔ አንዴ እናቴ ሌላ ጊዜ ወይንሽት የምትሆንብኝ ዓለሜ ልትሞት ነው፡፡ ሞታ ልትገድለኝ ነው።

#አሁን......

የወለደቻቸው፣ ያሳደገቻቸው፣ ያበላቻቸው፣ ያለበሰቻቸው፣ ያባበለቻቸው፣ የመከረቻቸው፣ በፍቅር ጉያዋ የተጠለሉ ህፃናት ሁላ አድገዋል። አይፈልጓትም። ሌላ የሚጠለሉበት ጉያ
ተሸሽገዋል።መሀን አድርገዋታል። ሊያለቅሱላት ግን ይመጣሉ።
እናታችን ነበረች ሊሉ።

#አሁን......

አግብተዋት ባሏ ያልነበሩ፣ በባልና በመሽማ ስም የተጣቧት፣
በውበቷ ፍሰሃ ያገኙ፣ ባለፈው እሷነቷ ውስጥ የነበሩ፣ የልቧን ዙፋን
የተቀራመቱ፣ በሴትነቷ የሰለጠኑ.... እነሱም አይፈልጓትም።ስግብግብ ምኞታቸውን አሟልተውባታል።
አሁን የሚቦጠቡጡት ጥቅም እሷጋ የለም። እነዚህም በእድሜና
ምቾት የሰባ ስጋቸውን አስቀድመው እና ፀጉር አልባ ራሳቸውን እየነካኩ ይመጣሉ። ሊያለቅሱላት፡፡ ወዳጃችን ነበረች፣ ፍቅራችን ነበረች፣ እያሉ ሊያለቅሱላት።

#አሁን......

ባሏ እንዳልሆን በልጅነቴ የሰለጠኑባት ባል መሳዮች ሲያበግኑኝ በጉርምስናዬ በግድ ያለፍላጎቷ አግብቻት እንዳለፉት ባሎቿ እንዳልመዘብራት ፈርቼ፣ በወጣትነቴ ፍላጎቷን አክብሬ፣ በዙፋኗ
ልትሾመኝ እንዳላመነችኝ ገብቶኝ ታግሼ፣ በጉልምስናዬ ደግሞ ባሏ ሆኖ ሙቀቷን ከመጋራት እና እናቴ ሆና ከምጠብቃት
የትኛውን እንደምመርጥ ግራ እየገባኝ ህልሜ፣ ዓለሜ......የመኖሬ ምክንያት የሞቷ አፋፍ ላይ ናት፡፡

አለቅስላታለሁ፡፡ እናቴ ሞተች ብዬ የልጆቿን ሁሉ አለቅስላታለሁ። ሚስቴ ሞተች ብዬ የሰውነቷን ጥፍጥና
የቀመሱትን ለቅሶ ሁሉ አለቅስላታለሁ። እኔ ህልሜ ሞተች ብዬ የራሴን አለቅስላታለሁ።እንደባል የሰለጠኑባትም እንደ ልጅ የተጠለሉባትም የተዋት
መታመሟ ያላመማቸው የሁሉም የነበረች እሷ በሞቷ ዋዜማ እጄ ላይ ናት።የእኔ እጅ ብቻ ላይ ሙሽራዬ!!!

አ...ለ...ቀ

በዚህስ ድርሰት ላይ ምን ውስጣቹ ተብላላ? አሳውቁኝ።

ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏
👍3
#ታዲያስ_ምን_አዲስ_ነገር_አለ?

ታዲያስ ምን አዲስ ነገር አለ?

ጀንበር በምራብ ወጣች
ሮብ ሰኞን ተከተለ
ኦጋዴን ላይ በረድ ፈላ
ስሃራ ላይ ዝናብ ጣለ?

ታዲያስ ምን እዲሰ ነገር አለ?

ኑሮ ታምና ተሻለ
ሸክሙ ከትናንት ቀለለ
አገር ጣጣውን ፈታ፥ ወይስ ጣጣውን አከለ
ዜጋው ራሱን ቻለ፥ ወይስ ራሱን ደለለ
“የጌታ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን” እያለ?

ታዲያስ ምን አዲስ ነገር አለ?

ማን ነበሩ እትየ እንትና
መቸም የድሀ ስሙ፥ ለትውስታ አይበቃምና
ምነው እኒያ እንኳ
በቁጥር ለማይሰፈር አመት
የሚጎበኝ እንጂ የማይሸመት
የቲማቲም ጉልት ዘርግተው
እንደብቅል ቀኑን ሙሉ፥ ከጸሐይ ሥር የሚስጡ
ሙያቸውን ለወጡ
በሙያቸው ተለወጡ
ከችግራቸው ወጡ
ወይስ በችግራቸው ተዋጡ
ከብረው መኪና ገዙ፥ ወይስ ሰመኪና ተዳጡ?
#ማንም_ግድ_አይሰጠው

ቂጡን ዙፋን ላይ፥ ስለዘፈዘፈ
በጭቦ በኖረ፥ ድሀ እየዘረፈ
ንጉሥ የተባለ፥ የተቀባ ሌባ
ወትሮ ይወደሳል
ሚያመልከው አያጣም፥ ያውም በግዜር አምሳል፤

ግና ለንባሩ
ከላይ በትረ መንግሥት፥ ለሚቀጠቅጠው
ከታች የማጣት ፊት፥ ለሚገላምጠው
ማንም ግድ አይሰጠው፤

መቸም በዚች ዓለም፥ ታሪክ የሚያደላው
ቅልጥም ለሚሰብረው
እንገት ለሚቀላው
መንገድ ሲሰራለት፥ እግር ለሚቆርጠው
ሐውልት ሲሰራለት፥ ሐውልት ለሚያፈርሰው
ከማውደም በስተቀር፥ ተሰጥኦ ለሌለው
ስጦታ የለሽ ሰው፤
ሕይወት ለሚመልሰ፥ ሕይወት ላመለጠው
ለወጌሻው ግና
ማንም ግድ አይሰጠው፤

ለሰላም ዝምታ፥ ላምባጓሮ መገን
ባዝማሪ ልሳን ላይ፥ ነፍሰ ገዳይ ሲገን
ባቆላማጭ ምላስ፥ ፋኖ ሲመሰገን፤

ከሴት ማሕፀን አፍ
ከህላዌ ደጃፍ
ጨቅላ ተቀብላ
እትብት ለምትቆርጠው
ለዚያች አዋላጅ ሴት
ማንም ግድ አይሰጠው።
#ሙሾ_ላመለጠ_ወጣትነት

ሳይደምን ይዘንባል
ይዶፋል
ከደጃፌ ግርጌ፥ የሕይወት ጎርፍ ያልፋል፤

የከንፌ ርጋፊ
አንድ የላባ ነዶ
ያካሌ ቅራፊ
የቀረ ተጎርዶ
ተጠርጎ ሲወሰድ፥ በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ፤

ሲጋልብ በፊቴ፥ ይህ የውሀ ሰጋር
ጀምበሬን አየኋት
ተጠርጋ ሰትሄድ፥ ከሰርዲን ጣሳ ጋር

የልጅነት ቅርሴ
ድዴ ያባረራት፥ ያች የወተት ጥርሴ
ካሮጌ ቆርኪ ጋር፥ አብራ ተቀላቅላ
ባረፋ ተከባ፥ በጎርፍ ጀርባ ታዝላ
ሰትሄድ እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ፤

የመጀመርያዋ፥ የጉንጨ ላይ ቡግር
የመጨረሻዋ፥ የራሴ ላይ ጠጉር
ከሳር ከትቢያው ጋር፥ እንደተቃቀፉ
በጎርፉ ጀርባ ላይ፥ እየተንሳፈፉ
እንደዋዛ ሲያልፉ
በጥሞና እያየሁ
ይሄው ቁጭ ብያለሁ።
#የመኖር_ትርጉሙ

የመኖር ትርጉሙ
የንባ ቅብብል ነው፥ በትውልዶች ማህል
አባትህ ያነባው፥ ላንተም ይደርስሃል፤
ስው የሆንሁ ለታ፥ ደርሶኛል ይህ እጣ
አልቅሼ አንደገባሁ
አስለቅሼ ልውጣ።
#አስታራቂ_የለም

ጠብ ምድርን ባይሞላት
አቤል ባይፈጠር
አቤል ያቤል ጠላት
አቤል የራሱ ጠር
አንድ ሰው ከሁለት፥ ተከፍሎ ሲፋለም
ሸምጋይ
ወይ ገላጋይ
አስታራቂ የለም።
Forwarded from አትሮኖስ (...) via @Qualitymovbot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንደምነሽ_ሸገር

እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የቤት አከራየ፥ የጋሽ ጣሰው አገር
እንዱ የሚተከልሽ
ሌላው የሚነቅልሽ
የዘመቻ ድንኳን፤

ቡግርና ችግር፥ ካባቴ ወርሼ
ብኖርብሽ እንኳን
የማልቀየምሽ
ሁሌ የማልምሽ፣

Oh, my God ይመስገን
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤

ከፊል ሩዝና፥ ከፊል ጤፍ እቡክቼ
እንጀራ ሚመሰል፥ ሰጋጃ በልቼ
አዋጅና ዜና፥ ባይፎኔ ሰምቼ
ሐሜት ሲናፍቀኝ፥ በፓልቶክ አምቼ
ጥቃት ሲበዛብኝቱ ፌስቡከ ላይ ሸፍቼ
በኮመንት ሩምታ፥ ጠላቴን ደፍቼ
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤
እንደምነሽ ሸገር
እንደምነሽ ሸገር
የማይበገረው
ወር እየጠበቀ፥ የሚያንገራግረው
የቤት አከራየ፥ የጋሽ ጣሰው አገር፤
የከሰመው ወንዝሽ
የነጠፈው ወዝሽ
የሚታየው ነጥፎ
እንደምነው ጣፎ
እንዴት ነው ቀበና
እስቲ ድንጋይ ላጥምድ፥ መረብ ልጣልና፤

ልከ እንደነ ፓሪሰ
እንደ ለንደን ሁላ
ፏፏቴም ባይኖርሽ፥ ሽቅብ የሚፈላ
ምንጭሽ ከማን ያንሳል
ከፈነዳ ቱቦ፥ የወጣ ሰገራ፥ ሰንጥቆሽ ይፈሳል፤

እንደምነሽ ሸገር
የቅጠላቅጠል፥ የፍራፍሬ አገር
አንድ ዘለላ ሙዝ፥ ልጠሽ ባታበይኝ
በሙዝ ልጣጭ ጠልፈሽ፥ ምታንከባልይኝ
አሳድገሽኛል፥ በማርና ወተት
የተሞላ ተረት
እየተረከሽልኝ
ጥማቴን በጥማት እያረካሽልኝ፤

እንደምነሽ ሸገር
Oh my God ይመስገን
እኔ እንዳለሁ አለሁ፤

ሰርቼ ቀፍየ
ሲነጋም ከፍየ
ሲመሽም ከፍየ
ሥጋ ምታወፍር፥ ነፍሶ የምታሳሳ
ዘናጭ አልጋ ሰጥታ፥ እንቅልፍ የምትነሳ
አገር ላይ ተጥየ።

🔘በውቀቱ ስዩም🔘
#ማንባት_ነው_ያሰኘኝ

ማንባት ነው ያሰኘኝ
ማልቀስ ነው ያማረኝ
ከቁጭቴ ጋራ፥ ወትሮ ከመታገል
የንባ ማድጋየን፥ ሰብሮ መገ
ላገል
ማልቀስ ነው ያማረኝ፤

ያደራ ሳንዱቄ፥ ሲሰበር ከዳኑ
የባልንጀርነት፥ ሲጣስ ቃልኪዳኑ
መጋኛ ሲመታው
ዝምድና ሲከፋ
ፍቅር መሬት ከድታው
ባፍጢሙ ሲደፋ
የዳመነ ፊቴን፥ መዳፌ ውስጥ ልቅበር
የንባ ጋኔን ልስበር፤

እኔ
እንደ በሬ ያረስሁ
እህል የጎመጀሁ፥ ዝማምን የጎረስሁ
እዝመራ ያደረሰው
ፍሬውን ያልቀመስሁ፤

እኔ
መከራን በበርሚል፥ መጥናናትን በፍኝ፥
ከዘመን ያተረፍሁ
እንቧይና ሙጃ፥ የወረሰው ሳሎን፥
ሳልፈልግ የታቀፍሁ
ቀስተ ደመናዬ፥ ምድጃ ሥር ወድቆ
እፍኝ አመድ ዝቆ፥ እፍኝ ትቢያ ቅሞ
ጥላሸቱን ጠግቦ፥ እድፍ ተሸከሞ
ኖህ ከነታሪኩ
ከነታይታኒኩ
እባሕር ውስጥ ሰጥሞ፥ ለማየት የበቃሁ
ፊቴን እየፈጀሁ፥ ደረት እየደቃሁ
ማልቀስ ነው ያማረኝ።
👍1