#ቅዳሴና_ቀረርቶ
፡
፡
#ክፍል_ሦስት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
፡
.."የአባቴን ገዳይ ገድዬ ነው ከሃገር የተሰደድኩት።" አለኝ ዳግማዊ ምንም የሚያስደነግጥ ነገር እንዳልነገረኝ ሁሉ በመሀከላችን የትራስ ድንበር አበጅተን በምንተኛበት አልጋ ላይ እንደተገደመ።
"ገድዬ ማለት? "
"በገንዘብ ተጣልተው የገዛ ጓደኛው ነው በስለት ወግቶ የገደለው።"
"ከዛስ?"
"ሰውየው እንዴት እንደሆነ ባላወቅነው ሁኔታ በሶስተኛው ወር ተፈታ።"
"ከዚያ በኋላ ያለውን?" አልኩት አስደንጋጩን የወሬ ክፍል 'ገደልኩት' ያለኝን ለማረጋገ። ደምስሩ ተገታተረብኝ። ፊቱ ተቀያየረ። የአሁን ትንግርት የሚነግረኝ ይመስል ሰውነቱ እየተንቀጠቀጠ ነው የሚያወራው። ሲያወራኝ ተመሳቀልኩ። ስሜቱን ለመረዳት እየሞከርኩ ስሜቴ ተሳከረ። ልክና ስህተት ውሉ ተጣረሰብኝ።
አባቱ ሲገደሉ በአይኑ አይቷቸዋል። በራፋቸው ላይ ነው የተገደሉት። ዳግማዊ አመሻሽ ላይ ወደ ቤት በሚወስደው ጭር ያለ ቀጭን መንገድ እየገሰገሰ ሰፈር ሲደርስ ከወዳጃቸው ጋር እየተጓዙ አባቱን በርቀት አይቷቸዋል። እንዲያዩት ስላልፈለገ ወደ ኋላ ቀረት ብሎ ከአይናቸው ሰወር አለ። ቤታቸው መግብያ ጋር ሲደርስ የተቃቀፉ መስለው። ብዙም ሳይቆይ ግን አባትየው ወደቁ። ወዳጃቸው አካባቢያቸውን ቃኘት እያደረጉ ከሩጫ ባልተናነሰ ፍጥነት ከዳግማዊ በተቃራኒ አቅጣጫ መሄድ ጀመሩ። ዳግማዊ እየሮጠ አባተቱጋ ሲደርስ ጣር ላይ ነበሩ። ከደረታቸው የሚፈስ ደማቸውንና በእጃቸው ፍራፍሬና የተጠቀለለ ኬክ መያዛቸውን እኩል ቃኘው። የቅድስት አሰራ አምስት ዓመት ልደት በዓሏ ነበር። በጣር ስቃይ ውስጥ ሆነው እጁን ጨብጠው ቤተሰቡን እንዲንከባከብ ለመኑት። ዳግማዊ ገዳያቸውን ከመከተልና አባቱን ከማንሳት የቱ እንደሚቀድም ግራ ገብቶት ዋለለ። በደመ ነፍስ የእናቱን፣ የእህቱን፣ የኸንድሙን፣ የሚያስታውሰውን ሰው ስም ሁሉ በጩህት ተጣራ።
"እናቴ የኔን ጩህት ሰምታ ስትሮጥ ከቤታችን መግቢያ ደረጃ ላይ ወድቃ እግሯ ተሰብሮ ነው ስታነክስ ያየሻት" አለኝ እያንዘፈዘፈው።
ገዳይ የተፈቱት ገና የፍርድ ሂደቱ እንኳን ሳያልቅ ነበር። ይመለከተዋል ላሉት አካል አቤት አሉ። አቤቱታቸው መልስ ከማግኘቱ አስቀድሞ ገዳይ ሀገር መቀየረቻው ተሰማ። ዳግማዊ ተከተላቸው። የአባቱን አገዳደል ተመሳሳዩን አድርጎ ወደ ሱዳን ተሰደደ። ቤተሰቡም የሚኖርበትን የደብረ ማርቆስ ከተማ ጥሎ ናዝሬት ከተማ።
"አንዳንዴ ህይወት ፍትህ አታውቅም። ይሄኔ ፍትህን በራስ እጅ መስጠት! !" አለ ከቀድሞው ተረጋግቶ።
"ለዚህ ነው ቤተሰቦችህ እንደ መሲህ የሚያዩህ? " አልኩት ያልኩት ተገቢ መሆኑ ግራ እያጋባኝ።
አባቱ ከሞቱ በኋላ በአባትየው የእህል ንግድ ይተዳደር የነበረው ቤተሰብ ውጥንቅጡ ወጣ። ዳግማዊ ለአራት አመታት እዚህ ግባ የማይባል ኑሮ ሱዳን አገር አንገላታው። ይሄኔ ቢኒያም ትምህርቱን አቁሞ እህቱንና እናቱን ማስተዳደር ግድ ሆነበት።
"ባንተ ቦታ ሆኜ ስሜቱን አላውቅም። ግን በምንም ሂሳብ ጠፋት በጥፋት ተጣፍቶ መልሱ ልክ አይመጣም።" አልኩት።
"አንዳንድ ጥቃትና መቀማጥሽ በይቅርታና በተፃፈ ህግ እንደማይዳኝ የሚገባሽ ባሏን ለተቀማች እናቱና አባታቸውን ላጡ ታናናሾቹ ብቸኛ ተስፋቸው የሆነ ወንድ ልጅ ሆነሽ ስታይው ነው። አለኝ።
"ሳትገባኝ ቀርተህ አይደለም።" አልኩት ስሜቱን የጎዳሁት መስሎኝ እጄን አሻግሬ እጆቹን እየዳበስኩ።
"እንደማልገባሽ ይገባኛል።" ሲለኝ የሳሎኑ በር ተንኳኳ እና ለመክፈት ተነሳ። ለምን እንደተከተልኩት ሳላውቅ ተከትየው ሳሎን ሄድኩ። ቢኒያም ነው። ተስተካክሎ መቆም እስኪያቅተው ሰክሯል። እናትየው ከመኝታ ቤታቸው ብቅ አሉ። ከመጣን አራተኛ ቀናችን መሆኑ ነው። ከአታካች የአራት ቀን መሰንበት በኋላ ዛሬ ቢኒያም ስላመሸ ሳንተኛ እየጠበቅነው ነበር።
"ደህና አደራችሁ? ማለቴ አመሻችሁ? አለ ሶስታችንንም ተራ በተራ እያየ። ዳግማዊ ተናዷል። እናት ከዝነዋል። እኔ ካለመዋሸት በሁኔታው ሳቄ መጥቷል።
"ደሞ ተጣላችሁ? " አሉ እናቱ።
"አልተጣላንም። ተጣላችኝ" አለ ቢኒያም በቁሙ ሶፋው ላይ እየወደቀ።
"ማናት?" ጠየቀ ዳግማዊ።
"አለችልህ የሴት ጉድ!!። መለሱ እናት ፍቅረኛው መሆኗን እና ከእርሷ ጋር ሲጣላ እየጠጣ እንደሚያመሽ አከሉበት። ቀጥለውም "ቢቆጠር ከፍቅራቸው ፀባያቸው ይበልጣል። ልጅቷም ብቻዋን አይደለችም የሆነ ጋኔን ቢጤ ያግዛታል። ልጁን ጂል እኮ ነው ያደረገችው።" እየተናገሩ ወደ መኝታ ቤታቸው ተመለሱ።
"አሁን ግባና ተኛ ጠዋት እንነጋገራለን።" አለ ዳግማዊ በቁጣ ወደመኝታ ቤት ለመግባት እየተነሳ።
"ዲጉ ግን ፍሪጅ ውስጥ ነበር እንዴ የከረምሽው?" አለ ቢኒያም ስካርና ሳቅ እየተቀላቀለበት። ዳግማዊ ዘወር ብሎ አየው።
"ማለቴ አልተለወጥሽም።" ሲለው እኔ ሳቄን ለቀኩት። ዳግማዊ እኔንም እሱንም በአንድ ዙር ገላምጦን ገባ። አታምኑትም!! ሰክሮ ሲለፋደድ እንኳን የሚፈታተን መስህብ አለው። ባልተሰማ ለማለፍ የሚከብድ ፍም ስሜት።
"ትልቅ ልጅ እኮ ነው ልትቆጣው ባልሆነ" አልኩት ዳግማዊን እንደቅድማችን እንደተጋደምን። በነገራችሁ ላይ ምንም ተፈጥሮ አያውቅም። የእኔ ምክንያት ዳግማዊ የሚያማልለኝ አይነት ወንድ አይደለም። የእርሱን አላውቅም።
"ቤች 'ፕሊስ' ከቤተሰቤ ጋር እንዴት መግባባት እንዳለብኝ ለኔ ተይልኝ!!" አለኝ እንደተለመደው ጀርባውን አዙሮ እየተኛ።
"አብረን እየዋሸን ነው አላልከኝም? ቤተሰባዊነቱንም አብረን እየኖርነው ነው።"አልኩት። አልመለሰልኝም። ራሱን የቤተሰቡ እረኛ አድርጎ መቁጠሩ ከእድሜው የበዛ ጭምት አድርጎታል።
ከነጋ በኋላ እንቅልፍ እንዲወስደኝ ስገለባበጥ አርፍጄ ተነስቼ ጎዳ ስገባ እታባ ቁርስ እያበሰሉ አገኘኋቸው እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ያለው አጥርና ገደብ ይጨንቃል።የተመጠኑ እና የተለመዱ ጨዋታዎችን ከመጫወት ያለፈ ቅርርብ የላቸውም።እዚህ ቤት መከባበር እና መፈራራት ድንበራቸው ተቀላቅሏል።አብሬአቸው ስቀመጥ ልቤ ምጥ ይይዛታል።
የክፍል አለቃ እነዳስጠነቀቀዉ ተማሪ እጄን ማጣመር ሁሉ ይዳዳኛል ገደባቸውን አፍርሼ ላወራቸው ብሞክርም መልሳቸው አጭርና ለሌላ ጨዋታ የማይጋብዝ ይሆንብኛል ።እታባ ቁርስ ማብሰሉን እንዳግዛቸው ስላልፈቀዱልኝ አገጠባቸው ሆኜ የባጥ የቆጡን አወራለሁ።አንድ ወሬ እጀምራለሁ። ሳልጨርስ ሌላ እጀምራለሁ በዝምታ ከስንት አንዴ ዓይኔን እያዩ ከመስማት ያለፈ አይመልሱልኝም ሁሉም ሰው ሌላን ሰው ወደራሱ የሚጋብዝበት ርቀት ገደብ አለው።ጭራሹኑ ማንንም የማያስደፍረው የራሱ ክልልም ይኖረዋል።እኔ ደግሞ መሰረታዊ ችግሬ የሰዎችን ድንበር መጣስ ደስ ይለኛል። አንድን ሰው ስቀርበውና ቀስ በቀስ አጥሩን እያለፍኩ መዝለቅ የቻልኩ ሲመስለኝ ክብረ ወሰኑን እንዳሻሻለ አትሌት ሀሴት አደርጋለሁ።
"በይ ባልሽን ቁርስ ደርሷል በይው።" አሉኝ እታባ ከወሬዬም ለመገላገል ይመስላል። ለዲጉ መልእክቱን ካስተላለፍኩ በኋላ የማደርገው ሳይገባኝ ወደ ቢኒ ክፍል አመራሁ። ባንኳኳ መልስ የለም። ደግሜ አንኳኳሁ።
"አቤት?" አለ ቢኒ በጎርናና አንደበት። ለመግባት ፍቃድ ሳልጠይቅ ነው የዘለኩት። አልጋው ላይ እንደተጋደመ ሲጋራ እያጨሰ ነበር።እኔ መሆኔን ሲያውቅ ሲጋራውን ለማጥፋት ፈጠነ። እንደ መአት የሚፈራው ሚሴቱ ነኛ!
"አጭስ ችግር የለውም። ጭስ አታባክን ።" አልኩት።
"ልግባ ወይ አይባልም እንዴ? ራቁቴን ብሆንስ?" አለኝ ቀልድ በመሰለ ቅሬታ።
"ጠባሳ አለብህ እንዴ ታድያ? ራቁትክን የሆንክ እንደሆነስ?" መለስኩለት ከንፈሩን
ወደ ጎን ሸፈፍ አድርጎ ፈገግ አለ። ከንፈሩ የሚያቀ

👍4
ነዝር ሽፍደት አለው።"ቁርስ እየጠበቅንህ ነው ።" አልኩት ቀጥዬ።
"ዲጉ ተበሳጭቶብኛል አይደል?" አለኝ ልወጣ ወደ በሩ እያቀናሁ ሳለ።
"ትንሽ"
ኑሮ በሚያህል ከባድ ዝምታ ቁርስ ተበላ።ቄጤማው ተጎዘጎዘ ፣ ቡና ተፈላ፣ እጣን ተጫጫሰ፣ ፈንድሻው ተበተነ፣ ግን ደስ አይልም። ሰዎች የሌሉበት ፍዝ ስነ ስርአት ቀብር አካሄጅ የሚመስል ጨዋታ የሌለበት ስብስብ የማላውቀው ሰው ቤት ተገድጄ ለቅሶ ልደርስ የመጣሁ መሰለኝ። ከሰሞኑ በባሰ ሁኔታ ልቤ በደነች።
"የምትናገረውን ተናገርና ልባችንን አውርደው"አልኩት ዲጉን። ሁሉም ፊቱን አቀጨመ።ኪዱ እንደ ማሳል አደረጋት።
"ምኑን?" ብሎ አፈጠጠብኝ።
"እኔ ምን አውቃለሁ። የማውቀው እንደተናደድክበት ነው።ዲጉ መልስ አልሰጠም። ከፈንዲሻው ጋር እየተጫወተ ዝም።ቢኒ ይጠብቃል። ደቂቃዎች አለፉ። ቃል ለማውጣት አፉን ለማላቀቅ የደፈረ የለም። ቢኒ ለመሄድ ሲነሳ
"ቁጭ በል!" አለው ዲጉ ቁጣና ትእዛዝ ለውሶ። ሁሉም ደነገጠ። እኔ ግን ደስ አለኝ። ቢኒ የተባለውን አደረገ።
"ምን ማድረግህ ነበር?" ብሎ ጀመረ። ነፍስ ያላወቀ ልጁን እንደማቆጣ አባት ወረደበት።ጣልቃ ገብቶ የተቃወመም የደገፈም የለም። ሲጨርስም ከአስፈሪ ፀጥታ ውጪ ጥያቄም መልስም አስተያየትም አልተሰማም።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን። 🙏

👍1😁1
Re-post
#ኢትዮጵያዊ_ነኝ
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደአክሱም ድንጋይ እንደሮሀ አለት
የጊዜ ሞገድ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ከዋርካ ባጥር ከእምቧይ ተልቄ
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ አደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ተራራ መራጭ
ልክ እንደአሞራ ብርንዶ ቆራጭ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
እንደመሐረብ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ የማልገታ
ኢትዮጵያዊ ነኝ።💚💛❤️
🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
#ኢትዮጵያዊ_ነኝ
ኑሮ ቢገፋኝ የማልወድቅለት
እንደአክሱም ድንጋይ እንደሮሀ አለት
የጊዜ ሞገድ ያላደቀቀኝ
የመከራ ዶፍ ያልነቀነቀኝ
ለሙሾ ሲያጩኝ ቅኔ የምቀኝ
በግራ ሲሉኝ የምገኝ በቀኝ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ከዋርካ ባጥር ከእምቧይ ተልቄ
ከፀሐይ ባንስም ከኩራዝ ልቄ
ተምድረበዳ ጅረት አፍልቄ
ጥሜን የምቆርጥ በእፍኝ ጠልቄ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
ግትር ጠላቴን በአጭር አንካሴ
ራስ ምታቴን በዳማከሴ
ነቅዬ ምጥል
ነገር በነገር የማብጠለጥል
ለወዳጆቼ አደይ ምነቅል
በጠላቴ ፊት ቀንድ የማበቅል
ልክ እንደዋልያ ተራራ መራጭ
ልክ እንደአሞራ ብርንዶ ቆራጭ
ኢትዮጵያዊ ነኝ
እንደመሐረብ ቤቴን በኪሴ
እንደንቅሳት ተስፋን በጥርሴ
ይዤ የምዞር
ከቦታ ቦታ
በዘብ በኬላ የማልገታ
ኢትዮጵያዊ ነኝ።💚💛❤️
🧿በእውቀቱ ስዩም🧿
#ቅዳሴና_ቀረርቶ
፡
፡
#ክፍል_አራት
፡
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
፡
"ይቅርታ ዲጉ!" ብቻ ብሎት ወደ ክፍሉ ገባ።
ቀለም አልባ ቀን ከዋልን በኋላ ቢኒ ዛሬም ስላመሸ እታባን እንዲተኙ ነዘነዝን፣ ዲጉ በጥናት ሰበብ (አዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ናት) ወደ መኝታቸው ሲሄዱ እኔና ዲጉ ጠባቧ ሳሎን ቀረን። ዝንብ እግሯን ወለም ቢላት በሚሰማ አይነት ዝምታ ተወጠርን።
"ኸረ ቢያንስ ቲቪውን ክፈተው።" አልኩት
ሪሞቱን አቀበለኝ።ሽለላ ሲቀረው እየተንጎራደደ እና ሰአቱን በማይክሮ ሰከንድ ልዩነት እየገላመጠ ሲጠብቅ ቢኒ እኩለ ለሊት ላይ ጥንቅቅ ብሎ ተከሰተ። በእጁ የያዘውን ሲጋራ ሲያይ ዲጉ አበደበት።
"ጋጠ ወጥነት ካማረህ ለምን ራስህን ችለህ አትወጣም?" ብሎት በሩን ቆልፎ ወደ መኝታ ቤቱ ገባ።
"ቆንጆ ናት?" አልኩት። ቢኒን ነው የጠየኩት።
"ማን?"
"እንዲህ ራስህን የምታዝረከርክላት።"
"እ..ሰይጣን እኮ ቆንጆ ነው።" መለሰልኝ።
"ሰይጣንነቷን እንዳይሆን የምትወደው"
"ምኖን እንደምወደው አላውቅም።" በስካር አንደበቱ ስለሷ ገለፃና ትንፋሽ እስኪያጥረው ጠረቀ።ሳላቋርጠው ሰማሁት። ውበቷን፣ ፍቅሪሩን፣ወፈፌነቷን እየፈገገ እና እየጨፈገገ ሳለልኝ።
"እኔ ማለት እይታው የደበዘዘበት ከንቱ ነበርኩ።እሷ የአይኔ መነፅር ናት። ፊቴን አጥርቼ የማይባት፣ ኋላዬን የምቃኝባት፣ ጎኔን የምፈትሽባት።ሳወልቃት አስተካክዬ መርገጥ አልችልም።ያለሷ ወልጋዳ ነኝ"። የገለፀበት መንገድ ቀላልም ከባድም ሆነብኝ።
"ዓለምን በሌላ መነፅር ለማየት ፈሪ ሆነክ እንዳይሆን?" ስለው ዝም አለኝ።
"ደህና አደር!!" ብዬው ወደኋላ የሚጎትተኝን ልቤን ወደ ፊት በሚራመድ እግሬ እየረታሁ ጥየው ገባሁኝ።
"ለእህቱ ምሳሌ ለእናቱ መመኪያ እንዲሆን እፈልጋለሁ።" አለኝ ዲጎ ገና ከመግባቴ ጠብቆ።"የሚያወራው ስለ ህፃን ልጅ እንጂ ሀያ ዘጠኝ ዓመት ስለሞላው ወንድሙ አይመስልም።
"ሁሌ ለሌሎች መኖር ይከብድ ይመስለኛል። የራሱን ስሜት ማዳመጡ ሰውኛ ነው።"
"የራሱ ስሜት ስርአት አልባ መሆን ነው? ለታናሽ እህቱ ዱርዬነት ማስተማር? ህመምተኛ እናቱን እኩለ ሌሊት ድረስ ማስጠበቅ?"
የሚናገረው ከሙሉ ቅንነትና ለቤተሰቡ ተቆርቋሪነት ነው። እንኳን የሌላን ሰው የመኖር ልጓም የራስን የሕይወት አቅጣጫ መወሰን የማይቻልበት አጋጣሚ የትዪለሌ መሆኑን ላስረዳው ምከርኩ። ስሜት፣ ሕይወት፣ ኑረት፣ ህልም፣ ቅዠት....ለእርሱ ከቤተሰቡ የሚበልጥ የለውም።ራሱን እንደ አባትም እንደ ታላቅ ወንድምም እንደ መልካም ልጅም እንዲቆጠር ከአባቱ የመጨረሻ ቃል በላይ የቤተሰቡ በእርሱ ላይ ያለው እምነት አስገድዶታል።አልፈርድበትም። በተቃራኒው የዘመኑን አጋማሽ ለቤተሰቡ መኖሩ አሳዘነኝ።በቤተሰቡ መሃል የሚፈጥረው ኢምንት ክስተት ሳትቀር የእርሱ ሃላፊነት እንደሆነ የሚሰማው መሆኑ ከቤተሰቡ ደስታ በላይ የሚያስደስተው ነገር አለመኖሩን ነገረኝ።
"ሳትዋሽ ንገረኝ አጭሰህ፣ ሰክረህ.. ምናምን አታውቅም?"
"አላውቅም። ቀጭራሽ!! መጠጣት እጠጣለሁ።ሰክሬ ግን አላውቅም" በሰላም?" ልለው ቃቶኝ ነበር።ለእሱ ቀልድ አይሆንም ብዬ ተውኩት።
"እሺ በህይወትህ የሰራኸው ትልቁ እብደት ምንድን ነው?"
"ለምን አብዳለሁ?"
"እሺ ስትበሳጭ ወይ ስትበሽቅ በምንድን ነው ብስጭትህን የምታበርደው?" ስለው ፈጥኖ አልመለሰልኝም።
"ምንም።" አለ እርግጠኝነት በጎደለው ድምፀት።
"አትዋሽ!!" ስለው ፊቱን አዙሮ ተኛ!! ጀርባውን እንደሰጠኝ "አንቺስ? ስትበሳጪ በምንድነው የምታበርጂው?" አለኝ። ለመልሴ ምንም ሳይጓጓ።
"በብዛት ክለብ ወጥቼ እጨፍራለሁ። አንዳንዴ ረጅም ወክ ሳደረግ እረጋጋለሁ" መለስኩለት። ዝም ብሎኝ ተኛ!!
ጠዋት ያለወትሮዬ አርፍጄ ስነቃ ቀድሞኝ ነቅቶ ኮርኒሱ ላይ ፈጧል።
"እስቲ ዛሬ ወጣ እንበል? አዋዋላችንን እንቀይር?" አልኩት።
"ወጥተንስ?"
"እህ...እዚህ ቤት ከገባን ስድስት ቀናችን"
"ቤች በጣም ይቅርታ! ለኔ ብለሽ ብዙ እያደረግሽ እንደሆነ አውቃለሁሁ። እንዴት እንደማመሰግንሽ አላውቅም። እኔ ከእናቴጋ ልቆይ። ከኪዱ ጋ ወጣ በሉ።"
"ኪዱ ነገ ፈተና አላት!!" ስለው መላ እንደሚፈልግ ሰው እንደማሰብ አደረገ። ግን ምንም አልተናገረም።
"ቤን ከስራ ስንት ሰዓት ነው የምትወጣው?" አልኩት ሆን ብዬ ቤተረቡ ለቁርስ በተሰበሰበበት።
"አስር ሰአት ገደማ" አለኝ እየተጣደፈ እየተመገበ።
"ማክያቶ እንድንጠጣ ነበር።" ስለው ምን እንዳስደነገጠው ክው አለ።
"እነማን ?" ሲል ሳቄን አፈንኩት። በቆረጣ ዲጉን አየው።
"እኔና አንተ!!! ኪዱ ነገ ፈተና ናት፣ዲጉ መውጣት አልፈለገም።" ያልኩትን እንዳልሰማ መሰለ።ሲሰርቅ እንደያዙት ህፃን ተቁለጨለጨ።
"እ?" አልኩት መስማቱን ለማረጋገጥ
"እ?" አለኝ መልሶ እንደባነነ ሰው።
"ነፃ በሆንክ ሰዓት ዘወር ዘወር አድርጋት።" አለው ዲጉ ማረጋገጫ ለመስጠት።የወንድሙ አኳኋን የእርሱን ሀሳብ ፍለጋ መሆኑ ገብቶታል።
"እሺ እንደጨረስኩ አመጣለሁ።" አለኝ።
እንዳለው ቀደም ብሎ መጣ።መክሰስ በልተን ወይን እየጠጣን ስንጫወት አመሸን።ወይኑን ለኔ ትቶልኝ ቢራ መጠጣት ቀጠለ። ያላነሳነው እና ያልጣልነው ርዕስ አልተገኘም። ብዙ ዘመን እንደሚተዋወቁ ጓደኛሞች ስለብዙ ነገር አወራን። ፍቅረኛውን ብቻ ያከለችበትን ዓለም ስፋት ላስረዳው ምከርኩ።በፍቅር ስሜት ተሟገተኝ። በተጨባጭ እውነት ተከራከርኩት።በቁም ነገራችን መሃል ከወይኑ ጋር ተደምሮ ውስጤ የሚንቀለቀል ልክፍቴን ለመግታት እታገላለሁ።
"አንቹ?" አለኝ።
"ምናባክ?"
"አሁን እንዴት ነው ያየሽኝ?"
"እንዴት አየሁህ?"
"እንደ ወንንድሜ ሚስት ባልሆነ አስተያየት።"
'ባንቺ እረፊ ለብልግናሽ ልጓም አበጂለት" አልኩት ራሴን፣ እሱን ግን
"ማታ የምትጠጣው ቢራ ጠዋት በጄሪካን ቢሰጡህ አታነሳውም።በል ተነስ እንሂድ!!" ብዬው ለመሄድ ተነሳን።
የሚቀጥለው ቀን የተሻለ ቀን ሆነ።
በሚቀጥሉት ቀናት ውስጥ ቤቱን ሳቅ እየሞላው ጨዋታ እየደመቀ መጣ።
በብዙ የሚደመጠው የኔ ሳቅና ወሬ ቢሆንም! ከቤን ጋር ወጥተን መፅሀፍት ገዛን።(ማታ ማታ የማነብላቸውን የግጥም በድብሎች ጭምር።)ከእታባ ጋር ቤተክርስቲያን፣ ከኪዱ ጋር አማርኛ ሲኒማ ሄደናል።(ሁለቱም ለራሴ ስል በፍፁም የማላደርጋቸው ናቸው።)ከቤን ጋር በተለይ ተግባባን።ሁለት ቀን ስልኩን ደብቄበት በሌላ ስልክ እንዳይደውልላት ቃል አስገብቼው ስለነበር ለፍቅረኛው ሳይደውልላት ዋለ።አድርጎት ስለማያውቅ ደጋግማ ስትደውል አላነሳሁላትም።እቤት ድረስ መጥታ ስልኩን ረስቶት መሄዱን ስነግራት እየተውረገረገች እና እያጉተመተመች ወጣች።ውብ ናት!! ቤን ሲሰማ በዲጉ ፊት መደነስ ቃጣው።ጉንጬን ስሞኝ "ቴንኪው"ብሎኝ ወደ ክፍሉ ገባ።
ከፍቅረኛው ውጪ በማንበብና ከቤተሰቡ ገር በመሆን መብሰልሰሉን ቀጥሏል።
"እቤት መምጣት እሷጋ ከመሄድ በላይ እንዲናፍቀኝ አደረግሽኝ" አለኝ የሆነ ቀን።
"እሰይ!! ታረቀችህ?" አሉ እታባ ቤኒ በጊዜ ወደቤቱ የገባ ቀን።
"ከራሴ ለመታረቅ የሞከርኩ ነው እማዬ !!" ብሏቸው ነበር።
በዚ ሁሉ ቀናትና ክስተቶች መሃከል በቀን ቢያንስ ሁለቴ እየደወለች አዲስ ነገር ካለ ለመስማት ለምትጠዘጥዘኝ ቹቹ ወሬ ማቀበል የየእለት ግዴታዬ ነው።
በአንዱ ቀን ማታ እቤት ውስጥ ወይንና ውስኪ ተገዝቶ እየተጎነጨን ስንጫወት አመሸን።በእርግጥ ዲጉ ከመጫወትና ከመጠጣት ይልቅ የኛን ልክ ሲቆጣጠር አመሸ ማለት ይቻላል።በልጅነት ስለሰራናቸው ጥፋቶችና እና ተንኮሎች እየተጫወትን ቤተሰቡ እየተበሻሸቀ ሳይታሰብ እኩለ ሌሊት ሆነ።ዲጉ

👍7❤1
ለመጫወቱም ለመሳቁም ሲሰስት አሰተዋልኩት።በእርግጥ እኔም ቢሆን ስለልጅነቴ የሚያስፈልገውን መርጬ አወራኋቸው እንጂ በብዙ ስርዝ ድልዝ የተማገረ ልጅነቴን አልነገርጓቸውም።
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ። 🙏
✨ይቀጥላል✨
ለአስተያየቶ @atronosebot ን ይጠቀሙ መልካም ቀን ። 🙏
#ኢትዮጵ!"
ቅድመ ካም ነገዱ፡ የኩሽ ፍሬ ክብሩ
ኢትኤል ታላቁ፡ የናምሩድ በኩሩ
ግራ ጎን አጋሩ፡ ዕንቆጳን ማግባቱ
ከምሥራቅ ሀገሩ፡ ከጊዮን ስሪቱ
"ዮጵ"ን ተሸልሞ፡ ንግሥናን ሰይሞ
ኢትዮጵን አነፃት፡ ጥበብ ተተልሞ።
የኢትኤል ወርቅ፡ "ዮጵ" አክሊል ቢሆንም
የደፋው አክሊል ግን...
የታሪክ ዕዳ ደም፡ ዘውድ ባለቀለም
ሰው ነው ሽልማቱ፡ ጥበብ ነበር ወርቁ
ፍቅር፣ እውነት ሀብቱ፡ "ኢትዮጵ" ናት ዕንቁ።
ቅጥሯን ያስከበረ፡ ዳር ድንበር ከልሎ
ኑቢያና ምስርን፡ ለራሱ ጠቅልሎ
አንገቷን ያቀናው፡ ለዓለም ሥልጣኔ
በጥበበ-ሄኖክ፡ ዓለምን ያነፀ፣ ዛሬን ያዘመነ
ያ’ዳም ቅድሜ ስሪት፡ መነሻ መድረሻው
የትውልዱ ምክነት፡ ታሪኩን ቢያስክደው
ኢትዮጵ ’ምትባል፡ ድብቅ ቅኔ ምስጢር
የት ገባች የጥንቷ፡ ኢትኤል ያ’ነፃት…
ያቺ ታላቅ ሀገር?
ደርቡሽን አባረው፡ ግብፅን ያዋረደ
እኔን ያስቀድመኝ፡ ብሎ የተዳፋ…
ማግዶ የታረደ
መቅደላ ጀግኖ፡ ባ’ድዋ የደገመው
ቃል ኪዳን ሰንደቋን፡ በነጭ ያላስነካው
ባ’ምላክ እጅ ሥራ፡ በጥበብ አሻራው…
ኢትዮጵን የሳለ
ያልመከነው ትውልድ፡ ኢትኤል የታለ?
አሁንማ!...
ሰልጥኖ መሴይጠን፡ እየተመዘዘ
በታሪክ ወለምታ፡ እየደነዘዘ
ጥበብ፣ ፍቅር፣ እውነት…እየደበዘዘ
ኢትኤል ባ’ነፃት…
በ"ኢትዮጵ" ምድር፡ ትውልዱ ቦዘዘ።
🔘 ዳዊት ፈቀደ 🔘
ቅድመ ካም ነገዱ፡ የኩሽ ፍሬ ክብሩ
ኢትኤል ታላቁ፡ የናምሩድ በኩሩ
ግራ ጎን አጋሩ፡ ዕንቆጳን ማግባቱ
ከምሥራቅ ሀገሩ፡ ከጊዮን ስሪቱ
"ዮጵ"ን ተሸልሞ፡ ንግሥናን ሰይሞ
ኢትዮጵን አነፃት፡ ጥበብ ተተልሞ።
የኢትኤል ወርቅ፡ "ዮጵ" አክሊል ቢሆንም
የደፋው አክሊል ግን...
የታሪክ ዕዳ ደም፡ ዘውድ ባለቀለም
ሰው ነው ሽልማቱ፡ ጥበብ ነበር ወርቁ
ፍቅር፣ እውነት ሀብቱ፡ "ኢትዮጵ" ናት ዕንቁ።
ቅጥሯን ያስከበረ፡ ዳር ድንበር ከልሎ
ኑቢያና ምስርን፡ ለራሱ ጠቅልሎ
አንገቷን ያቀናው፡ ለዓለም ሥልጣኔ
በጥበበ-ሄኖክ፡ ዓለምን ያነፀ፣ ዛሬን ያዘመነ
ያ’ዳም ቅድሜ ስሪት፡ መነሻ መድረሻው
የትውልዱ ምክነት፡ ታሪኩን ቢያስክደው
ኢትዮጵ ’ምትባል፡ ድብቅ ቅኔ ምስጢር
የት ገባች የጥንቷ፡ ኢትኤል ያ’ነፃት…
ያቺ ታላቅ ሀገር?
ደርቡሽን አባረው፡ ግብፅን ያዋረደ
እኔን ያስቀድመኝ፡ ብሎ የተዳፋ…
ማግዶ የታረደ
መቅደላ ጀግኖ፡ ባ’ድዋ የደገመው
ቃል ኪዳን ሰንደቋን፡ በነጭ ያላስነካው
ባ’ምላክ እጅ ሥራ፡ በጥበብ አሻራው…
ኢትዮጵን የሳለ
ያልመከነው ትውልድ፡ ኢትኤል የታለ?
አሁንማ!...
ሰልጥኖ መሴይጠን፡ እየተመዘዘ
በታሪክ ወለምታ፡ እየደነዘዘ
ጥበብ፣ ፍቅር፣ እውነት…እየደበዘዘ
ኢትኤል ባ’ነፃት…
በ"ኢትዮጵ" ምድር፡ ትውልዱ ቦዘዘ።
🔘 ዳዊት ፈቀደ 🔘
#ሮዛ_2
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_አንድ(🔞)
፡
፡
#ቺቺንያዊው_ፍቅሮቭስኪ
፡
፡
እግር ጥሎኝ ጆሲ ባር ገብቼ ስዝናና ሄለን ፒንክን አገኘኋት። ሄለን አሁንም ኩል ክለብ ውስጥ እንደምትሰራ ነገረችኝ። ማርቲ እዚሁ አዲሳባ መሆኗን እስክትነግረኝ ድረስ እንደሌሎቹ ጓደኞቻችን ዱባይ የገባች መስሎኝ ነበር። ከሄለን ጋር እየጠጣን የሆድ የሆዳችንን ተጫወትን። ሁለታችንም መጀመሪያ ስለተዋወቅንባት ቺቺንያ አንስተን ብዙ የጋራ ትዝታዎቻችንን አነሳን-ጣልን። ሄለን ፒንክ ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችን አሁንም እዚያው ቺቺንያ እንዳሉ ስትነግረኝ ዛሬውኑ ሄደን እንድንጠይቃቸው
በሞቅታ ሀሳብ አቀረብኩ። እውነትም ሞቅ ብሎኝ ነበር። ሄለን ፒንከ አላቅማማችም።
ከሌሊቱ 8፡00 ሰዓት ሲል ጆሲ ባርን ለቀን ጥቂት የድሮ ወዳጆቻችንን ለማግኘት ወደ ቺቺንያ አመራን።
እንዲሁ ሳንተኛ ሌሊቱ ይነጋታል እንጂ ሄለንን ብዙ ክለቦች ልወስዳት እዚያው ጆሲ ባር ውስጥ እያለን አስቀድሜ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር። ምን ጣጣ አለው?! ሲነጋ እኔ አፓርታማ ሙሉ ቀን ተጋድመን
እንውላለን ብዬ አሰብኩ። የዛሬን አያድርገውና ሄለን ፒንክ ባለውለታዬ ነበረች። ሁላችንም በራሳችን
የህይወት ሀዲድ ላይ ፋታ አጥተን ስንጣደፍ በተለያየ ወቅት መልካም የዋሉልንን እንረሳለን።
ሰአቱ ገና ስለነበር እዚያው ቺቺንያ ትልቁ ክለብ ዉስጥ ገብተን በዲጄ ሙዚቃ ወለሉ ላይ በዳንስ እየሾርን ስንጠጣ እስከ ሌሊቱ 9፡30 ቆየን። እንደ ጆሲ ባር ሁሉ እዚህም የከለቡን ለፍዳዳ ወንዶች
ለከፋ እና ጅንጀና እንዲሁም የአብረን እንዝናና ጥያቄ መቋቋም ነበረብን ወንዶች መለፋደድ ከጀመሩ ደግሞ ቶሎ አይፋቱም፡ እምቢ ሲባሉ ይብስባቸዋል። እንደዉሻ ከቂጣችን ስር መርመስመስ ጀመሩ።በዚህን ጊዜ ክለቡን ጥለንላቸው ከትልቁ የቺቺንያ ክለብ ወጥተን ወደ ትንሿ ቪቪያን Tብ አመራን።ከዋናው የቺቺንያ አስፋልት የተወሰኑ ሜትሮችን ገባ ብሎ ነው የሚገኘው፡ ገና እግራችን ከመግባቱ ብሌን በጩህት ተቀበለችን።
"ሮዛ!!! እኔ አላምንም፤ በአገሩ አለሽ? ማርቲ ነግራሻለች? ብዙ ጊዜ ያለሽበትን ሁኔታ እጠይቃት ነበር፤ ከሄሊ ጋር እንኳን አልፎ አልፎ እንገናኛለን፤ ሄሊ ፒንክ እንዳንቺ አልረሳትንም ፤ እየመጣች ትጠይቀናለች ወይ ሮዚና እንዳጠፋፍሽ ግን አላማረብሽም ጥፍጥፍ..."
ብሌን ከባንኮኒው ውስጥ ወጥታ በደስታ ተጠመጠመችብኝ፤ ለደቂቃዎች አለቀቀችኝም። ከብሌን ጋር በጣም ነበር የምንዋደደው። ብሌን አልተለወጠችም፤ ውበትዋ፣ ፍልቅልቅነቷ፣ ሸንቃጣነቷ፣
ተጫዋችነቷና ማራኪ ለዛዋ አሁንም እንዳለ ነው። በህይወቷ ውስጥ የቱንም ያህል ሀዘን፣ ስቃይና መከራ ሲደርስ ብሌን እንደ አይሁዶቹ ቀልድ ፈጥራ ትዝናናበታለች። ይሄ የብሌን ልዩ ተሰጥኦ ነው። ምንም ቢደርስባት ሁሌም ሳቂታ፣ ቀልደኛና ተጫዋች ስለሆነች ሀዘን ለቅጽበት እንኳን ነክቷት የሚያውቅ አይመስልም።
እኔና ሄለንን በአሪፉ ለማስተናገድ ሽር ጉድ ስታበዛ አስቆምናት፡ ብሌን አሁንም ድረስ ያልተወጋና ንጹህ ውስኪ ከሚሸጡ እጅግ ጥቂት ታማኝ የቺቺንያ የባርና የፐብ ባለቤቶች ቀዳሚዋ ነች።
ከብሌን ባሻገር ባንኮኒው አጠገብ አንገቱን ደፍቶ በፍጹም ተመስጦ ጠርሙስ ጎርደን ጂን ወደ ሚጠጣው
ጎልማሳ ማተረች። በቪቪያን ፐብ ውስጥ ከሱ ሌላ ሰው የለም። ጂኑ አልቆ የጠርሙሱ ቂጥ ላይ ሊደርስ
ትንሽ ይቀረዋል፤
“ፍቅሮቭስኪን ልሸኝና ፐቤን ዘግተን ቤቴ እወስዳችኋለሁ፣ አሪፍ ኮንዶሚንየም ገዝቼያለሁ ደሞ።ሄልዬን አሳይቻታለሁ፤ ሮዝ ግን ዛሬ ትመርቂልኛለሽ እሺ!”
ብሌን ጉንጩን በለስላሳ መዳፏ መታ አድርጋኝ ያን ደማቅ ፈገግታዋን ለገሰችኝ፤ ፈገግታዋ አለም ሁሉ በጨለማ ቢዋጥ ለመላው አለም ብርሃን የመለገስ ሃይልና ጉልበት አለው። አይ ብሌን! ሁሌም
ፍልቅልቅ ናት። ግራና ቀኝ ከጉንጮቿ መሀል የተሰደሩት ዲምፕሎቿ በምትስቅበት ወቅት ፈገግታዋን
አድምቀውት የልእልት ገጽታን ያላብሷታል። ከበፊት ጀምሮ ከምትሀታዊ ፈገግታዋ ጀርባ አንድ ከባድ ሀዘን ወይም የማይሽር የህይውት ቁሰል እንዳለ ባስብም ያን ደፍሬ ሳልጠይቃት ነበር ከበርካታ አመታት በፊት ቺቺንያን የለቀቅኩት። በጨዋታ በጨዋታ እድርጌም ቢሆን ከደማቅ ፈገግታዋ አድማስ ማዶ የተደበቀውን የህይወት ስንክሳር ባውቅ ደስተኛ ነኝ። ከአንዳንድ ዝነኛ ኮሜድያን ህይወት ጀርባ ስፍር ቁጥር የሌለው ሀዘንና መከራ እንዳለ ሁሉ፣ የብሌን ውብ ምትሀታዊ ፈገግታ ምናልባትም በህይወት የደረስነባትን አንዳች ከባድ ስብራት መሸፈኛ ጭምብል ሊሆን ይችላል። በፊት የማውቀው ባህሪዋ አሁንም እንዳለ ነው።
ሰብለን ከቀልድና ጨዋታዋ ሌላ ልብ አንጠልጣይ የትርጉም ልቦለድ መጻህፍት መለያዎቿ ነበሩ።መጽሐፍ በማንበብ ከጓደኞቼ ብቸኛዋ ሳትሆን አትቀርም። ነገር ግን ልብ አንጠልጣይ ካልሆነ
አታነብም። የሳንድራ ብራውንን፣ የጃኪ ኮሊንስን፣ የኤሪካ ዮንግን፣ የዳኔላ ስቲልን፣ የአጋታ ክሪስቲን፣የሲድኒ ሼልደንንና የኬን ፎሌትን ስራዎች እንደዉስኪ አንጠፍጥፋ ነው የምትጠጣቸው።
ብሌን ከመደርደሪያው ላይ ሙሉ ሬድ ሌብል አውርዳ ለኔና ለሄለን ከዚያም ለሷ በብርጭቆ ቀዳች።ብርጭቆዎቻችንን አጋጭተን እየጠጣን መጨዋወቱን ቀጠልን። ደሞ ለጨዋታ! ብሌን ጋ ቀልድ፣
ጨዋታና ሳቅ በሽ ነው።
ብሌን እንደገና ወደ ጎልማሳው ጠጪ ማተረች፤
“ሮዝ! አላወቅሽውም እንዴ?”
ጎልማሳውን ገና አሁን ነበር በሙሉ አይኔ የተመለከትኩት። ፊቱን እንደ ሃምሌ ደመና አጨፍግጎታል፣ዝምታው የመርግ ያህል ይከብዳል። በራሱ አለም ውስጥ ነው ያለው። ባዶ ሊሆን ጥቂት የቀረው
የጎርደን ጠርሙሱ ላይ አፍጥጧል። ከገባንበት ቅጽበት ጀምሮ እይታውን ከጠርሙሱ ላይ አላነሳም።
በዙሪያው ያለውን ትእይንት ከነመኖሩም እስኪረሳ ድረስ በራሱ የሀሳብና የትካዜ አለም ተሳፍሮ ሩቅ የነጎደ ይመስላል።
አውቅኩት፤ ብረት አስመጪው ፍቅረዝጊ ነው። ተክለሀይማኖት አካባቢ ትልቅ መጋዘን እንዳለው ይወራ ነበር። አመታቱ የቱንም ያህል ቢረዝሙ ድሮ የሚያውቁት ሰው መሰረታዊ ገጽታ አይጠፋም።
ካልሰከረ እሱም እንደሚያውቀኝ እርግጠኛ ነኝ።
"ፍቅረዝጊ ነው አይደል ብሌን?"
ብሌን እንደ ድሮ አስካካች
ሮዝ ሰፈራችንን ከለቀቅሽ ብዙ ጊዜ ስለሆነሽ የስሙን ለውጥ አላወቅሽም ማለት ነው፡፡ ፍቅረዝጊን
| 'ፍቅሮቭስኪ' ብለን የቺቺንያን የክብር ዜግነት ሰጥተነዋል እኮ። ላለፉት አስር አመታት ዊከ ኤንዶችን ከቺቺንያ ርቆ አያውቅም፤-በተለይ ከዚህ ከቪቪያን ፐብ። በርካታ የቺቺንያ ቆነጃጅት በተገኙበትና ድል ባለ ድግስ ነበር የቺቺንያ ዜግነቱን ያቀዳጀነው”
የማስካካቱና በሳቅ የመንከትከቱ ተራ የኔ ተራ ሆነ። እንዲህ እንዲህ እያለ ጨዋታችን ደራ። ድንገት ብሌን ያልጠበቀችውን ጥያቄ አስከተልኩ፤
“የኔ ውብ! ትዳር መሰረትሽ?”
ብሌን እንደገና በሳቅ ተንከተከተች፤
“አይ ሮዝ፤ አላወቅሽም እንዴ?! ትዳር ማለት እኮ ሾርት ወይም አዳር ገብቶ እንደመውጣት ሆኗል።ባለትዳሮቹ ራሱ ሚስታቸውን እያስተኙ እኛ ጋር አይደል እንዴ የሚያመሹት? ለአንድ ለስድስት ወር ያህል ሞክሬው ነበር-ባል ተብዬው አስካሉ የተባለች ሰራተኛዬን በገዛ አልጋዬ ላይ ሲያንከባልል እጅ ከፍንጅ ይዤው በቀይ ካርድ አሰናበትኩት…” ጣሪያው እስኪሰነጠቅ በራሷ ንግግር ሳቀች።
ሶስታችንም በሞቅታ ውስጥ ነን፤ ብሌንን በሳቅ አጀብናት። ሆኖም የፍቅሮቭስኪ ጎርናና ብሶተኛ ድምጽ ከሳቅና ከጨዋታችን መለሰን። ፍቅሮቭስኪ ከባድ ሀዘን ባረበበበት ጨፍጋጋ ፊቱ ሶስታችንንም በየተራ ገረመመን።ቡናማ ኮቱን በንዴት መሬት ላይ ወረወረው። ባንኮኒውን በግዙፍ ቡጢው በተደጋጋሚ
ነረተው። ጨርቁን ሊጥል ቅጽበት የቀረው

👍2
ወፈፌ ይመስል ነበር።በየተራ አፈጠጠብን፤
“እስቲ ንገሩኝ! እዚህ ሰፈር ውስጥ ምን አይነት ድግምት ነው የተደረገብኝ? ሺ ጊዜ ሰፈሩን በድጋሚ ላለመርገጥ ምዬ ብገዘትም አክለፍልፎ የሚያመጣኝ አዚም አለ። ምንድነው ያረጋቸሁብኝ? ምን
አይነት አፍዝ አደንግዝ ነው የነሰነሳችሁብኝ? ብሌን ምንም ሳትደብቂ ንገሪኝ የምትለማመኚው ቃል።
፣ ጠንቋይ ፣ ሼክ ወይም ቆሪጥ በኔ ላይ ምን እንድታደርጊ ነው ያዘዘሽ? ያው ባንቺ ቤት ስንት ዘመኔ ሌሎች የሰፈሩ ቡና ቤቶችና ፐቦች ጋ ቆይቼ አንቺ ቤት ነው ሁሌም የማሳርገው። ያንቺን ቤት ሳልሳለም ይህን ኩሻንኩሽ ሰፈር የተለየሁበት ጊዜ የለም። ይህን አንቺም አሳምረሽ ታውቂዋለሽ ስለዚህ የዚህ ሰፈር ሴቶች በኔ ላይ ምን እንዳደረጋችሁብን ሳትደብቂ ንገሪኝ ብሌን አንቺን ነው የማናግርሽ"
የሆነ ማይም ቲያትር የሚሰራ መሰለኝ። ፍቅሮቭስኪ አመልካች ጣቱን ብሌን ላይ ቀስሮ ረዘም ላለ ቅፅበት አፈጠጠባት።ብሌን አልፈራችውም ።እንዲህ እያማረረ ይህው ስንት አመቱ።ችላ ግን አላለችውም።ልታረጋጋው ሞከረች፣
“ምነው ፍቅሮቭስኪ….ምን ሆንክብኝ…ኧረ እኔ ካልካቸው ቦታዎች አንዱም ጋ ሄጄ አላውቅም፤ወላዲት አምላክን እኔ እንዲህ አይነት ልማድ የለኝም"
-ፍቅሮሽስኪ አሁንም እይኖቹን ከብሌን ላይ አልነቀለም፤
“ቀጣፊ ሸርሙጣ ነሽ፤ በመጀመሪያ አላመንኩትም እንጂ ሰናይ ሁሌም ቤትሸን ምሸት ላይ ልትከፍቺ ስትይ አዶ ከርቤ እንደምታጨሺና አውሊያሽን እንደምትለማመኚ ብዙ ጊዜ ነግሮኛል። እሱም በስንት ጸበል ነው ከዚህ ስፈር የተነቀለው።እምቢ አልኩት እንጂ ጻድቃኔ ማርያም አብሬው ጸበል እንድጠመቅ በተደጋጋሚ ወትውቶኝ ነበር።”
ፍቅሮቭስኪ እንደገና ባለጌው ወንበር ላይ ተቀምጦ ባንኮኒውን በቡጢው መድቃት ጀመረ፤ አይፎኑን በንዴት ወርውሮ ከአንዱ ግድግዳ ጋር አላተመው፤ ፊቱን በድጋሚ ወደኛ አዞረ። ደም ስሮቹ በቀይ ፊቱ ላይ ተገታትረው
በጉልህ ይታያሉ፤ይህን ጊዜ ሶስታችንም በድንጋጤ ደርቀን ቀረን።
"ወይዘሪት ብሌን! እያወቅሽ አትደብቂኝ፣ ይሄ ድግምታምና መተተኛ ሰፈር ምን አድርጎብኝ ነው ለዘመናት የሰፈሩ ቋሚ እስረኛ ያደረገኝ?! የቢዝነስ አጋሮቼ አርብና ቅዳሜን ሸራተን በጋዝላይት፣
በዱባይና በባንኮክ እየተዝናናን እንድናሳልፍ ለዘመናት በየሳምንቱ ሲወተውቱኝ አንድም ጊዜ እንኳን
ግብዣቸውን ሳልቀበል እዚህ ሰፈር ኩሽና በሚያካክሉ ቤቶች እንድልከሰከስ የሚያደርገኝ ድግምት ምንድን ነው? ብሌን ምንም ቢሆን የዘመናት ደምበኛሽ ነኝ፤ በፈጠረሽ ሚስጥሩን ንገሪኝ!”
ፍቅሮቭስኪ ከተቀመጠበት የባለጌ ወንበር ላይ ተነሳ፤ ሊረጋጋና ሊሰክን አልቻለም፤ ጥቂት የመቶ ብር
ኖቶችን ከቆጠረ በኋላ ባንኮኒው ላይ ወረወረ። ፊቱን ወደ ብሌን መለሰ፤
ብሌን ካንቺ ጋ እኮ ነው የማወራው ለምን እትመልሺልኝም? አልቀየምሽም እውነቱን ብቻ ንገሪኝ ይሄ ሰፈሩን ለመጨረሻ ጊዜ የምረግጥበት ሌሊት ነው። ከነገ ጀምሮ እንደ ሰናይ ለተወሰኑ ቀናት ጸበል
ለመግባት ቁርጥ ውሳኔ ወስኛለሁ። ስለዚህ አትፍሪ በግልጽ የምታውቂውን ንገሪኝ! ለምንድነው የዚህ ሰፈር ባርያና ምርኮኛ የሆንኩት? የትኛው ደብተራ ጋ ነው ያስደገማችሁብኝ? አርብ፣ ቅዳሜና
እሁድ ቤቴን፤ ሚስቴንና ልጆቼን እንድጠላና ከቤት ጥፋ ጥፋ የሚል ምን አይነት መስተባርር ነው ያረጋችሁብኝ? የትኛው ደብተራ ጋ ሄዳችሁስ ነው ለዘመናት ከዚህ ስፈር ጋ በፍቅር እንድወድቅ ያደረገ ማስተፋቅር ያሰራችሁብኝ? የቀራችሁ እኔን በድግምት ማሳበድ ብቻ ነው፡፡ ምኔ ሞኝ ነው!መስተአድርት አሰርታችሁ ሳታሳብዱኝ ነገ ጸበል እገባለሁ። መጥኔ ለናንተ! እኔስ በቃኝ…በቃኝ አልኩ።
ፍቅርቭስኪ ኮቱንና አይፎኑን ጥሎ ውጪ ወዳቆማት ቡናማ ፕራዶ መኪናው አመራ። ብሌን ኮቱንና ስልኩን ይዛ ወደ መኪናው ሄደች። ከአፍታ በኋላ ስጥታው ተመለሰች።
ብሴን በየተራ ተመልክታን ፈገግታውን ብልጭ አደረገች፤
“ፍቅሮቭስኪ በውሳኔው ከጸና ቺቺንያዊ የከብር ዜግነቱን በነገው እለት እንገፈዋለን።" በረዥሙ ሳቀች።
“በቃ ቤቱን ዘጋግተን ወደኔ ቤት እንሂድ። ጉዞ ወደ ብሌን ኮንዶሚኒየም ዳይ ዳይ….” በድጋሚ ሳቀች እኔ ግን ድንጋጤው አለቀቀኝም ነበር።
ሮዚ ደሞ፤ ፍቅሮቭስኪው ታውቂው የለ? ሁልጊዜም እንደዛተ ነው እኮ ሙዳችንን ሰለበው አይደል ይሄ ሰላቢ…ኑ ባካችሁ ቤት ሄደን የሆድ የሆዳችንን እንጫወት…"
ብሌን በራሷ ንግግር ፐቧ እስክትነቃነቅ በሳቅ አስካካች።ፍቅሮቭስኪ በተናገራት ነገር ዉስጥ ዉስጡን ተብከንከናለች ማለት ነው። የንዴት ሳቅ እንደሆነ ያስታውቅባት ነበር።
💫ይቀጥላል💫
Like 👍 እና #Share #Share ማድረግ እንዳይረሳ
#ለሮዚ_መልክታችሁን
#ለማስተላለፍ_ከፈለጋችሁ #ከታችያለውን_email #መጠቀም_ትችላላችሁ👇
rozachichinia@gmail.com
ለኛ ደሞ ማንኛዉንም አስተያየት በ @atronosebot አድርሱን

#ይገርማል_ባልቀና
ባልነት ካቆምኩህ በውስጤ ካመንኩኝ
ሌላ አትስጠኝ ብዬ ለአምላክ ከነገርኩኝ
ውስጤ ላይወላውል በገሃድ ካመንኩኝ
ታድያ በማን ልቅና? ባንተ ካልቀናሁኝ።
ባልነት ካቆምኩህ በውስጤ ካመንኩኝ
ሌላ አትስጠኝ ብዬ ለአምላክ ከነገርኩኝ
ውስጤ ላይወላውል በገሃድ ካመንኩኝ
ታድያ በማን ልቅና? ባንተ ካልቀናሁኝ።
❤1
#ቅዳሴና_ቀረርቶ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
#በሜሪ_ፈለቀ
፡
..በልጅነቴ እንደ ድንቡሽቡሽ ህፃን አቅፈው ጉንጬን የሚቆነጥጡኝ አልነበርኩም።
ንፍጥና ዝንብ የማያጣው የፊቴ ገፅታ፤ሁሌ በዝንብ የሚወረረው ትንሽዬ የቤታችን ቆሻሻማ ቀለም ያለው መመገብያ ጠረጴዛ አፍ፣ ጆሮ፣ አፍንጫና ዓይን ቢኖረው እኔን የሚመስል ይመስለኝ ነበር። እንደውም "ውይ መድሃኒያለም!! 'ሴት ልጅ ስጠን' ብለው ቢሳሉ ወንድ የመሰለች ሴት ልጅ ይስጣቸው?" ይሉ ነበር የሰፈር ሰዎች ሲያሽሟጥጡ።ሳድግ ፍፁም ተቀየርኩ። 'አዲስ አበባ ነው ያቆነጃት' ሲሉ እሰማቸዋለሁ አንዳንዶች። 'ወትሮም ንፍጣም ስለሆነች እንጂ ውበትስ አላነሳትም' ይላሉ ሌሎች። እንደ እውነቱ ግን የልጅነት ፎቶዬን ሳየው የአሁኗ ባንቺ ከየት እንደተፈለቀቀች ይገርመኛል።ከፀጉሬ እና በጥቂቱ ከአይኔ ውጪ አንዳች የሚቀራረብ ነገር የለኝም።
ግን የስለት ልጅ ነኝ።
በስንት እግዚኦታ የተገኘሁ። ሲመስለኝ አባቴ ለእናቴ 'እስኪ ዛሬ ደግሞ እንሞክር' እያለ ሰውነቷን ዘልቆ ሲዋሃዳት የሚሰጣትን የፍስሃ ስርቅርቅታዋን ትታ ታቦታትን ስትለማመን የተረገዝኩ ይመስለኛል።እንጂ እንደብዙዎቻችሁ በስሜት ግልቢያ፣ በላብና ወዝ አጀባ፣ በስግብግብ ትንፋሾች ልውውጥ መሃል በአጋጣሚ የጓጎልኩ አይደለሁም። 'እንደው ዛሬስ ተከስታ ይሆን?'እየተባልኩ በጉጉት ቀናት የተቆጠሩልኝ ነኝ እንጂ እረስተውኝ ሰንብተው የእናቴ ደም ሲቆም ደንግጣ፣አባቴ ሲሰማ በርግጎ፣ 'ትወለድ? ወይስ ተጨናገፍ?' ተመክሮብኝ፣ በ'ምን ይደረግ ወደዝህች ዓለም አልመጣሁም።
ግን ደግሞ ንፍጣም ነኝ......
የስለት ልጅ መሆኔ እንደሌሎቹ ወንድሞቼ እናቴ ለገበያ ለመሸጥ የምትጋግረውን ጥቁር የገብስ ዳቦ በየቀኑ ከዝንቦች ጋር ተጋርቼ ከመብላት ያስከነዳ እድል አልጨመረልኝም።ቢጫ ፍሬ ካለው የበደና ዛፍ ስር ፍሬውን እየለቀምኩ ስመጥ፣ዝንቦቹ ከአፌ ለሀጭና እጄ ላይ ከተራረፈው የፍሬው ጭማቂ ሲልሱ እውላለሁ።አንዳንዴ እቤቴ ስመገብ የሚቀራመቱኝ ዝንቦች ራሳቸው የትም ብሄድ እየተከተሉ የሚያባሉኝ ይመስለኛል። ብቻዬን እንዳልበላ ሲያባሉኝ። የትም የሚያጅቡኝ ወዳጆቼ መሆናቸው እንድለምዳየው አድርጎኝ ይሁን ከአፌ ጠርዝ ለሀጩንና የበደና ፍሬ ጭማቂ ሲልሱ 'እሽ' ሳልላቸው ይጠጣሉ።
ቢሆንም የስለት ልጅ ነኝ።
ታድያ ለምን ተለማምነው ወለዱኝ? እናቴ በየዓመቱ ቦሎ (ክላውዶ) ታሰራለች እያሉ ያሟታል።ሃሃሃ እንኳን መኪና በቅጡ የምትጫማው ኮንጎ ጫማ የላትም። በየአመቱ ከምንኖርበት ክፍለ ሀገር ደብረዘይት ድረስ እየሄደች ለቆሪጡ አታጓድልም ይሏታል።ለዛ ነው ዓመታዊ ሁለገብ ምርመራ እንደሚያደርግ መኪና ቦሎ ታሰራለች የሚሏት።
ባለውቃቢው መርቅኖ ይሆን እናቴ የወሰደችለት አረቄ አናቱ ላይ ፊጥ ብሎበት እንጃ ብልፅግናን የምታዘግናቸው፣ልዑል የሚንበረከክላት ቆንጆ፣ ከአፏ የጥበብ ወንዝ የሚፈልቅ ሴት ልጅ እንደሚወልዱ ነገራት።
ሲመስለኝ 'ሴት ትሁን ወንድ ገፅታዋ ያልለየ ልጅ ይኖርሻል፣ ስሟንም ታንዘላዝይዋለሽ፣ ለቤተሰቡ ችጋር ትደምራለች።' ለማለት ፈልጎ ይመስለኛል። ሳስበው የአባቴ ኩትኳቶ ድብቅ ኢላማው የሴት ልጅ ጉጉት ሳይሆን ከእናቴ መሃፀን ሀብት ቆፍሮ ማውጣት ነበር።ቢሆንም ቢሆንም የስለት ልጅ ነኝ።
አባትና እናቴ የተስፋውን ቃል ቢጠብቁ ቢጠብቁ ከመልክ ማስጠሎ፣ ከአንደበት ኮልታፋ ገመድ አፍ፣እንኳን የደለበ ብልፅግና ወደ ቤታቸው ላመጣለቸው ቀርቶ ያላቸውን ቀለብ የምቦጠቡጥ ነቀዝ እንደወለዱ ገባቸው። ከኛ ምግብነት ተርፎ እናቴ ገብያ የምትሸጠው የገብስ ዳቦ ገቢና አባታችን በሹፌርነት በሚያገኛት ደምወዝ የሚተዳደረው ቤታችን ችግር ይጫጫነው ጀመር። ታላላቆቼ እያከኩ እቤት የሚውሉ ፎከታሞች እንጂ የሚማሩም የሚሰሩም አልነበሩም።
ስምንት አመት ሲሆነኝ አዲስ አበባ የምትኖረው የእናቴ እህት እናኒ ልታሳድገኝ ወሰደችኝ።ከወላጆቼ ጋር ችጋር ከሚጠብሰኝ እናኒ ጋር መምጣቴ እድለኛነት ነበር።ደስታ እንጂ ቅሬታ አልነበረኝም። እናኒ መሀን ናት! ልጅ የላትም። አባቴ ከስጋ እህቶቹ አስበልጦ ነው እናኒን የሚወዳት። 'እንዴት አንድ ሴት ልጅህን ትሰጣለህ?' ሲሉት "እንኳን ለእናኒ ለአፈርስ ይሰጥ የለ እንዴ?" ይላል ውስጥ ውስጡን እኔን ማጣቱ ይሆን ድንገት ያ የተተነበየለት ብልፅግና በሱ ፋንታ የእናኒን ቤት እንዳያጠምቀው ስጋት ስቅዞት ቅር መሰኘቱን መደበቅ እያቃተው።
'እኛ ሰፈር' ካልኳችሁ አዲስ አበባ የምንኖርበትን የእናኒን ቤት ሰፈር ነው። ድሮ ድሮ በአፄው ዘመን የሁለት ወንድማማቾች ቤት ነበር። በደርግ ዘመን መንጌ በህይወት ላሉ የወነድማማቾች ቤተሰቦች መኖርያ የሚሆን ያልተንዛዛ ማረፍያ ሰጥቷቸው የተቀሩትን ቤቶች ወረሰባቸው።ለተለያዩ መኖርያ አልባ አስራ ሶስት አባራዎች ሸንሽኖ ሰጣቸው።የቀበሌ ቤት ተባለ። ሰፈራችን ከወድያ ጥግ የእናኒ ባል ዘመዶች ቤት በብዙ የቀበሌ ቤት ተከቦ ሲያናፋ በወዲህ ጥግ የእናኒ ቤት በሌሎች የቀበሌ ቤቶች አጀብ ተጀንኖ ነግሷል።
እኛ ሰፈር አጥር የለም። ድንበር ብሎ ፈሊጥ አይሰራም። በራሳቸው ቤት እና በተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚኖሩት የእናኒ ባል ዘመዶችም ሆነ እናኒ ሳይቀር ድንበራቸው በቀበሌ ቤት ከሚኖሩት ጋር ተቀላቅሏል። የ 'እኔ' ነው የሚባሉ ንብረቶች እንደየቤቱ ቢለያዩም አይበዙም ግለኝነት የሚያጠቃት ሙሉ እንኳን እየአፈሏት ከምትተኛላቸው ወንዶች ጋር እንጀራዋን ከምትጋግርበት አልጋዋና ለገመድነት ከቀረቡ ፓንቶቿ በቀር እንዳንነካባት የምትከለክለን ነገር የለም።
እናኒ የሰራችልኝን ፓስታ ቁርስ በልቼ፣ አልማዝ የምትሰጠኝን አንባሻ ለትምህርት ቤት በብብቴ ሸጉጬ፣ የአለሚቱን ጆሮ ጌጥ ሰርቄ በእረፍት ሰዓት ጆሮዬ ላይ ለጥፌ ያን ነጫጭባ ማቲ ሁላ አስቀንቼ፣ የቀናኝ ቀን ከእትዬ ሰርካለም ቤት ረከቦት ላይ ስኳር ሰርቄ በባለማንገቻው ጅንስ ሱሪዬ የደረት ኪስ አስቀምጥና የእናኒን ቀሰም እንደ ስትሮው በመጠቀም ከደረት ኪሴ ስኳር እየሳብኩ ስቅም ትን ብሎኝ ተይዤ ፣ ከትምህርት ስመለስ እናኒ በር ዘግታ ቡና ልትጠጣ ሄዳ ከሆነ የበሩ ደረጃ ላይ ስጠብቃት እንቅልፍ ይዞኝ እብስ ሲል አንዳቸው ተሸክመው እቤታቸው አስገብተው አስተኝተውኝ፣የሚሰራልኝን ከሰፈሩ ህፃናት የተለየ ምግብ እናኒ ሳታየኝ ደብቄ ለእኩዮቼ አጉርሼ፣የሁሉም ልጅ ሆኜ ሁሉም ቤተሰቦቼ ሆነው በደቦ አደግኩ። እድገት ነው ብለው ባሳዩኝ መስመር ተምወገዘግኩ።
እትዬ ሰርካለም ቤት ለሰረቅኩት ስኳር አስናቀች ቤት ተመዝልጌ፣ የእናኒን ብርጭቆ ለሰበርኩት ትልቋ ፀሃይ ቤት ጭኔ ተፈትሎ፣ ከጎረቤት ልጅ ለተጣላሁት ስሞታ ለመምህሬ ተነግሮ መምህሬ ከትምህርት በፊት በጭነረ እጃቸውን አፍታተው፤ ጭኔን በቁንጥጫ ሲቀራመቱት ነው ያደኩት።
ለጋሽ አበባ (ትልቅ ከሆንኩ በኋላም ስማቸውን አላውቀውም)ከፈትለ ቤት በጠርሙስ አረቄ እንድገዛ ተልኬ ስመለስ አንድ ጉንጭ አረቄ መዋጥ ሱስ ሆኖብኝ ስትንቀለቀዪ አጉድለሽ አመጣሽ ብለው ሲነጫነጩብኝ ፣ ሙሉ በማስታጠብያ ያጠራቀመችውን የእንትኗን እጣቢ እና ከእጣቢው ላይ የተንሳፈፈ ኮንደም ጓሮ እንድደፋላት ልካኝ ኮንደሙን በእንጨት ከውሃው አውጥቼ በምንነቱ ስገረም፣ ለደራረሱ ልጃገረዶችና ጎረምሶች ደብዳቤ አመላላሽ ሆኜ ስላክ በየመንገዱ የተፃፃፉትን የፍቅር መሸፋፈድ ሳነብ፣ የበለጡ ልጅ የካራቴ ፊልም አምጪልኝ ብሎ ሲልከኝ ያመጣሁለትን ፊልም እቤት በለጡ ሳትኖር ጠብቆ በር ዘጋግቶ ሲያይ እኔ ብቻ በማውቀት የኋላው መስኮት ማጮለቂያ እያጮለኩ የማየው የራቁት ካራቴ ትንግርት ፊልሙን ለእርሱ ብዬ ሳይሆን ለራሴው እንደማመጣው ሁሉ ሲያስፈነጥዘኝ ያልላከኝ

👍1
ቀን ስበሳጭ ፣ በራሴ ስህተት ብቻ ሳይሆን በሰፈሬ ስህተት እየተላተምኩ አደግኩ።
እንደ እገሌ እየተባለ ለምሳሌነት በሚጠቀሱ በትምህርታቸው በጎበዙ ልጆቻቸው እንቁልልጭ እየተባልኩ በገፉኝ ግፊት ትምህርቴን ሳጠብቅ አጎብዘውኝ አደግኩ። በጥሩ ውጤት ስሸለም በመሳም ጉንጬን ሲያቀሉት በአድናቆታቸው ክምር አጀግነውኝ ተመነደገግኩ።
"ሰማሽ?" ይላሉ እትዬ ጠጄ ለሹክሹክታ በማይመቸው መንደራችን ያልሰማም አይኖርም። የመለሰም አይኖርም።
"አንቺኔ አይደል እንዴ?" ይደግማሉ
"እኔን ነው እንዴ? ስም ስላልጠራሽ እኔን አልመሰለኝም።"
"ኡቴ አንቺ መባሉ ባይሻልሽ? ደሞ ደህና ስም እንደያዘ ሰው?" (አልጋነሽን ነው)
"አይ እንግዲህ ጠጄ! በርሽን ከፍተሽ ብቅ ስትይ ለዓይንሽ ማረፍያ ግስጥ ብዬ ታገኚኛለሽ የነገር አምሮትሽ መወጣጫ ሆንሻለው።አልጋ ይማረራሉ
(እትዬ ጠጄ በቀን አንድ ሰው ካላስከፉ ይደብራቸዋል።ወገቧን ሰብቃ የምትመላለሳቸው ባልቴት ካገኙ እሰየው አንጀታቸው ይርሳል።የቤቷን መቀርቀርያ አንስታ ለፀብ የምትጋበዘዋ ካጋጠመቻቸው እልል በቅምጤ!! ለሁለት ቀን ይወጣላቸዋል።)

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እመኝኝ_ኢትዬጵያዬ
እንደ ነ ቴወድሮስ ራሴን ለሽጉጥ ባላቀርብልሽም
እንደ አሉላ በጦር ባላስደስትሽም
እንደ ነ ዮሐንስ አንገቴን ለስለት ባላደርግልሽም
እንደ ነ ጃጋማ የበረሀ መብረቅ ባልባልልሽም
እንደ ሊቀ መኳስ አነጣጥሮ ተኳሽ ባልባልልሽም
እንደ ነ ሊጋባው ጠጅ አልጠጣም ብየ ውሀ ባልልሽም
እንደ ጀግናው በላይ በሶማ በረሀ ባልጓዝልሽም
እንደ አብርሐም ሞገስ የጠላት መግደያ ቦንብ ባልሖንሽም
እንደ አቡነ ጴጥርስ ደ
ያ ኡመር ሰመተር ቆራጥ ባልሆንሽም
እንደ ሸዋረገድ ብልሗ ጣይቱ ብልሕ ባልሖንሽም
ጉንደት ና ጉራ ካራማራ አደዋ ዘማች ባልሖንሽም
ከታሪክ ጥፋትን ቆፋሪ ብሖንም
ሳላውቅሽ አውቄ ስምሽን ባጠፋውም
ምስጢር ሆነሽብኝ ምስጢርሽን ባላውቅም
ሥለአንች ለመፃፍ ብዕሬ ባይደፍርም
ጀግንነት ለማድረግ መንፈሴ ቢዝልም
ለእድገትሽ ሕይወቴን መስጠት ቢያቅተኝም
እመኝኝ ሐገሬ በደሜ ውስጥ አለሽ
ይህን አልክድሽም፡፡💚💛❤️
እንደ ነ ቴወድሮስ ራሴን ለሽጉጥ ባላቀርብልሽም
እንደ አሉላ በጦር ባላስደስትሽም
እንደ ነ ዮሐንስ አንገቴን ለስለት ባላደርግልሽም
እንደ ነ ጃጋማ የበረሀ መብረቅ ባልባልልሽም
እንደ ሊቀ መኳስ አነጣጥሮ ተኳሽ ባልባልልሽም
እንደ ነ ሊጋባው ጠጅ አልጠጣም ብየ ውሀ ባልልሽም
እንደ ጀግናው በላይ በሶማ በረሀ ባልጓዝልሽም
እንደ አብርሐም ሞገስ የጠላት መግደያ ቦንብ ባልሖንሽም
እንደ አቡነ ጴጥርስ ደ
ያ ኡመር ሰመተር ቆራጥ ባልሆንሽም
እንደ ሸዋረገድ ብልሗ ጣይቱ ብልሕ ባልሖንሽም
ጉንደት ና ጉራ ካራማራ አደዋ ዘማች ባልሖንሽም
ከታሪክ ጥፋትን ቆፋሪ ብሖንም
ሳላውቅሽ አውቄ ስምሽን ባጠፋውም
ምስጢር ሆነሽብኝ ምስጢርሽን ባላውቅም
ሥለአንች ለመፃፍ ብዕሬ ባይደፍርም
ጀግንነት ለማድረግ መንፈሴ ቢዝልም
ለእድገትሽ ሕይወቴን መስጠት ቢያቅተኝም
እመኝኝ ሐገሬ በደሜ ውስጥ አለሽ
ይህን አልክድሽም፡፡💚💛❤️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ሮዛ_2
፡
፡
#ክፍል_ሀያ_ሁለት(🔞)
፡
፡
#ቪላ_ኖቫ
ወይንሸት ወሬ ስታወራ አፍ ታስከፍታለች። ያየሁትን ፊልም ስትተርክልኝ ምንም ሳልሰለች እንደ አዲስ እሰማታለሁ። ግርም ነው የምትለኝ። አዳምቃ ስታወራ ትንሽ ታጋንናለች እንጂ ነፍስ ናት። ማንኛውንም ወሬ ስታወራ ልክ አሁን እንደሆነ፣ ወይም ትናንት እንደተከሰተ አድርጋ ነው። ስለ ቪላ ኖቫ ህይወቷ
አንድ ከሰአት ሙሉ ሺሻ ቤት ቁጭ አድርጋ የተረከችልኝን ነገር መቼም አልረሳውም። ያንኑ ቀን ምሽት
ነበር እንደወረደ ማስታወሻዬ ላይ ያሰፈርኩት። ወይኒና ቪላ ኖቫ።
ወይኒና ቪላ ኖቫ
"ሮዛ! "ታምኛለሽ? የኮሌጅ ትምህርቴን ካቋረጥኩ 6 አመት አለፈ። ተማሪዎች በተመረቁ ቁጥር እደነግጣለሁ፤ እንኳን ደስ አላችሁ» የሚለው መዝሙር ይረብሸኛል። ይሄኔ እኮ አሪፍ ስራ ይዤ
ጨዋ የቢሮ ሰራተኛ እሆን ነበር። ቢዝነስ ከጀመርኩ 5 አመታት ተቆጠሩ ማለት ነው አይደል? ወይኔ ጉዴ ጊዜው እንዴት እንደሚሮጥ.…!
ሽርሙጥናን በድብቅ ያስጀመሩኝ ጓደኞቼ አብዛኞቹ የሉም። ሀበሻ ደንበኞቻቸውን በአረብ እና በነጭ ተከተው ሁሉም ዱባይ ከትመዋል። እኔ ግን የዚህች አገር ቋሚ ንቅሳት ሆኛለሁ። ጓደኞቼ ይሄኔ
ከሰማይ ጠቀሶቹ የዱባይ ሆቴሎች፣ ክለቦችና የስርቆሽ ቪላዎች ዉስጥ ቢዝነሳቸውን አጡፈውታል።
ኪኪ፣ ሜሪና ኤልሲ በየሳምንቱ በፌስቡከ ላይ የሚለጥፏቸውን ፎቶዎችን አያለሁ። አምሮባቸዋል፤ወፍረውና ቢጫ ሆነው እነሱ ራሱ አረብ መስለዋል። ያን የአረብ መንዲ፣ ኩብዝና ፈጠራ በየእለቱ
እስኪሰለቻቸው እያግበሰበሱ እንዴት አይስማማቸው?
ሮዚ ሙች ቤተሰቦቼ አሁን የምሰራውን ስራ ቢያውቁ ምን ይውጣቸዋል?›› ብዬ ሳስብ ዛፍ ላይ ታናቂ ታንቂ ይለኛል አምስት አመት ሙሉ ስዋሻቸው ኖሬያለሁ እኔ የነገርኳቸውን አምነው በአንድ
የውጭ ድርጅት ወስጥ በደህና ደሞዝ ተቀጥሬ እየሰራሁ እንደሆነ ነው የሚያውቁት። በእርግጥ በአካል
እስካላገኙኝና እጅ ከፍንጅ እስኪይዙኝ ድረስ አይጠረጥሩም፡፡ በየጊዜው የምልከላቸው ገንዘብ ያን
እንዲጠረጥሩ ሊያደርግም፡፡ አራት ታናሽ ወንድሞቼን ያሻቸውን እያለበሰኩ እንቀባርሬ የማስተምረው እኔ ነኝ፡፡ ሁለቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሆነዋል፡፡ በህይወቴ የሚያረካኝ ምንም ነገር ባይኖርም ዩኒቨርስቲ የገቡትን ታናናሾቼን ሳስብ ግን እጽናናለሁ፡፡ የመጀመሪያ ታናሼ ሲቪል ምህንድስና የሱ ታናሽ ደግሞ የህክምና ትምህርትን ያጠናሉ። ኮንትራክተርና ዶክተር ሊሆኑ እንደሚችሉ ሳስብ በደስታ እምባዬ ይመጣል። ገላዬን ሸጬ እንደማስተራቸው ቢያውቁ ምን ይሰማቸው ይሆን ? ብዬ ሳስብ ግን
እበረግጋለሁ። ስሜቴ ይረበሻል፣ ሞራሌ ይሰበራል፣ እንቅልፍ አጥቼ ስብሰለሰል አድራለሁ።
ስለ ቪላ ኖቫ ገፅታ
ሮዚ! ቪላ ኖቫን አታውቂውም አይደል? እድለኛ አይደለሽም። ቪላ ኖቫ ሳትሰሪ አዲስአበባን አውቃታለሁ እንዳትይ ደሞ። ቪላ ኖቫ ሁሉን አይነት አገልግሎት የሚሰጥ ሳርቤት ገብሬል የሚገኝ
ቪላ ነው። በቪላ ኖቫ ውስጥ ደምበኛ ፈልጎ የሚያጣው አንድም አገልግሎት አይኖርም። ቪላ ኖቫን ሚሊዮን ብር አየርባየር የሚያንቀሳቅሱ፣ ሳይታሰብ ባንድ ጊዜ በአቋራጭ ሞጃ የሆኑ “ስፓይደርማን ሃብታሞች"ያዘወትሩታል። ሺህ ብሮች እንደ ሳንቲምና እንደ ጉርሻ የሚታዩበት ሰፊ ቅጥር ነው፤ ቪላ ኖቫ።
በዉስጡ የከፍተኛ መደብ መቃሚያና ሺሻ ቤት አለው። መስቀል ፍላወር ጋዜቦ አካባቢ ካለው ጫት መሸጫ ውጭ የትም አይቼው የማላውቀው እስሩ 1200 ብር የሚሸጥ ጫት በቪላ ኖቫ ውስጥ ይገኛል። ጫቱ እስካሁን እንደነ ኮሎምቢያ፣ ቆቦ ፣ በለጬ፣ ገለምሶ፣ አወዳይ፣ ቁርጮ፣ አቡ ምስማር
ወንዶ፣ ባህርዳርና ጉራጌ ጫቶች መደበኛ መጠሪያ ስም አላገኘም። የምርቃና ከፍታው ለየት ያለ ስለሆነ እንፈራዋለን፣ ደፍረን ቅመነው አናውቅም። እንኳን ይህን ከሄሮይንና ኮኬይን የማይተናነስ ከባድ ስም የለሽ ዕጽ ቀርቶ ሊና ጓደኛዬ አንዴ ዋናውን የኮሎምቢያ ጫት ቅማ በምርቃና የሰራችውን በአይኔ
በብረቱ ስለታዘብኩ ኮሎምቢያ እንኳን ቅሜ አላውቅም፡፡ ሊና ሙሉ ከሰአቱን እሱን ጫት ቅማ አይደል እንዴ ማታውን "ይሄ ቤት በፕላን አልተሰራም” ብላ የቤቷን ግድግዳ ለማፍረስ ስትታገል ያደረቸው!(ተያይዘን ሳቅን)
በያንዳንዱ የቪላ ኖቫ የመቃሚያ ክፍል ውስጥ በአለም ዙሪያ የሚገኙ ውድ የአልኮል መጠጦችን የያዘ ፍሪጅ አለ። ሁሉም ክፍሎች ሙቅና ቀዝቃዛ ሻወር፣ ንጹህ የመቃሚያ ልብሶች፣ ሙሉ24 ሰአት ከመላው አለም የሚገኙ የዲሽ ፕሮግራሞችን የሚያስኮመኩሙ ባለ 41-ኢንች ፍላት ስክሪን ቴሌቪዥኖች፣ ውድ የአረቢያን መጅሊሶች፣ ሺሻ ማጨሺያዎች አሏቸው። የቪላ ኖቫ ደምበኛ ለአንድ ቡሪ ሺሻ 300 ብር
ይከፍላል፡፡ ሁሉም የቪላ ኖቫ ክፍሎች ለመንፈስ የደስታ ስሜትን በሚለግሱ ውብ የፋርስ ምንጣፎች ደምቀዋል። የቪላ ኖቫ ደመበኛ ቺቺንያ ውስጥ እንደሚገኙ ቪላዎች ከሳሎኑ የሚለቀቀውን ሙዚቃ በየከፍላቸው በሚገኘው ማስተጋቢያ በግድ እንዲያደምጡ አይደረጉም። በየክፍላቸው ውስጥ ጂ-ፓስ
ስላለ ፍላሽ ሜሞሪያቸውን ሰከተው የመረጡትን ሙዚቃ መኮምኮም ይችላሉ። በየከፍሉ ውስጥ
ደምበኞች ምንም ነገር ሲፈልጉ ወደ ሪሴፕሽን ደውለው የሚያዙበት ፊክስድ ላይን ስልክ አለ። በስልኩ ደረት ላይ ባለሶስት ዲጂት የሪሴፕሽን ስልክ በጉልህ ጥቁር ቀለም ተጽፏል።
የቪላው ምድር ቤት ስፊና ማራኪ ባር አለው። በባሩ ወስጥ ቆነጃጅቱ አለን። የቪላ ኖቫ ደምበኛ ምርቃና ወይም የአልኮል ሞቅታ ላይ ሆኖ ሴት ቢያሰኘው ወደ ሪሴፕሽኗ ስልክ መምታት ብቻ ነው
የሚጠበቅበት። ደመበኛው ኪሱን ይጭነቀው እንጂ ከሶስት እስከ ግማሽ ደርዘን ሴቶች ወደ ክፍሉ ቢያዝም ይችላል። ደምበኛውን የሚያነሆልለው የሚካኤላ ውብ ድምጽ ይቀበለዋል፤ “Your wish is our command. The girls will be in your room in just a few moments. Thank you for calling!"
አማርኛዋ ራሱ ቅንጦት የተጫነው እንግሊዝኛ ነው የሚመስለው፤ ሚካኤላ ጎላ ጎላ ያሉ አይኖች ያሏትና
የሞዴል ተከለ-ቁመና ያላት ሴት ናት፤ ያለ ቱፒስ እትለብስም፤ የእግሯን ውብት አሳምራ ስለምታውቀው እጅግ አጭር ቀሚሶችን ነው የምታዘወትረው። ሚካኤል ከብራንድምርቶች ጋር ክፉኛ በፍቅር የወደቀች ሴት ናት። የምትቀያይራቸው መነጽሮች፣ የጸጉር ቅባቶችዋ፣ የቆዳ ቅባቶችዋ፣ ሽቶዎችዋ ፣ሸሚዞችዋ፣ ሙሉ ልብሶቿ፣ ጫማዎቿ፣ ሴክሲ ስልኮቿ...ሁሉም ዝነኛ ብራንድ ናቸው። ዶልቼ ጋባና ነፍሷ ነው።
“ሮዚ አይሆንም” እና “የለም” የሚሉት ቃላት በቪላ ኖቫ መዝገበ በቃላት ውስጥ ጭራሽ እንዳይኖሩ የተቻላትን ሁሉ አድርጋለች። ብርቱ የብቸኝነት ስሜት የሚሰማቸው ደምበኞች ብዙ ሴቶችን አዘው ክፍላቸውን ሲያደምቁ ብዙ ጊዜ ታዝቤያለሁ ድንገት የደምበኞቹ የሴት ፍላጎት በዝቶ የቪላው ሴቶች ቢያንሱ እንኳን ተደውሎላቸው በግል መኪናቸውና በኮንትራት ታክሲ ከተፍ የሚሉ በርካታ ለአይን የሚያሳሱ የኮሌጅ ሴቶች አሉ። Escort service ነው የሚባለው።ሚካኤል ናት የነገረችኝ ውጭ ሃገር የተለመደ ነው ብላኛለች።በኛ አገር እሷ ናት የጀመረችው
ቪላ ኖቫ ማሳጅ ደረጃውን ጠብቆ ይሰጣል። ወደ ክፍሉ ከመግባቱ በፊት ወይም ከገባ በኋላ ሰውነቱን በመታሸት ዘና ለማለት የሚፈልግ ደምበኛ አንደኛ ፎቅ ላይ ባሉት ቄንጠኛ ክፍሎች ገብቶ በቆነጃጅት ከስዊዲሽ እስከ አሮማ ማሳጅ ያሉትን አገልግሎቶች አንድ ላይ ይሰጣሉ
የቪላ ኖቫ አንደርግራውድ ቁማር ቤት ነው ትንሹ የቁማር መደብ 5000 ብር ነው። ቁማርተኞቹ ሽጉጥ ከታጠቁ ወደ ሰፊው ቁማር ቤት ከመግባታቸው በፊት በራፍ ላይ ቀልሀዎቹን

በሙሉ አውጥተው
በር ላይ ለሚቆው ግዙፍ ጋርዶች መስጠት አለባቸው ውስጥ ቁማር እየተጫወቱ ብዙ እንደሚቆዩ
ስለሚታሰብ ለዛ የተለየ ልብስ ተዘጋጅቶላቸዋል። በቪላ ኖቫ አንድ ምስኪን ደሞዝተኛ በአስር አመት
የማያገኘውን መቶ ሀምሳ ሺህ እና ሁለት መቶ ሺህ ብር በአንድ ሌሊት በጥቂት ሰአታት ቁማር መብላትና መበላት ብርቅ አይደለም።ከዋናው መንገድ በርካታ መቶ ሜትሮችን ወደ ውስጥ ገባ ብሎ
የሚገኝ ስዋራ የስርቆሽ ቪላ ስለሆነ ባለሀብቶች ይመርጡታል። ደግሞ አራት የስርቆሽ በሮች አሉት.ምናልባት ሰው በብዛት ሲወጣና ሲገባ ጥርጣሬ እንዳይፈጠር ተብሎ ነው የተዘጋጁት።
እዚህ ቪላ ውስጥ እኔ ቀን ቀን ብቻ ነበር የምሰራው። እንደ በፊቱ ሌሊት ከሰካራም ጋር መባዘን የለም።ጎልማሶቹና አዛውንቶቹ ከሚስታቸው ተደብቀው ከሚስት ያጡትን ወሲባዊ ደስታ ለማጣጣም ነው ይህን ቪላ የሚመርጡት። አብዛኞቹ ሲበዛ ደግ እና ለጋስ ናቸው።ገንዘብ ላይ አይከራከሩም።
ጥዋት ረፋድ ላይ 4፡00 ሰአት ሲል እገባና አመሻሽ ላይ ጀምበር ልትጠልቅ ስትል እስከ 12፡00 ሰአት በቪላው እየሰራሁ እቆያለሁ። በቪላው ውስጥ የኔን አይነት የመስተንግዶ አገልግሎት የሚሰጡ 16
ሴቶች አሉ። ከታዳጊ ህጻናት ጀምሮ የበርካታ አመታት የሸርሙጥና ልምድ ያላቸው አሮጊት ሴቶች በዚህ ቪላ ውስጥ ይገኛሉ። ልጆቹ ከአውሮፓና ከአሜሪካ በሚልኩት ገንዘብ ከሚጦሩት አዛውንት
ጀምረሸ ዱባይና ቻይና እስከሚመላለስ ወጣት አስመጪና ላኪዎች ድረስ በርካታ ቋሚ ደምበኞቸን በዚህ ቪላ ቆይታዬ አፍርቼያለሁ። አብዛኞቹ ደምበኞቼ ከዋናው ባለ ፎቅቪላ በስተጀርባ ባሉት በርካታ ሰርቪስ የመኝታ ክፍሎች ውስጥ
ጊዜያዊ ስሜታቸውን አርክተው ወደ ጉዳያቸው የሚሄዱ ናቸው።እዚህ ቪላ ውስጥ የቢዝነስ ድርቅ ገጥሞኝ አያውቅም።ሆኖም ሁሉም ስሜታቸውን እስክታረኪላቸው ነው የሚንከባከቡሽ ከዚ በኋላ ትዝ አትያቸውም።
ቤተሰብ እንደምደግፍ ነግሬሻለው በዚያ ላይ አንድ ጎረምሳ boyfriend አለኝ። ስሞኦን ይባላል።እድሜው ከኔ ያንሳል" ብዙ ገዘቤን የማጣፈው በሱ ላይ ነበር። ለልብሶቹ እና ለሱሶቹ እንኳ ያን ያህል አላወጣም ምኑን እንደዘደድኩት አላቅም አንድ ቀን ሳላገኘው ከቆየሁ ላብድ
እደርሳለሁ፥ እንደ ወፈፌ ያደርገኛል፡ አለም ይገለበጥብኛል።
ከልጁ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዋወቅነው ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ነበር፡፡ እኔ ሁልጊዜም በላዳ ነበር
የምንቀሳቀሰው። ያን ቀን የላዳ ደምበኛዬ ቀርቶብኝ እርሜን በሚኒባስ ብሄድ ፈጣሪ ከስሞኔ ጋር አገናኘን። መጀመሪያ የሰነዘረው አረፍተ ነገር መቼም አይረሳኝ።
“ቆንጆ! ውበትሽን ቀንሼው በውበት ብዛት የሚታመም ሰው አለ" ኮስተር ብሎና serious ሆኖ ነበር
ይህን የተናገረው፡፡ ይህ ሁኔታው ብቻ በሳቅ እንከተከተኝ፡፡ serious ሆኖ ሲትን የለከፈ የመጀመሪያው ወንድ እሱ ሳይሆን አይቀርም። በዚያን እለት የታክሲ.ጉዟችን ሳቅ በሳቅ ካረገኝ በኋላ ስልከ ተለዋወጥን። ይኸው አሁን 8 ወር ሆኖናል፡፡ ሸሌ እንደሆንኩ ነገርኩት፡፡ እንደመጀመሪያው እለት series ሆኖ
“ወይኔ ትምህርቴን ጨርሼ ስራ ስይዝ ከዚህ ስራ አወጣሻለሁ" ይለኛል። በልቤ "ቂላቂል! ስራፈት” እለዋለሁ፡፡ ግን ደግሞ ያሳዝነኛል፡ ሮዚ መች የውነቱን እኮ ነው እንደዚያ የሚለኝ። ተጫዋችነቱ፣ ቀና
አሳቢነቱና የዋህነቱ ነፍሴን ይገዛታል፡፡
የቪላ ኖቫ አዛወ'ነቱ ደምበኛዬ
ነግሬሻለሁ ስለኚህ ሰወዬ? አልነገርሽኝም እንዳትይኝ ብቻ! ሮዚ ሙች ነግሬሻለሁ፤ አውቀሽ ልታስለፈልፊኝ ነው አይደል? ለማንኛውም ደግሜ ልንገርሽ
በዚህ ቪላ በየሳምንቱ የሚጎበኙኝ አንድ አዛውንት ደምበኛ ነበሩኝ። ከኚህ አዛውንት ጋ ቆይታ ባረግኩ ቁጥር አስተሳሰባቸው ያስገርመኛል። አዛውንቱ እድሜያቸው ከ65 ቢዘልም “ገና እኮ ነኝ፤ ‹አንተ እያልሽ ጥሪኝ ይሉኛል።
አዛውንቱ ኮካ ያዛሉ። እኔ ስፕራይት እዛለሁ። ጨዋታ ይጀምራሎ፡ ወሬ ሲወዱ። እኔ እንደውም ወሬ ማውራት የቻልኩት ከሳቸው ኮርጄ ይመስለኛል፡፡ (ትስቃለች) |
በዚያ ላይ ጉረኛ ናቸው ። አቤት ጉራ ኤክስፖርት ቢደረግ እንደኚህ አዛውንት ሀብታም የሚሆን ያለ አይመስለኝም እዛውንቱ ጉራቸውን መንዛት ከጀመሩ በቃ ፌንት ነው የምትሰሪውና ሮዚ ሙች እውነቴን ነው።
ወይንሸት ልጄን ለተራ ሰው የዳርኩ እንዳይመስልሽ! በሰፈርም በአገርም ታይቶ የማይታወቅ የሰርግ ድግስ ነበር የተደገሰው"
“ልጅህ ማንን ነው ያገባችው?” (አንተ ስላቸው እንዴት እንደሚቀፈኝ ግን አትጠይቂኝ)
"የፈረንሳይ (ሞናኮ) ንጉሳዊ ቤተሰብ የቅርብ ዘመዶች ናቸው። ከነርሱ ውስጥ አንዱን ነው ያገባቸው”
"ስንት አመቷ ነው?"
| “ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ አስራ ዘጠነኛ የልደት በአሷን በዚያው በሞናኮ አክብራለች። ከፈለግሽ ሙሉ የልደት በአሏን አልበም አምጥቼ አሳይሻለው።"
"ባሏ ድሜው ስንት ነው?"
“ሃምሳ ስምንት! እንዴት ያለ ንጉሳዊ ግርማ ሞገስ ያለው መልከ ቀና መሰለሽ! ኮራ ጀነን ያለ፣አረማመዱንና የፊቱን ላህይ ብትመለከቸው የንጉስ ዘር መሆኑንና እጅግ ከተከበረ ቤተሰብ መገኘቱን
በፍጥነት ተረጂያለሽ ?”
አዛውንቱ ጉራቸውን ይቀጥላሉ። በልቤ እታዘባቸዋለሁ።
ልጃቸው በእድሜ ሶስት እጥፍ የሚበልጣትን ነጭ አዛውንት ማግባቷ ኩራት እንዴት ይፈጥራል? ሮዚ ሙች፤ ቅኝ አልተገዛንም ብለን በከንቱ እንደነፉለን እንጂ ከፍተኛ የሆነ የነጭ አምልኮ እንዳለብን በኚህ አዛውንት ነው የገባኝ። ፈረንጅ ማግባት የክብር መገለጫ ሆኖ ቀረ እኮ። አይገርምሽም? ልጅት
ያገባችው ጨርጫሳ ሽማግሌ ፈረንጅ ቢሆንም ይህ ክብር ቅንጣት አይጓደልም። ከአንዴም ሁለቴ ነጭ
የጠበሱ ጓደኞቼ የሰርግ ድግስ ላይ ተገኝቼያለሁ። በሁለቱም ሰርግ ወቅት የሰርግ ዘፋኞቹ ተከታዩን ሲያንጎራጉሩ ሰምቼያለሁ።ነጮቹ ጓደኞቼን በእድሜ ብዙ ይበልጧቸዋል።
..የኛ ሙሽራ ኩሪባቸው
በእንግሊዝ አፍ አናግሪያቸው.. (ተያይዘን ሳቅን)
ሮዚ ቆይ_እንግሊዝኛ መናገር እና ነጭ ማግባት በምን ስሌት ነው ኩራት የሚሆነው? አይገባኝም!!
ይሄኔ እኮ አኚህ አዛውንት የአድዋ ድል ወይም የአርበኞች ቀን ላይ በከፍተኛ የአርበኛነት ስሜት እየተንጨረጨሩ ፉከራ፣ ሽለላና ቀረርቶ ያሰሙ ይሆናል። (በድጋሚ ተያይዘን ሳቅን)
ሊለው የሚያስገርመኝ ሮዚ፣ እኚህ አዛውንት ደምበኛዬ ወሲብ አይፈጽሙም። ምን እንደሚያደርጉ
ታውቂያለሽ? መኝታ ከፍል ከገባን በኋላ ሁሌም ሁለት ትእዛዝ አላቸው፤
እስቲ እንደው ልብሶችሽን በዝግታ አውልቀሽ በክፍሉ ውስጥ ከግራ ቀኝ ተንጎማለይ! ጎርደድ ጎርደድ በይ} ይህን ውብ ገላሽን እርቃኑን በክፍሉ ውስጥ ሲንከላወስ መመልከት እፈልጋለሁ። አደራሽን! ታኮ ጫማሽን በፍጹም እንዳታወልቂ! ድምጹ እንዴት አስደሳች መሰለሽ…."
አረማመዴን በጣም እንደሚወዱት በተደጋጋሚ ስለሚነግሩኝ ይህ አፈንጋጭ ወሲባዊ ፍላጎታቸው ብዙም አይገርመኝም። እኔ ክፍሉን በእርምጃ ሳካልል እሳቸው የሆነ ያልሆነ እየቀባጠሩ ሴጋ ይመታሉ፤ጫፌን ግን አይነኩኝም። አይገርሙሸም ሮዚ!
ሌላኛው የአዛውንቱ ትእዛዝ ደግሞ ልንገርሽ፤
“ወይንዬ እንዲያው ዛሬ ሁለመናዬ ደካከሟል ። ድብርት ተጫጭኖኛል። ቅባት ይዤ መጥቻለሁ።
መላ ሰውነቴን በለስላሳ ጣቶችሽ እንድታሻሺኝ እፈልጋለሁ፤ ምን ትያለሽ ታዲያ…"
ሙሉ እርቃናቸውን አልጋው ላይ በሆዳቸው ይተኛሉ። ቅባቱን እየቀባሁ እርጅና ያጨማደደውን ቆዳቸውን ማሻሸት ስጀምር በማይገባኝ ቋንቋ መለፍለፍና መቀባጠር ይጀምራሉ ከተወሰነ ደቂቃ
በኋላ ልከ እርቃኔን ስራመድ እንደሚያደርጉት አንዳች ከባድ ድምጽ አሰምተው ጫፌን ሳይነኩኝ ስሜታቸውን ይጨርሳሉ።
ደስ የሚለው
ነገ

❤1👍1